ሰሞኑን ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ከተማ አንድ ሆስፒታል «ቡግሻን» hospital ተኝተው የሚገኙት አቶ በረከት ስሞኦን የህክምና ግዜያቸውን ሳይጨርሱ ከሆስፒታሉ እንዳይርቁ ዶክተሮቹ አስጠነቀቁ ፡፤ የመንግስት ባለስልጣኑ ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን ሲያቀኑ በሁለት እና በሶስት ቀናት የተጠቀሰውን ህክምና በአጭር ግዜ ውስጥ አጠናቀው እንደሚመለሱ ተስፋ ቢያደርጉም ቀደም ብሎ ደቡብ አፍሪካ ላይ የተደረገላቸው የልብ ህክምና ባለስልጣኑን ለከፋ አደጋ ሳይዳርጋቸው እንዳልቀረ የሚገልጹት የሆስፒታሉ የምርመራ ምንጮች አቶ በረከት ስምኦን ዕረፍት ካልወሰዱ እና የዶክተሮች ቀርብ ክትትል ካልተደረገላቸው በህይወት ሊቆዩ እንደማይችሉ አስታውቀዋል።
አቶ በረከት በአሁኑ ሰአት በተጠቀሰው ሆስፒታል ውስጥ የእግር እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ ዶክተሮች እንዳዘዟቸው እና የሆስፒታሉ አርማ ያረፈበት የማታልብስ «ቢጃማ» መስል ነገር ለብሰው 4 ፎቅ ሲዊት ሩም 501 በረዳ ላይ ከአንድ ረዘም ካለ ደንዳን ሰውነት ካለው ሰው ጋር ሲጓራደዱ መታየታቸውን የአየን እማኞች አረጋግጠዋል። አቶ በረከትን ለማረጋጋት አላሙዲን በስልክ እና በአካል ከሚያደርጉላቸው ማጽናናት ውጭ እስካሁን ሄዶ ያያቸው ዲፕሎማተም ሆነ የመንግስት ባለስልጣን እንደሌለ እየተነገረ እንዚህ እማኞች ገልጸዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ አቶ በረከትን አልፎ አልፎ ወሰድ « ፌንት » የሚያደርጋቸው ነገር የልብ ምት አለመስተካከል መሆኑን በድፍረት መናገር ቢቻለም የኚህን የመነግስት ባለ ስልጣን እድሜ መገመት አግባብ እንዳልሆነ የገለጹ አንድ ስለ አቶ በረከት ጤንነት በቀርብ የሚከታተሉ ዶክተር ለታካሚውም ሆነ ለቤተሰቦቹ ታካሚው ይሞታል ብሎ መናገር ሙያዊ ስነምግባር እንዳልሆነ ተናግረው ታካሚው የልብ ምታቸው ተሰተካ ክሎ ከዚህ ሆስፒታል በሰላም መውጣት ከቻሉ ቀሪው የፈጣሪ ነው ብለዋል። እንደሚታወቀው እኚሁ ሚኒስቲር የዶክተሮችን የሰጧቸውን መረጃ አብነት በማድረግ የቀድሞው የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር የጤነንት ጉዳይን አስመልከተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅላይ ሚንስትር መለሰ ዜናዊ የጤንነታቸው ሁኔታ ተስተካክሎ በቀርብ ግዜ ወደ ነበሩበት መደበኛ ስራ እንደሚመለሱ ለኢትዮጵያ ህዝብ በገለጹ ማገስት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው የሚታወስ ነው ።
በአሁኑ ሰአት የመግስት ባለስልጣኑ መረጋጋት እንደማይታይባቸው እና አልፎ አልፎ እንደ እንቀልፍ ቢጤ ጭልጥ አድርጎ የሚወስዳቸው ነገር ከልብ ምት አለመስተካከል ጋር የተያያዘ የሚፈጠር አደገኛ ነገር መሆኑን የተለያየ ሙያዊ ግምታቸውን የሚሰጡ የአካባቢው ታዛቢዎች በእንደዚህ አይነት መልኩ ወደ ሆስፒታሉ ለህክምና ከገቡ ሃብታሞች እና ታዋቂ ሰዎች በሰላም ህይወታቸው ተርፎ የወጡ ጥቂቶች ብቻ በመሆናቸው የአቶ በረከት ህይወተም ከጥቂቶቹ አንድ ይሆን ዘንድ እያለቀሱ ሃዘናቸውን ገልጸዋል።
ይህ መረጃ እስከተጠናክረበት ግዜ ድረስ አቶ በረከት ስሞኦን በህይወት መኖራቸውን ያረጋገጡለን የአይን እማኞች የኢትዮጵያ መንግስት ሎኡካን ቡድን ሰሞኑን ለጉብኘት በይፋ ወደ ጅዳ ሳውዲ አረቢያ እንደሚመጣ እና የአቶ በረከት ስሞኦን የጤንነት ሁኔታ አስተማማኝ ካለሆነ መንግስት ቅድመ ዝግጅቶችን ማድረግ እንዲያስችለው ለኢትዮጵትያ ህዝብ በይፋ ሊገለጽ እንደሚችል ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት ያገኙትን ምስጢራዊ መረጃዎቻቸውን አድረስውናል ።
ማሳሰቢያ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ስለኚህ የመንግስት ባለስልጣን የጤንነት ሁኔታ ለመረዳት የሚፈልግ ወገን ለትክክለኛ መረጃ እንደ አመቺነቱ የሆስፒታሉን ስልክ ቁጠር ከወዲሁ ለመግለጽ ይሞከል። ምንጭ ታምራት ይደጎ