Wednesday, January 7, 2015

በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዓውደ ዓመቱን አስመልክተው ያስተላለፉት አጭር መልዕክት !

እንኳን ለብረሃነ ልደቱ በስላም አደረሳችሁ ።
በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽቤት እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዘንድሮ ታህሳስ 29 /2007 በመላው ሀገራችን የኦርቶዶክስ እመነት ተከታዮች ዘንድሮ ተከብሮ የሚውለውን የጌታች መደሃኒታችን እየሱስ ከርስቶስ ልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ዝግ ሆኖ እንደሚውሉ ተገለጾል ። በተመሳሳይ መልኩ የጅዳ ዓለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት በነገው ዕለት ዝግ መሆኑን ከት/ቤቱ አመራሮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ዛሬ በመላ ሃገራችን ተከብሮ የሚውለውን እና ተከታታይ አናጻራዊ አውደ ዓመታትን በሳውዲ አረቢያ የምንኖር መእመናን በጋራ ተሰባስበን ለፈጣሪያቸው መስጋና የምናደርስበት የጸሎት ስፍራ እንዲፈቀድልን በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባችን ይታወሳል።
ይህ ጥያቄያችን እስካሁን መልስ ማግኘት ባለመቻሉ ሳውዲ አረቢያ የተለያዩ ግዛቶች እንደ ጨው ተበትነው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእምነቱ ተከታዮች  በያሉበት በየቤታቸው እንደ አመቺነቱ ተሰባስቦው በዓሉን ለማክበር በሚያደርጉት ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ አደጋዎችን መጋፈጥ ግድ ሆኖባቸዋል። በመሆኑ ህዝበ ከርስቲያኑ ማህበረሰብ  በአውዳ ዓመቱ ከሚደርስበት አደጋ ለመታደግ የሚያስችሉ ዘላቂ መፍትሄዎች ተነድፈው ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት  ለጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ጸሎታችን በቤታችን በሚል ረእስ ጥያቄ ማቀረባችን አይዘነነጋም ። ጥያቄው የቱንም ያህል ውስብስብ እና አስቸጋሪ ቢሆነም ቆንስላው እና ኤንባሲው የዜጎቻቸውን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተገንዝበው አንጻራዊ መላሽ ከመስጠት ይልቅ ዝምታን መርጠዋል። ዛሬም ሳንታክት ጥያቄያችንን እንደገና በማንሳት ሳውዲ አረቢያ ውስጥ እንድሚኖሩት ፊልፒን ፡ ሲሪላንካ ፡ ህንድ ...ወዘተ የውጭ ሃገራት ዜጎች እኛም በኤምባሲያችን ስር ባሉ የኮሚኒቲ ተቋሞት ውስጥ የጸሎት ቦታ እንዲፈቀድልን በድጋሜ አበክረን እንጠይቃለን ። 
እኛ በሳውዲ አረቢያ የምንኖር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር ባለን መልካም ግንኙነት ያልተደሰቱ የቆንስላው አንዳንድ ሹመኞች ይህን ህጋዊ መስረት ያለውን የመብት ጥያቄ  ለመቀልበስ በተለያዩ የሶሻል ሚድያ ገጾቻቸው እያነፈሱ ካለው ጥላቻ  ታቅበው የእግዛብሄን መንገድ መከተል እንደሚገባቸው እናሳስባለን። እነዚህ ወገኖች በየትኛውም አቅጣጫ እያደረጉ ሴጣናዊ  ሙከራ የቱንም ያህል ሃይማኖቱንም ሆነ ሰላማችንን ሊጎዳ እንደማይችል ጠንቅቀን ብንረዳም የህዝብ ከርስቲያኑን የጸሎት ቦታ ጥያቄን እንደ ነገር ትንኮሳ በመፈረጅ ህዝበ ሙስሊሙ ወገናችን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በሚኖረው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኑ ላይ ጥላቻ እንዲያድርበት እየተፈጸመ ያለው ደባ በይቀራት ሊታለፍ የማይችል ፀረ ሰላም ድርጊት መሆኑን በየትኛውም አቅጣጫ የተሰለፉ ወገኖች ሊረዱ ይገባል።
በሰላም ስም እይነገዱ ህዝብን በህዝብ ላይ ለማነሳሳት የሚቃጣቸው እንዚህ ወገኖች ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኤንባሲው ስር በሚገኙ የኮሚኒትው ንብረቶች ላይ ህዝበ ክርስቲያኑ መበት እና ስልጣን እንዳይኖረው እስከ ማግለል ርቀው ሄደዋል። ለዚህም በኮሚኒው ውስጥ ታቀፈው የነበሩ አንጋፋ አመራር አባላት በክርስትና ሃይማኖቱ ተከታይነታቸው ብቻ ቅጽል ስም እየሰጦቸው ከኮሚኒው ቅጥር ግቢ እንዲርቁ አድረገዋቸዎል። እንዚህ ጅዳ ቆንስላ እና ሪያድ ኤንባሲ የመሸጉ የዘመናችን ጭቃ ሹሞች ለህዝበ ክርስቲያኑ ባላቸው ጥላቻ ሰሞኑን በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ታትሞ የወጣውን የእንኳን አደረሳችሁ መለዕክት ያዘለውን ማስታወቂያ በጨቀየው ጽንፈኛ አስተሳሰባቸው ለመተቸት ሲቃጣቸውም ተስተውሏል። ህዝበ ክርስቲያኑ በሳውዲ አረቢያ ጅዳ እና ሪያድ ኮሚኒቲ ለመሸጉ ጸረ ሰላም ወገኖች ሳይበገር የጀመረውን ሰላማዊ የጸሎት ስፍራ ጥያቄ ከፍ በማድረግ እንደማንኛውም ዜጋ በጅዳ ቆንስላ እና በሪያድ ኤንባሲ ስር በሚገኙ ተቋማት ውስጥ አባልነታችን ማግኘት የሚገባንን መብት ለማስከበር የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን መቀጠል ይገባናል ። በአንጻሩ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዓውደ አመቱን አስመልክታችሁ ቢሮዎቻችሁን ከመዝጋት ባሻገር በስራችሁ በሚገኙ የኮሚኒቲ ተቋማት ለኦርቶዶክስ ምዕመናኑ የጸሎት ቦታ በመፍቀድ ታሪክ መስራት ይጠበቅባችሃል ። ታህሳስ 28/ 2007 በሳውዲ አረቢያ ፀሎታችን በቤታችን አስተባባሪ ኮሚቴ ጅዳ !

No comments:

Post a Comment