Tuesday, August 19, 2014

ለራሱ ነፃነት የሌለው ድረጀት የህዝቦችን ሰበአዊ እና ዴሞክራሲያዊ መበት ተግባርዊ አያደርግም ! የመኢአድ ሰሞነኛ ውዝግቡ !

 መኢአድ በመጣባቸው አስቸጋሪ የትግል ጊዜያት አሁን ላይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ታህሣስ 15- 17, 2003 ዓ. ም ወዲህ በአመራሩ ላይ በደረሰ ክፍፍል ፓርቲው ይህ ነው የሚባል ስራ ለመስራት እየተውተለተለ እስከ ነሐሴ 11 ቀን 2006 ዓ. ም ደርሶ በመካከሉ ይፈታል የተባለው የእርቅ ሂደት መና ሊቀር ችሏል፡፡

ጉዳዩ በፍ/ ቤትና በምርጫ ቦርድ ተይዞ መጠራቅቅ ውስጥ የወደቀው የፓርቲው ሕልውና የውስጥ ችግሩን ፈትቶ ከአንድነትና ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ተዋህዶ አንድ ወጥ ሀገራዊ  ችግር ይፈታል ተብሎ ሲታሰብ ‹‹ሽማግሌ›› ተብለው በተመረጡት በነ ዶ/ር በዛብህ ዝርክርክነት ያለውጤት በቁርሾ እንዲበተን ተደርጓል፡፡

ለአለመግባባቱ ምክንያት አቶ አበባው መሀሪ፣ ወያኔ አስርጎ ካስገባቸው፡- ሙላጌታ አበበ÷ ተስፋሁን አለሙ÷ መላኩ…እና ከትግራይ በወያኔ ተልከው ከመጡ መሰሉና ጋዳፊ በተባሉ‹ባልና ሚስት›(እነዚህ ቀደም ሲል በመኢአድ ውስጥ የትግራይ ተወካይ ነን በማለት መኖሪያ ቤታቸውን ቢሮ ነው በሚል ኪራይ ሲቀበሉና በጀት ተመድቦላቸው ሲያምታቱ የነበረ÷ ከ2004 ዓ. ም በኋላ አንድነት ፓርቲ ገብተው 4.000.00ብር በመቀበል አንዷለም አራጌን በመሰለል ለእስር ከአበቁ በኋላ ራእይ ፓርቲ ገብተው ሲያንጎዳጉዱ የነበረ÷ አሁን ከአቶ አበባው ጋር በመኢአድ የሚያነኩሩ ዋና ተሰላፊ ናቸው) ÷…ትክክለኛ አባላቱ ገብተው በተመረጡ ‹ሽማግሌዎች› አማካኝነት የተከሰተው ችግር በጭዋነት ተወያይተው ይፈታል ተብሎ በመታመኑ፡- ወ/ሮ ሳባ መኮንን የመአሕድ/መኢአድ መስራችና ታጋይ በቦታው በመገኘት፣ በምርጫ ግርግር ልጃቸው የሞተባቸው ወ/ሮ ይታይሽ አያሌው ድፎ ዳቦ ይዘው በመምጣት፣ ታህሣስ 17 ቀን 2003 ዓ. ም በጠቅላላ ጉባኤው ወቅት የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ በኢ/ር ሀይሉ ጉልበት ላይ በማስቀመጥ የተፈጠረው ችግር ሳይፈታ የት ነው የሚሄዱት ያሉት(ዛሬ ላይ ሞቸ በነበር ብለው የሚፀፀቱ) አቶ ነብዩ ዓለምይሁን ከስምምነቱ በኋላ ሁሉም አባላት የሚደርስ ጧፍና ሻማ ይዘው በመምጣት፣….ሌሎችም ነባር አባላት ተገኝተው እያለ ነው ከላይ በተጠቀሱት ‹አመራር › ተብየዎች ሊከሽፍ የቻለው፡፡ በእለቱ ቁጥሩ የበዛ ‹ደህንነት›፣ ፖሊስ፣ ኢዜ..አ….በጽ/ ቤቱ ዙሪያ ከበው ጉዳዩን ሲከታተሉ ነበር፡፡
መኢአድ ለአለፉት 3ዓመት ከ8 ወር ከ5 ቀን ወይምለ1349 ቀናት ከ18 ስዓትት ወይም ለ80,445 ሠዓታት ከማባከኑም በላይ ፤ የምዕራብ በለሳ የ2002 የተወካዮች ም/ ቤት ዕጩ አቶ ምሳው ዮሐንስን ጨምሮ ከማእከል 4 አባላቱን በወያኔ ገዳዮች በማስገደል፣ አቶ ብርሀኑ አባሆይን በመጥረቢያ ወገቡን በማስመታት፣….ቁጥሩ የበዛ አመራሩና አባላቱን በማሳሰርና በማስደብደብ፣…ለዘርፈ ብዙ ችግር የተጋለጠ፣ 2 በኢየሩሳሌም ሆቴልና በዋናው ጽ/ ቤቱ ያልተገባ ጠቅላላ ጉባኤ‹አድርጌአለሁ› ብሎ ብዙ ገንዘብ ያባከነ፣ በጽ/ ቤቱ ውስጥ ላሉት የወያኔ ደህንነቶች ወርሀዊ ደሞዝና አበል የሚከፍል፣ የበርካታ አባላቱንና የህዝቡን ምስጢር ለወያኔ እያሰጠ በራሱ ላይ ችግር የሚያደርስ(ገዥው ፓርቲ የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ 99% በእጃችን ነው ይላል)፣…..እቶ ያእቆብ ልኬ፣ አሰፋ ሀ/ ወልድ፣ አበባው መሀሪ፣….የተባሉ ፎርጅድ ‹መሪዎችን› በኢ/ር ሀይሉ ፈቃጅነት ባልተሟል ጉባኤ መርጫለሁ ብሎ እየዳከረ፣ ….የሚገኝ ፓርቲ ነው፡፡
ይሁንና በጠናካራ አባላቱ፣ አመራሩ፣ ደጋፊውና፣…..በሚቻለው መጠን ወደነበረበት ለማስመለስ ጥረትና ተጋድሎ እየተካሄደ ነው፡፡
አንድ ሊገነዘቡት የሚገባ አብይ ነገር ግን ለሚባክነው፡- ጊዜ፣ ጉልበት፣ የሰውኃይል፣ ገንዘብ፣ ውድ የቅስቀሳ ሥራዎች፣ በአባላቱና በአመራሩ ለደረሱትና ለሚደርሱት ማናቸውም ነገሮች፣…..ሁሉ አቶ አበባው(ኢ/ር ሀይሉ)እና በስራቸው ያሉት ወያኔዎች የሚያወራርዱት መሆኑን እንዲያውቁት የእምየ ኢትዮጵያ ቁርጥ ልጆች አበክረው ያሳስባሉ!!! በሕይወት፣ በደም፣ በሀገርና በሕዝብ፣ በገንዘብና በጊዜ ላይ የሚቀልዱት፣…. ሁሉ ‹‹ዝም›› ተብሎ የሚታለፍ አይደለም!!!
ርእየ- ሁለንተና             « ታምራት ይደጎ »
13/ 12/ 2006 ዓ. ም
አዲስ አበባ- ኢትዮጵያ

No comments:

Post a Comment