Monday, September 1, 2014

ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤል ተሰደደ ( በጌታቸው ሺፈራው )


  • 461
     
    Shar
ብስራት ወ/ሚካኤል
በተለያዩ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች የራሱ “አዲስሚዲያ” ብሎግን ጨምሮ በተለያዩ ድህረ-ገፆች አዘጋጅ እና ፀሐፊ ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤል መሰደዱ ታወቀ፡፡ ጋዜጠኛው ቀደም ሲል የፍኖተ-ነፃነት ጋዜጣ አዘጋጅ፣የኢቦኒ መፅሔት ዋና አዘጋጅ፣ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ኢሳው መፅሔት ባልደረባና አምደኛ፤ በኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣና በቅርቡ ወደህትመት የገባው ቀዳሚ ገፅ ጋዜጣ ላይም የተለያዩ የፖለቲካ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ በራሱና በብዕር ስም እንደሚፅፍ ይወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተመሰረተውና በመንግስት ከፍተኛ ቁጥጥርና ጫና ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) መስራች አባል፤ በኋላም የማኀበሩ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ በመሆን እያገለገለ እንደነበር ይታወቃል፡፡ 

ጋዜጠኛው ከዚህ በፊትም በመንግስት ደህንነት ኃይሎች በምሽት እገታ እንደገጠመው፣ ከስልክ ጠለፋ እስከ ዛቻና ማስፈራራት ይደርስበት እንደነበር ከዚህ ቀደም የወጡ መረጃዎች ቢያመለክቱም፤በተለይ ከጥቅምት 2006 ዓ.ም. ከአዲሱ ጋዜጠኞች ማኀበር መመስረት ሂደት ጀምሮ እና በሚያዚያ ወር 2006 ዓ.ም. 3 ጋዜጠኞችን እና 6 የዞን 9 ብሎገሮች በመንግስት ከታሰሩ በኋላ የመንግስት ደህንነቶች ክትትል ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ቀጣዩ እስር እሱ ላይም ሊፈፀም እንደሚችል በመረዳት ለቅርብ ጓደኞቹ አሳውቆ ነበር፡፡ 

ብስራት ባለፈው ነሐሴ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. አርብ ጠዋት አዲስ ባወጣው የስልክ መስመር የማዕከላዊ ስልክ ጥሪ ካስተናገደ በኋላ ለጊዜው ከአዲስ አበባ ውጭ መሆኑን በማሳወቅ ለሰኞ እንደሚቀርብ ምላሽ ከሰጠ በኋላ ባለፈው እሁድ ድንገት ሀገር ጥሎ መሰደዱ ታውቋል፡፡ 

በቅርቡ ከታሰሩት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች የእስር ስም ዝርዝር ውስጥ የማኀበሩ አመራሮች መኖራቸውና በቀጣይም መንግስት በአመራሮቹ ዙሪያ መረጃ እየሰበሰበ መሆኑ ምንጮች አረጋግጠው እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ቀደም ሲል የማኀበሩ ፕሬዘዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ፣ ገንዘብ ያዥ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ስዩም እና መስራች አባል ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ መሰደዳቸው አይዘነጋም፡፡ በአጠቃላይ ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤልን ጨምሮ በ2006 ዓ.ም. ብቻ 25 የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ሲሰደዱ፤3 የውጭ ዜጎች ጋዜጠኞችን ጨምሮ 20 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ደግሞ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል





ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ጋዜጠኛ ነበዩ ሲራክን ለማፈን የተቃጣው ሴራ ከሸፈ ።

ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ በመላው አረብ አለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እና በደል በማለዳ ወጉ መረጃዎችን በማቀበል የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በማያውቀው ጉዳይ  ተከሶ ዛሬ ፍ/ቤት መቀረቡን ውስጥ አውቂ ምንጮች ገለጹ ።      ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ኦገስት  27/8/2014 ማለዳ 4:00  በደረሰው የከስ ጥሪ የመጣውን ሁሉ በጸጋ ለመቀበል ህግ እና ስረአት አክብሮ ወደ     ፍ/ቤት መሄዱን የሚናገሩ    ምንጮች   በአካባቢው የሚገኙ የሳውዲ ህግ አሰከባሪዎች ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ተመስረተበት ስለተባለው   ወንጀል ምንም አይነት     መረጃ እንደሌላቸው አውስተው ጥሪውን ወዳስተላለፈለት ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ሪፖረት እንዲያደርግ መላኩን ይገልጻሉ ። 
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እረፍ ሲነሳው የከረመውን የሃስተ ክስ ለማጣራት መደበኛ ስራውን አቋርጦ ዛሬ እሁድ ለ31/8/2014 ማለዳ ደግሞ ፍ/ቤት ቢቀርበም ተመሳሳይ መልስ ስለተሰጠው ጥሪውን ወዳ ስተላለፈለት በተለምዶ ሽማልያ ስለላ የሚባል ፖሊስ ጣቢያ በማቅናት ሪፖርት ቢያደርግም ተረኛ የሳውዲ ፖሊስ መኮንኖች ስለጉዳይ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸው ጋዜጠኛውን በነጻ እንዳሰናበቱት ለመረዳት ተችሏል ። ጋዜጠኛ ነበዩ ሲራክ በማለዳ ወጎቹ ያቀርባቸው በነበሩ አሳዛኝ እና አሰቃቂ የእቶቻችን የአረበ አለም ህይወት ገጽታ በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ዘንድ አድናቆት እና ክበርን ያተረፈ ታላቅ ግዜጠኛ መሆኑ ቢታወቀም በዚህ ስራው ባልተደሰቱ ምስለኔዎች ቀደም ብሎ በቀረበበት የሃሰት ከስ ለእስር ተዳርጎ እንደነበር የሚያስታውሱ ወገኖች ጋዜጠኛውን በእጅ አዙር ለማዋከብ የሚደረገው ጥረት አንዱ አካል ሊሆን እንደሚቸል ይናገራሉ። ይህ ጋዜጠኛ በወቅቱ በተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች እና የኢትዮጵያ ህዝብ ተዕጸኖ ነጻ ቢወጣም በአረብ አለም ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ምን አይነት ዘጋባ እንዳያቀረብ በተላልፈበት ከባድ ማስጠንቀቂያ ከጀርመን ድምጽ ዘጋቢነቱ በመራቅ እስካሁንም የህሊና እረኛ መሆኑን ይናገራሉ ። 

በአሁኑ ግዜ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ ስለሚፈጸመው ግፍ እና በደል መናገር ወንጀል ሆኗል የሚሉት ምንጮች ። በተለይ በኮንተራት ሰራተኛ እህቶቻችን ሬሳ ዶላር የሰበሰቡ አንዳንድ የአሰሪ እና ሰራተኛ ኤጀንሲ ባለቤቶች ሃላፊነት የማይሰማቸውን ደካማ የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሻቸው እያሸከረከሩ በወገኖቻችን ላይ ስለሚደርሰው ግፍ እና በደል በአደባባይ በሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ ተጸዕኖ ማሳደር መቻላቸውን ይገልጻሉ። እንዚህ ምንጮች አያይዘው ሲገልጹ ምን እንኳን በኮነትራት ሰራተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ግፍ እና በደል ሃገር አቀፍ ተቃውሞ በማስነሳቱ መንግስት ከግል ጥቅማቸው ባሻገር የወገኖቻቸው ህይወትን ማየት በተሳናቸው የአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ በወስደው አንጻራዊ እርምጃ የአያሌ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ከስቃይ መታደግ ቢቻልም እነዚህን ወንጀለኞቸ ለፈርድ በማቅረብ ረገድ የውጨ ጉዳይ ሚንስተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብተው የነበረውን ቃል ማጠፋቸው ግፉ የተፈጸመበትን ድፈን የኢትዮጵያን ህዝብ እጀግ በጣም አሳዝኗል ብለዋል:: እንደሚታወቀው በተጠቀሱት ኤጀንሲዎች አማካኝነት ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ ወደ ተለያዩ አረብ ሃገራት በኳንተራት ቪዛ ገበተው ያሉበት ሁኔታ እሳክሁን በወል ከማይታወቀው በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ባሻገር በሰው እጅ ተገለውም ሆነ በተለያየ ምክንያት ህይወታቸው አጥተው የኤንባሲ አሊያም የቆንስላ ባለስልጣናት ለወላጆቻቸው ሳያሳውቁ መርዶ ነጋሪ በሌለበት አረብ በረሃ ስረአተ ቀብራቸው የተፈፀመ እህቶቻችን ማንነት በሚስጠር መያዙ ይነገራል። 
ምንጭ Ethiopian Hagere Jed Bewadi