Saturday, December 21, 2013

የሸራተን ሰራተኞች “መብታችን ተጣሰ” በማለት ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጡ ነው!!!!


የሸራተን አዲስ ሆቴል ሰራተኞች፤ የውጭ አገር ዜጋ በሆኑት የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ የሚደርስብን ችግር ከአቅም በላይ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፍ ልንወጣ ነው አሉ፡፡ ከዚህ በፊት  የመብት ጥሰት እንደደረሰብን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በደብዳቤ ብንገልፅም ምላሽ ባለማግኘታችን በድጋሚ ደብዳቤውን አስገብተናል ብለዋል - ሰራተኞቹ፡፡ 
በትምህርት ደረጃና በእውቀት ከሀበሾቹ የማይበልጡ የውጭ ዜጐች አሰሪዎቻችን ያንቋሽሹናል፤ ዛሬ ፆም ነው ይህን አንበላም ስንል “ድሮ ረሀብተኞች ስለነበራችሁ ረሀባችሁን ለማስታወስ የምታደርጉት ነው” ይሉናል፤ ጥቅማጥቅሞቻችን አይከበሩም፣ እድገት እንከላከላለን ያሉት ሠራተኞቹ፤ “ፈረንሳዊው ስራ አስኪያጅ ዲፓርትመንቶችን በመበታተን፣ ሰራተኞችን ወዳልፈለጉትና ወደማይመለከታቸው ቦታ ይመድባሉ፤ ይህን ስንቃወም እስከመደብደብ እንደርሳለን” ብለዋል፡፡ 
“የዜጐች ደህንነት ጥበቃ ከአገር ውስጥ ይጀምራል፤ በአገራችን ነጮች እያንቋሸሹን እና ሞራላችን እየተነካ ነው” የሚሉት ሰራተኞቹ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ችግራችንን በዝምታ ማለፋቸው አሳዝኖናል ብለዋል፡፡ 
“ችግራችን ሲብስ ፒቲሽን ተፈራርመን ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያስገባነው ደብዳቤ፤ ለሆቴሉ ስራ አስኪያጅ ለሚስተር ዦን ፒይር ማኒንጐፍ ከደረሰ በኋላ፣ ስቃያችን በዝቷል ያሉት ሰራተኞቹ፤ አንድ ነገር ለማስፈቀድ፣ አቤቱታ ለማሰማትና ለእድገት ለመወዳደር ስንጠይቅ ስራ አስኪያጁ  ፒቲሽን የፈረሙትን ሰራተኞች ስም ያወጡና “በእኔ ላይ ፈርመሀል፤ እድሜ ልክህን እድገት አታገኝም፣ ይህ አይፈቀድም” እያሉ እንደሚያንገላቷቸው ተናግረዋል፡፡ ሸራተን አዲስ ሆቴል ከ800 በላይ ቋሚ ሰራተኞች እንዳሉት የገለፁት ሰራተኞቹ፤ ይህ ሁሉ ሰራተኛ ባለበት ስራ አስኪያጁን ጨምሮ አንዳንድ የውጭ አሰሪዎቻችን እያንጓጠጡንና ጫና እየፈጠሩብን ስለሆነና የሚመለከተው የመንግስት አካል ምላሽ ስላልሰጠን በቅርቡ ሰላማዊ ሰልፍ ለመውጣት አስበናል ብለዋል፡፡ 
የሆቴሉ ሰራተኞች ማህበር ሊቀመንበሩ አቶ ዳንኤል አለሙ ታሪኩ በበኩላቸው፤ “ሰራተኞቹ ከማህበሩ ወጥተው በራሳቸው ተደራጅተዋል፤ ነገር ግን ማኔጅመንቱና ሰራተኛው ተቀራርበው እንዲሰሩና በውይይት ችግራቸውን እንዲፈቱ ብዙ ርቀት ብንሄድም የሆቴሉ ስራ አስኪያጅ ሚስተር ዦን ፒይር ማኒንጐፍ ፈቃደኛ አልሆኑም” ብለዋል፡፡ 
የሆቴሉን ስራ አስኪያጅ  ሚስተር ዦን ፒይር ማኒንጐፍን ለማነጋገር ብንሞክርም እረፍት ላይ በመሆናቸው ሳይሳካልን ቀርቷል፡፡ ሌላ ሃላፊ ለማነጋገር ፀሃፊዋን ጠይቀን፤ በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሚሰጡት ስራ አስኪያጁ ብቻ እንደሆኑ ገልፃልናለች፡፡ 
   ምንጭ
 አዲስ አድማስ

ወ/ሮ ስንቅነሽ እጅጉ ከሚኒስትርነት ወርደው በአምባሳደርነት መሾማቸውን አያውቁም ነበር ተባለ

የማዕድን ሚኒስትር በመሆን ባለፉት ሶስት ዓመታት ያገለገሉትት ወ/ሮ ስንቅነሽ እጅጉ ከኃላፊነታቸው ተነስተው ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው ሲሾሙ ምንም የሚያውቁት ነገር እንዳልነበር የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

ከ16 ዓመታት በላይ በማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ውስጥ ከኤክስፐርትነት እስከ ሚኒስትር ዴኤታ ባሉት የሀላፊነት ቦታዎች ሲሰሩ የቆዩትና እ.ኤ.አ በጥቅምት ወር 2010 የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር የተለያየ አደረጃጀት ይዞ ለሁለት ሲከፈል የማዕድን ሚኒስትር በመሆን በአቶ መለስ ዜናዊ አቅራቢነት የተሾሙት የኦህዴድ አባሏ ወ/ሮ ስንቅነሽ ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ሳይነገር ከአማራው ክልል ፕሬዚደንት አቶ አያሌው ጎበዜ ጋር ባለሙሉ አምባሳደር በመሆን በፕሬዚደንት ሙላቱ ተሾመ መሾማቸው ይታወሳል፡፡

ምንጮቻችን እንደተናገሩት ወ/ሮ ስንቅነሽ በአቅም ችግር ከዚህ ቀደም የተገመገሙ ሲሆን ከሃላፊነታቸው ሲነሱ እንደማንኛውም ሰው በራዲዮና በቴሌቪዥን ከመስማታቸው ውጪ በቀጥታ የተነገራቸው ነገር አልነበረም፡፡
ወ/ሮ ስንቅነሽ የአዳሚ ቱሉ የኬሚካል ድርጅትና የኢትዮጽያ ማዕድን ልማት ድርጅትን በቦርድ ሰብሳቢነት፣የመንገዶች ባለስልጣን፣የኢትዮጽያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ፣የመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባልም ነበሩ፡፡

ወ/ሮ ስንቅነሽ ግልጽነት ከጎደለው የጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔ በይፋ ከተነሱ ሴት ሚኒስትሮች መካከል ከወ/ሮ አስቴር ማሞ የቀጠሉ ናቸው፡፡

ምንጭ ESAT
L

Friday, December 20, 2013

በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል ! ======================================================= በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ አንባሳደር ዘነበ ከበደ የሚመሩት የመንግስት ሹማምንቶች ጅዳ ከተማ ውስጥ፡መሽገዋል ያሏቸው 80 ሺህ ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላም ካልሰጡ የመንፉሃው አይነት እልቂት እንደሚጠብቃቸው ሲያሞርቱ ! ሪያድ በኢትዮጵያው አንባሳደር መሃመድ ሃሰን የሚመራው ቡድን የሚያሰማው « ጅብ ከሄድ ውሻ ጮህ ጥሪ » ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ተገለጸ !


                         በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል !
               =======================================================
በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ አንባሳደር ዘነበ ከበደ የሚመሩት የመንግስት ሹማምንቶች ጅዳ ከተማ ውስጥ፡መሽገዋል ያሏቸው 80 ሺህ ኢትዮጵያውያን እጃቸውን በሰላም ካልሰጡ የመንፉሃው አይነት እልቂት እንደሚጠብቃቸው ሲያሞርቱ ! ሪያድ በኢትዮጵያው አንባሳደር መሃመድ ሃሰን የሚመራው ቡድን የሚያሰማው « ጅብ ከሄድ ውሻ ጮህ ጥሪ » ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ተገለጸ !






ከ9 ሚልዮን በላይ የተለያዩ የውጭ፡ሃገር ዜጎች በጥገኝ ነት እንደሚኖሩባት የምትታወቀው ሳውዲ አረቢያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን እንዲያስተካከሉ የተሰጠ የ 7 ወር የግዜ ገደብ መጠናቀቅን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ ባነጣጠረ እርምጃ እስካሁን ቁጥሩ በወል ለማይታወቅ ወገናችን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት ስቃይ እና መከራ ምክንያት መሆኑ ይታወቃል። በተለይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ ሰፈር ሃገራቸው ለመግባት ጥያቄ ባቀረቡ ወገኖቻችን እና በሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች መሃከል በተነሳ ግጭት አያሌ እህቶቻችን በአረብ ጎረምሷች ተደፍረዋል እህቶቻቸውን እና ሚስቶቻቸውን ለመከላከል ጩሀታቸውን ያሰሙ ንጽሃን ወገኖች በአሰቃቂ ሁኔታ በሳንጃ እና በጓራዴ ተገድለዋል ፡፤



ይህንንም ተከትሎ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻች ከአሰቃቂው ጥቃት እርሳቸውን ለመታደግ ከዳር እስከዳር «ሆ »ብለው አደባባይ በመውጣት የሳውዲ አረቢያ አውራጎዳናዎችን በማጨናነቅ የአለምን መገናኛ ብዙን ሽፋን በማጝት በሳውዲ አረቢያ በጠራራ ፀሃይ እና በሌሊት በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም የነበረው ጭፍጨፋ ስቃይ እና በደል በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚገኙ ወገኖቻቸውን ዘንድ ቁጣን በመቀስቀስ በሳውዲ መንግስት ላይ ባደረጉት ተጸዕኖ በማን አለብኝነት በወገኖቻችን ላይ ሲፈጸም የነረውን ኢሰባዊ ድርጊት ለግዜውም ቢሆን ጋብ እንዲል አስችሏል። 


የኢትዮጵያኑ አለማቀፍ ቁጣ ያስደነገጠው የሳውዲ አረቢያን መንግስት በሚልዮን ለሚቆጠሩ የውጭ፡ሃገር ያወጣው ህግ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ እንዲያትኩር አስገድዶታል። ይህ በዚህ እንዳለ እስካሁን በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያ ውያን ስደተኞች የስውዲ አረቢያን ምድር በሰላም ለቀው ለሃገራቸው እንደብቁ የሚናገሩ ምንጮች አሁንም 80 ሺህ ህገወጥ ኢትዮጵያውያን ጅዳ ጣይፈ መካ መዲና ከተሞች ውስጥ መሸገዋል ተብሎ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት እይተሰጠ ያለው መግለጫ ቅንነት የጎደለው መሆኑንን ይገልጻሉ። በሃጂ እና ኡምራ አሊያም በባህር ወደ ሳውዲ ምድር ድንበር አቅርጠው ገብተውል ተብለው የሚነገርላቸው ኢትዮጵያውያን ያሉበትን ሁኔታ የማይዘረዘርው በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንላ የመንግስት ሹማምቶች መግለጫ ህገወጥ የተባሉት ወገኖች በግዜ እጃቸውን ሰጠተው ወደ ሃገር ካልተመልሱ በሪያድ መንፉሃ የተከስተው አይነት አልቂት እንደሚገጥማቸው አስጠንቅቀዋል። 


ይህ በቆንስል ዘነበ ከበደ የሚመራው ጽ/ቤት ሰሞኑንን እያሰማን ያለው ጩህት ወገናዊነት የጎደለው እና ሳውዲያኖቹ በኢትዮጵያውያኑ ላይ ብቻ በማነጣጠር መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ጭምር ከሳውዲ ምድር ጠራርጎ ለማስወጣት የተያዘ እቅድ አንዱ አካል መሆኑንን የሚናገሩ የጅዳ ነዋሪዎች የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ወገኖች በሳውዲ ምድር በሰላም ሰርቶ የመኖር ህልውናቸው አስተማማኝ ባልሆነበት አጋጣሚ እንደዚህ አይነት መግለጫ ማውጣት ሃላፊነት የጎደለው መሆኑንን ይናገራሉ። እንዚህ ወገኖች የጅዳው ቆንስላ ጽ/ቤት እንደዚህ አይነት አስገራሚ መረጃ በአረብኛ እና በአማርኛ ቋንቋ በተዘጋጁ በራሪ ወረቅቶች ቅስቀሳ ማካሄዱ ትላንት ሪያድ ከተማ መንፉሃ ውስጥ፡ቆጨራ እና ሳንጃ ታጥቀዋል የሚል የተሳስተ መለዕክት በማስተላለፍ ወገኖቻቸውን ካስፈጁት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አንባሳደር መሃመድ ሃሰን ከፈጸሙት ስህተት የማይለይ መሆኑንን ይገልጻሉ። 

በሌላ በኩል ሰሞኑንን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ በየጥጋጥጉ ማስታወቂያዎችን በመለጠፍ እና በራሪ ወረቀቶች በመበትን እያሰማ ያለው የተለመደ የአዞ እንባ « ጅብ ከሄደ ውሻ ጮህ » መሆኑንን የሚገልጹ የአካባቢው ነዋሪዎች የምህረቱን አዋጅ ተከትሎ ጉዳዮቻቸውን እስካሁን ማስፈጸም ተስኗቸው በሳውዲ አረቢያ ውስጥ ለመኖር የሚያስችሏቸውን ማመዘኛ ያላሞሉ ወገኖች በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ እየቀረቡ ምዝገባ እንዲያካሂዱ የሚለው መለዕክት ለኢትዮጵያውያኑ ታስቦ ሳይሆን ዲፕሎማቱ የተለመደውን ድብቅ አጀንዳቸውን በቀሪው ኢትዮጵያዊ ወገናችን ላይ ለማስፈጸም እንደሆነ ይናገራሉ። 


በተለያዩ አቅጣጫዎች ያለደረስኝ፡በወገኖቻችን ሽፋን በመቶሺ የሚቆጠሩ ሪያሎችን በመሰብሰብ ላይ የሚገኘው በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች ከተጠቀሱት ወገኖች ኪስ ለተለያዩ ገዳዮች ማስፈጸሚ የሚውል ገንዘብ ለመሰብሰብ እቀድ እንዳላቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይገልጻሉ። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ክቡር ቴድሮስ አድሃኖም በወገኖቻችን ላይ ለተፈጸመው አስቃቂ ግድያ ግፍ እና በደል ተመጣጣኝ እርምጃ እንደሚወስድ የገቡትን ቃል ከፖለቲካ ግበአትነት እንደማያልፍ የሚናገሩ ወገኖች የኢትዮጵያ መንግስት በሳውዲ አረቢያ መንግስት ላይ ያሳረፈው ምንም አይነት ዲፕሎማሲያዊ ተጸኖ ባለመኖሩ ሳውዲያኑ ለኢትዮጵያውያኑ ያላቸው ጥላቻ አገርሽቶ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን «በሪስፖንሰሮቻቸው» የመኖሪያ ፈቃዳቻቸው በመሰረዙ አያሌ ወገኖች ለህገወጥነት እይተዳረጉ መሆናቸው ይነገራል። 


Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

በወር አበባ ሰሞን ህመም እና ምቾት ማጣትን የምትቀንሺባቸው 6 ስልቶች

በወር አበባ ሰሞን ህመም እና ምቾት ማጣትን የምትቀንሺባቸው 6 ስልቶች

ከቅድስት አባተ
(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 57 ላይ ታትሞ የወጣ)
የሴቶች ጉዳይ ብንላቸው የምንግባባቸው ጥቂት ነገሮች አሉ፡፡ አንዱ ወር ጠብቆ ፅንስ ለመፍጠር ዝግጁ መሆናቸውን ለመናገር የሚመጣው የወር አበባ ነው፡፡ እጅግ በርካታ የሆኑ እና ሴቶች የወር አበባቸው በሚመጣ ወቅት ከቀላል መነጫነጭ አንስቶ ሁሉን ነገር እስከመጥላት የሚያደርስ የህመም እና ምቾት የማጣት ስሜት ይገጥማቸዋል፡፡ ሁነቱ ተፈጥሯዊ የሆነና ለክፉ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ይሁንና የዚያን ሰሞን ስሜት እና ህመም ማቅለል እና ንጭንጩንም ጭምር ማቃለል እንደሚቻል ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡ የዛሬው ትኩረታችንም ይህ ነው፡፡ ቀላል የሚባሉ እና የህክምና ጥበብን እጅግም በማይጠይቁ ስልቶች የወር አበባ ሰሞንን ማቅለል የምትችይባቸውን ስልቶች እነሆ ብለንሻል፡፡

የወር አበባ ለምን?
ተፈጥሮ የወር አበባን ስትፈጥር መራባትን አስባ ነው፡፡ ሴቶች አዲስ ነፍስ የመፍጠር ስልጣን በየወሩ ይሰጣቸዋል፡፡ አብሮ ለመፍጠር የተዘጋጀ ጥንድ እስካለ ድረስ ይህ ይሰራል፡፡ በየወሩ የሚዘጋጁት እንቁላሎች የሚዳብርና ፅንስ የሚያደርጋቸው የወንድ ዘር ሲያገኙ እዚያው ሆነው ጽንሱ ሲፈጠር ያ ካልሆነና ሴቲቱም በመፀነስ እቅድ ውስጥ ካልሆነች ደግሞ እንቁላሎቹ ወደ ውጪ መውጣት ይኖርባቸዋል፡፡ እንግዲህ በየወሩ ከደም ጋር ተቀላቅለው የሚወጡት እነዚህ እንቁላሎች ናቸው፡፡ ታዲያ ይህ ክስተት በብዙ ሆርሞኖችና የሰውነት ውስጥ ውስብስብ ተግባራት የሚከወን እንደመሆኑ ብዙ ለውጦችን ሴቶች ማስተናገዳቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቢያንስ 80 ከመቶ የሚሆኑ የዓለማችን ሴቶች ከቀላል ህመም አንስቶ እስከ ከበዱት ድረስ በወር አበባ ሰሞን ይገጥማቸዋል፡፡ እጅግ አሳማሚ የሆድ ቁርጠት፣ የስሜት መቀያየር፣ መነጫነጭ ራስ ምታት እና ሌሎቹም የሚጠቀሱ ማሳያዎች ናቸው፡፡ እነዚህን የወር አበባ ሰሞን ችግሮች ማቅለያ ዘዴዎችን ታዲያ የህክምና ሰዎች ለሴቶች ሁሉ ያጋራሉ፡፡ የዲስከቨሪ መፅሔት እና ውሜን ሄልዝ ኤክስፐርቶች ካነሷቸው መካከል ዮጋ ማዘውተር ጨው መቀነስ፣ አመጋገብ ማስተካከልና አንዳንድ ቀለል ያሉ መድሃኒቶችን መውሰድን ያነሳሉ፡፡
የወር አበባ ሰሞን ጨው ቀንሺ
በወር አበባ ሰሞን እንቁላሎች ዝግጁ ሆነው የሚጠብቁት ልጅ እንደሚፈጠር በማሰብ ነው፡፡ ስለሆነም ጽንሱ ቢፈጠር የሚያስፈልገውን የጨው ፈሳሽ እና ኤሌክትሮላይት ለመሙላት ሰውነትሽ ብዙ ጨው የዚያን ሰሞን ይኖረዋል፡፡ ብዙ ጨው መኖሩ ደግሞ ውሃን የመሳብና በሰውነት ውስጥ መጠራቀምን ይፈጥራል፡፡ ይህ በራሱ የሚፈጥረው ሰውነትን የማስጨነቅ ተፅዕኖ ስለሚኖር ከውጪ የምትወስጂውን ጨው የወር አበባ ከሚመጣባቸው ቀናት አስቀድመሽ ቀንሽ፡፡ በተለይ የተጠባበሱ ምግቦች ውስጥ ከፍተኛ የጨው ክምችት ስለሚኖር ከእነዚህ ምግቦች በዚያ ሰሞን መቆጠብ ጥሩ እንደሆነ ባለሞያዎቹ ያሰምሩበታል፡፡
ዮጋ እንደ መዝናኛም እንደ መድሃኒትም
የወር አበባ ወቅትን ህመም ለማስታገስ መዝናናት፣ ውጥረትን መቀነስ እና የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ በእጅጉ የሚመከሩ መላዎች ናቸው፡፡ ዮጋ ደግሞ ሁሉንም በአንድ አዋህዶ የያዘ የተመስጦ ስፖርት ከመሆኑ አንፃር ቁጥር አንድ ተመራጭ ስፖርት ያሰኘዋል፡፡ ‹‹ዮጋ ስፖርት ብቻ አይደለም፣ አዕምሮና አካልን በአንድነት ከውጥረት መንጥቆ የሚያወጣ መድሃኒትም ነው›› ይላሉ የዲስክቨሪ መፅሔት የህክምና አማካሪ፡፡ በኢንዲያን አካዳሚ ኦፍ አፕላይድ ሳይኮሎጂ የጥናት መፅሔት ላይ የሰፈረ የጥናት ውጤትም ተመሳሳይ ጥቅሞችን ያነሳል፡፡ ጥናቱ ዮጋ የስነ ልቦና እና የአካላዊ መዝናናትን በማጎናፀፍ ከወር አበባ ወቅት ህመምና ምቾት ማጣት በመገላገል በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ይናገራል፡፡
ካልሲየምና ቫይታሚን ዲ ውጤት አላቸው
በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ አሜሪካ ውስጥ በዚህ ላይ ምርምር ያደረጉ ባለሞያዎች ቫይታሚን ዲ እና ካልሲየም ማዕድን የወር አበባ ጊዜዎትን በእጅጉ ቀላል የማድረግ ሚና እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ በጥናቱ በየዕለቱ እስከ ስድስት መቶ ሚሊግራም ካልሲየም የወሰዱ ሴቶች ዘንድ የወር አበባ ወቅት ህመሞች የሚባሉት እንደ ሆድ ቁርጠት፣ ራስ ምታት፣ የምግብ አምሮት እና የስነ ልቦና ጫናው በግማሽ ቀንሶ መገኘቱን በጥናታቸው ፅፈዋል፡፡ ይህ የካልሲየም መጠን አንድ ብርጭቆ ወተትና አንድ ብርጭቆ እርጎ በጋራ ቢጠጡ የሚያገኙት ምጣኔ ነው፡፡ ባለሞያዎቹ ካልሲየምን በክኒን መልክ መውሰድ ቢቻልም ተመራጩ ግን ከወተት ተዋፅኦ ውጤቶች ማግኘቱ እንደሆነ አበክረው ያሳስባሉ፡፡ ቫይታሚን ዲ ተመሳሳይ ተፅዕኖ እንዳለው ባለሞያዎቹ አስረድተዋል፡፡ እንደ ካሮት እና መሰል አትክልቶች ቫይታሚኑን ማግኘት ወር አበባን ቀለል ያደርጋል፡፡
ለማይግሬይንና ራስ ምታቱስ?
በወር አበባ ወቅት የሚከሰተው ራስ ምታት ከወትሮው በተለየ አናትን የሚነቁርና ሁሉን ነገር የሚያስጠላ ሊሆን ይችላል፡፡ ቀደም ሲል ያነሳናቸው የመዝናኛ እና ችግሩን የመቅረፊያ ስልቶች እየሰሩ ካልሆነ በባለሞያ የሚታዘዝ ህመም ማስታገሻን መውሰድ ይመክራል፡፡ ምናልባት ሌላ ጊዜ ከሐኪም ትዕዛዝ ውጪ የምንወስዳቸው ማስታገሻዎች በዚህ በኩል ውጤታቸው አርኪ ስለማይሆን ነው፡፡ ሌላ ማስታገሻ ለመጠየቅ ባለሞያን እንዲያዩ የሚመክረው በውጪ ሀገራት ለዚህ ተብለው የሚሰሩ ልዩ ማስታገሻዎች አሉ፡፡ በእኛ ሀገር ፋርማሲዎች በስፋት የሚገኙ ባለመሆናቸው ባለሞያ መገናኛቸውን ሊያመላክትዎት ይችላል፡፡
ፋይበር ያላቸውን ጠጠር ያሉ ምግቦች ጥቅም
ባለሞያዎቹ እንደሚሉት በወር አበባ መምጫ ሰሞን ህመሙን እና ሆድ ቁርጠቱን የሚያመጡት የሆርሞን ለውጦች የሆድ ህመም እና ተቅማጥ ከሚያመጡት ጋር ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ስለሆነም ሆድን ያዝ የሚያደርጉ እንደ ጎመን አጃ፣ ሙዝና የመሳሰሉትን ምግቦች ብትወስጂ ሆድሽን ያዝ አድርገው የምግብ አምሮቶሽን ይገቱታል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ዘንድ የሚታየውንም የዚያን ሰሞን የሆድ መለስለስና መለስተኛ ተቅማጥ ለመቆጣጠር ያግዛሉ፡፡
በዚያ ሰሞን ዋና መዋኘት?
ብዙ ሴቶች በወር አበባ መምጫ ሰሞን ከሰው ራቅ ብለው ቤት አካባቢ ሆነው ቢቆዩ ይመርጣሉ፡፡ የባለሞያዎች ሀሳብ ግን ይለያል፡፡ ከሰው መቀላቀሉ እና ዘና ማለቱ ይመከራል፡፡ በተጨማሪም ዋና መዋኘት ከፍተኛ ጠቀሜታም እንዳለው ጨምረው ያስረዳሉ፡፡ በዋና ወቅት በሰውነት እና በውሃው መካከል በሚደረገው ፍትጊያ የሚፈጠረው ግፊት የሆድ ቁርጠትና የዚያን አካባቢ ቁስለት የሚመስል ስሜት አዝናንቶ የማፍታትና ህመምንም የመቀነስ አቅም አለው፡፡ በቀን ቢያንስ ለ20 ደቂቃ ብትዋኚ ጥሩ ነው ተብሎ ተመክሯል፡፡ ነገር ግን የግድ ወደ ዋና ገንዳ እንድትገቢ አትገደጂም፡፡ የዋናው ነገር ካልተመቸሽ በቤት ውስጥ መታጠቢያ ቤት ለብ ያለ ውሃ በገንዳው ሞልተሽ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰውነትሽን ብታሳርፊው የዋናውን ያህል ባይሆንም ጥሩ ውጤት ታገኚያለሽ፡፡
posted by Aseged Tamene

ምስጋና ለአያሌው ጎበዜ – አክባሪዎ አቢሲኒያዊ

እርስዎ ብዐዴን/ህወሀትን ወክለው የአማራን ህዝብ ሲመሩ መቆየትዎ ይታወቃል በዚህም የክልሉ ህዝብ ኤያሌው ጎበዜ ለዘላለም ይኑር እያለ እንዲኖር ማድረግዎትን የሚያስታውሱት ነው እርስዎ በጣም ያሳዘኑኝ ያ ወዳጅዎ ደመቀ መሬቱን ድንጋይ ያድርግለት እና በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ይገባሻል ብሎ መለስም ብራቮ እንዲህ ነው እንጂ ተላላኪ ብሎ ትምህርት ሚኒሰቴር ሲያደርገው ለእርስዎ ግን ቅንጣት ታህል አለመስጠቱ ሱዳኖች እንኴን እንዲታዘቡት አድርጔል፡፡
እርስዎም ደመቀ ምክትል ጠ/ሚኒስቴር ሲሆን ቅናት ቢጤ አድርዎቦት ከሳምንታት በፊት 40 ካ.ሜ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የሀገሮትን መሬት ለሱዳን ማስረከብዎን ሰምቼ ድሮስ የጎበዤ ልጅ ከማን ያንሳል ብዬ ኮራሁ፡፡ በነገራችን ላይ ሰሞኑን መሬታችን ለሱዳን መሰጠቱን ተከትሎ የእርስዎ የቅርብ ዘመዶች ቤታቸው የተሸጠው መሬት ላይ በመገኘቱ ሱዳን ለዘላለም ትኑር አባይ የሱዳን ነው እያሉ መዘመራቸውን ሱዳን የሚገኝ ወዳጄ ሹክ ብሎኛል፡፡
እናማ ይሄውልዎ ተሰናባች አያሌው የእርስዎ ክልል ግዞት የሆነው የአማራ ህዝብ ብዙ እየሰማ እና እየተሰማው ሲኖር አንድም ቀን ተናግርዎት አያውቅም ለምን መሰለዎት ምን አልባት ነጋዴው ክልሉን ለሱዳን ሸጠው ከመለስ ዜናዊ አገዛዝ ነፃ ያወጡናል ብሎ ስላሰበ ይሆናል፡፡ የአማራ ክልል ህዝብ ለእርስዎ ያላቸውን ፍቅር የተረዳሁት ጉራፈርዳ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ጉራፈርዳ በቃን አያሌው ጎበዜ ናፈቀን ብለው ቢለመኑ እምቢኝ ብለው እርስዎ ክልል ሲመጡ ነው፡፡
እናም በመጨረሻም እንኩ ምስጋናዬን ተቀበሉ
1.   ሰፊውን መሬታችንን ሽጠው ጠጋ ጠጋ ብለን በመኖር ማህበራዊ ህይወታችን እንዲጠናከር በማድረግዎ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
2.   እንደ መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ ሳይሞቱ በመልቀቅዎ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
3.   በ1998 በኮምቦልቻ፣ በ1999 በደሴ፣ በ2000፣ በ2003 የጎንደር እና የጎጃም ህዝብን በወያኔ ወታደሮች በጥይት አስገድለው ከዘንድሮው የኑሮ ውድነት እንዲያመልጡ ስላደረጉ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
አክባሪዎ ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ
posted by Aseged Tamene

የኢህአዴግ መንግስት ሃላፊነት ስልጣን እየሰጠ እያወጣቸው ያሉ ባለስልጣናት በሙስና ለተጨማለቁት ነው


በመረጃው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በሙስና ተከሰው ጉዳያቸው እየተጣራ ከቆዩ የበላይ ባለስልጣኖች ውስጥ። ኩማ ደመቅሳና አለማዮህ ታፈሰ ክስ ህዳር 30/ 2006 አ/ም ያየው የወረዳው ፍርድ ቤት። ተከሳሽ ለሆነው አለማዮህ ታፈሰ ለ10 አመታት ፅኑ እስራት ፍርድ ሰጥቶ። ለኩማ ደመቅሳ በሌላ ቀን ቀጠሮ እንዲታይ በወሰነበት ግዜ። የፍርድ ውሳኔ የተሰጠው አለማዮህ የይግባኝ ጥያቄ በማቅረቡ። የወረዳው ፍርድ ቤት የወሰነውን በድጋሚ ያየው ምንም ነፃነት የሌለው የዞኑ ፍርድ ቤት። በላይኞቹ የስርአቱ ባለስልጣናት ውስጣዊ ትእዛዝና ተንኮል መሰረት። ወንጀሉ ኩማን እንዳይነካው በማለት ለተከሳሹ ነፃ ብሎ እንደለቀቀው ለማወቅ ተችለዋል፣
ሁለቱም ተከሳሾች ተከፋፍለው በልቶውታል ተብሎው የተከሰሱበት 70 ሚሊዮን የሚገመት ብር። ለተለያዩ የከተማው መሰረተ ልማቶች እንዲውል በማለት ከህዝብና ከሃገር ሃብት የተመደበው ባጀት። ይዘውት ያሉትን ስልጣን ተጠቅመው ሥራ ላይ እንደዋለ በማስመሰልና ወጪ በማድረግ። ለግል ጥቅማቸው እናዳዋሉት የሚያረጋግጥ እውነተኛ መረጃ እንዳለ ከከተማው የተገኘው መረጃ ኣረጋግጠዋል::
ይህ በእንዲህ እያለ ኩማ ደመቅሳ በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል። ህጋዊ ውሳኔ ለመስጠት እየተቃረበ በነበረበት ግዜ። ከአዲስ አበባ ከንቲባነት ተነስቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማካሪነት እንዲሰራ ስልጣን ከተሰጠው በኋላ። ክሴታው ውሳኔ ሳያገኝ እስካሁን መስተጓጎሉና። ይኸውም ስርአቱ ሆን ብሎ በሙሱና ለተጨማለቁ ባለ ስልጣናት ተጨማሪ ስልጣን እየሰጠ ወደ ላይ እንዲወጡ ማደረጉ። የስልጣኑ የተዛባና ግለኝነት የተጠናወተው አካሄድ እንደሆነ። በውስጣቸው ፀሃፊ ሆና ለረጅም ግዜ ያገለገለች ወይዘሮ ህድረማርያም የተባለች ዜጋ። ቀደም ሲል ስርአቱ እየተጠቀመበት ለነበረ ውስጣዊ አስራር መሰረት አድርጋ እንደተናገረች ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል::
Source : Debirihan
posted by Aseged Tamene

በህወሓት/ወያኔ መቃብር ላይ ብቻ ኢትዮጵያ በሰላምና በብልጽግና ትኖራለች!



አበራ ሽፈራው/ ከጀርመን/
የኢትዮጵያ ህዝብ ማናቸውም መብቶቹ ተነፍጎ የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ላይ እንገኛለን:: የህዝቡ የሰብዓዊ መብቶችበየትኛውም ዓለም በማይገኝ መልኩ ይጨፈለቃል ለዚህ ያበቃን ደግሞ ትልቁ ምክንያት የህወሓት/ወያኔን የወንበዴነት ጭካኔ ለመጋፈጥ ያለመፈለጋችን ወይም የጭካኔያቸውን መጠን የሚቋቋም ትግል ባለመኖሩና መስዋዕትነትን ለመክፈል ባለመቁረጣችን የመጣብን መከራ እንጂ ህወሓት/ወያኔ ምንም ስለሆነ አይደለም:: የተቃራነውን ጎራ የልብ ትርታ የተረዳው ህወሓት/ወያኔ ሲፈልገው ይገድላል፣ያስራል፣ ያዋክባል፣መሬትንና ንብረትን በሠበብ አስባቡ ይነጥቃል፣ ከስራ ያባርራል፣ የትምህርትና ሌሎች መብቶችን ገፎ ለመከራ ይዳርጋል ካልሆነም ከአገር ማሳደድን እንደትልቅ አማራጭ ተያይዞታል::
በኢትዮጵያ የመኖር መብት እንዳለንና አገራችን መሆኑን እያወቀ መብቶቻችንን የነፈገን ህወሓት/ወያኔ በማን አለብኝነት መቀጠላቸውን ይሁን ብለን ተቀብለን እኛም መስማማታችን ለዛሬው የባሰበት ችግር አድርጎናል:: እነሱ አገራችን አይደለችም ብለው በሚበዘብዟት አገር ላይ ተንደላቀው እየኖሩ ኢትዮጵያ አገሬ የሚሏት እየተዋከቡ ለችግርና ለመከራ መዳረጋችን እጅግ ያሳዝናል:: አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ለውጥ ልታመጣ የምትችለው ህወሓት/ወያኔ ይዞት ከተነሳው አገርን የማጥፋት እኩይ ተግባሩና አስተሳሰቦቹ ጋር ወደመቃብር ሲወርድ ብቻ ነው :: ህዝቡም ጨክኖ ለዚህ እውነት ሲነሳ ብቻ ነው::
ከመቼውም ጊዜያት በላይ ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ውርደት የተጋለጥንበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል:: በሃገራችን መኖር አልቻልንም፣ በሃገራችን ጉዳይ ላይ መወሰን አልቻልንም ፣በሃገራችን ላይ የበይ ተመልካች ሆነን እንገኛለን፣ በህወሓት/ወያኔ ቀኝ ገዥነት ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ብዝበዛ ተጋልጠናል፣ በከፍተኛ ሁኔታ በታጠቁ የህወሓት/ወያኔ በዝባዞች ቁጥጥር ውስጥ ወድቀናል፣ ከፍተኛ ህዝብ ከረሃብ አልፎ ለከፍተኛ ጠኔ ተጋልጦ ይገኛል፣ ይህ አልበቃ ብሎ የአገሪቷ ህዝብ ወደ ውጭ ወጥቶ እንኳን እንዳይሰራ ለከፍተኛ ውርደት ተዳርጎ ማንም እንደፈለገው የሚያደርገውና ተከላካይ የሌለው በዓለማችን ላይ የሚገኝ ህዝብ ለመሆን በቅተናል::
ህዝቡ በአገር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጦ ማንም እንደፈለግ የሚጫወትበት ህዝብ ከመሆኑም በላይ በየትኛውም ነገሩ ላይ ሃይማኖታዊ ጉዳዮቹን ጨምሮ በፈለገው መልኩ እንዳያከናውን መደረጉ ይታወቃል:: ከዚህም አልፎ ደግሞ የአገሪቷ መሬት በተለያዩ ጊዜያት ለተለይዩ ጎረቤት አገራትና ሃይሎች በመስጠትና በማካለል ትልቅ የታሪክ ውርደት ገጥሞናል:: ኢትዮጵያ መቼም ባልታየ መልኩ ለትልቅ ችግር ተጋልጣለች:: ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ትልቅ መስዋእትነትን የሚጠይቅ ትግል ከፊታችን ተጋርጦብናል ይኸውም በህወሓት መቃብር ላይ አገራችንን እንደገና ለማከም የሚያስገድድ ሁኔታ ገጥሞናል:: የህዝብ መብት ጉዳይ ሲነሳ ግድያ፣እስራትና ሞት ሆኗል እጣችን የአገሪቷን ወሰን ለማስጠበቅ የተወሰደው እርምጃም ምንም ባለመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ መሬቷንና የግዛት ክልሎቿን እየተነተቀጭ ትገናለች::
በአባቶቻችን ተከብረው የነበሩ ድንበሮችን አሳልፎ ለመስጠት ዛሬ ለሱዳንና ለኤርትራም ጭምር እንደፈለገ የሚደራደረው ህወሓት/ወያኔ ገና ያልጨረሳቸው ኢትዮጵያን የማጥፋት አላማዎቹ አላለቁም እና እንዲሁም ቀደምት ወራሪዎቻችን የፈለጉትን መሬት አባቶቻችን በትግላቸው ያቆዩትን አገር በባንዳዎች በእጅ አዙር ለማግኘት እየጣሩ መሆኑና ለዚህም ተፈጻሚነት ደግሞ የህወሓት/ወያኔ የባንዳ ቡድን ሃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑን ስንመለከት ያሳዝናል::
የእነዚህ ባንዳዎች አስተሳሰባቸው እና ድርጊታቸው በኢትዮጵያ ላይ መቀጠሉ እንዲያበቃ ዛሬ በህብረት ሆ ብለን መነሳት ካልቻልን ተግባራቸውም ከመፈጸም ሊያቆሙ የሚችሉ አይደሉም :: ህወሓት/ወያኔን ለማሸነፍ ሰዎች የተለያዩ የትግል አማራጮች አዋጭ ናቸው ብለው ባሰቡበት መንገድ ሊሄዱ ይችላሉ፣ ይሁንና አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ግን ህወሓት/ወያኔን በሰላማዊ ትግል እናሸንፋለን ለሚሉ ትግሉ ተገቢ ውጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ ትግሉን ማቀጣጠልና በአጭር ጊዜ ወደውጤት እንዲመጣ ማድረግ ወይም ትግሉን ትቶ መውጣት ሌላኛው አማራጭ ይሆናል :: ምክንያቱም ህወሓት/ወያኔ በናንተ ስም የኢትዮጵያን ህዝብ እያታለለና ብልጭ ድርግም በሚለው የሰላማዊ ትግል ውስጥ አማራጭ እየመሰላችሁ እየገባችሁ የህዝቡን ተስፋ ሟሟጠጥና ከትግል ማራቅ በፍጹም አዋጭ የትግል ሥልት እንዳልሆነ ሁላችንንም እንረዳለን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ ህወሓት/ወያኔ በአገሪቷ ታሪክ ውስጥ የፈጠራቸው ዘርን ከማጥፋት ጀምሮ እስከግለሰቦችና ቡድኖች ጭምር ለወሰዳቸው ግፎች የሚፈለግ ቡድን ከመሆኑም በላይ በትግራይ ህዝብ ሳይቀር በተለያዩ ቡድኖችና ግለሰቦች የሚፈለጉ ሰዎች ስብስብ በመሆኑ ሰላማዊ ሽግግርን ይፈልጋሉ ብሎ ማሰብ በፍጹም የሚታሰብ አይደለምና ነው::
ለዚህም ምስክር ይሆን ዘንድ በቅርቡ በራያ በተደረገው ስብሰባ ለአቶ አብርሃ አንድ ተሰብሳቢ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ መስማት ብቻ ይበቃል እሱም ህወሃት የሽፍታ ቡድን መሆኑን እና ከእነሱ የሚያላቅቋቸው መሆኑን በጥያቄ መልክ ማቅረባቸውን “ሽፍታ” ማለት ደግሞ ምን ማለት እንደሆነ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ የሚታወቅ በመሆኑ ነው::
ይህ ብቻ አይደለም በተለያዩ ጊዜያት አገርን በመክዳትና የአገሪቷንና የህዝቦቿን ጥቅሞች አሳልፎ በመስጠትም የሚፈለጉ ከመሆናቸውም በላይ በሠብዓዊ መብት ረገጣ በኩል አሁን ህወሓት/ወያኔን የሚመሩ ሃይሎች በአገራችን ውስጥ የተፈጸሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎችን በማቀድ፣ በመተግበርና በማስተግበር በከፍተኛ ሁኔታ በአገር ውስጥና በውጭ ሃገራት የህግ አካላት እንደሚፈለጉ ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆናቸውም ጭምር ነው::
ስለሆነም ይህ ችግራቸው ሊያመጣባቸው የሚችለውን አደጋ በማየት አገሪቷን ለመከላከል ሳይሆን ይህንን የራሳቸውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችላቸውን ሁሉ ለማድረግ እንደቆረጡና ይህንን ችግራቸውን ሊያቃልልላቸው የሚችልን ካልሆነም ጊዜ ሊያራዝምላቸው የሚችልን ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል ማናቸውንም የአገሪቷን ጥቅሞች አሳልፈው ለመስጠት መቁረጣቸውን በቀላሉ መረዳት እንችላለን፣ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ከሚወስዱት አረመኔያዊ እርምጃ ልንመለከታቸው እንችላለን::
ከሁሉም በላይ ህወሓት/ወያኔ በተለያዩ ሰዓት የሚቀብራቸው በአንድ ወቅትና ወይም በተለያዩ ጊዜያት ሊፈነዱ የሚችሉ እምቅ ችግሮች በአገራችን ህዝቦች መካከል የፈጠራቸው እንዳሉ ሆነው አሁን ደግሞ ከጎረቤት አገራት በተለይም ከሱዳን ጋር ድንበር ለማካለል በሚል በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተጠንሥሶ የነበረውና አብሮት ያልተቀበረው አስተሳሰቡ ዛሬ በቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሊተገበር ከፍ ዝቅ እያሉ ያሉበት ጊዜ በመሆኑና በሌላ በኩል ከህወሓት/ወያኔ ማንነትና ይዞት ከተነሳው ዓላማው አንጻር ህወሓት/ወያኔ ሲፈልግ ኢትዮጵያዊ ይሆናል ሳይፈልግ ደግሞ ታላቋ ትግራይ ይሆናል ስለሆነም ለመሆኑ የማንን መሬት ነው ህወሓት/ወያኔ የሚደራደርበት ? ህዝቦች ለተወሰነ ጊዜ ሊጨቆኑ ይችሉ ይሆናል ሁል ግዜ ግን እየተጨቆኑ ይኖራሉ ማለት ግን እንዳልሆነ አውቆ መረዳት ያልፈለገው ህወሓት/ወያኔ እራሱ ላይ ትልቅ ችግርን ሊያመጣ መቃረቡን በትክክል መገመት ይቻላል::
ህወሓት/ወያኔ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆነና ኢትዮጵያዊነት ምኑም እንዳልሆነ የራሱ ታሪክ ያሳየናል:: ለዚህም ማስረጃ ለታላቋ ትግራይ ሲሆን አሰብ ይካለላል ለኢትዮጵያ ሲሆን አሰብ የኤርትራ ይሆናል ፣ ለህወሓት/ወያኔ ሲሆን ህገመንግስት ይጣሳል ለህዝብ ጥቅም ሲሆን ይኸው ህገመንግስት እንደፈለገ ይተረጎማል፣ የኢትዮጵያውያን ደም በሳውዲ ሲፈስ ህገወጥ ያሰኛል ለዚሁ ሰብዓዊ ግፍ ካሳን ከሳውዲ መጥየቅ ሲግባ 360 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት እቅዶች ለሳውዲዎች ያሸልማል፣ በኢትዮጵያ ላይ የመበታተን አደጋ ስትፈጥር የነበረችው ሱዳን በአምላክ እጅ መልሷን አግኝታ ስትበታተንና ደረቅ መሬቷን ስትታቀፍ ለህወሓት በታታኝ ቡድን ላደረገችው አስተዋጾ ከ1200 ኪ. ሜ በላይ በሚሸፍን መሬት ላይ እስከ 50 ኪ.ሜ ወደ ውስጥ የሚገባን መሬት ለመስጠት ሲሆን ሽንጡን ገትሮ ህወሓት/ወያኔ ሲንቀሳቀስ ምን ይባላል ? ህዝብን የሚያሸብርና ሽብርተኛ እራሱ ህወሓት/ወያኔ ሆኖ ሳለ የህዝብ ወገኖች የሆኑ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ታጋዮች ምንም ትጥቅ ሳይኖራቸው በሽብርተኝነት እየተፈረጁ በየዕስር ቤቶች የሚንገላቱ ለመሆን በቅተዋል::
በአጠቃላይ ህወሓት/ወያኔ የኢትዮጵያዊነት መለኪያም ሆነ ተግባር የሌላቸው ህይሎች ስብስብ የሆነና በኢትዮጵያውያን ደምና ላብ የራሳቸውን የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት ጥማት ለማርካት በቋመጡ ሃይሎች የተዋቀረ ቡድን በመሆኑና ይህንን የማፍያ ቡድንን እኩይ ተግባርን ለማገዝ በነዚሁ ዘረኞች በተዋቀረ ሠራዊት እየታገዙ አገራችንን ይዘው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናልና አገራችንን ለማዳን መቁረጥ ይኖርብናል:: ማንም ሊረዳን አይችልም ትግላችን ወደፊት ሲገፋ ግን ብዙዎች አቋማቸውን አስተካከለው ከኢትዮጵያውያን ጋር ይወግናሉ:: ምክንያቱም አገራችን በህወሓት/ወያኔዎች የባንዳ ሃይሎች ብቻ ሳይሆን በታሪካዊ ጠላቶችችንም እጅ ስር በመውደቃችንም ጭምር ነውና ::
ህወሓት/ወያኔ በወልቃይት ጥገዴ ህዝብ ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሰላም የተጠናቀቀ መስሎት ከሆነ ተሳስቷል:: የወልቃይት ጠግዴ ህዝብ፣ የሲዳሞ ህዝብ፣ የጋምቤላ ህዝብም ሆነ ሌሎች የህወሓት/ወያኔ የጅምላ ጭፍጨፋ ተጠቂዎች ሁሉ እንዳልተሸነፉ መታወቅ ይኖርበታል በእርግጥ መከራቸው ሁሌም የሚያደማ ቢሆንም :: ይልቁንም ህወሓት/ወያኔ አሁንም ሆነ ለወደፊትም ቢሆን በህዝብና በታሪክ ፊት በፍርድ ፊት ሊሆን የቀረበበት ጊዜ ነው:: ህወሓት/ወያኔ የሚቀብራቸው ፈንጂዎች ምን አልባትም በመጀመሪያ የሚያጠፉት እራሱን ህወሓትን/ወያኔን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ:: ምክንያቱም ለህዝቦች መከፋፈልና እልቂት የቀበራቸው ፈንጂዎች አቅጣጫቸውን ወደ እራሱ ወደ ህወሓት/ወያኔ እያደረጉ በመሆኑም ጭምር ነው:: ህወሓት/ወያኔና ባለሟሎቹ የኢህአዴግን ስም ተከናንበውና ተሸፋፍነው በህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ደባ ለማስቆም በሚደረገው ትግል ውስጥ ተሳትፎአችንን እናጠናክር በህወሓት/ወያኔ መቃብርም ላይ አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ እንመስርት:: ካልሆነ ህወሓት/ወያኔ አገሪቷን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊበታትናት መቁረጡን ከድርጊቱ መመልከት እንችላለን:: ቸር ይግጠመን::
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!