Friday, March 20, 2015

እናቶችን የሚያስለቅስ አገዛዝ - የፍርድ ድቤት ዉሎ (ለገሰ ወልደሃና)

የካትት 10/2007 ዓም የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀበት የነዘመነ ምህረት ችሎት፣ በቀጠሮው መሠረት፣ ዛሬ መጋቢት 10/2007 ዓም ተሰይሟ።
ዘመነ ምህረት፣ መለሰ መንገሻና ሌሎች ወደ 25 የሚጠጉ ወጣቶች በማእከላዊ ፓሊሶች ታጅበው 8:ሰአት 20 አካባቢ ፍርድ ቤት ግቢ ገቡ። እንደተለመደው በርቀት እጃቻችንን በማውለብለብ ሰላም አልናቸው። እነሱም ባልታሰረው እጃቸው አፀፋውን መለሱልን።
ዘመነ ምህረት ብዙም አልተጎሳቆለም። መለሰ መንገሻ ግን በጣም ከስቷል። ሰውነቱ ቢጫ ሆኗል። እንደዛም ሆኖ ፈገግታ ግን አልተለያቸው። ችሎት ከመግባታቸው በፊት የተቀመጡበት አግዳሚ ወንበር ላይ ሆነው፣ በምልክት ለመነጋገር ሞክረን ለመግባባት ችለን ነበር። ነገር ግን ፓሊሶች ከኛ ጋር የሚያደርጉት የምልክት መግባባት አይተው፣ ፊታቸውን አዙረው አስቀመጧቸው ። ተስፋ ሳንቆርጥ ሞከርን። አልተሳካም።

የችሎት ሁኔታ እንደሚታወቀው በዝግ የታየ በመሆኑ የነበረውን ሁኔታ ማወቅ አይቻልም። ዘመነና መለሰ መንገሻ ችሎት የገቡት ተለያይተው ነው። ከዚህ መረዳት የሚቻለው የተከሰሱበት መዝገብ ይለያያል ማለት ነው ። ሁለቱም ችሎት ሲገቡ ሌሎች ወጣቶች አብረዋቸው ገብተዋል።
የዛሬው የችሎት ሁኔታ ተጨማሪ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፓሊስ ጠይቆ ለመጋቢት 08/7007 ዓም ተቀጥሯል።
አንድነት ዘመነ ምህረት፣ የዘመነ ምህረት የበኩር ልጅ፣ በፍርድ ቤት አልተገኘም። የሕጻን አንድነትን ቦታ ተክተው፣ ከሰሜን ጎንደር ተጉዘው የመጡት፣ የቆራጡ ታጋይ ዘመነ ምህረት እናት ነበሩ። እኚህ እናት ታማሚ ናቸው። የወለደ አንጀታቸው አልችል ብሏቸው ህመማቸውን ችለው፣ ከሰሜን ጎንደር፣ ከ700 ኪሎሜትር በላይ ተጉዘው፣ «ልጄ በህይወት መኖሩን ካላየሁ አላምንም» ብለው፣ አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተገኝተዋል። በጣም ያሳዝናሉ።
የመጡበትን ምክንያት የልጃቸውን በህይወት መኖር አለመኖር ለማረጋገጥ ነበር። በካቴና ታስሮም ቢሆን አይተዋል። በውስጣቸው ምን እንደተሰማቸው ባላውቅም። ጥልቅ የሆነ ሀሳብ ገብቷቸዋል። ለሰው ከመናገር ዝምታን ። ከኚህ የጀግና እናት ጋር ትንሽ ለመጨዋወት ሞክረን ነበር ። እንባቸው እየቀደማቸው ማውራት አልቻልንም። በመጦሪያቸው ጊዜ መንከራተት በጣም ያማል። እስኪ የኝህ እናት ፀሎት ተሳክቶ ዘመነ ተፈቶ ከመንከራተት ያድናቸው ዘንድ እንፀልይላቸው ። (ምንጭ: Millions of voices for freedom)

ድምጻዊ ብረሃኑ ተዘራ ሰሞኑን የለቀቀው ነጠላ ዜማ የስረአቱን ካድሬዎችና ቱባ ባለስልጣናቱን አስበርገገ ።

ኢትዮጵያን ሀገሬ ጅዳ በዋዲ

ከሁለት ሳምንት በፊት « ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ አንድነት ይብጀናል ዛሬ » በሚል ነጠላ ሃገራዊ ዜማው የተደናገጡ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ድህንነት አባላት ክተትል ይደረግበት የነበረው ድምጻዊ ብረሃኑ ተዘራ ሰሞኑንን ወደ አሜሪካ ማቅናቱን ለማወቅ ተችሏል። የህዝብን ፍላጎት በሆነ ነገር በመጨበጥ መግታት እንደ ማይቻል የሚናገረው ድምጽዊ ብርህኑ ተዘራ በተለይ ከኢሳት ድምጽ ጋር ሰሞኑን ባደረገው ቃለ ምልልስ ሲገልጽ « በመንግስት የተከለከለ አንድ ነገር በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው በመጥቀስ ህዝቡ በተቃራኒ ጎራ መቆሙን አውስቷል ይህንንም ተከትሎ ሃገራዊ አንድነትና እውነታን ማንም መገደብ ስለማይቸል « ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ አንድነት ይብጀናል ዛሬ » የሚል ነጠላ ዜማው ወቅታዊና የህዝብን ስሜት የሚገልጽ በመሆኑ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ ተደማጭነትን 

ማግኘቱን አክሎ ገልጾል፡ በዚህ ነጠላ ዜማ ውስጥ

« አይደለም አየሩ አይደለም ተራራው ፣

ሲርብ የሚያበላው ሃገር ማለት ሰው ፣

ለሆዱ ያደረ ወዳጁን የረሳ ፣

ነፃነት ምኑ ነው ቢነገር ቢወሳ ፣

» በሚለው የስንኝ ቋጠሮ የተበሳጩ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎችና ቱባ ባለስልጣናት አርቲስቱ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ተደማጭነት ካለው የኢሳት ድምጽ ጋር ቃለ ምልልስ በማድረጉና ዛሬ አሌክስ አንደር ቨሪጂንያ ውስጥ የህዝብን ትግል መቀላቀሉን በሚያበስረው ዝግጀት በአሁኑ ግዜ ጥላቸውን በማያምኑ የመንግስት ሃይሎች ጥርስ ውስጥ የገባው አርቲስት ወደ ሃገር ሲመለስ ወከባ ሊፈጸምበት እንደሚችል ምስጢራዊ ምንጮች ይገልጻሉ። በአጭር ግዜ ውስጥ የአብዛኛውን ኢትይጵይዊ ትኩረት የሳበው የአርቲስት ብረሃኑ ተዘር ነጠላ ዜማ ኢትዮጵያ በመዲናይቱ አዲስ አበባና በተለያዩ ክፍለ ህገራት ምግቤቶች ቡና ቤቶችና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ተሽክርካሪዎች ውስጥ ጭመር ሳይቀር በስፋት በመደመጥ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡

«ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ፤

አንድነት ይበጀናል ዛሬ ፤

መቼም አይሻረም ኢትዮጵያዊነቱ፤

መኖር ግን አይሻም ያለነጻነቱ ፤

እኮ ! ማነው ሰጪ ማነውስ ከልካይ፤

ሰው እንዳሻው ቢኖር በሃገሩ ላይ ፤
እያለ የሚያዜማው ድምጽዊ ብርሃኑ ክኢስት ለቀርበለት ጥያቄ አያሌ የሃገር ፍቀር ዘፈኖችን እንደዘፈነ ግልጾ ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ የሚለውን ነጠላ ዜማ ከለቀቀ ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ ይህዝብን ተኩረት ማግኘቱ አግርሞትን እንደ ደጫረበት በመናገር ከአቅሙ በላይ የሆኑ ምስጋናዎች ከህዝብ ስለተቸረው በህዝብ ውስጥ ያለውን እውነታ በሙያው ማንጸባረቅ በመቻሉ መደሰቱን ገልጾ ክብርና አድናቆትን ለቸሩት ሀገር ውስጥና በውጭ ሃገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናውን አቅርቧል ። ድምጻው ብረሃኑ ተዘራ ዛሬ በአሜሪካ ቨርጅኒያ ግዛት ውስጥ አዲስ ያወጣውን ነጠላ ዜማ ሲዲ በነጻ እንደ ሚያድል ለመረዳት ተችሏል፡ ይህ በዚህ እንዳለ ከዝግጀቱ በኃላ አርቲስት ብረሃኑ ወደ ህገር ይመለስ አይመለስ እስካሁን በግልጽ የተባለ ነገር ባይኖረም ምናልባት ከመንግስት ጥቃት እራሱን ለመከላከልና በነጻነት ለመኖር አርቲስቱ የሌሎች የህዝብ ትግል አጋሮቹን ፈለግ ሊከተል ይችላል ተብሎ ይታመናል። Ethiopian Hagere Jed bewadi