Tuesday, April 8, 2014

« ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም » ግብፅ ለኅዳሴ ግድብ ግንባታ ገንዘብ ላዋጣ አለች

በአባይ ወንዝ ላይ እየተገነባ ያለውን የታላቁን ህዳሴ ግድብ በመቃወም ግንባታውን ለማደናቀፍ የተለያዩ ዘመቻዎችን እያካሄደች ያለችው ግብፅ፤ ግድቡ ሁለቱን ሃገራት የጋራ የሚጠቅም ከሆነ ቦንድ በመግዛት በገንዘብ ለመደገፍ እንደ
ምትፈልግ የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማስታወቃቸውን የዜና ምንጮች ገለፁ፡፡
በቤልጅየም ብራሰልስ እየተካሄደ ባለው የአፍረካ ህብረት እና የአውሮፓ ህብረት የጋራ ጉባኤ ላይ ለመካፈል የተጓዙት የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነቢል ፋህሚ  የህዳሴ ግድብን ለማስቆም ከፍተኛ ዘመቻ ሲያካሂዱ ሰንብተዋል፡፡ ሮያል ኢንስቲትዪት ፎር ኢንተርናሽናል ሪሌሽን በተባለው ተቋም ሃሙስ እለት ባደረጉት ንግግርንና፣ ሃገራቸው የህዳሴውን ግድብ ግንባታ በገንዘብ ለመደገፍ ማቀዷን አስታውቀው ግድቡ ተሰርቶ ሲጠናቀቅ ግድቡን የማስተዳደር ስልጠን ከሁለቱ ሃገራት በተውጣጣ ኮሚቴ ስር መሆን አለበት፡፡
ቀደም ሲል የህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያና የግብፅ የጋር ፕሮጀክትነት እንዲሆን ተመሳሳይ ጥያቄ መቅረቡ የሚታወስ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ መንግስት ግን ጉዳዩ ከሉአላዊነት ጋር የተያያዘ መሆኑን በማመልከት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል፡፡  

ግድቡን የጋራ ለማድረግ በሚሆንበት ጉዳይ ላይ አበክራ እንደምትሰራ የተናገሩት ነቢል ፋህሚ፤ ከግድቡ ጋር በተያያዘ የግብፅን ጥቅም የሚቀናቀን ጉዳይ ላይ ግን ትዕግስት እንደሌላት ተናግረዋል፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በጉባኤው ላይ ከአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኃላፊ ካትሪን ጋር የመከሩ ሲሆን በጉባኤው ላይም የግድቡ ጉዳይ መነጋገሪያ እንደሆነ ኃላፊዋን መጠየቃቸው ተጠቁሟል፡፡ የህዳሴው ግድብ የመሰረት ድንጋይ የተጣለበት 3ኛ አመት መከበሩን በተመለከተ የግብፅ የሚዲያ ተቋማት በርካታ ዘገባዎች ሲያቀርቡ የሰነበቱ ሲሆን፤ የተለያየ አቋም አስተጋብተዋል፡፡ 

ግድቡ ሁለቱንም ሃገራት እንደሚጠቅም መሆኑ የሚገልፅ ዘገባ ያሰራጩ የሚዲያ ተቋማት እንዳሉዋሉ፤ ሌሎች ደግሞ ግብፅ ጥቅሟን ለማስከበር በተለይም በ1902 እ.ኤ.አ ሚኒልክ ፈርመውበታል የተባለውን ስምምነት በመጥቀስ በአለማቀፉ ፍ/ቤት ክስ እንድታቀርብ እየመከሩ ነው፡፡
የግብፅ ምሁራንና ባለስልጣናት በተደጋጋሚ የግድቡ መገንባት ማንኛውም 95 በመቶ ውሃ ፍላጎቷን ከናይል በምታገኘው ሃገራቸው ላይ የውሃ መጠኑን በ20 በመቶ በመቀነስ ጉዳት ያመያል ሲሉ እየተከራከሩ ሲሆን አንዳንድ የኢንጅነሪንግ እውቀት ያላቸው ምሁራኖቿ ግን ከዚህ በተቃራኒው ግድቡ ዓመቱን ሙሉ የውሃ ፍሰት ሳይቀንስ እንዲዘልቅ ይረዳል ሲሉ መከራከሪያ ሲያቀርቡ ተደምጧል፡፡ ግንባታው ከተጀመረ 3 ዓመት የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ 32 በመቶ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን ለግድቡ ግንባታ 11.5 ቢሊዮን ብር ከህብረተሰቡ ቃል የተገባ ሲሆን አጠቃላይ ወጪው 80 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

ምንጭ አዲስ አድማስ 

Monday, April 7, 2014

ኖርዌይ ኢህአዴግ ያሰረባትን ዜጋዋን ጉዳይ እየተከታተለች ነው


ማዕከላዊ እስርቤት ከፍተኛ ስቃይ ይደርስባቸዋል በሚል ተሰግቷል


የኢህአዴግን ካዝና የምትሞላዋ ኖርዌይ በማዕከላዊ እስር ቤት የሚገኙትን ዜጋዋን አስመልክቶ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ እየሰራች መሆንዋ ታወቀ። በማዕከላዊ እስር ቤት የታሰሩት ዜጋዋ ድብደባና ቶርቸር እንዳይካሄድባቸው በቅርብ ክትትል እያደረገች መሆንዋን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታውቀዋል።


ኢህአዴግን ከልጅነቱ ጀምራ ስትደጉም የኖረቸውና አሁን ደግሞ “በልማታዊ መንግሥትነት” መድባ ድጋፏን የምትዘረጋለት ኖርዌይ ዜጋዋን አስመልክቶ አስፈላጊውን ሁሉ የማድረግ ግዴታ እንዳለባት ይታወቃል። በዚሁ መሰረት የኖርዌይ ትልቁ ጋዜጣ ቀደም ሲል ጎልጉል ምንጮቹን ጠቅሶ ይፋ ያደረገውን ዜና የሚያረጋግጥ ዜና አሰራጭቷል።

ደቡብ ሱዳን የጸጥታ ሃይሎች አሳልፈው ለኢህአዴግ የሰጧቸው የቀድሞ የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦኬሎ አኳይ የኖርዌይ ዜግነት እንዳለቸው በማረጋገጥ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በቅርበት እንደሚከታተለው፣ አዲስ አበባ የሚገኘው የኖርዌይ ኤምባሲም ስራውን እየሰራ እንደሆነ አፍተን ፖስት አመልክቷል።

አፍተን ፖስት “የሰብአዊ መብት ተከራካሪ” ሲል በዜናው መክፈቻ የጠቀሳቸውን አቶ ኦኬሎ አኳይን አስመልክቶ የውጪጉዳይ ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን አማካሪ ስቫይን ሚኬልሰንን ጠቅሶ “አቶ ኦኬሎ የደቡብ ሱዳን የደህንነት ሃይሎች በደቡብ ሱዳንና በዩጋንዳ ድንበር መካከል ይዘዋቸዋል። አንደተያዙም ወደ ጁባ ሳይወሰዱ ተላልፈው ተሰጥተዋል” በማለት የጉዳዩን አካሄድ አመላክቷል።

የኢህአዴግን የገቢ ምንጭ የሆነችው ኖርዌይ በጉዳዩ አቋም በመያዝ ያስታወቀችው ስለመኖሩ ዜናውን የዘገበው አፍተን ፖስት ያለው ነገር የለም። ይሁን አንጂ ድርጊቱን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ኖርዌይ እንደምትቃወመው አልሸሸገም። አቶ አኳይ ለምን ወደ ስፍራው እንደተጓዙ በውል የተገለጸ ነገር እንደሌለ ዜናው ጠቁሟል። “በተመሳሳይ” በማለት ከዜናው ግርጌ ኢህአዴግ ለዴሞክራሲና ለሰብአዊ መብት ክብር እንደሌለው፣ በነጻ ፕሬስና በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ እያደር የከረረ ርምጃ በመውሰዱ ክፉኛ የሚዘለፍበት ጉዳይ እንደሆነ አጣቅሷል።

ጎልጉል መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓም (March 28, 2014) ቀን ዜናውን ይፋ በማውጣት ቅድሚያ ወስዶ ሲዘገብ አቶ ኦኬሎ ከደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸውን ጠቁመን ነበር። አሁን አዲስ በመጣው መረጃ በዩጋንዳና በደቡብ ሱዳን ድንበር ላይ ተያዙ መባሉ ምን አልባትም ኢህአዴግ ሊመሰርትባቸው ላሰበው ክስ አመቺ ሁኔታ ለመፍጠር ታስቦ እንደሚሆን ጥርጣሬ አለ። የዜናው ምንጭ አቶ ኦኬሎ ከጁባ በሄሊኮፕትር መወሰዳቸውን እንደሚያውቁ ገልጸዋል።

በመለስ ዜናዊ ውሳኔና ትዕዛዝ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማት፣ አድርጉ ተብለው የታዘዙትን ባለመቀበል አገር ጥለው የኮበለሉት አቶ ኦኬሎ ስለ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን ያገባናል በሚሉ “አክቲቪስቶች”፣ የፖለቲካ ድርጅቶችና፣ ማህበራት ዘንድ ዋንኛ ርዕስ ያለመሆናቸው ምክንያት አስገራሚ እንደሆነባቸው የሚጠቁሙ ዲያስፖራዎች ጥቂት አይደሉም። ከዚያም አልፎ አሁንም የመታሰራቸው እና እርሳቸውን ለማስፈታት በሚደረገው ሁኔታ ላይ የተፈጠረው ዝምታ አጠያያቂ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

አቶ ኦኬሎ ማዕከላዊ እስር ቤት እንደሚገኙና፣ በዚያም በከፍተኛ ደረጃ ቶርቸር ይደረጋሉ በሚል ስጋት ሁኔታውን ለሚመለከታቸው በማሳወቅ በኩል አንዳንድ ወገኖች እንቅስቃሴ መጀመራቸው ታውቋል። ኢህአዴግ እስካሁን ፍርድ ቤት ያላቀረባቸው አቶ ኦኬሎ “አሁን ስለሚገኙበት የጤና ሁኔታ የኖርዌይ ኤምባሲ የጉብኝት ሪፖርትና ይጠበቃል” ሲሉ እኚሁ ክፍሎች አመላክተዋል።

ከቤተሰባቸው ተነጥለው በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመሩት የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ደቡብ ሱዳን በህወሃት ሙሉ ቁጥጥርና ፈቃድ የምትንቀሳቀስ አገር መሆኗን እያወቁ ወደዚያ ማቅናታቸውን “ታላቅ ጥፋት” መባሉን መዘገባችን ይታወሳል። ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አሁንም አልተሳካም። ባምቤላ የአኙዋኮች ጭፍጨፋ ላይ ቀጥተኛ ተሳታፊ የነበሩት አቶ ኦሞት ኦባንግ በቅርቡ መኮብለላቸውና በብዙዎች ዘንድ አውሮጳ እንዳሉ ቢነገርም በትክክል ያሉበት አገር በይፋ አለመታወቁን መዘገባችን አይዘነጋም።
******************
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

ቤተሰብ አልባው የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ባልደረባ የአፈላልጉኝ ጥሪ !


ቤተሰብ አልባው የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ባልደረባ የአፈላልጉኝ ጥሪ !
የዘር የሃይማኖት የፖለቲካ ጽንፈኝነት ህሊናችንን ሳይጋርደው ይህን ከርታታ የቀድሞው የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት ባልደረባ ከቤተሰብ አልባነት ለመታደግ መለዕክቱን ሊንክ በማድረግ የበኩላችንን ድርሻ መወጣት ይጠበቅብናል ። ወደ ሙሉ ታሪኩ ይግብ
መጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ እባላለሁ ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ በውትድርና ስኖር በ1971 ዓ.ም ኤርትራ ሀገር ሄጄ ከ1ዓመት ቆይታ በኋላ ከወ/ሮ ወይኒቱ ወንድዬ ከ1972 እስከ 1983 ዓ.ም ትዳር መስርቼ አብሬ ስኖር 3 ልጆችን ማፍራት ችያለሁ የልጆቼም ስም 1ኛ. ገመቹ ጉርሜሳ በ1976 ዓ.ም የተወለደ ፣2ኛ. ምህረት ጉርሜሳ በ1977 ዓ.ም የተወለደች ፣ 3ኛ. ሚካኤል ጉርሜሳ የመጨረሻው ልጄ ሲሆን በ1983 ዓ.ም እኔ ግንባር ላይ በነበርኩበት ወቅት ቤተሰቦቼን እየተመላለስኩ እረዳና እጠይቅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ ጥቅምት 16 1983 ዓ.ም አዲስ አበባ (ሆለታ ገነት) ለኮርስ ሜጀር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሌ ማሠልጠኛ ተቋም ገባሁ ፡፡በዚያን ወቅት የ9 ወር ስልጠና ወስጄ ልመረቅ ስል ኢህአዴግ ስልጣን ያዘ እና ወደ አስመራ መሄድ አልቻልኩም ፡፡ በስልጠናው ወቅት በደብዳቤ ፣በስልክ ከቤተሰቦቼ ጋር ስንገናኝ የነበረ ሲሆን ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘ በኋላ ስልጠናው የተቋረጠ ሲሆን እኔም በእስር ለአመታት ቆይቻለው ፡፡ በ1988 ዓ.ም እስከ 1992 ዓ.ም ስለ ቤተሰቦቼ የተወሰነ መረጃ ባገኝም እነሱን ግን በአካል ለማግኘት ብጥርም አልተሣካልኝም፡፡ እናም ወዳጆቼ እነሱን ማግኘት በጣም ነው የምፈልገው ና ቤተሰቦቼ በፊት ይኖሩ የነበረው ቦታም አስመራ ከተማ ልዩ ስሙ ትልቁ ገጀረት አካባቢ ነበር፡፡ እባካችሁ አድራሻቸውን የምታውቁ ካላችሁ በ 09-35-32-60-98 /011-8-96-76-73 / ደውሉልን፡፡ ወዳጆቼ ሼር በማድረግ ተባበሩኝ !
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ ከመጋቢ፶ አለቃ ጉርሜሳ ገለልቻ በውስጥ መስመር የደረስኝ

Wednesday, April 2, 2014

ሰበር ዜና በእጅ አዙር የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት ስለባ የሆነው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ለወግኖቹ ክበር እስከ መስወአትነት እንደሚቆም ከስርቤት አረጋገጠ !

ባልታወቀ ምንክንያት ክቀርብ ግዜህ ወዲህ በሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ለእስር የተዳረገው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በወገኖቹ ላይ የሚፈጸመውን በደል እይተከታተለ ለሚዲያ የሚያበቃ በአረቡ አለም የሚገኝ ብቸኛ ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ነው ። ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ለወህኒ ከመዳረጉ በፊት ባለፉት አመታት በወገኖቹ ላይ የሚደርስውን ግፍ እና በደል አስመለክቶ ያቀርብ በነበረው የማለዳ ወግ መረጃ ቅበላው ያልተደሱቱ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ሹማምንቶች እና በወገኖቻቸው ህይወት ዶላር ሲሰበስቡ በከረሙ አፋኞች ማስፈራያ ይደርሰበት እነደበር ለማወቅ ተችሏል ። ጀግናው ጋዜጠኛ ለነዚህ ወሮበሎች ሳይበረከ እስከመጨረሻው ለወገኑ ክበር የህይወት መስወአትነት ለመክፈል የግባውን ቃልኪዳን ጠብቆ በእሳት ተፈትኖል። ዛሬ በዚህ ጀግና ጋዜጠኛ ላይ የተፈጸመውን ደባ እና ከጀርባው እና ማን እንዳሉ በስፋት መግለጽ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ነጻ ለማውጣት ለወህኒ ከተዳረገበት ግዜ ጀምሮ እሳካሁን እተደረገ ያለውን ጥረት ስለሚያወሳስበው ወደ ዝርዝር ሃስቡ ከመግባት መቆጠብ ግድ ብሏል ። ይህን ታላቅ ጋዜጠኛ ከተቻለ ከሳውዲ አረቢያ እንዲባረር አሊያም ወህኒ እንዲማቅቅ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ያለፈጸመውን ፈጸመ በሚል የጥላቻ ዘመቻ ከፌስ ቡክ አንስተው ለሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች የተሳሳተ መረጃ እስከመስጠት የድረሱ ዛሬም ዛሬም እንቅልፍ አጥተው የሚያማትሩ የህዝብ ጠላቶችን የሃሰት ውንጀላ በመከላለከል ይህን ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ ከደረሰበት አደጋ ልንታደገው ይገባል። 

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ