
ኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሮጌው ተርሚናል እያደረገ ካለው የወረደ መስተንግዶ ይልቅ « ጅዳ » ሳውዲ አረቢያ አየር ማረፊያ በባዕዳኑ የአየር መንገዱ ሰራተኞችና የፀጥታ ሃይሎች የሚደረጉላቸው አቀባበልና / መስተንግዶ ምንም እንደ ማይገናኝና የትየለሌ መሆኑንን ሰሞኑን ጅዳ ከገቡ ምዕመናን የሃጅ ጸሎት ተጓዥ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ማረጋገጥ ተችሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገዱ መስተንግዶ መንግስት ሃገር ውስጥ በጋራ እና በተናጠል ህዝበ ሙስሊሙ ተቋም ላይ ከሚፈጽመው በደል አይለየም የሚሉ አንዳንድ ወገኖች በአሮጌው ተርሚናል በኩል የሚያልፍ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም እንደ ዜጋ ቀርቶ አንድ ቆዳው ነጣ ያለ መንገደኛ የሚሰጠውን ክብር ያህል ቦታ የለንም ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገዱ መስተንግዶ በኢትዮጵያዊን ሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ብቻ ያነጣጠር ይሁን እስካሁን ማረጋገጫ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም «ከተላብ የተገኘ ስሊጥ አብረህ ተወቀጥ » እንዲሉ በኮንተራት ስራም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተጠቀሱት ሃገርት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ሳይቀሩ በደሉ እየተፈፀመባቸው መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የሃገሪቱን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ አርማው በማድረግ ከግማሽ መዕተ አመት በላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ይህ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ህዝብ የሆነው አየር መንገድ በገዥው ፓርቲ ህ.ወ.ሃ.ት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት ካድሬዎች እጅ ከወደቀ ወዲህ ዜጎች በማንነታቸው እየተለዩ የዜግነት ክብራቸውን የሚያጡበት ብቻ ሳይሆን የአየር መንገዱ ሰራተኞች ጭምር በብሄር ማንነታቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸው እየተለዩ ግፍና በደል የሚፈፀምባቸው ማዕከል እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል። ህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረዓት የዜጎችን ከሃገር ወደ ሃገር የመዘዋወር ህገመንግስታዊ መበት በመጣስ ከሳውዲ አረቢያ ቤተዘመድ ጥየቃ ለረእፍት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎች የዕረፍት ግዜያቸውን ጨርሰው ሲመለሱ የሚኖሩበትን ሃገር የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያ « ኢቃማ » ካላመጣችሁ አታልፉም በሚል ምክንያት በአየር መንግዱ ውስጥ በተሰገሰጉ የፀጥታ ሃይሎች እስከ 10 ሺህ ሪያል የሚደርስ ጉቦ በግልጽ እንደሚጠየቁ ለመረዳት ተችሏል። በሳውዲ አረቢያ ህግ ማንኛውም የወጭ ሃገር ዜጋ ፓስፖርቱን ከአሰሪው እጅ ሲቀበል የመኖሪያ ፈቃዱን ለኣሰሪው ማስረከብ እንደሚገባ ይደነግጋል። Ethiopian
Hagere Jed Bewadi