Sunday, December 1, 2013

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች በወገኖቻችን ስም ለሁለተኛ ግዜ ህገወጥ የገቢ ማሰብሳቢያ ፕሮግራም አደረጉ ።




በዚህ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የመግስት ልኡካን ቡድን መሪ የወገኖቻችን ህይወት አሳስቢ መሆኑን ገለጹ ። 
=======================================================
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የመንፉሃን ሁከት ተከትሎ በቅርቡ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያቀናው የመንስት ሎኡካን ቡድን በየመጠለያው እና በየእስርቤቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ህይወት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ሳይሸሽጉ የአይን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ። ወገን ለወግን ደራሽ ወገን ነው በሚል ኖቬብር 29 2013 ምሸት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ከስደት ወደ ሃገራቸው ተመላሽ ወገኖቻችን ድጎማ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ከህዝብ ጋር ለመጀምሪያ ግዜ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ እንድተገኙ የሚነገርላቸው የመንግስት ሎኡካን ቡድን ተወካዮች በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ እየደርሰ ያለው ስቃይ እና በደል ከመቸውም ግዜ በላይ አስቃቂ እየሆነ መምጣቱን በወቅቱ ለነበሩ ታዳሚዎች ባድረጉት ነግግር መናገራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። 

በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን በንግግራቸው ላይ የገለጹት የመንግስት ልኡካን ቡድን ተጠሪ አንባሳደር ውብሸት አባዛኛው ወገኖቻችን ያሉበት ሁኔታ አሳዛኝ እና ልብ የሚነካ ከመሆኑም በላይ ሴት እቶቻችን እና ህጻናት ልጆቻቸው በመጸዳጃ ቦታ እና በፓፐርስ እጦት ንጽህናቸውን መጠበቅ ያልቻሉበት ሁኔታ እና ከቁጥጥር ውጭ የወጣ መሆኑን ተናግረዋል። ሚንስትሩ አክለው ሲገልጹ በአንድ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ባለው ትርምስ ወደ ሳውዲ አረቢያ ከገባች 3 ወር ያልሞላት የኮንሷ ብሄረሰብ ተወላጅ ኢትዮጵያዊት ወጣት ችግሯን በአረብኛ ወይም አማርኛ ቋንቋ መግለጽ ተስኖዋት ሌሎች ወገኖቿ ሊረዳዎት በማይችሉ የትውልድ ቋንቋዎ እይተናገረች ስቅስቅ በላ ስታለቅስ መታዘባቸውን ልብ በሚነካ አቀራረብ ለተሰብሳቢው በማስረዳት ወገኖቻችን አሁን ሳውዲ አረቢያ ስላሉበት ፈታኝ እና አስቃቂ የመከራ ግዜ አፋጣኝ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል። 

በሳውዲ አረቢያ ወደ ሃገሩ መግባት የሚፈልገው ኢትዮጵያዊ ቁጥር ከግዜ ግዜ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የሳውዲ አረቢያ እስርቤቶች በመሙላታቸው ለደህነቱ ዋስትና ያጠው ህዝባችን ከቤት ንብረቱ በመፈናቀል በየግዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ያለበቂ ምግብ ወሃ እና መስረታዊ ፍጆታ እየተሰቃየ እንዳለ እና ወደ ሃገሩ ለመግባት በሚያደርገው ቆይታ የከፋ እና አሰቃቂ አደጋዎች ሊገጥሙት እንደሚችል በማውሳት ለወገኖቻችን ትኩረት ሰጥቶ የህዝባችንን ህይወት ለመታደግ መረባረብ የሚገባን አሁን ነው ብለዋል። ይህ በዚህ እንዳለ ሰሞኑን በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃላ አቀባይ አንባስደር ዲናሞ ሙፍቲ በሳውዲ አረቢያ ወገኖቻችን ላይ እየደረስ ያለውን ችግር አስመልክተው የሚጋነን እንዳልሆነ በማጣጣል የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ የሪያድ ነዋሪዎች የመረጃ እጠረት ያለበት እና በግል ስሜት የተነገረ መሆኑን በማስታወስ በነ አንባሳደር ዲናሞ አይነት ለዜጎች ህይወት ዴታ በሌላቸው ደካማ የመንግስት ባለስልጣናት ሀገሪቷ መመራቷ ወደፌት በጣም አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል። 
ትላንት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ በተደረገ በዚህ ጥቂት የልማት ማህበር አባላት እና ደጋፊዎቻቸው ጨምሮ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግርም ላይ የመድረኩ መሪ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ወገኖቻችን በሃይማኖት በብሄር በቋንቋ ሳይለያዩ በአንድ ድምጽ አደባባይ በመውጣት በሳውዲ አረቢያ መንግስት ላይ ላደረጉት ጫና መስጋና ሊቸራቸው እንደሚገባ የገለጹበት አጋጣሚ በደማቅ ጭብጨባ እና ሆታ ለደቂቃዎች የአዳርሹን ድባብ ለውጦት እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች አንባሳደር ውብሸት በውጭ የሚኖሩ ፀረ ሰላም ሃይሎች ብለው እንዚህን ወገኖቻችንን በመፈረጅ መንግስታቸው ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው ጸረ ሰላም ድርጊት እያካሄዱ ያሉትን ቅጥረኞች በቅርብ እይተከታተሉ መሆኑንን በመግለጽ ከመደርክ አስተባባሪዎቹ አድናቆት የተቸራቸውን የኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እንቅስቃሴ በማውገዝ ታዳሚውን ክፉኛ አሳዝነዋል። 

በወቅቱ አንዳንድ ወገኖች መድረክ አጊተው እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች አንድ የህገር ሽማግሌ አባት የገቢ ማሰባሰባሰቢያ ፕሮግራሙን የተቀደሰ አላማ በማለት ገልጸው ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን ዛሬ የሳውዲዎቹ ጥቃት ያነጣጠረው መኖሪያ ፈቃድ በሌለው ወገኖችን ላይ ብቻ ሳይሆን የሃበሻ ደም ባለው ላይ ሁሉ ስለሆነ መንግስት ለደህነታችን ዋስትና ምን እየሰራ ነው በሚል ለልኡካን ቡድኑ ያቀረቡላቸው ጥያቄ ተድበስብሷ እንደታለፈ ገልጸዋል ። ጉዳዩ በብሄራዊ ደረጃ መታየት እንደሚገባው የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን የሪያድ ነዋሪዎች በወገኖቻችን ስም በየጓሮው ያለ ደረሰኝ የሚሰብሰበው ገንዘብ አሁን ሪያድ ውስጥ ላለው ወገናችን በምንም አይነት መልኩ ሊደርስ እንደማይችል ገልጾው ገንዘቡ የስደተኞቹን ጉዳይ ለመስፈጸም የጸህፍሀት መስሪያዎች እና መሰል ተዛማጅ ነገሮች የገንዘብ እጥረት አለብን እያሉ ለሚያዛጉት በሪያድ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች ኪስ ማደለቢያ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል። 

በስልክ ያነጋገርኳቸው አንድ ሪያድ ከተማ የሚኖሩ የሃይማኖት አባት በበኩላቸው ገቢ በማሰባሰቡ ጽንሰ ሃሳብ ላይ ተቃውሞ እንደሌላቸው ተናግረው የወገኖቻችንን ህይወት ለመታደግ ለአለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች በዚህ ዙሪያ ተሳታፊ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንክሮ መስራት እንደሚገባው እና ከሰደት ተመላሽ ወገኖቻችንን ለማቋቋም ካሰፈለገ በብሄራዊ ደረጃ ህጋዊ በሆነ መንገድ የገቢ ማሰባሰቢያው ፕሮግራም መደረግ ተገቢ መሆኑን መክረው አሁን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ በዲፕሎማቱ እየተድረገ ያለው የገበያ ግርግግር የተለመደ በመሆኑ በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። በወገኖቻችን ስም በሚደረግ በዚህ የገቢ መሰባሰቢያ ፕሮግራም በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤት 2 ሺህ ተማሪዎች ከያንድንዱ 10 ሳ ሪያል ለመሰብሰብ ዲፕሎማቱ እቅድ መያዛቸውን የሚገልጹ ምንጮች አርብ ምሽት በተድረገው ፕሮግራም ከልማት ማህበራት ከእድሮች ከኮሚኒቲው ማህበር እና ጉዳዩ ካልገባቸው አንዳንድ ወግኖች እስከ 3 መቶሺህ ሪያል በወገኖቻችን ስም መሰብሰቡን ለመረዳት ተችሏል ብለዋል። 

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳርሽ እንደዚህ አይነት የግቢ መሰባሰቢያ ፕሮግራም ሲደረግ ለሁለተኛ ግዜ መሆኑን የሚናገሩ ወገኖች ቀደም ሲል ላለፉት 11 ወራት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ አነስተኛ ኮንቴነር ውስጥ በር ተቆልፎባቸው ሲሰቃዩ ለነበሩ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ከ200 ለሚበልጡ እህቶቻችን የአይሮፕላን ትኬት መግዣ ፤ በተዘጋጀ የግቢ ማሰባሰቢያ ፕሮራም ላይ እስከ 1መቶ ሺህ ሪያል « ግማሽ ሚልዮን ብር » ተገኝቶ እንደበር በማስታወስ የተጠቀሰው ገንዘብ ለታቀደለት አላማ ሳይውል በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ መጠለያ ውስጥ የነብሩትን ወገኖቻችን ስበዕና ያልፈጠረባቸው በነዚህ አረመኔ ዲፕሎማቶች ለሳውዲ አረቢያ ፖሊስ ተላልፈው በመስጠታቸው ለከፋ ችግር እንደዳረጓቸው ገልጸዋል። እነዚህ የሪያድ ምንጮች አክለው ሲገልጹ የተጠቀሱት ወገኖች ለረጅም ግዜያት የሪያድ ኮሚኒት ግቢ ሲሰቃዩ የነበሩ መሆናቸው ግምት ውስጥ ገብቶ ከህዝብ በተሰብሰብው ገንዘብ የአይሮፕላን ትኬት ቀርቦላቸው በክብር ለሃገራቸው መብቃት ሲገባቸው በገዛ ዲፕሎማቶቻችን እንደዚህ አይነት ኢሰባዊ ድርጊት መፈጸሙ በምድርም በሳማይም የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን በምሬት ይገልጻሉ። 

ይህ በዚህ እንዳለ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያውያኑ ስም የተሰበሰብው 1 መቶ ሺህ ሪያል ወይም « ግማሽ ሚልዮን ብር » ዲፕሎማቱ ኪሳቸው መክተታቸውን የሚናገሩ ወገኖች 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ እስከ ከ200 የሚጠጉ ወገኖቻችንን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ጊዚያዊ መጠለያ በኖሩባቸው ግዜያቶች ከኮሚኒቲው ካፍቴሪያ እየወስዱ ሲበሉ ለከረሙት ቀልብ ወሃ እና መብራት ሂሳብ መወራረዱን ዲፕሎአምቱ በድፍረት መናግራቸው በጣም እንዳሳዘናቸው ጠቅሰው « ውሻ በላበት አፉ ይጮሃ እንዲሉ» እንዚህ አረመኔ በሪያድ የሚኖሩ ዲፕሎማቶች ሰሞኑንን በዚሁ አዳርሽ ለሁለተኛ ግዜ ያለደረስኝ ሲሰበሰብ የከረሙት 3 መቶ ሺህ ሪያል ወይም « 15 ሚልዮን ብር » ለስደተኛው ወገናችን በቀጥታ መድረሱን እንጠራጠራለን ብለዋል ።

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

Thursday, November 14, 2013

መቋጫ ያጠው መንግስት አልባው ኢትዮጵያዊ ስቃይ እና ሞት በሳውዲ አረቢያ ፡አሁንም ቀጥሏል !



ትላንት አመሻሹ ላይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፍሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርሽቶ በዋለው ተቃውሞ የሞተ ባይኖርም ኢትዮጵያውያኑ ድምጻቸውን ከፍ አድረገው አንድነን አንድነን ... መብታችን ይከበር ....እኛም ሃገር አለን ወዘተ... በሚል መፈክር ታጅበው ብሷታቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን የሚገልጹ የአይን እማኞች የሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመብተን በከፈቱት መንፉሃ እና ቶክስ  አካባቢውን ወደ ጦርነት አውድማ ለውጦት ማምሸቱን የገልጻሉ። 

የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች በመድረስ ተቃውሞውን መግታት ተችሎል ብለዋል ። እንዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሷ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መደሱን አክለው ገልጸዋል። ሰምኑን የሳውዲ አረቢያ መንግስት በውጭ፡ሃገር ነዋሪዎች ላይ ያወጣው ህግ የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያውያኑ ላይ እየወስዱ ባሉት የተናጥል እርምጃ አያሌ ወገኖቻችን ወደ ሃገሩ ለመመለስ ከየመኖሪያ ቤቱ ነቅሎ አደባባይ ቢወጣም ወደ ሃገር መግባት የሚያስችሉት ነግሮች በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ባለመመቻቸቱ ሰሞኑንን ከእልቂት ተርፈው ወደ እስርቤት የተጓጓዙ ከ 20 ሺህ የሚበልጡ ወገኖቻችን በምግብ ወሃ እና የመጸዳጃ ቦታ እጦት እይተሰቃዩ እንደሚገኙ ተግልጾል።

በአንድ ማጎሪያ 4 ቀናቸውን እንዳስቆጠሩ የሚነገርላቸው  ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያዊያን  እና ሪያድ መንፍሃ ጅዳ እና መካ እስከነ ልጆቻቸው በየመገዱ ፈሶ ቁም ስቅሉን እያየ ያለውን በመቶሺህ የሚቆጠር ወገን ብሷት ለማድመጥም ሆነ ለማየት ከሃገር የመጣ የመግስት ባለስልጣን አለመኖሩ ታውቋል። ይህ በዚህ እንዳለ ዛሬ ጅዳ በተለምዶ መስፈላ እይተባለ የሚጠራ አካባቢ በሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች እና በኢትዮጵያውያን መሃከል በተነሳ ግጭጥ 76 ሰዎች መቁሰላቸውን የሚገልጹት ምንጮች በዛ ቀውጢ የቶክስ እሩምታ በጥይት ተደብድቦ የተገደለ ኢትዮጵያዊ ሊኖር እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

ተቀማጭነታቸው ሪያድ እና ጃዳ ከተማ በሆኑት በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር እና የቆንስላው ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች ላይ ተስፋ የቆረጠው ኢትዮጵያዊ ሰድተኛ ወገናችን  በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ወደ ሳውዲ አረቢያ ተጉዘዋል የተባለው


 ለኡካን ቡድን ምንም አይነት የሚጨበጥ፡ነገር መስራት ባለመቻሉ ኢትዮጵያውያኑ ለከፋ አልቂት በመዳረግ ላይ መሆናቸው ተገልጾል ።ሰሞኑን የውጭ፡ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ክቡር አምባሳደር ዲናሞ ሙፍቲህ ኢትዮጵያውያኑ በሳውዲ አረቢያ እየተፈጸመባቸው ነው የሚባለው የጅምላ ግፍ እና በደል ይሄን ያህል የሚጋግነን እና ቦታ የሚሰጠው አለመሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ትላንት ምሽት መንፉሀ አካባቢ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ከ 17 በሚበልጡ አውቶብስ ተጭነው እንደተወሰዱ የሚነገርላቸው ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ህጻናት ሴቶች አረጋውያን ጨምሮ አያሌ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከሪያድ የ6 ሰአታት ጉዞ በሃላ ያልታወቀ መድረ በዳ የሆነ አካባቢ እንዲወርዱ መገደዳቸውን እና እስካሁንም ያሉበት ሁኔታ በውል እንደማይታወቅ ተገልጾል።

Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ

Thursday, November 7, 2013

አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ኢትዮጵያውያኑን ሰደተኛ ሳንጃ እና ቋጨራ ታጠቀዋል ብለው መናገራቸው ተቃውሞ ገጠመው።



ዕለቱ ኖቬበር 4 2013 የሳውዲ አረቢያ መንግስት የምህረት አዋጅ የግዜ ገደብ መጠናቀቅ አስመልክቶ ለተለያዩ የልማት ማህበር አባላት ኤንባሲው አርብ ኖቬብር 1 2013 በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ስብሰባ ጠርቶ እንደነበር የሚገልጹ ምንጮች ስብሰባው በኢትዮጵያውያን ቆጨራ እና ሳንጃ መታጠቅ ዙሪያ ኤንባሲው ማህብረሰቡን ለመነጋጋር አጀንዳ ኢዞ መቅረቡ ስብሰባው በጣም አሳፋሪ እና ኢትዮጵያውያንን በጅምላ ለመወንጀል ሆን ተብሎ የታቀደ ከስም ማጥፋት ዘመቻ ተለይቶ የማይታይ መሆኑንን ገልጸዋል ። 

በተለይ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን በወቅቱ ለተሰባስቢው ስለአጀንድው ሲገልጹ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው አካባቢ አያሌ በባህር የመጡ ኢትዮጵያውያን በተለምዶ «ባህር ሃይል እይተባሉ የሚታወቁ » መኖሪያ ፈቃድ የሌላቸው ኢትዮጵያውያን እንዳሉ ጠቀሰው እንዚህ ህገወጦች የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያወጣውን ህግ ተከትሎ የሚወሰድባቸውን እርምጃ ለመከላከል ሳንጃ መታጠቃቸውን ኤንባሲው በመረጃ አረጋገጦል ብለው መናገራቸው በአብዛኛው ተሰብሳቢ ዘንድ ተቃውሞን ቀስቅሷባቸዋል። ክቡር አምባሳደሩ በዚህ ዙሪያ ሰላማዊ ወገኖቻችንን በመወንጀል የሃገራችንን በጎ ገጽታ ለማጠልሸት በኤንባሲ ደረጃ አጀንዳ ተይዞ ስብሰባ መጠራቱ ያበሳጫቸው ተሰብሳቢዎች የአንባሳደሩን ጤናማነት እስከ መጠራጠር መድረሳቸውን ምንጮቻን አክለው ገልጸዋል። ድጋፍ እናገኛለን በልው የጠሯቸው ታማኝ የልማት ማህበራቱ ስራ አመራር የአባስደር መሃመድ ሃሰን ያቀረቡት ክስ ከምን ጭብጥ ተነስተው እንደሆነ ማብራሪያ እንዲሰጦቸው ስብሰባው ላይ ወጥረው ይዘዋቸው እንደነበር የሚገልጹት ምንጮች ስብሰባው ገና ከመነሻው በተሳታፌው ከፈተኛ ተቃውሞ አለመግባባቶች ተፈጥረው እንደነበር ይገልጻሉ፡፤ 

አንዳንድ የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን አባባል ያንገበገባቸው አስተያየት ሰጪ የቀረበው አንጀዳ ስህተት መሆኑንን ገልጸው ሴት እህቶቻችን ጉልበታቸውን ያፈሰሱበትን የወር ደሞዛቸውን ተነጥቀው ተደብድበው እና ተደፍረው በይጎዳናው ወድቀው የፍትህ ያለህ እያልን ጣረሞት እያሰማን ባለንበት የስደት አለም እኛው አጥፊ እኛው ገዳይ አረመኔ እና ጨካኝ ተብለን በተለያዩ ሚዲያዎች ስማችን ሲጠፋ እና የሃገራችን በጎ ገጽታ በማጉደፍ በባእዳን ጥላቻ የተቃጣብንን የስም ማጥፋት ዘመቻ አምባሳደሩ እንደ አንድ ሃገር መሪ ተወካይ መጋፈጥ ሲገባቸው የዝሆን ጆሮ ይስጥኝ ብለው ከርመው ዛሬ በድፍረት እኛፊት ቆመው እኛኑ ለመወንጀል መቃጣታቸው በጣም ያሳዝናል ብለዋል። 

በሌላ በኩል አንድ አስተያየት ሰጪ በበኩላቸው ሲናገሩ አንባሳደር መሃመድ ሃሰንን ከእንግዲህ እንደማያውቋቸው ገልጸው ስለኢትዮጵያውያን ለመናገር የሞራል ብቃት የሌላቸው ከሳቸው ይልቅ በዲፕሎማት ደረጃ አንቱ የሚባሉ እንደነ አቶ መስፍን እና መስል ዲሲፒሊን ያላቸው ኢትዮጵያዊያን የመግስት ተወካዮች ስለኮሚኒቲው ችግር ህዝቡን ማወያየት እንደሚገባቸው በአጽኖት ጥቀስ በኤምባሲው ዝርክርክ አሰራር የእድሉ ተጠቃሚ መሆን የተሳናቸው ወገኖቻችን ላይ ለሚደረሰው ማንኛውም አደጋ አንባሳደሩ ሃላፊነትን መውሰድ እንደሚገባቸው በሰጡት አስተያየት ከተሰብሳቢው በተደረገላቸው የድጋፍ ጭብጨባ በወቅቱ የስብሰባ አዳርሹን ድባባ ለውጦታል። 

አምባሳደር መሃመድ ሃሰን በአምባሳደርነት ማዕረግ ተሹመው ወደ ሳውዲ አረቢያ ከተላኩ ጀምረው በተለያዩ የግል ንግድ ላይ በእጅ አዙር ተሰማርተው ያለአግባብ የበለጽጉ ከበርቴ አምባሳደር መሆናቸውን የሪያድ ነዋሪዎች ያናገራሉ ። አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ኢትዮጵያ ውስጥ በአቶ ሙስጥፋ ሁሴን አሊዬ ስም በከፈቱት 2 የአሰሪ እና ስራተኛ ኤጄንሲ አማኝነት ወደ ሳውዲ አረቢያ መጠተው እስካሁን ድረስ ህልፈተ ህይወታቸውን ቤተሰቦቻቸው ላልተረዱ 3 ሴት እህቶቻችን ሞት ተጠያቂ ከመሆናቸውም በላይ በቅርቡ 2 ሚልዮን ሪያል « 5 ሚልዮን ብር » ወደ ሌላ ሃገር ለማሸሽ ሲሞክሩ በሳውዲ ደህነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር ከዋሉት ከቀድሞው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር አቶ ሙስጠፋ ሁሴን አልዬ ጋር አምባሳደሩ እጃቸው እንዳለበት ይጠረጠራል ። 

በአጠቃላይ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን መንፍሃ ውስጥ ቆጨራ እና ሳንጃ ታጥቆ መሽጓል በለው ለመወንጀል የፈለጉት የይተኛውን ብሄር አባል እንደሆነ ስብሰባው ላይ በይፋ ባይናገሩም በዚህ አካባቢ ቀደም ብሎ ጥቂት ስረአት አልበኛ ኢትዮጵያውያን መሃከል አልፎ አልፎ በሚቀሰቀስ የጉሩፕ ግጭት በሳንጃ እርስ በእርሳቸው እይተራረዱ በአካቢው ማህበረሰብ የለዕለት ተዕለት እንቅስቅሴ ላይ ቀላል የማይባል ተጸኖ ያሳድሩ የነብሩ ወጣቶችን ለምስታረቅ ኤምባሲው ቢጠይቀም ፈቅደኛ ሳይሆን መቅረቱ ይታወሳል። ይህ በተለምዶ መንፉ እይተባለ የሚጠራው አካባቢ ብዛት ያላቸው በባህር የሚመጡ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የከተሙባት እና አብዛኛ ኢትዮጵያዊ በንግድ ዘርፍ የተሰማራባት በመሆኑ በመርካቶነት የሚሰይሞት ወገኖች ለያሌ ኢትዮጵያውያን አሌናት እና የእድገት ማዕከል በመሆኗ  የአምባሳድሩን ንግግር ቀደም ሲል በተለያዩ ሚዲያዎች በኢትዮጵያውያን ላይ ከተቃጣ ውንጀላ ለይተው እንደማያዩት ይገልጻሉ። 

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

Sunday, November 3, 2013

ይህን ጉዳይ አይቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ፤ ልጆቼም እኔም ፍትህ እንሻለን”



“ልጆቼም እኔም ፍትህ እንሻለን”


“ልጆቼም እኔም ፍትህ እንሻለን”
(የሟች ኢ/ር ጀሚል ባለቤት፤ ወ/ሮ ፋጡ የሱፍ)
“ለመጀመሪያ ጊዜ የባሌን መታመም በስልክ ነው የሰማሁት፡፡ ሌላ ጊዜ ወገቡን ያመው ስለነበር ያው ህመሙ ነበር የመሰለኝ። ተኝቷል ወደተባለበት አሚን ጀነራል ሆስፒታል በፍጥነት ስሄድ ያጋጠመኝ ሌላ ታሪክ ነው፡፡ ባለቤቴ ጭንቅላቱ ተጐድቷል፤ አንድ የቀረ የሰውነት ክፍል የለውም፡፡ ተደብድቧል፡፡ ራሱን ስቶ እየቃዠ ነበር ያገኘሁት (… ከፍተኛ ለቅሶ …) ነገሩን ሳጣራ በብዙ ሰዎች ተደብድቦ ከቡታጅራ ነው ወደ አሚን ጀነራል ሆስፒታል የመጣው”
ይሄን የተናገሩት ግንቦት 20 ቀን 2004 ዓ.ም የ“ሊቃ” በዓልን ለማክበር ወደ ጉራጌ ዞን መስቃን ወረዳ፣ ሚኬኤሎ ገበሬ ማህበር፣ መልካሜ መስጊድ፣ ከጓደኞቻቸው ጋር ሄደው፣ ባደረሰባቸው ድብደባ ህይወታቸው ያለፈው የኢ/ር ጀሚል ሀሰን ባለቤት ወይዘሮ ፋጡማ የሱፍ ናቸው፡፡ በጉራጌ ዞን በመስቃን ወረዳ በየወሩ የሚከበረውን “ሊቃ” የተሰኘ ሀይማኖታዊ በዓል ለማክበር ግንቦት 20 ቀን 2004 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ሱማሌ ተራ ከሚገኘው መስጊድ ተነስተው ከ50 በላይ ሰዎች ወደ ስፍራው ተጉዘው ነበር፡፡ በእለቱ ሚኬኤሎ በተባለው አካባቢ መልካሜ መስጊድ ደርሰው ስርዓቱን ለመከታተል ገና እንደገቡ እጅግ በርካታ ዱላ የያዙ ሰዎች ከአዲስ አበባ የሄዱትን ሰዎች መደብደብ ጀመሩ። አገር ሰላም ብለው የሄዱት እንግዶች፤ በአካባቢው ሰው የዱላ ውርጅብኝ ሲወርድባቸው ያመለጠው አመለጠ፤ የተጐዳው ተጐዳ፤ ነገር ግን ኢ/ር ጀሚል ማምለጥ ባለመቻላቸው ዱላው ሁሉ ሰውነታቸው ላይ አረፈ። ጭንቅላታቸውም ላይ ድንጋይ ተጫነ፡፡ በሞትና በህይወት መሀል ሆነው ከአዲስ አበባ በተላከ አምቡላንስ አሚን ጀነራል ሆስፒታል ገቡ፡፡
ህይወታቸውን ለማትረፍ ዶክተሮችና ነርሶች አቅምና እውቀታቸውን እስከመጨረሻው አሟጠው ቢጠቀሙም የኢ/ር ጀሚል ህይወት ተስፋ ሰጪ አልነበረም፡፡ በአስቸኳይ ወደ ቱርክ ሄደው እንዲታከሙ የአሚን ጀነራል ሆስፒታል ዶክተሮች ትዕዛዝ አስተላለፉ። ጉዞ ወደ ቱርክ ሆነ፡፡ ቱርክ በደረሱ በሶስተኛው ቀን ኢ/ር ጀሚል ሀሰን ይህቺን አለም እስከወዲያኛው ተሰናበቱ። “በሰው አገር ደህና ሰውነት የሌለውን፣ በዱላ ባዘቶ የሆነውን የባሌን አስክሬን ይዤ ግራ ገባኝ፤ ልጆቼን አሰብኳቸው፤ ለልጆቼ አባታቸው ምን ማለት እንደሆነ የማውቀው እኔ ነኝ” ይላሉ፤ የአቶ ጀሚል ባለቤት ወ/ሮ ፋጡማ የሱፍ፡፡ “ልጄ ኪናን ጀማል በትምህርቱ ጐበዝ ነበረ፤ ኢትዮጵያን ወክሎ ቱርክ በመሄድ ተወዳድሮ አንደኛ በመውጣቱ ከኢስታምቡል ፓርላማ ሽልማት ተቀብሏል፤ አሁን ግን በአባቱ ሞት የተነሳ መማር አልቻለም” ብለዋል፤ ወ/ሮ ፋጡማ፡፡
የድርጊቱ መንስኤ
ወልቄጢ አካባቢ “ቃጥባሬ” የተሰኘ መስጊድ ይገኛል፡፡ መስጊዱ በኢ/ር ጀሚል ገዳይ ቅድመ አያት በሀጂ ኢሳ እንደተሰራ የአካባቢው ነዋሪዎች ያስረዳሉ፡፡ ሀጂ ኢሳ በአካባቢው እስልምናን ያስፋፉ አስተማሪና በአካባቢው ህዝብ ተቀባይነት ያላቸው ሼክ እንደነበሩ ነዋሪዎቹ ይመሰክራሉ፡፡ ሀጂ ኢሳ ካለፉም በኋላ ልጃቸው ሻለቃ ሱልጣን ሀላፊነቱን ተረክበው የእስልምናን እምነት በትክክለኛው መንገድ ሲያስተምሩ፣ የተጣላን ሲያስታርቁ፣ ለታመመ ሲፀልዩና ሲያድኑ የቆዩ የሀይማኖት አባት እንደነበሩ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው የአካባቢው ሰዎች ይናራናሉ፡፡ እኚህ አባት በስልጤ፣ ጉራጌ፣ በሶዶ ወረዳ የተለያዩ መስጊዶችን በማሰራት እምነቱ በትክክለኛው መንገድ እንዲቀጥል የራሳቸውን አሻራ ጥለው ማለፋቸውን ነዋሪዎቹ ይመሰክራሉ፡፡
እንደ አካባቢው ነዋሪዎች ገለፃ፤ ሀይማኖቱ እየተበላሸና ሌላ መልክ እየያዘ የመጣው ከሻለቃ ሱልጣን ልጅ እና ከልጅ ልጃቸው በኋላ ነው፡፡ በተለይ የልጅ ልጃቸው አቶ ሰልማን ሰይድ ፋሪስ፤ ከቅድመ አያቶቻቸውና ከአያቶቻቸው የተረከቡትን የእምነት ስርዓት ወደ ጐን በመተው፣ “ከአላህ ይልቅ እኔን አምልኩ” በሚል ወደ ጥንቆላና ባዕድ አምልኮ ቀየሩት ይላሉ፤ ነዋሪዎቹ፡፡ ይህን ጉዳይ አጥብቀው ከሚቃወሙት ውስጥ ደግሞ የሰልማን ሰይድ ፋሪስ አጐት በድሩ ሱልጣን አንዱ እንደነበሩ ይነገራል፡፡ በድሩ ሱልጣን፤ የሰልማን ሰይድ ፋሪስ የአባታቸው ወንድም (አጐታቸው) ናቸው፡፡
“ይሄ ነገር አይሆንም፤ ሰው ሁሉ ማመን ያለበት በፈጣሪው በአላህ ነው፤ ወደ አላህ መንገድ መመለስ አለብህ እያልኩ ሰው ሁሉ እሱን እንዲያመልክ የሚያደርግበትን መንገድ እቃወም ነበር፤ በዚህ ነው ሊገድለኝ የነበረው” ይላሉ፤ ከሞት የተረፉት አጐቱ አቶ በድሩ ሱልጣን፡፡ መጀመሪያ ሊገደሉ እቅድ የተያዘባቸው አጐቱ አቶ በድሩ ሱልጣን እንደነበሩና ግንቦት 19 ቀን 2004 ዓ.ም እራሱን “የሀይማኖት መሪ” እያለ የሚጠራው አቶ ሰልማን ሰይድ ፋሪስ፤ ለታናሽ ወንድማቸው እና ለተከታዮቻቸው መመሪያ ሲያስተላልፉ ሰምቻለሁ ብለዋል - አንድ የአይን እማኝ፡፡
የቡታጅራና የአካባቢው ከፍተኛ ፍርድ ቤት ጉዳዩን ሲመረምር ከቆየ በኋላ ህዳር 7 ቀን 2005 ዓ.ም (ኢ/ር ጀሚል ሐሰን ከተገደሉ ከስድስት ወራት በኋላ) የግድያው ዋና መሪ፣ አዘጋጅና አዛዥ እንዲሁም የግድያው ቀድሞ ጀማሪዎች የሀይማኖት መሪ ናቸው በተባሉት:- ሰልማን ሰይድ ፋሪስ ሱልጣን፣ ወንድማቸው ነሲቡ ፋሪስ ሱልጣን፣ ወልዩ ቦንሰሞና ሁሴን አብደላ በተባሉት ተከሳሾች ላይ በሶስት ተደራራቢ ወንጀል ክስ ተመስርቶ እንደነበር የአቃቤ ህግ መዝገብ ያስረዳል፡፡ ክሱም ከባድ የነፍስ ግድያ፣ በከባድ የነፍስ ግድያ ሙከራ እና ታስቦ የሚፈፀም የንብረት ማውደም የሚል ሲሆን ተከሳሾቹ የፈፀሙት ወንጀል፤ (በሁለት ተደራራቢ ክሶች) ከእድሜ ልክ እስራት እስከ ሞት የሚደርስ ፍርድ የሚያሰጥ ቢሆንም በቅጣት ማቅለያ ከ20 እስከ 11 ዓመት እስር ተፈረደባቸው፡፡ ክስ የቀረበባቸው 22 ሰዎች ቢሆኑም ሁለቱ አቃቤ ህግ አላስመሰከረባቸውም በሚል በነፃ ሲሰናበቱ፣ 20ዎቹ እንደየጥፋታቸው መጠን እስር ተፈረደባቸው - ከ11-20 ዓመት፡፡
የቡታጅራና አካባቢው ነዋሪና አቃቤ ህግ ግን በፍርዱ ደስተኛ አልነበሩም፡፡ ጥፋተኞቹ ሞት እና እድሜ ልክ እስር ሊፈረድባቸው ሲገባ ፍ/ቤቱ የሰጠው ብያኔ አግባብ አይደለም ያለው አቃቤ ህግ፤ ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሆሳዕና ምድብ ችሎት ይግባኝ ጠየቀ፡፡
በቡታጅራና አካባቢው የህግ ባለሙያ የሆኑትና ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ አንድ ግለሰብ ጉዳዩን በቅርበት እንደሚያውቁ ጠቁመው፤ ጥፋተኛ የተባሉት ግለሰቦች በፊናቸው ምድብ ችሎት ሆሳዕና እያለ፣ እነሱ ግን ሀዋሳ በመሄድ ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ማለታቸው አግባብ አልነበረም ይላሉ፡፡ የሆነ ሆኖ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት የጥፋተኞችን ፋይል ከፍቶ ጉዳያቸውን ካየ በኋላ፣ የቡታጅራና አካባቢው ጠ/ፍ/ቤት አቃቤ ህግ ሆሳዕና ምድብ ችሎት ይግባኝ ያለበትን መዝገብ አጣምሮ ለማየት የሟች ጉዳይ መዝገብም ወደ ሀዋሳ ተዛወረ፡፡ የጉዳዩ ሂደት መዝገብ እንደሚያሳየው፤ በክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት በአቶ ታረቀኝ አበራ አይዶ እና በሌሎች ዳኞች የታየው የሁለቱ ወገኖች ይግባኝ የሟችን መዝገብ በዝርዝር ሳይመለከት እንዲሁም ተከሳሾቹ ጥፋተኛ የተባሉበትን ከፍተኛ የነፍስ ግድያ ወንጀል ተራ አምባጓሮ ወደሚለው በመለወጥ፣ “ከአዲስ አበባ ሊቃችንን ሊያበላሹ ይመጣሉ፤ ዱላ (ሽመል) ይዛችሁ ደብድቧቸው፣ ይህን ያላደረገ ከእኔ ጋ እንደተጣላ ይቁጠረው” የሚል ትዕዛዝ በማስተላለፍ ግድያውን በቀጥታ መርቷል በሚል 14 ዓመት የተፈረደበትን ሰልማን ሰይድ ፋሪስ፤ አቃቤ ህግ ማክበጃ አላቀረበም በሚል በቅጣት ማቅለያ ወደ አምስት አመት፣ የግድያውን ሂደት ዱላ በማሳረፍ አስጀምሯል የተባለውና የሰልማን ሰይድ ፋሪስ ታናሽ ወንድም የሆነው ነሲቡ ፋሪስ ከ19 ዓመት ወደ ዘጠኝ አመት ሲቀነስላቸው፤ የሌሎቹም ከ13 እና ከ11 ዓመት ወደ አንድ አመት ከስምንት ወር በመቀነሱ በጠቅላይ ፍ/ቤቱ ውሳኔ፣ እጃቸው ከተያዘ ጀምሮ አመት ከስምንት ወር ያለፋቸው 14 ሰዎች በነፃ ሊለቀቁ ችለዋል። ይህም ውሳኔ በሟች ቤተሰብ ዘንድ ለቅሶና ዋይታን ፈጥሯል። በዚህ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸውና ሂደቱን ሲከታተሉት እንደነበር የገለፁልን የህግ ባለሙያ፤ ጉዳዩን የስር የቡታጅራና አካባቢው ፍ/ቤት፤ ተንትኖ እንዳየው፤ ከ50 በላይ የሰነድና ከ50 በላይ የሰው ማስረጃ ቀርቦለት በትክክል መወሰኑን ይናገራሉ፡፡ ይህን ውሳኔ ጠቅላይ ፍ/ቤቱ በአንድ አንቀፅ መሻሩ ፍትህ መዛባቱን እንደሚያሳይ የህግ ባለሙያው ገልፀዋል፡፡
“አጠቃላይ የሂደቱ መዝገብ እጄ ላይ ስላለ በደንብ ተመልክቼዋለሁ” ያሉት የህግ ባለሙያው፤ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ የኢፌዲሪን የቅጣት አወሳሰን መመሪያ የጣሰ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በሌላ በኩል ባለሙያው “ስህተት” ነው ያሉት 539 1(ሀ) ከፍተኛ የነፍስ ግድያ ወንጀል ወደ 540 ተራአምባጓሮ መቀየሩን ነው። ከተቀየረም የተቀየረበት አጥጋቢ ምክንያት መኖር ነበረበት፤ ነገር ግን “ይህን አልተቀበልኩም፣ ይሄ አያስኬድም” እያለ ጠ/ፍ/ቤት የወሰነው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት እንዳለበት በግልፅ ያሳያል ብለዋል፡፡
የሟች ባለቤት ወ/ሮ ፋጡማ የሱፍ በበኩላቸው፤ በጠ/ፍ/ቤቱ የተሰጠው ውሳኔ በእርሳቸውም ሆነ በልጆቻቸው ላይ ከፍተኛ ሀዘን እንደፈጠረባቸው ይናገራሉ፡፡ “አባቴን የገደለው ሰው አምስት አመት ከተፈረደበት እኔም እሱን ገድዬ አምስት አመት መታሰር አያቅተኝም” በሚል ልጄ ወደበቀለኝነት ሀሳብ ገብቷል ሲሉ “የፍትህ ያለህ” ብለዋል፡፡ “እኔም ሆንን ልጆቹ ኢትዮጵያዊያን ነን ልጆቼን የት ሄጄ ላሳድግ የልጄን ሀዘንና የበቀለኝነት ስሜት እንዴት ነው የማስወግደው?” በማለት ያለቅሳሉ፡፡
“ትክክለኛ ፍርድ አገኛለሁ ብዬ ከአዲስ አበባ ሀዋሳ 35 ጊዜ ተመላልሻለሁ፤ እዛም ደርሼ ለሌላ ጊዜ ተዛውሯል፣ ከሰዓት ነው እየተባልኩ ልጆቼንና ስራዬን ጥዬ ተንከራትቻለሁ” ያሉት ወ/ሮ ፋጡማ፤ በውሳኔው በጣም ማዘናቸውን ተናግረዋል፡፡ “የጠ/ፍ/ቤቱን ፕሬዚዳንት አነጋግሪ ተብዬ አቶ ታረቀኝን እያለቀስኩ ትክክለኛ ፍርድ እንዲሰጡኝ ጠይቄ ነበር” ያሉት ወ/ሮዋ፤ “ትክክለኛ ፍርድ ታገኛለሽ፤ መዝገቡ በእኔ እጅ ነው” ብለውኝ ስጠብቅ፣ ጭራሽ 14 ሰዎች በነፃ ሲለቀቁ፣ የነፍሰ ገዳዮቹ ቅጣት ወደ አምስትና ዘጠኝ አመት መቀነሱ አሳዝኖኛል ብለዋል፡፡
“ውሳኔው ከአድልዎ፣ ከአምቻ ጋብቻ የፀዳ ነው”
አቶ ታረቀኝ አበራ
በጉዳዩ ዙሪያ ሀዋሳ ቢሯቸው ተገኝተን ያነጋገርናቸው የደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ታረቀኝ አበራ፤ “ጉዳዩን በደንብ አውቀዋለሁ፤ ውሳኔውም በትክክል ታይቶ ተፈትሾ የተወሰነ ከአድልዎ፣ ከአምቻ ጋብቻ የፀዳ ነው” ብለዋል፡፡ ሆሳዕና ምድብ ችሎት እያለ፣ አቃቤ ህግም በሆሳዕና ይግባኝ ብሎ ሳለ ጥፋተኞቹ ወደ ክልሉ ጠ/ፍ/ቤት መጥተው ይግባኝ ሲሉ ፋይል ተከፍቶ መስተናገድ ነበረባቸው ወይ? በሚል ላነሳነው ጥያቄ ሲመልሱ፣ “መንግስት በየአቅራቢያው ምድብ ችሎቶችን የከፈተው ሰዎች የጊዜ፣ የገንዘብና መሰል ብክነቶች ለመከላከል ነው” ያሉት ፕሬዚዳንቱ ሆኖም ለየት ያሉ ጉዳዮች ሲመጡ የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፋይል እንደሚከፍት ገልፀው፤ ይሄኛውን ጉዳይ ለየት የሚያደርገው ሀይማኖታዊ ይዘት ስላለው ነው ይላሉ፡፡ አንቀፁ ከ539 /ሀ/ (1) እንዴት ወደ 540 (ተራ አምባጓሮ) ወደሚለው ለምን ተቀየረ? በሚል ላቀረብነው ጥያቄም፤ “ጉዳዩ የተፈፀመው በሀይማኖት ቦታ ሆኖ በድንገት በተነሳ ግርግር እንጂ የታሰበበት እንዳልሆነ ፍ/ቤቱ አጣርቷል፤ በዚህም ውሳኔ ሰጥቷል” ይላሉ፡፡
ይሁን እንጂ የስር የቡታጅራ አካባቢ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፤ ሰልማን ሰይድ ፋሪስ ተከታዮቹን በመልካሜ መስጊድ በ19/09/2004 ዓ.ም ሰብስቦ “ነገ-ከአዲስ አበባ የሚመጡ እንግዶች አሉ፤ የሊቃ ስርዓቱን ለማበላሸት ስለሆነ ጅሀድ (ጦርነት) እናውጅባቸዋለን፡፡ ሁላችሁም ዱላ ሽመል ይዛችሁ ቀጥቅጣችሁ ግደሉ” ስለማለቱ 50 የሰው፣ 50 የሰነድ ማስረጃ አቅርቦ የቅጣት ውሳኔ ማስተላለፉን መዝገቡ ያስረዳል፡፡ “አቶ ሰልማን ሰይድ ፋሪስ ከዚህ ቀደም ብዙ የግድያ ሙከራዎች አድርጓል” የሚሉት አንድ የቡታጅራ አካባቢ ነጋዴ ስለተፈጠረው ነገር በደንብ እንደሚያውቁና በቅድሚያም ድርጊቱን እንደሚያወግዙ በመግለፅ ነው አስተያየታቸውን የጀመሩት፡፡ ከዚህ በፊት ወንጀለኛው (ሰልማን ሰይድ ፋሪስ) በሀይማኖት ሽፋን ህብረተሰቡን ያለ አግባብ “የሀይማኖት መሪ ነኝ” በማለት ራሱን ሰይሞ ምንም የሀይማኖት ምልክት በሌለበት እየበዘበዘ እንደሚገኝ ይናገራሉ፡፡ “ሰውንም ወዳልተፈለገ እምነትና ጥንቆላ ከቶታል” የሚሉት ነጋዴው፤ ይህ ሰው ከአቶ ጀሚል በፊት በጠራራ ፀሀይ ሁለት ጊዜ ሌሎች ሰዎች ላይ ሽጉጥ መተኮሱን፣ በዚህም ክስ እንደተመሰከረበት ጠቁመው “የሀይማኖት መሪ ነው” በሚል በነፃ መለቀቁን ይናገራሉ። “የወረዳው ይህን ያህል ሽፋን መስጠት አሁን ወደ ነፍስ ግድያ አሸጋግሮታል” ብለዋል፡፡
ከዚህ በፊት የሊቃ ስርዓት በሰላም ነው በየወሩ ሲከበር የነበረው ያሉት እኚህ ግለሰብ፤ “ከአዲስ አበባ የሚመጡ ስርዓቱን የሚያበላሹ ሰዎች ስላሉ በሰላም እንዳይመለሱ በዱላ ደብድባችሁ ግደሉ” የሚል ትዕዛዝ ማስተላለፉንና በዓሉ በሚከበርበት ቀን እርሱ በበዓሉ ላይ አለመገኘቱን፣ ከዚያ በፊት ግን ከሊቃ ስርዓቱ ቀርቶ እንደማያውቅ መስክረዋል፡፡
“አሁንም ቢሆን ማረሚያ ቤት ሆኖ በየጊዜው በመኪና እየታጀበ ወደ ቤቱ ይሄዳል፣ ኦሮሚያ ክልል ላይ የእርሻ ማሳ አለው፤ እርሱን ሊያሰራ ይሄዳል” ያሉት ግለሰቡ፤ ይህ የሚደረግለት ሽፋን ለቀጣይ ነፍስ ግድያ ያበረታታዋል ብለዋል፡፡ “ድብደባውን እና ግድያውን ፈፅመው ሲመለሱ ሌላው ተባባሪ የዛሬው ግንቦት 20 የድል ቀን ነው በደንብ አክብረነዋል እባክሽ ቅቤ ቀቢኝ ብሎ ለዋርሳው ሲናገር በጆሮዬ ሰምቻለሁ” የሚሉት ግለሰቡ፤ “ይህ ሰው ታስሮ ነበር፤ በይግባኙ ሂደት ተለቆ ወጥቷል ግን ድጋሚ እየተፈለገ ነው፤ ለአካባቢው ስጋት ሆኗል” ብለዋል፡፡
“በአካባቢያችን አንድ አርሶ አደር በቀን 60 ብር እየተከፈለው በሚሰራበት ወቅት ብዙ አርሶ አደሮች በነፃ እርሱን ሲያገለግሉ ይውላሉ” በማለትም አክለዋል፡፡
“በድሩ ሱልጣን የተባለው አጐቱ ሌሎች እንግዶችን ከአዲስ አበባ ይዞ እንደሚመጣ ያውቅ ነበር፤ አቶ በድሩ የተማረ በመሆኑ አጥብቆ ይቃወመዋል፤ ህዝቡን የሚበዘብዝበትን መንገድ እንዳያጣ ነው አጐቱን ግደሉት ያለው” ብለዋል፡፡ ሆኖም የአላህ ፈቃድ ሆኖ አቶ በድሩ ተደብድቦ ሲተርፍ፣ ኢ/ር ጀሚል ለሞት በቃ ብለዋል፡፡
“ወንጀሉን ፈፃሚውም ሟቹም ቤተሰቤ ነው ያለው ሌላ የቡታጅራ ከተማ ወጣት ነዋሪ፤ አጐቱ በድሩ ሱልጣን የሊቃን ስርዓት ከማክበር ባሻገር ከቃጥባሬ እስከ ወልቂጤ ያለ 12 ኪ.ሜ ኮረኮንች መንገድ በአስፋልት ለመቀየር አስቦ፣ ሟችን ጨምሮ ወደ 60 የሚጠጉ ሰዎችን ከአዲስ አበባ ይዞ እንደሚመጣና መንገዱን በተመለከተም ከህዝቡ ጋር ምክክር ለማድረግ ቀጠሮ አስይዞ እንደነበር ወጣቱ ይናገራል፡፡ “እወጃውን በግንቦት 19 አውጆ፣ ለበዓሉ ቀረ፤ ከዛን በፊት ቀርቶ አያውቅም” የሚለው ወጣቱ እነዚህ ሰዎች አገር ሰላም ብለው ሁለት ሚኒባስና አንድ ቅጥቅጥ አይሱዙ ይዘው ግንቦት 20 ቀን 2004 በስፍራው መገኘታቸውን ገልጿል፡፡ “በዋና ገዳይነት ተፈርዶበት እስር ቤት የሚገኘውታናሽ ወንድሙ ነሲቡ ሱልጣን “የተባሉት ሰዎች መጥተዋል ተነሱ” በሚል ድብደባውን መጀመሩንና ከሞቱት ግለሰብ ውጭ 19 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ወጣቱ ገልጿል።
የገዳይ የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ የነገሩን ሌላው አዛውንት የአካባቢው ነዋሪ፤ ወንጀለኛው በእናቱ በኩል ዘመዳቸው እንደሆነ ገልፀው፤ “አንድ ጊዜ ወፍጮ ቤትህ በደንብ እንዲሰራ፣ ንግድህ እንዲቃና ከሱዳን ያስመጣሁት አዋቂ ስላለ 30 ሺህ ብር ከፍለህ መድሀኒት ላሰራልህ ብሎኝ እምቢ ብየዋለሁ” ብለዋል፡፡ ወንጀለኛው ጥንቆላ ውስጥ መግባቱንና ህዝቡን እያንቀጠቀጠ ገንዘብ እንደሚቀበልም ነዋሪው ተናግረዋል፡፡
የቡታጅራና አካባቢው ነዋሪዎች በእስር ላይ ስለሚገኘው ፍርደኛ፤ ሲናገሩ “እስር ቤቱ ለእርሱ መዝናኛው ነው፤ ድንኳን ተጥሎለት አሁንም ከህዝቡ ገንዘብ እየሰበሰበ ነው፤ ከእስር ቤት እየወጣ በየጊዜው ወደ ቤቱ ይሄዳል፣ “ወራ” የተባለውን የራሱን ሀይማኖታዊ ስርዓት ከማረሚያ ቤት ወጥቶ እቤቱ ነው ያከበረው፤ እርሻውን 50 ኪ.ሎ ሜትር እየሄደ ያሰራል፤ በየጊዜው ከማረሚያ ቤቱ 18 ኪ.ሜትር ወደሚርቀው ቤቱ ይሄዳል፤ ከፍተኛ ሀዘንና ችግር ቢከሰት እንኳን ከማረሚያ ቤቱ ሰባት ኪሎ ሜትር ራዲየስ መራቅ በህጉ አይፈቀድም፤ ለዚህ ሰው ሽፋን የሚሰጥበት ሁኔታ ለአካባቢው ስጋት ነው” በማለት ተናግረዋል፡፡
“ከፖሊስ ጣቢያ በህገ-ወጥ መንገድ ነው ያመጣነው”
ኮማንደር ወንደሰን አበበ
የቡታጅራ ማረሚያ ተቋም ሀላፊ ኮማንደር አበበን በማረሚያ ተቋሙ ተገኝተን ስለጉዳዩ ጠይቀናቸው፤ “በ2004 በነፍስ ግድያ ወንጀል ተከሰው የመጨረሻ ውሳኔ ያገኙ ሰዎች አሉ” በማለት ነው ጥያቄያችንን መመለስ የጀመሩት፡፡ በነፍስ ግድያው ወደ ማረሚያ ቤት የመጡት 19 ሰዎች እንደነበሩ ጠቁመው 14ቱ በአመክሮ እንደተፈቱ ኮማንደሩ ገልፀዋል፡፡ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ካሉት መካከል አንዳንዶቹ እንደፈለጉት እየወጡ ይገባሉ የሚባለውን በተመለከተ ሲናገሩም፤ “የህግ ታራሚዎች ገና ወደ ማረሚያ ቤት እንደገቡ በርካታ ማህበራዊ ችግሮች እንዳሉባቸው ይናገራሉ” የሚሉት የተቋሙ ሀላፊ፣ ንብረታቸውን ሳይሰበስቡ ቤተሰባቸውን ሳያረጋጉ፣ ማረሚያ ቤት እንደሚገቡ ጠቅሰው፤ ከዚህ አንፃር ህጉ ፈቃድ ይሰጣቸዋል ይላሉ፡፡ “ይህ ማለት ግን በየቀኑ ይወጣሉ ማለት አይደለም” ያሉት ኮማንደሩ፤ “በርካታ ንብረት በትኜ ነው የመጣሁት” የሚል ማመልከቻ ካቀረቡ በኋላ ጉዳዩ ተጣርቶ አጃቢ ተመድቦላቸው ሄደው እንደሚመጡ፣ ይህን የሚፈቅድ ህግ እንዳለም አብራርተዋል፡፡ ከኢ/ር ጀሚል ግድያ ጋር በተያያዘ በተቋሙ በእርምት ላይ የሚገኙት ሰልማን ሰይድ የአያያዝ አግባብ ሲያስረዱም፤ ሰውየው የልብ ህመም ስላለባቸው በየሶስት ወሩ ለህክምና ወደ አዲስ አበባ እንደሚመላለሱ ገልፀው፣ ይህ የሀኪም ትዕዛዝ እና የጤና ጉዳይ ስለሆነ የግድ መሄድና መታከም እንዳለባቸው፤ ምንም ማድረግም እንደማይቻል ኮማንደሩ በአፅንኦት ተናግረዋል፡፡
“የሰልማን ሰይድ ፋሪስን ጉዳይ በተመለከተ ውጭ ይወጣሉ በሚል ተደጋጋሚ ጥያቄ ከተለያዩ አካላት ይቀርብልናል” ያሉት ኮማንደር ወንድወሰን፤ ይህንንም በትክክለኛው መንገድ እየመለሱ እንደሚገኙ፣ ጤንነታቸውን በተመለከተና የመኝታን ጉዳይም ጭምር ዶክተሮች በሰጡት መመሪያ መሰረት ለብቻቸው እንዲተኙ መደረጉን ያብራራሉ፡፡
ለሰልማን ሰይድ ከህጉ ውጭ የተለየ ነገር አልተፈቀደለትም ይላሉ የማረሚያ ቤቱ ሃላፊ፤ አንድ የህግ ታራሚ ወላጆቹና ቤተሰቦቹ ቢሞቱበት 6 ኪ.ሜ ራዲየስ ድረስ ሄዶ እንዲቀብር የማረሚያ ቤቱ አሰራር ይፈቅዳል ያሉት ኮማንደሩ፤ ቡታጅራ ሆስፒታል የተኛ የቅርብ ቤተሰብ (ዘመድ) ካለውም ጠይቆ እንዲመጣ ፈቃድ እንዲሰጥ ህጉ ያዛል ብለዋል፡፡ “እርግጥ ሰልማን ሰይድ ፋሪስ በአንድ ወቅት እህል መሰብሰብ አለብኝ፣ ገንዘብ ያለበትንም ለባለቤቴ ልንገር ብለውን ፈቅደንላቸው ሄደው መጥተዋል፤ ከዚህ የዘለለ ግን እንደ ውሀ ቀጂ የሚመላለሱበት ጉዳይና የተለየ እድል የሚሰጥበት የህግ አግባብ የለም” ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ኦሮሚያ ክልል ሄደው ማሳ ያሰራሉ፣ “ወራ” የተባለውን የራሳቸውን የሀይማኖት በዓል በቤታቸው ያከብራሉ፤ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ ዳስ ተጥሎ ገንዘብ ይሰበስባሉ በሚል በታራሚው ላይ የሰማነውን መረጃ የጠቀስንላቸው ኮማንደሩ ሲመልሱ፣ “ኦሮሚያ ድረስ የሚሄዱበት ምክንያት የለም፤ ምክንያቱም በነፍስ ግድያ የገቡ ሰው ናቸው በቀል ስለሚኖር በሰው ጉዳት ሊደርስባቸውም ጉዳት ሊያደርሱም ይችላሉ በሚል የማረሚያ ተቋሙ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋል” ብለዋል፡፡
ሌላ ታራሚ፤ ገንዘቤን ልሰብስብ፤ ቤተሰቤን ላረጋጋ ቢል ይፈቀድለት እንደሆነ ጠይቀ ናቸውም፤ ድንገት ተይዞ ለገባ ታራሚ ህጉ ለአንድ ቀን ብቻ እንደሚፈቀድ ተናግረዋል፡፡
ዳስ ተጥሎላቸው ገንዘብ ይሰበስባሉ የሚለውን በተመለከተም፤ እኔ በማረሚያ ተቋሙ ስሰራ 11 ዓመቴ ነው፤ በዚህ አመት ውስጥ በቀን ብዙ ጠያቂ መጣ ከተባለ 10 ወይም 15 ሰው ነው” ያሉት ሃላፊው፤ እኚህ ሰው ወደማረሚያ ቤቱ ከመጡ በኋላ በቀን ከ100 እስከ 250 ሰው ወደማረሚያ ቤቱ መምጣት መጀመሩን ይናገራሉ፡፡ የታራሚ መጠየቂያም በጣም ጠባብ በመሆኑ የግድ ዳሱ መጣል ስለነበረበት በላስቲክ ዳስ ተሰርቶ እንዲጠየቁ መደረጉን ገልፀው፤ “ይህንን ያደረግነው የሌሎች ታራሚዎችን ጠያቂዎች እድል ላለመንፈግ ነው” ያሉት ኮማንደሩ፤ ሰውየው ገንዘብ ይሰብስቡ አይሰብስቡ ማረሚያ ተቋሙን አይመለከተውም ብለዋል፡፡ ጠያቂው ከጠየቀ በኋላ ገንዘብ ሰጥቷቸው እንደሚሄድ በመግለጽ። “ከዚህ በተረፈ ከሌሎች ታራሚዎች የተለየ እድልና ቅድሚያ ለእርሳቸው የምንሰጥበት ምክንያት የለም፤ ዳሱንም ቢሆን ተቋሙ ሳይሆን ራሳቸው ታራሚው ናቸው ያዘጋጁት፡፡” ብለዋል፡፡ (በነገራችን ላይ በሰማያዊ ላስቲክ የተጣለውን ዳስና የተነጠፈውን ጂባ ምንጣፍ በስፍራው ተመልክተናል፡፡)
“እንኳን የተለየ እድል ልንሰጣቸው ከፖሊስ ጣቢያም ያመጣናቸው በህገ ወጥ መንገድ ነው” ያሉት ኮማንደሩ፤ ግድያው ራሱ የተፈፀመው በሃይማኖቱ የተነሳ መሆኑን፣ ሟችም አደጋው የደረሰባቸው በሰው ማመን የለብንም በሚል መሆኑ እንደሚታወቅ ገልፀው፣ “ታራሚው ከአያቴ፤ ከአባቴ የወረስኩት ነው የሚለውን እምነት እንዲያራምድ እንዴት ወደቤቱ እንልከዋለን” ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ እንደውም ከታራሚው ጋር የተፈጠረ ግጭት እንደነበር የሚያስታውሱት ሃላፊው፤ በአንድ ወቅት በማረሚያ ተቋሙ ውስጥ ከብት ሲታረድ “ሼኩ ያረዱትን ሳይሆን እራሳችን ያረድነውን ነው የምንበላው” በሚል ከታራሚው ጋር በነፍስ ግድያው ተፈርዶባቸው የመጡት ችግር ፈጥረው እንደነበረና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቄራ እየታረደ ስጋ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ታራሚው ከዚህ በፊት በሰዎች ላይ ሽጉጥ ስለመተኮሳቸው፣ ብዙ ጊዜ ስለመከሰሳቸውና በማረሚያና በፖሊስ ጣቢያ ሽፋን ይሰጣቸዋል ስለመባሉ ያውቁ እንደሆነ ጠይቀናቸው፤ ሰውየው ወደማረሚያ ቤቱ የገቡት ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ጠቅሰው ቀደም ሲል፣ ፖሊስ ጣቢያ ገብተው ይሆናል እንጂ ማረሚያ ቤት አልመጡም ብለዋል፡፡ “እርግጥ እኛም ከፖሊሶች እኒህን ታራሚና ሌሎች 19 ሰዎችን በህገወጥ መንገድ ነው የተቀበልናቸው ያልኩሽም፤ ገና ሳይፈረድባቸው ፖሊስ ጣቢያ እያሉ ሰዎችን ማነሳሳትና መሰል ድርጊቶችን ይፈጽሙ ስለነበር፣ ነገሩ ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳይዞር በመፍራት ነው ፍርድ ከማግኘታቸው በፊት ያመጣናቸው” ብለዋል፡፡
ድሮ አሜሪካም ሆኜ እዚህም ከመጣሁ ጀምሮ ሰልማንና ወንድሞቹ የሚያራምዱት እምነት አይስማማኝም ነበረ “የግድያው መንስኤም ይሄው ይመስለኛል” የሚሉት አቶ በድሩ፣ የጀሚል ሞት ግን የእድሜ ልክ ሀዘን እንደሆነባቸው በሀዘን ገልፀዋል፡፡ ፍ/ቤቱ ነፍሰ ገዳዮቹንና ግብረአበሮቻቸውን በይግባኙ የቀነሰላቸው የእስራት ጊዜና 14 ሰው በነፃ የለቀቀበት መንገድ ለኢ/ር ጀሚል እና ለቤተሰቦቹ፤ ለእኛም ጭምር ሁለተኛ ሞት ነው ብለዋል፡፡
ምንም እንኳ የክልሉ ፍትህ ቢሮ ለሰበር ሰሚ ይግባኝ ቢጠይቅም ይግባኙ የዘገየ መሆኑን የሚናገሩት ወ/ሮ ፋጡማ፤ ወደ ሰበር ችሎት ጉዳዩ ከመጣ በኋላ 14ቱን ሰዎች ያስቀርባቸዋል በሚል ሰበር ችሎቱ ከአንዴም ሁለት ጊዜ ትዕዛዝ ቢሰጥም የተፈቱት 14 ሰዎች ግን ራሳቸውን በመሰወራቸው ሊገኙ እንዳልቻሉ ገልፀውልናል፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱ ለሶስተኛ ጊዜ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ለጥቅምት 26 ቀን 2006 ሰዎቹ እንዲቀርቡ ያዘዘ ሲሆን በቀጠሮው ቀን ይቅረቡ አይቅረቡ የሚታወቅ ነገር የለም ብለዋል - የሟች ባለቤት ወ/ሮ ፋጡማ፡፡
የ58 አመት ጐልማሳ የነበሩት ኢ/ር ጀሚል ሃሰን፤ ኪናንጀሚልና ኢፕቲሀጅ የተባሉ ሁለት ልጆችን አፍርተዋል፡፡ ከዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን ዲግሪያቸውን ያገኙ ሲሆን ከኮሜርስ በአካውንቲንግ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርክቴክቸር ትምህርት መማራቸውንም ባለቤታቸው ወ/ሮ ፋጡማ ተናግረዋል፡፡ ከረጅም ዓመት በፊት “ርብቃ” የተባለ መጽሐፍ የተረጐሙ ሲሆን መታሰቢያነቱንም ለገዳይ አያት ሻለቃ ሱልጣን እንዳደረጉ ከመጽሐፉ መረዳት ይቻላል፡፡ ስድስት ያልታተሙ የትርጉም ስራዎች እንዳሏቸውና በመጨረሻው የእድሜ ዘመናቸው አካባቢ “the three Cup of Tea” የተሰኘ መጽሐፍ ተርጉመው ለህትመት ሲያዘጋጁ እንደነበር ባለቤታቸው ተናግረዋል፡፡ “አፒክስ” የተሰኘ የጉዞ ወኪል ድርጅት የነበራቸው ኢ/ር ጀሚል፤ “ኦፕቲፋም” የተሰኘ የኔትወርክ ቢዝነሳቸውን በማናጀርነት ይመሩም እንደነበር ታውቋል፡፡
ኢ/ር ጀሚል ከመሞታቸው በፊት “ሁሉንም ሰው ይቅር ብያለሁ፤ ገዳዮቼንም ጭምር” የሚል ቃል መናገራቸውን፣ ተጨማሪ መልዕክት ለማስተላለፍ እስኪርቢቶ ጠይቀው መፃፍ እንደተሳናቸው ባለቤታቸው በእንባ ታጅበው ነግረውናል፡፡ “ይህን ጉዳይ አይቶ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ፤ ልጆቼም እኔም ፍትህ እንሻለን” በማለት ሃሳባቸውን ቋጭተዋል፡፡

Saturday, November 2, 2013

የውጭ ሃገር ዜጎች ውጥረት ጭንቀት እና ስጋት በሳውዲ አረቢያ !


ኖቬበር 4 2013 የምህረት አዋጁ መጠናቀቅ ተከትሎ በውጭ ሃገር ዜጎች ላይ የሚደረገው የቤት ለቤት አሰሳው አይቀሬነት እይተነገረ ነው ።

ለ 3 ወር የተራዘመው የሳውዲ አረቢያ መንግስት የስደተኞች ምህረት አዋጅ የፊታችን ሰኞ ኖቬበር 4 2013 መጠናቀቁን ተከትሎ ጭንቀት ስጋት እና ውጥረት በትለያዩ ሃገራት ዜጎች ላይ ነግሷል። ይህ አዋጅ ቀደም ብለው ከወጡት የሳውዲ አረቢያ የስደተኞች ህግ የንጉሱ ትዕዛ ያረፈበት አሊያ « አምረል መሊክ » መሆኑ የተፈጻሚነቱ አይቀሬነት በውጭ ሃገር ዚጎች ላይ ያለውን ስጋትን ከወትሯው ለየት እንዲል አድርጓታል ። 

ከእንግዴህ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በፈለጉት የስራ ዘርፍ እንዳሻቸው ተሰማርተው መንቀሳቀስ እንደማይችሉ ህጉ እንደማይፈቅድላቸው ቀደም ብለው የተረዱ አያሌ የውጭ፡ሃገር ዜጎች ቤተስቦቻቸውን ወደ ሃገራቸው ሸኝተዋል አሊያም ላይመለሱ ጎዛቸውን ጠቅልለው ከሃገሪቷ በመውጣት ላይ መሆናቸው እይተነገረ ነው። 

በተለይ ያለመኖሪያ ፈቃድ ወልደው የከበዱ ኢትዮጵያውያን ሪያድ እና ጅዳ ላይ በብዛት እንዳሉ እይተነገረ ባለበት በዚህ ቀውጢ ወቅት የነዚህ ዜጎቻችን እጣፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል በህብረትሰባችን ውስጥ ያለው ጭንቀት ከመቸውም ግዜ የከፋ አድርጎታል። ጅዳ እና ሪያድ ኢትዮጵያውያን በብዛት ይኖሩባቸዋል ተብለው የሚነገርላቸው አካባቢዎች በሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች ፍተሻ እንደሚካሄድባቸው ውስጥ አዋቂ ምንጮች በመግለጽ ላይ ናቸው ። 
ከጅዳው ይልቅ በብዛት በተለምዶ ባህር ሃይል እይተባሉ የሚነገርላቸው ድበር አቋርጠው ህገወጥ በሆነ መንገድ ወደ ሳውዲ ምድር የገቡ ዜጎቻችን ሪያድ ከተማ ውስጥ በተለምዶ መንፉሃ ኡም ሃማም ነስሪያ እና ነሲም የከተሙ በመሆናቸው በአካባቢው ባሉ ኢትዮጵያውያን ላይ ያለው ስጋት ጨምሯል። ትላንት ምሽት ሪያድ ከተማ መንፉሃ እና ነሲም አካባቢ አልፎ አልፎ ፍተሻ እንደነበር የሚጠቁሙ ምንጮቻችን ከግዜው ገደብ መጠናቀቅ ጋር ተዳምሮ ውጥረትን መፍጠሩ ይነገራል። 

በአብዛኛው ሪያድ ውስጥ በንግድ እና በት/ቤት አውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት ስራ ላይ እንደተሰማራ የሚነገርላቸው ዜጎቻችን የሳውዲ መንግስት ያወጣው ህግ ብዙም እንዳልተመቻቸው ይናገራሉ። በዚህም መስረት ከፊታችን ኖቬበር 4 2013 የምህረት አዋጁ የግዜ ገድብ መጠናቀቁን ተከትሎ በእለት ተዕለተ እንቅስቃሴያቸው ላይ አሉታዊ ተጸኖ ስለሚኖረው አብዛኛው የንግድ ቤቶች ተዘግቶ ሊውሉ እንደሚችል እና አብዛኛው የት/ቤት ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ የአውቶብስ ባለቤቶች የስራ ገበታቸው ላይ ሊገኑ እንደማይችሉ እየተነገረ ነው። ይህ በዚህ እንዳለ በባህር ወደ ሳውዲ አረቢያ ህገወጥ፡በሆነ መንገድ እንደገቡ የሚነገርላቸው ዚጎቻችን በየጎዳናው ያለ ስራ ለመባዘን ተገደዋል። እንዚህ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ ካላቸው ዜጎቻችን ይልቅ ያለምንም ስጋት በነጻነት ሪያድ ከተማ ላይ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው የነገራል። 

በመጨረሻም የግዜ ገድቡ መጠናቀቁን ተከትሎ በሚደረገው አሰሳ ጉዳያቸው በሂደት ላይ ያሉትን ወገኖች እንደማይመለከት የሚናገሩ የሳውዲ ጸጥታ ሃይል ምንጮች የምህረት አዋጁን መራዘም አስመልክቶ እስካሁን ምንም ያሉት ነገር እንደ ሌለ ለማረጋገጥ ተችሏል ። 

ከዚህ በታች የሚታየው ሰዕላዊ መግለጫ በሪያድ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ የትላንት ውሎ ነው።

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

Thursday, October 31, 2013

አሳዛኝ ዜና -በጀርመን ህክምና እየተከታተለ የሚገኘው ኮሜዲያን አብርሐም አስመላሽ አረፈ።


21
አብርሃም አስመላሽ
አርቲስት አብርሃም አስመላሽ ባደረበት ህመም ምክንያት ላለፊት ጥቂት ወራት በጀርመን ኑረንበርግ ከተማ አካባቢ የእክምና እርዳታ ሲደረግለት ቆይቶ ባለፈው አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በአብዛኛው በገጠርኛ ዘይቤ አቀራረቡና በኮሜዲ ስራዎቹ የሚታወቀው አርቲስት አብርሃም አስመላሽ በዲስክ መንሸራተት ህመም ምክንያት ለረጅም ጊዜያት ሲሰቃይ ቆይቷል።
አርቲስት አብርሃም ከዲስክ መንሸራተት በተጨማሪ በጉበትና በኩላሊት እንዲሁም በሳምባ ምች በሽታዎች ሲታመም የነበረ ቢሆንም ከወዳጆቹና ከጥቂት የስራ ባልደረቦቹ ባገኘው የገንዘብ እርዳታ ህክምና አግኝቶ ከተወሰኑት በሽታዎች ሊድን ችሎ ነበር።
ይሁንና የዲስክ መንሸራተት መሙን በግሉ ከፍሎ መታከም ባለመቻሉ ህብረተሰቡን ለህክምና የሚሆን የገንዘብ እርዳታ በመጠየቅ ላይ እንደነበር ይታወሳል።
በዚህ የዲስክ መንሸራተት ህመም ምክንያት አርቲስት አብርሃም እንደልቡ መንቀሳቀስ ባለመቻሉ ለረጅም ጊዜያት በህዝብ ከሚታወቅባቸው የመነባንብና የኮሜዲ ስራዎቹ ሊርቅ ተገዶ ነበር።
በተለይ ”እረኛውና” ፣ ”ጠበል ቅመስ” በሚል ስራዎቹ የሚታወቀው አርቲስት አብርሃም አስመላሽ ከሃያ ያላነሱ ዓመታትን በኢትዮጵያ ራዲዮ ቅዳሜ መዝናኛ የተለያዩ ማህበረሰብ ነክ በመነባንቦችንና የኮሜዲ ስራዎችን ሲያቀርብ እንደነበር በተለያዩ ጊዜያት በሰጣቸው ቃለመጠይቆች ላይ ገልፃል።
አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ተወልዶ ያደገው አርቲስት አብርሃም አስመላሽ የገጠርኛ ዘይቤ አቀራረቡን ለበግ ንግድ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢው ወደሚገኘው ”ደንሴ ተራራ” ይመጡ ከነበሩ የመንዝና የወሎ አካባቢ ነጋዴዎች ቀስሞ እንዳደገ ይገልፃል።
አርቲስት አብርሃም ከተለያዩ አካባቢዎ ወደ ”ደንሴ ተራራ” ይመጡ ከነበሩ የገጠር የሀገሪቱ አካባቢ ነዋሪዎች ለየት ያለ የአማርኛ አነጋገር በመመሰጡ የተነሳ ”ሌሎች ሰዎች በገበያዎች በጎችን ሲሰርቁ እኔ ግን የአማርኛ አነጋገር ዘይቤያቸውን ነበር ስሰርቅ ያደግኩት ”ሲል ገልፆ ነበር።
አርቲስቱን ከሞት ለመታደግ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የድረሱለት ጥሪ ቢያሰሙም ከጥቂት ግለሰቦች በስተቀር ማንም ምላሽ የሰጠው አልተገኘም።
አርቲስት አብርሃም አስመላሽ ወደ ቀድሞው ጤንነቱ ቢመለስ ኖሮ ለህትመት ያልበቁ በርካታ ስራዎችን የማሳተም እቅድ እንደነበረው ገልፆ ነበር።
አርቲስት አብርሃም ትዳር እንዳልመሰረተና ያፈራው ልጅም እንደሌለው ገልፆ የነበረ ሲሆን በህመም ተይዞ ለህክምና እርዳታ እጁን እስከዘረጋበት ጊዜ ድረስ መነኩሴ እናቱን በመርዳት ብቻ ይኖር እንደነበር ገልፃል።
ለአርቲስቱ ቤተሰቦችና አድናቂዎች መፅናናትን እንመኛለን!
zehabesha.com

Wednesday, October 30, 2013

አቶ በረከት ስምኦን የኢቲቪ ቦርድ ሰብሳቢነቱን ለአቶ ሬድዋን ሁሴን አስረከቡ



October 30th, 2013


የሹመቱ አግባብነት ጥያቄ አስነስቷል

አፈጉባዔ አባዱላ ጠ/ሚኒስትሩ በሹመቱ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት አይገደዱም አሉ
የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊነት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን ሹመት ተቀብሎ አጸደቀ። በዚሁ መሠረት ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ በቦርድ ኃላፊነት ባገለገሉት አቶ በረከት ስምኦን ምትክ አቶ ሬድዋን ሁሴን የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ትናንት ለም/ቤቱ በላኩትና የአማካሪ ም/ቤት አስቀድሞ ሳይመክርበት በድንገት በቀረበው ደብዳቤ መሰረት ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ስምንት አባላት ያሉት የስራ አመራር ቦርድ አባላትን መሾማቸውን አሳውቀዋል። በዚሁ መሠረት በቅርቡ የመንግሰት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ሬድዋን ሁሴን የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲሾሙ በቅርቡ ለረዥም ጊዜ ካገለገሉበት የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃላፊነታቸው ተነስተው በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የሕዝብ ተሳትፎ አደረጃጀት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው የተሾሙት አቶ ደስታ ተስፋው አባል፣ በቅርቡ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የምክትል ጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ በመሆን የተሾሙት አቶ አማኑኤል አብርሃም አባል፣ አቶ ዓቢይ መሐመድ ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል፣ አቶ ገበየሁ በቀለ ከአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ አባል፣ ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ ከአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ አባል፣ መጋቢ ዘሪሁን ደጉ ከእምነት ተቋማት አባል፣ አቶ ዘርዓይ አስገዶም ከኢቲቪ አባል በመሆን ተሹመዋል።

የተሰናባቹ የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ አባል መሆናቸውን የተናገሩ አንድ የም/ቤት አባል ሹመቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ሹመቱ ግልጽነት የጎደለው መሆኑን በመጥቀስ ማብራሪያ ጠይቀዋል። እንደእሳቸው አባባል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተጠሪ የሆኑ የመንግስት የሚዲያ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መሆናቸውን በማስታወስ ለሁለቱ ተቋማት 4ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሹመት መስጠቱን አስታውሰዋል። አሁን የቴሌቪዥን ቦርድ በድክመት ባልተገመገመበት ሁኔታ ለብቻው ተለይቶ በተናጠል እንዴት ሹመት ሊሰጥ እንደቻለ ጠይቀዋል። “ምናልባት ሰብሳቢው ቦታውን ለውጦ ከሆነ ያ ቦታ የተካው ሰው መያዝ ሲገባው የስራ አመራር ቦርድ አባላት ድክመት ባልገመገምንበት ሁኔታ ቦርዱ እንደ አዲስ ሊሰየም የተፈለገበት ምክንያት አልገባኝም” ሲሉ አባሉ አስቀምጠዋል። በተጨማሪም የቀድሞ ቦርድ ቁጥሩ ዘጠኝ የነበረ ሲሆን አሁን ቁጥሩ ለምን ወደ ስምንት ዝቅ አለ ሲሉ የጠየቁ ሲሆን ሌሎች የም/ቤቱ አባላትም ከእምነት ተቋም ተወካይ ቦርዱ ውስጥ የገባበት ምክንያት እንዳልገባቸው፣ ከዚህ ይልቅ ከሲቪል ማህበር ቢሆን ይሻል እንደነበር እንዲሁም የሴቶች ተሳትፎ በሹመቱ ውስጥ መዘንጋቱ በጥያቄ መልክ ተነስቷል።

አቶ አባዱላ ገመዳ የም/ቤቱ አፈጉባዔ በሰጡት ምላሽ ጠ/ሚኒስትሩ በማንኛውም ጊዜ ሚኒስትሮችን ሲያነሱ ማብራሪያ እንደማይጠየቁ ሁሉ የቦርድ አባላትንም ሲሰየሙ ማብራሪያ ለመስጠት እንደማይገደዱ ተናግረዋል። የአሁኑ ቦርድ አሰያየም ፖለቲካን ብቻ ሳይሆን የሙያ አቅምንም መሰረት ያደረገ ነው ካሉ በኋላ የሴቶች ተሳትፎ መጓደልን በተመለከተ መልዕክቱን እንደሚያደርሱ ገልፀዋል።