Friday, December 20, 2013

በወር አበባ ሰሞን ህመም እና ምቾት ማጣትን የምትቀንሺባቸው 6 ስልቶች

በወር አበባ ሰሞን ህመም እና ምቾት ማጣትን የምትቀንሺባቸው 6 ስልቶች

ከቅድስት አባተ
(በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 57 ላይ ታትሞ የወጣ)
የሴቶች ጉዳይ ብንላቸው የምንግባባቸው ጥቂት ነገሮች አሉ፡፡ አንዱ ወር ጠብቆ ፅንስ ለመፍጠር ዝግጁ መሆናቸውን ለመናገር የሚመጣው የወር አበባ ነው፡፡ እጅግ በርካታ የሆኑ እና ሴቶች የወር አበባቸው በሚመጣ ወቅት ከቀላል መነጫነጭ አንስቶ ሁሉን ነገር እስከመጥላት የሚያደርስ የህመም እና ምቾት የማጣት ስሜት ይገጥማቸዋል፡፡ ሁነቱ ተፈጥሯዊ የሆነና ለክፉ የሚሰጥ አይደለም፡፡ ይሁንና የዚያን ሰሞን ስሜት እና ህመም ማቅለል እና ንጭንጩንም ጭምር ማቃለል እንደሚቻል ባለሞያዎች ያስረዳሉ፡፡ የዛሬው ትኩረታችንም ይህ ነው፡፡ ቀላል የሚባሉ እና የህክምና ጥበብን እጅግም በማይጠይቁ ስልቶች የወር አበባ ሰሞንን ማቅለል የምትችይባቸውን ስልቶች እነሆ ብለንሻል፡፡

የወር አበባ ለምን?
ተፈጥሮ የወር አበባን ስትፈጥር መራባትን አስባ ነው፡፡ ሴቶች አዲስ ነፍስ የመፍጠር ስልጣን በየወሩ ይሰጣቸዋል፡፡ አብሮ ለመፍጠር የተዘጋጀ ጥንድ እስካለ ድረስ ይህ ይሰራል፡፡ በየወሩ የሚዘጋጁት እንቁላሎች የሚዳብርና ፅንስ የሚያደርጋቸው የወንድ ዘር ሲያገኙ እዚያው ሆነው ጽንሱ ሲፈጠር ያ ካልሆነና ሴቲቱም በመፀነስ እቅድ ውስጥ ካልሆነች ደግሞ እንቁላሎቹ ወደ ውጪ መውጣት ይኖርባቸዋል፡፡ እንግዲህ በየወሩ ከደም ጋር ተቀላቅለው የሚወጡት እነዚህ እንቁላሎች ናቸው፡፡ ታዲያ ይህ ክስተት በብዙ ሆርሞኖችና የሰውነት ውስጥ ውስብስብ ተግባራት የሚከወን እንደመሆኑ ብዙ ለውጦችን ሴቶች ማስተናገዳቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቢያንስ 80 ከመቶ የሚሆኑ የዓለማችን ሴቶች ከቀላል ህመም አንስቶ እስከ ከበዱት ድረስ በወር አበባ ሰሞን ይገጥማቸዋል፡፡ እጅግ አሳማሚ የሆድ ቁርጠት፣ የስሜት መቀያየር፣ መነጫነጭ ራስ ምታት እና ሌሎቹም የሚጠቀሱ ማሳያዎች ናቸው፡፡ እነዚህን የወር አበባ ሰሞን ችግሮች ማቅለያ ዘዴዎችን ታዲያ የህክምና ሰዎች ለሴቶች ሁሉ ያጋራሉ፡፡ የዲስከቨሪ መፅሔት እና ውሜን ሄልዝ ኤክስፐርቶች ካነሷቸው መካከል ዮጋ ማዘውተር ጨው መቀነስ፣ አመጋገብ ማስተካከልና አንዳንድ ቀለል ያሉ መድሃኒቶችን መውሰድን ያነሳሉ፡፡
የወር አበባ ሰሞን ጨው ቀንሺ
በወር አበባ ሰሞን እንቁላሎች ዝግጁ ሆነው የሚጠብቁት ልጅ እንደሚፈጠር በማሰብ ነው፡፡ ስለሆነም ጽንሱ ቢፈጠር የሚያስፈልገውን የጨው ፈሳሽ እና ኤሌክትሮላይት ለመሙላት ሰውነትሽ ብዙ ጨው የዚያን ሰሞን ይኖረዋል፡፡ ብዙ ጨው መኖሩ ደግሞ ውሃን የመሳብና በሰውነት ውስጥ መጠራቀምን ይፈጥራል፡፡ ይህ በራሱ የሚፈጥረው ሰውነትን የማስጨነቅ ተፅዕኖ ስለሚኖር ከውጪ የምትወስጂውን ጨው የወር አበባ ከሚመጣባቸው ቀናት አስቀድመሽ ቀንሽ፡፡ በተለይ የተጠባበሱ ምግቦች ውስጥ ከፍተኛ የጨው ክምችት ስለሚኖር ከእነዚህ ምግቦች በዚያ ሰሞን መቆጠብ ጥሩ እንደሆነ ባለሞያዎቹ ያሰምሩበታል፡፡
ዮጋ እንደ መዝናኛም እንደ መድሃኒትም
የወር አበባ ወቅትን ህመም ለማስታገስ መዝናናት፣ ውጥረትን መቀነስ እና የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ በእጅጉ የሚመከሩ መላዎች ናቸው፡፡ ዮጋ ደግሞ ሁሉንም በአንድ አዋህዶ የያዘ የተመስጦ ስፖርት ከመሆኑ አንፃር ቁጥር አንድ ተመራጭ ስፖርት ያሰኘዋል፡፡ ‹‹ዮጋ ስፖርት ብቻ አይደለም፣ አዕምሮና አካልን በአንድነት ከውጥረት መንጥቆ የሚያወጣ መድሃኒትም ነው›› ይላሉ የዲስክቨሪ መፅሔት የህክምና አማካሪ፡፡ በኢንዲያን አካዳሚ ኦፍ አፕላይድ ሳይኮሎጂ የጥናት መፅሔት ላይ የሰፈረ የጥናት ውጤትም ተመሳሳይ ጥቅሞችን ያነሳል፡፡ ጥናቱ ዮጋ የስነ ልቦና እና የአካላዊ መዝናናትን በማጎናፀፍ ከወር አበባ ወቅት ህመምና ምቾት ማጣት በመገላገል በኩል ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ይናገራል፡፡
ካልሲየምና ቫይታሚን ዲ ውጤት አላቸው
በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ አሜሪካ ውስጥ በዚህ ላይ ምርምር ያደረጉ ባለሞያዎች ቫይታሚን ዲ እና ካልሲየም ማዕድን የወር አበባ ጊዜዎትን በእጅጉ ቀላል የማድረግ ሚና እንዳላቸው አሳይተዋል፡፡ በጥናቱ በየዕለቱ እስከ ስድስት መቶ ሚሊግራም ካልሲየም የወሰዱ ሴቶች ዘንድ የወር አበባ ወቅት ህመሞች የሚባሉት እንደ ሆድ ቁርጠት፣ ራስ ምታት፣ የምግብ አምሮት እና የስነ ልቦና ጫናው በግማሽ ቀንሶ መገኘቱን በጥናታቸው ፅፈዋል፡፡ ይህ የካልሲየም መጠን አንድ ብርጭቆ ወተትና አንድ ብርጭቆ እርጎ በጋራ ቢጠጡ የሚያገኙት ምጣኔ ነው፡፡ ባለሞያዎቹ ካልሲየምን በክኒን መልክ መውሰድ ቢቻልም ተመራጩ ግን ከወተት ተዋፅኦ ውጤቶች ማግኘቱ እንደሆነ አበክረው ያሳስባሉ፡፡ ቫይታሚን ዲ ተመሳሳይ ተፅዕኖ እንዳለው ባለሞያዎቹ አስረድተዋል፡፡ እንደ ካሮት እና መሰል አትክልቶች ቫይታሚኑን ማግኘት ወር አበባን ቀለል ያደርጋል፡፡
ለማይግሬይንና ራስ ምታቱስ?
በወር አበባ ወቅት የሚከሰተው ራስ ምታት ከወትሮው በተለየ አናትን የሚነቁርና ሁሉን ነገር የሚያስጠላ ሊሆን ይችላል፡፡ ቀደም ሲል ያነሳናቸው የመዝናኛ እና ችግሩን የመቅረፊያ ስልቶች እየሰሩ ካልሆነ በባለሞያ የሚታዘዝ ህመም ማስታገሻን መውሰድ ይመክራል፡፡ ምናልባት ሌላ ጊዜ ከሐኪም ትዕዛዝ ውጪ የምንወስዳቸው ማስታገሻዎች በዚህ በኩል ውጤታቸው አርኪ ስለማይሆን ነው፡፡ ሌላ ማስታገሻ ለመጠየቅ ባለሞያን እንዲያዩ የሚመክረው በውጪ ሀገራት ለዚህ ተብለው የሚሰሩ ልዩ ማስታገሻዎች አሉ፡፡ በእኛ ሀገር ፋርማሲዎች በስፋት የሚገኙ ባለመሆናቸው ባለሞያ መገናኛቸውን ሊያመላክትዎት ይችላል፡፡
ፋይበር ያላቸውን ጠጠር ያሉ ምግቦች ጥቅም
ባለሞያዎቹ እንደሚሉት በወር አበባ መምጫ ሰሞን ህመሙን እና ሆድ ቁርጠቱን የሚያመጡት የሆርሞን ለውጦች የሆድ ህመም እና ተቅማጥ ከሚያመጡት ጋር ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ ስለሆነም ሆድን ያዝ የሚያደርጉ እንደ ጎመን አጃ፣ ሙዝና የመሳሰሉትን ምግቦች ብትወስጂ ሆድሽን ያዝ አድርገው የምግብ አምሮቶሽን ይገቱታል፡፡ አንዳንድ ሴቶች ዘንድ የሚታየውንም የዚያን ሰሞን የሆድ መለስለስና መለስተኛ ተቅማጥ ለመቆጣጠር ያግዛሉ፡፡
በዚያ ሰሞን ዋና መዋኘት?
ብዙ ሴቶች በወር አበባ መምጫ ሰሞን ከሰው ራቅ ብለው ቤት አካባቢ ሆነው ቢቆዩ ይመርጣሉ፡፡ የባለሞያዎች ሀሳብ ግን ይለያል፡፡ ከሰው መቀላቀሉ እና ዘና ማለቱ ይመከራል፡፡ በተጨማሪም ዋና መዋኘት ከፍተኛ ጠቀሜታም እንዳለው ጨምረው ያስረዳሉ፡፡ በዋና ወቅት በሰውነት እና በውሃው መካከል በሚደረገው ፍትጊያ የሚፈጠረው ግፊት የሆድ ቁርጠትና የዚያን አካባቢ ቁስለት የሚመስል ስሜት አዝናንቶ የማፍታትና ህመምንም የመቀነስ አቅም አለው፡፡ በቀን ቢያንስ ለ20 ደቂቃ ብትዋኚ ጥሩ ነው ተብሎ ተመክሯል፡፡ ነገር ግን የግድ ወደ ዋና ገንዳ እንድትገቢ አትገደጂም፡፡ የዋናው ነገር ካልተመቸሽ በቤት ውስጥ መታጠቢያ ቤት ለብ ያለ ውሃ በገንዳው ሞልተሽ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰውነትሽን ብታሳርፊው የዋናውን ያህል ባይሆንም ጥሩ ውጤት ታገኚያለሽ፡፡
posted by Aseged Tamene

ምስጋና ለአያሌው ጎበዜ – አክባሪዎ አቢሲኒያዊ

እርስዎ ብዐዴን/ህወሀትን ወክለው የአማራን ህዝብ ሲመሩ መቆየትዎ ይታወቃል በዚህም የክልሉ ህዝብ ኤያሌው ጎበዜ ለዘላለም ይኑር እያለ እንዲኖር ማድረግዎትን የሚያስታውሱት ነው እርስዎ በጣም ያሳዘኑኝ ያ ወዳጅዎ ደመቀ መሬቱን ድንጋይ ያድርግለት እና በመለስ ዜናዊ ትዕዛዝ የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን ይገባሻል ብሎ መለስም ብራቮ እንዲህ ነው እንጂ ተላላኪ ብሎ ትምህርት ሚኒሰቴር ሲያደርገው ለእርስዎ ግን ቅንጣት ታህል አለመስጠቱ ሱዳኖች እንኴን እንዲታዘቡት አድርጔል፡፡
እርስዎም ደመቀ ምክትል ጠ/ሚኒስቴር ሲሆን ቅናት ቢጤ አድርዎቦት ከሳምንታት በፊት 40 ካ.ሜ ወደ ኢትዮጵያ ገብተው የሀገሮትን መሬት ለሱዳን ማስረከብዎን ሰምቼ ድሮስ የጎበዤ ልጅ ከማን ያንሳል ብዬ ኮራሁ፡፡ በነገራችን ላይ ሰሞኑን መሬታችን ለሱዳን መሰጠቱን ተከትሎ የእርስዎ የቅርብ ዘመዶች ቤታቸው የተሸጠው መሬት ላይ በመገኘቱ ሱዳን ለዘላለም ትኑር አባይ የሱዳን ነው እያሉ መዘመራቸውን ሱዳን የሚገኝ ወዳጄ ሹክ ብሎኛል፡፡
እናማ ይሄውልዎ ተሰናባች አያሌው የእርስዎ ክልል ግዞት የሆነው የአማራ ህዝብ ብዙ እየሰማ እና እየተሰማው ሲኖር አንድም ቀን ተናግርዎት አያውቅም ለምን መሰለዎት ምን አልባት ነጋዴው ክልሉን ለሱዳን ሸጠው ከመለስ ዜናዊ አገዛዝ ነፃ ያወጡናል ብሎ ስላሰበ ይሆናል፡፡ የአማራ ክልል ህዝብ ለእርስዎ ያላቸውን ፍቅር የተረዳሁት ጉራፈርዳ ይኖሩ የነበሩ የአማራ ክልል ተወላጆች ጉራፈርዳ በቃን አያሌው ጎበዜ ናፈቀን ብለው ቢለመኑ እምቢኝ ብለው እርስዎ ክልል ሲመጡ ነው፡፡
እናም በመጨረሻም እንኩ ምስጋናዬን ተቀበሉ
1.   ሰፊውን መሬታችንን ሽጠው ጠጋ ጠጋ ብለን በመኖር ማህበራዊ ህይወታችን እንዲጠናከር በማድረግዎ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
2.   እንደ መለስ ዜናዊ ስልጣን ላይ ሳይሞቱ በመልቀቅዎ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
3.   በ1998 በኮምቦልቻ፣ በ1999 በደሴ፣ በ2000፣ በ2003 የጎንደር እና የጎጃም ህዝብን በወያኔ ወታደሮች በጥይት አስገድለው ከዘንድሮው የኑሮ ውድነት እንዲያመልጡ ስላደረጉ ምስጋና ይገባዎታል፡፡
አክባሪዎ ሁኔ አቢሲኒያዊ
ከፒተርቦሮው ዩ.ኬ
posted by Aseged Tamene

የኢህአዴግ መንግስት ሃላፊነት ስልጣን እየሰጠ እያወጣቸው ያሉ ባለስልጣናት በሙስና ለተጨማለቁት ነው


በመረጃው መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ በሙስና ተከሰው ጉዳያቸው እየተጣራ ከቆዩ የበላይ ባለስልጣኖች ውስጥ። ኩማ ደመቅሳና አለማዮህ ታፈሰ ክስ ህዳር 30/ 2006 አ/ም ያየው የወረዳው ፍርድ ቤት። ተከሳሽ ለሆነው አለማዮህ ታፈሰ ለ10 አመታት ፅኑ እስራት ፍርድ ሰጥቶ። ለኩማ ደመቅሳ በሌላ ቀን ቀጠሮ እንዲታይ በወሰነበት ግዜ። የፍርድ ውሳኔ የተሰጠው አለማዮህ የይግባኝ ጥያቄ በማቅረቡ። የወረዳው ፍርድ ቤት የወሰነውን በድጋሚ ያየው ምንም ነፃነት የሌለው የዞኑ ፍርድ ቤት። በላይኞቹ የስርአቱ ባለስልጣናት ውስጣዊ ትእዛዝና ተንኮል መሰረት። ወንጀሉ ኩማን እንዳይነካው በማለት ለተከሳሹ ነፃ ብሎ እንደለቀቀው ለማወቅ ተችለዋል፣
ሁለቱም ተከሳሾች ተከፋፍለው በልቶውታል ተብሎው የተከሰሱበት 70 ሚሊዮን የሚገመት ብር። ለተለያዩ የከተማው መሰረተ ልማቶች እንዲውል በማለት ከህዝብና ከሃገር ሃብት የተመደበው ባጀት። ይዘውት ያሉትን ስልጣን ተጠቅመው ሥራ ላይ እንደዋለ በማስመሰልና ወጪ በማድረግ። ለግል ጥቅማቸው እናዳዋሉት የሚያረጋግጥ እውነተኛ መረጃ እንዳለ ከከተማው የተገኘው መረጃ ኣረጋግጠዋል::
ይህ በእንዲህ እያለ ኩማ ደመቅሳ በተከሰሰበት የሙስና ወንጀል። ህጋዊ ውሳኔ ለመስጠት እየተቃረበ በነበረበት ግዜ። ከአዲስ አበባ ከንቲባነት ተነስቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማካሪነት እንዲሰራ ስልጣን ከተሰጠው በኋላ። ክሴታው ውሳኔ ሳያገኝ እስካሁን መስተጓጎሉና። ይኸውም ስርአቱ ሆን ብሎ በሙሱና ለተጨማለቁ ባለ ስልጣናት ተጨማሪ ስልጣን እየሰጠ ወደ ላይ እንዲወጡ ማደረጉ። የስልጣኑ የተዛባና ግለኝነት የተጠናወተው አካሄድ እንደሆነ። በውስጣቸው ፀሃፊ ሆና ለረጅም ግዜ ያገለገለች ወይዘሮ ህድረማርያም የተባለች ዜጋ። ቀደም ሲል ስርአቱ እየተጠቀመበት ለነበረ ውስጣዊ አስራር መሰረት አድርጋ እንደተናገረች ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል::
Source : Debirihan
posted by Aseged Tamene

በህወሓት/ወያኔ መቃብር ላይ ብቻ ኢትዮጵያ በሰላምና በብልጽግና ትኖራለች!



አበራ ሽፈራው/ ከጀርመን/
የኢትዮጵያ ህዝብ ማናቸውም መብቶቹ ተነፍጎ የመኖርና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ ላይ እንገኛለን:: የህዝቡ የሰብዓዊ መብቶችበየትኛውም ዓለም በማይገኝ መልኩ ይጨፈለቃል ለዚህ ያበቃን ደግሞ ትልቁ ምክንያት የህወሓት/ወያኔን የወንበዴነት ጭካኔ ለመጋፈጥ ያለመፈለጋችን ወይም የጭካኔያቸውን መጠን የሚቋቋም ትግል ባለመኖሩና መስዋዕትነትን ለመክፈል ባለመቁረጣችን የመጣብን መከራ እንጂ ህወሓት/ወያኔ ምንም ስለሆነ አይደለም:: የተቃራነውን ጎራ የልብ ትርታ የተረዳው ህወሓት/ወያኔ ሲፈልገው ይገድላል፣ያስራል፣ ያዋክባል፣መሬትንና ንብረትን በሠበብ አስባቡ ይነጥቃል፣ ከስራ ያባርራል፣ የትምህርትና ሌሎች መብቶችን ገፎ ለመከራ ይዳርጋል ካልሆነም ከአገር ማሳደድን እንደትልቅ አማራጭ ተያይዞታል::
በኢትዮጵያ የመኖር መብት እንዳለንና አገራችን መሆኑን እያወቀ መብቶቻችንን የነፈገን ህወሓት/ወያኔ በማን አለብኝነት መቀጠላቸውን ይሁን ብለን ተቀብለን እኛም መስማማታችን ለዛሬው የባሰበት ችግር አድርጎናል:: እነሱ አገራችን አይደለችም ብለው በሚበዘብዟት አገር ላይ ተንደላቀው እየኖሩ ኢትዮጵያ አገሬ የሚሏት እየተዋከቡ ለችግርና ለመከራ መዳረጋችን እጅግ ያሳዝናል:: አሁን ባለው ሁኔታ ኢትዮጵያ ለውጥ ልታመጣ የምትችለው ህወሓት/ወያኔ ይዞት ከተነሳው አገርን የማጥፋት እኩይ ተግባሩና አስተሳሰቦቹ ጋር ወደመቃብር ሲወርድ ብቻ ነው :: ህዝቡም ጨክኖ ለዚህ እውነት ሲነሳ ብቻ ነው::
ከመቼውም ጊዜያት በላይ ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ውርደት የተጋለጥንበት ሁኔታ ላይ ደርሰናል:: በሃገራችን መኖር አልቻልንም፣ በሃገራችን ጉዳይ ላይ መወሰን አልቻልንም ፣በሃገራችን ላይ የበይ ተመልካች ሆነን እንገኛለን፣ በህወሓት/ወያኔ ቀኝ ገዥነት ህዝባችንና አገራችን ለከፍተኛ ብዝበዛ ተጋልጠናል፣ በከፍተኛ ሁኔታ በታጠቁ የህወሓት/ወያኔ በዝባዞች ቁጥጥር ውስጥ ወድቀናል፣ ከፍተኛ ህዝብ ከረሃብ አልፎ ለከፍተኛ ጠኔ ተጋልጦ ይገኛል፣ ይህ አልበቃ ብሎ የአገሪቷ ህዝብ ወደ ውጭ ወጥቶ እንኳን እንዳይሰራ ለከፍተኛ ውርደት ተዳርጎ ማንም እንደፈለገው የሚያደርገውና ተከላካይ የሌለው በዓለማችን ላይ የሚገኝ ህዝብ ለመሆን በቅተናል::
ህዝቡ በአገር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጦ ማንም እንደፈለግ የሚጫወትበት ህዝብ ከመሆኑም በላይ በየትኛውም ነገሩ ላይ ሃይማኖታዊ ጉዳዮቹን ጨምሮ በፈለገው መልኩ እንዳያከናውን መደረጉ ይታወቃል:: ከዚህም አልፎ ደግሞ የአገሪቷ መሬት በተለያዩ ጊዜያት ለተለይዩ ጎረቤት አገራትና ሃይሎች በመስጠትና በማካለል ትልቅ የታሪክ ውርደት ገጥሞናል:: ኢትዮጵያ መቼም ባልታየ መልኩ ለትልቅ ችግር ተጋልጣለች:: ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ትልቅ መስዋእትነትን የሚጠይቅ ትግል ከፊታችን ተጋርጦብናል ይኸውም በህወሓት መቃብር ላይ አገራችንን እንደገና ለማከም የሚያስገድድ ሁኔታ ገጥሞናል:: የህዝብ መብት ጉዳይ ሲነሳ ግድያ፣እስራትና ሞት ሆኗል እጣችን የአገሪቷን ወሰን ለማስጠበቅ የተወሰደው እርምጃም ምንም ባለመሆኑ ዛሬ ኢትዮጵያ መሬቷንና የግዛት ክልሎቿን እየተነተቀጭ ትገናለች::
በአባቶቻችን ተከብረው የነበሩ ድንበሮችን አሳልፎ ለመስጠት ዛሬ ለሱዳንና ለኤርትራም ጭምር እንደፈለገ የሚደራደረው ህወሓት/ወያኔ ገና ያልጨረሳቸው ኢትዮጵያን የማጥፋት አላማዎቹ አላለቁም እና እንዲሁም ቀደምት ወራሪዎቻችን የፈለጉትን መሬት አባቶቻችን በትግላቸው ያቆዩትን አገር በባንዳዎች በእጅ አዙር ለማግኘት እየጣሩ መሆኑና ለዚህም ተፈጻሚነት ደግሞ የህወሓት/ወያኔ የባንዳ ቡድን ሃላፊነት ወስዶ እየሰራ መሆኑን ስንመለከት ያሳዝናል::
የእነዚህ ባንዳዎች አስተሳሰባቸው እና ድርጊታቸው በኢትዮጵያ ላይ መቀጠሉ እንዲያበቃ ዛሬ በህብረት ሆ ብለን መነሳት ካልቻልን ተግባራቸውም ከመፈጸም ሊያቆሙ የሚችሉ አይደሉም :: ህወሓት/ወያኔን ለማሸነፍ ሰዎች የተለያዩ የትግል አማራጮች አዋጭ ናቸው ብለው ባሰቡበት መንገድ ሊሄዱ ይችላሉ፣ ይሁንና አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ግን ህወሓት/ወያኔን በሰላማዊ ትግል እናሸንፋለን ለሚሉ ትግሉ ተገቢ ውጤት እንዲያመጣ ከተፈለገ ትግሉን ማቀጣጠልና በአጭር ጊዜ ወደውጤት እንዲመጣ ማድረግ ወይም ትግሉን ትቶ መውጣት ሌላኛው አማራጭ ይሆናል :: ምክንያቱም ህወሓት/ወያኔ በናንተ ስም የኢትዮጵያን ህዝብ እያታለለና ብልጭ ድርግም በሚለው የሰላማዊ ትግል ውስጥ አማራጭ እየመሰላችሁ እየገባችሁ የህዝቡን ተስፋ ሟሟጠጥና ከትግል ማራቅ በፍጹም አዋጭ የትግል ሥልት እንዳልሆነ ሁላችንንም እንረዳለን ለዚህም ምክንያቱ ደግሞ ህወሓት/ወያኔ በአገሪቷ ታሪክ ውስጥ የፈጠራቸው ዘርን ከማጥፋት ጀምሮ እስከግለሰቦችና ቡድኖች ጭምር ለወሰዳቸው ግፎች የሚፈለግ ቡድን ከመሆኑም በላይ በትግራይ ህዝብ ሳይቀር በተለያዩ ቡድኖችና ግለሰቦች የሚፈለጉ ሰዎች ስብስብ በመሆኑ ሰላማዊ ሽግግርን ይፈልጋሉ ብሎ ማሰብ በፍጹም የሚታሰብ አይደለምና ነው::
ለዚህም ምስክር ይሆን ዘንድ በቅርቡ በራያ በተደረገው ስብሰባ ለአቶ አብርሃ አንድ ተሰብሳቢ ያቀረቡላቸውን ጥያቄ መስማት ብቻ ይበቃል እሱም ህወሃት የሽፍታ ቡድን መሆኑን እና ከእነሱ የሚያላቅቋቸው መሆኑን በጥያቄ መልክ ማቅረባቸውን “ሽፍታ” ማለት ደግሞ ምን ማለት እንደሆነ ለኢትዮጵያውያን በሙሉ የሚታወቅ በመሆኑ ነው::
ይህ ብቻ አይደለም በተለያዩ ጊዜያት አገርን በመክዳትና የአገሪቷንና የህዝቦቿን ጥቅሞች አሳልፎ በመስጠትም የሚፈለጉ ከመሆናቸውም በላይ በሠብዓዊ መብት ረገጣ በኩል አሁን ህወሓት/ወያኔን የሚመሩ ሃይሎች በአገራችን ውስጥ የተፈጸሙ የጅምላ ጭፍጨፋዎችን በማቀድ፣ በመተግበርና በማስተግበር በከፍተኛ ሁኔታ በአገር ውስጥና በውጭ ሃገራት የህግ አካላት እንደሚፈለጉ ጠንቅቀው የሚያውቁ መሆናቸውም ጭምር ነው::
ስለሆነም ይህ ችግራቸው ሊያመጣባቸው የሚችለውን አደጋ በማየት አገሪቷን ለመከላከል ሳይሆን ይህንን የራሳቸውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችላቸውን ሁሉ ለማድረግ እንደቆረጡና ይህንን ችግራቸውን ሊያቃልልላቸው የሚችልን ካልሆነም ጊዜ ሊያራዝምላቸው የሚችልን ሁኔታን ለመፍጠር ሲባል ማናቸውንም የአገሪቷን ጥቅሞች አሳልፈው ለመስጠት መቁረጣቸውን በቀላሉ መረዳት እንችላለን፣ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆኑ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ ከሚወስዱት አረመኔያዊ እርምጃ ልንመለከታቸው እንችላለን::
ከሁሉም በላይ ህወሓት/ወያኔ በተለያዩ ሰዓት የሚቀብራቸው በአንድ ወቅትና ወይም በተለያዩ ጊዜያት ሊፈነዱ የሚችሉ እምቅ ችግሮች በአገራችን ህዝቦች መካከል የፈጠራቸው እንዳሉ ሆነው አሁን ደግሞ ከጎረቤት አገራት በተለይም ከሱዳን ጋር ድንበር ለማካለል በሚል በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስቴር ተጠንሥሶ የነበረውና አብሮት ያልተቀበረው አስተሳሰቡ ዛሬ በቀሪዎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች ሊተገበር ከፍ ዝቅ እያሉ ያሉበት ጊዜ በመሆኑና በሌላ በኩል ከህወሓት/ወያኔ ማንነትና ይዞት ከተነሳው ዓላማው አንጻር ህወሓት/ወያኔ ሲፈልግ ኢትዮጵያዊ ይሆናል ሳይፈልግ ደግሞ ታላቋ ትግራይ ይሆናል ስለሆነም ለመሆኑ የማንን መሬት ነው ህወሓት/ወያኔ የሚደራደርበት ? ህዝቦች ለተወሰነ ጊዜ ሊጨቆኑ ይችሉ ይሆናል ሁል ግዜ ግን እየተጨቆኑ ይኖራሉ ማለት ግን እንዳልሆነ አውቆ መረዳት ያልፈለገው ህወሓት/ወያኔ እራሱ ላይ ትልቅ ችግርን ሊያመጣ መቃረቡን በትክክል መገመት ይቻላል::
ህወሓት/ወያኔ በምንም መለኪያ ኢትዮጵያዊ እንዳልሆነና ኢትዮጵያዊነት ምኑም እንዳልሆነ የራሱ ታሪክ ያሳየናል:: ለዚህም ማስረጃ ለታላቋ ትግራይ ሲሆን አሰብ ይካለላል ለኢትዮጵያ ሲሆን አሰብ የኤርትራ ይሆናል ፣ ለህወሓት/ወያኔ ሲሆን ህገመንግስት ይጣሳል ለህዝብ ጥቅም ሲሆን ይኸው ህገመንግስት እንደፈለገ ይተረጎማል፣ የኢትዮጵያውያን ደም በሳውዲ ሲፈስ ህገወጥ ያሰኛል ለዚሁ ሰብዓዊ ግፍ ካሳን ከሳውዲ መጥየቅ ሲግባ 360 የኢንቨስትመንት ፕሮጀክት እቅዶች ለሳውዲዎች ያሸልማል፣ በኢትዮጵያ ላይ የመበታተን አደጋ ስትፈጥር የነበረችው ሱዳን በአምላክ እጅ መልሷን አግኝታ ስትበታተንና ደረቅ መሬቷን ስትታቀፍ ለህወሓት በታታኝ ቡድን ላደረገችው አስተዋጾ ከ1200 ኪ. ሜ በላይ በሚሸፍን መሬት ላይ እስከ 50 ኪ.ሜ ወደ ውስጥ የሚገባን መሬት ለመስጠት ሲሆን ሽንጡን ገትሮ ህወሓት/ወያኔ ሲንቀሳቀስ ምን ይባላል ? ህዝብን የሚያሸብርና ሽብርተኛ እራሱ ህወሓት/ወያኔ ሆኖ ሳለ የህዝብ ወገኖች የሆኑ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ታጋዮች ምንም ትጥቅ ሳይኖራቸው በሽብርተኝነት እየተፈረጁ በየዕስር ቤቶች የሚንገላቱ ለመሆን በቅተዋል::
በአጠቃላይ ህወሓት/ወያኔ የኢትዮጵያዊነት መለኪያም ሆነ ተግባር የሌላቸው ህይሎች ስብስብ የሆነና በኢትዮጵያውያን ደምና ላብ የራሳቸውን የኢኮኖሚና የፖለቲካ የበላይነት ጥማት ለማርካት በቋመጡ ሃይሎች የተዋቀረ ቡድን በመሆኑና ይህንን የማፍያ ቡድንን እኩይ ተግባርን ለማገዝ በነዚሁ ዘረኞች በተዋቀረ ሠራዊት እየታገዙ አገራችንን ይዘው ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናልና አገራችንን ለማዳን መቁረጥ ይኖርብናል:: ማንም ሊረዳን አይችልም ትግላችን ወደፊት ሲገፋ ግን ብዙዎች አቋማቸውን አስተካከለው ከኢትዮጵያውያን ጋር ይወግናሉ:: ምክንያቱም አገራችን በህወሓት/ወያኔዎች የባንዳ ሃይሎች ብቻ ሳይሆን በታሪካዊ ጠላቶችችንም እጅ ስር በመውደቃችንም ጭምር ነውና ::
ህወሓት/ወያኔ በወልቃይት ጥገዴ ህዝብ ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ በሰላም የተጠናቀቀ መስሎት ከሆነ ተሳስቷል:: የወልቃይት ጠግዴ ህዝብ፣ የሲዳሞ ህዝብ፣ የጋምቤላ ህዝብም ሆነ ሌሎች የህወሓት/ወያኔ የጅምላ ጭፍጨፋ ተጠቂዎች ሁሉ እንዳልተሸነፉ መታወቅ ይኖርበታል በእርግጥ መከራቸው ሁሌም የሚያደማ ቢሆንም :: ይልቁንም ህወሓት/ወያኔ አሁንም ሆነ ለወደፊትም ቢሆን በህዝብና በታሪክ ፊት በፍርድ ፊት ሊሆን የቀረበበት ጊዜ ነው:: ህወሓት/ወያኔ የሚቀብራቸው ፈንጂዎች ምን አልባትም በመጀመሪያ የሚያጠፉት እራሱን ህወሓትን/ወያኔን እንደሚሆን እርግጠኛ ነኝ:: ምክንያቱም ለህዝቦች መከፋፈልና እልቂት የቀበራቸው ፈንጂዎች አቅጣጫቸውን ወደ እራሱ ወደ ህወሓት/ወያኔ እያደረጉ በመሆኑም ጭምር ነው:: ህወሓት/ወያኔና ባለሟሎቹ የኢህአዴግን ስም ተከናንበውና ተሸፋፍነው በህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን ደባ ለማስቆም በሚደረገው ትግል ውስጥ ተሳትፎአችንን እናጠናክር በህወሓት/ወያኔ መቃብርም ላይ አዲሲቷን ኢትዮጵያ በጋራ እንመስርት:: ካልሆነ ህወሓት/ወያኔ አገሪቷን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ሊበታትናት መቁረጡን ከድርጊቱ መመልከት እንችላለን:: ቸር ይግጠመን::
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ!

Wednesday, December 4, 2013

ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ የለም”

ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ የለም” Ethiopian government did not request to negotiate with Ginbot 7

December 4/2013 (በሰንደቅ ጋዜጣ) “መንግሥት ከግንቦት ሰባት ጋር ለመደራደር ያቀረበው ጥያቄ የለም” Ethiopian government did not request to negotiate with Ginbot 7
በኢትዮጵያ ፓርላማ በአሸባሪነት የተፈረጀው የግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ፤ ኢህአዴግ ለደርድር ጥያቄ አቅርቦልኛል በሚል እያናፈሰ ያለው መሰረተ ቢስ የፈጠራ ወሬ መሆኑን አቶ ሽመልስ ከማል የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ አስታወቁ።
ግንቦት 7፤ ህዳር 23 ቀን 2006 ዓ.ም በኢሳት ቴሌቪዥን በኩል ባወጣው መግለጫ ይፋ እንዳደረገው ገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በሁለት ወር ጊዜያት ውስጥ ለሶስት ጊዜያት ያህል የእንደራደር ጥያቄ አቅርቦልኛል ብሏል። ንቅናቄው ለእንደራደር ጥያቄው ምላሽ በሚል ባሰፈረው ሐተታ የኢህአዴግ የእስካሁኑ ተሞክሮዎች እንደሚያሳዩት ውጥረት ሲበዛበትና መዉጪያና መግቢያዉ ሲጠፋዉ፣ ተቃዋሚ ድርጅቶችን “እንወያይ፣ እንደራደር” በማለት ለውጥረት ማስተንፈሻ ጊዜ ይገዛል ካለ በኋላ ስማቸው ባልተገለጸ መልዕክተኞች በኩል ደርሶኛል ያለውን “የእንደራደር” ጥያቄ ንቅናቄው በዋናነት ያየው ኢህአዴግ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም እየሞከረ ነው በማለት ለድርድሩ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጧል።
አቶ ሽመልስ ከማል ግን በመንግስት በኩልም ሆነ በገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ በኩል ለግንቦት 7 የቀረበ እንደራደር ጥያቄ እንደሌለ አረጋግጠው መንግስት ቢፈልግ ጌታው እያለ ከተላላኪው ጋር ምን ያደራድረዋል ሲሉ ጠይቀዋል። ይህ የእነዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ቅጥፈት መሆኑን ጠቅሰው “በዚህ መንገድ እያሞኙ ገንዘብ መሰብሰብ ለምደዋል፤ ይህም ውሽት ለዚሁ ተግባር የተፈበረከ ነው” ብለዋል። ባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ሁኔታ ድጎማና ድጋፍ ለሚሰጧቸው አካላት ሒሳብ ለማወራረድ ድል አድርገን ልንገባ ነው በማለት ሲቀጥፉ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሽመልስ ይህ ዓይነቱ አካሄድ በባዶ ሜዳ ራስን አግዝፎ ለማየት ከመመኘት የሚመነጭ ቅዥት ነው ብለውታል።

የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ካድሬዎቻቸው በፓስፖት እና በቀበሌ መታወቂያ ንግድ ላይ ተሰማርተው እንደነበር ተገለፀ።



የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ካድሬዎቻቸው በፓስፖት እና በቀበሌ መታወቂያ ንግድ ላይ ተሰማርተው እንደነበር ተገለፀ።


ሰሞኑንን ኢ.ቲ.ቪ አይናችን በሚል ፕሮግራሙ ባሰራጨው በዚህ ስፊ ዘግባ ላይ የኢሚግሬሽን እና ስደተኞች ጉዳይ መምሪያ መቤ/ት እና የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት መዋቅር እንደሆኑ የሚነገርላቸው ቀበሌዎች ውስጥ የተሰማሩ ካድሬዎች በመታወቂያ እና በፓስፖርት ህገወጥ ስራ ላይ ተሰማርተው እንደነበር ከቀረበው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። 

በአንድ ቤት እስከ 40 መታወቂያ የሚወጣበት አጋጣሚ መኖሩን በተጨባጭ፡ያረጋገጠው የፕሮግራሙ አዘጋጅ የኤምግሬሽኝ እና ስደተኞች ጉዳይ መመሪያ ሃላፊዎች ለውጭ፡ሃገር ዜጎች ፓስፖርት በመሸጥ የአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎችን ከፍተው አያሌ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ወደ አረብ ሀገር በመላክ ለሞት እና ለስቃይ መዳረጋቸውን ጸሃይ የሞቀ የአደባባይ ሚስጥር መሆኑ ቢታወቅም ኢቲቪ የተጠቀሱትን ባለስልጣኖች በግርድፉ የህገሪቱን ሰነድ አሳልፈው የሸጡ ብሎ አድበስብሷት አልፎል። 

እንደሚታወቀው ከዛሬ 4 አመታት በፊት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የኢትዮጵያ መንግስት ለሳውዲ አረቢያ የቤት ሰራተኛ ለማቀረብ በገባው ውል መስረት አንዳንድ ከፍተኛ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ባለስልጣናት በውጭ፡ሃገር ዜጎች ስም በእጅ አዙር ሰራተኛ እና አስሪ ኤጀንሲዎችን ከፍተው ከእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ተጓዥ እስከ 7መቶ ዶላር በማስከፈል በወር ከ 45 ሺህ ያላነሱ እድሜያቸው ለአካለ መጠን ያልደረሱ ኢትዮጵያውያንን ህጻናት እህቶቻችንን ጭምር ያለምንም የህይወት ዋስትና ወደ ሳውዲ አረቢያ በመላክ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ.መንግስት ባወጣው ህግ ሸፋን በወገኖቻችን ደም ንግድ ላይ ተሰማርተው መኖራቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ ። የሳውዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ወደ ሃገሩ እንዳይገቡ የመግቢያ ቪዛ ማገዱን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግስት የተጠቀሱትን ኤጀንሲዎች ላልተወሰነ ግዜ መዝጋቱን ለማረጋገጥ ተችሏል። 

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

Sunday, December 1, 2013

በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዲፕሎማቶች በወገኖቻችን ስም ለሁለተኛ ግዜ ህገወጥ የገቢ ማሰብሳቢያ ፕሮግራም አደረጉ ።




በዚህ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የመግስት ልኡካን ቡድን መሪ የወገኖቻችን ህይወት አሳስቢ መሆኑን ገለጹ ። 
=======================================================
በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የመንፉሃን ሁከት ተከትሎ በቅርቡ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያቀናው የመንስት ሎኡካን ቡድን በየመጠለያው እና በየእስርቤቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ህይወት አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ሳይሸሽጉ የአይን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ። ወገን ለወግን ደራሽ ወገን ነው በሚል ኖቬብር 29 2013 ምሸት በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ ከስደት ወደ ሃገራቸው ተመላሽ ወገኖቻችን ድጎማ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ከህዝብ ጋር ለመጀምሪያ ግዜ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ እንድተገኙ የሚነገርላቸው የመንግስት ሎኡካን ቡድን ተወካዮች በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ እየደርሰ ያለው ስቃይ እና በደል ከመቸውም ግዜ በላይ አስቃቂ እየሆነ መምጣቱን በወቅቱ ለነበሩ ታዳሚዎች ባድረጉት ነግግር መናገራቸውን ምንጮች ገልጸዋል። 

በተለያዩ የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ተዘዋውረው መጎብኘታቸውን በንግግራቸው ላይ የገለጹት የመንግስት ልኡካን ቡድን ተጠሪ አንባሳደር ውብሸት አባዛኛው ወገኖቻችን ያሉበት ሁኔታ አሳዛኝ እና ልብ የሚነካ ከመሆኑም በላይ ሴት እቶቻችን እና ህጻናት ልጆቻቸው በመጸዳጃ ቦታ እና በፓፐርስ እጦት ንጽህናቸውን መጠበቅ ያልቻሉበት ሁኔታ እና ከቁጥጥር ውጭ የወጣ መሆኑን ተናግረዋል። ሚንስትሩ አክለው ሲገልጹ በአንድ የመጠለያ ጣቢያ ውስጥ ባለው ትርምስ ወደ ሳውዲ አረቢያ ከገባች 3 ወር ያልሞላት የኮንሷ ብሄረሰብ ተወላጅ ኢትዮጵያዊት ወጣት ችግሯን በአረብኛ ወይም አማርኛ ቋንቋ መግለጽ ተስኖዋት ሌሎች ወገኖቿ ሊረዳዎት በማይችሉ የትውልድ ቋንቋዎ እይተናገረች ስቅስቅ በላ ስታለቅስ መታዘባቸውን ልብ በሚነካ አቀራረብ ለተሰብሳቢው በማስረዳት ወገኖቻችን አሁን ሳውዲ አረቢያ ስላሉበት ፈታኝ እና አስቃቂ የመከራ ግዜ አፋጣኝ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል። 

በሳውዲ አረቢያ ወደ ሃገሩ መግባት የሚፈልገው ኢትዮጵያዊ ቁጥር ከግዜ ግዜ እየጨመረ መምጣቱን ተከትሎ የሳውዲ አረቢያ እስርቤቶች በመሙላታቸው ለደህነቱ ዋስትና ያጠው ህዝባችን ከቤት ንብረቱ በመፈናቀል በየግዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ያለበቂ ምግብ ወሃ እና መስረታዊ ፍጆታ እየተሰቃየ እንዳለ እና ወደ ሃገሩ ለመግባት በሚያደርገው ቆይታ የከፋ እና አሰቃቂ አደጋዎች ሊገጥሙት እንደሚችል በማውሳት ለወገኖቻችን ትኩረት ሰጥቶ የህዝባችንን ህይወት ለመታደግ መረባረብ የሚገባን አሁን ነው ብለዋል። ይህ በዚህ እንዳለ ሰሞኑን በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃላ አቀባይ አንባስደር ዲናሞ ሙፍቲ በሳውዲ አረቢያ ወገኖቻችን ላይ እየደረስ ያለውን ችግር አስመልክተው የሚጋነን እንዳልሆነ በማጣጣል የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ የሪያድ ነዋሪዎች የመረጃ እጠረት ያለበት እና በግል ስሜት የተነገረ መሆኑን በማስታወስ በነ አንባሳደር ዲናሞ አይነት ለዜጎች ህይወት ዴታ በሌላቸው ደካማ የመንግስት ባለስልጣናት ሀገሪቷ መመራቷ ወደፌት በጣም አሳሳቢ መሆኑን ተናግረዋል። 
ትላንት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ በተደረገ በዚህ ጥቂት የልማት ማህበር አባላት እና ደጋፊዎቻቸው ጨምሮ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግርም ላይ የመድረኩ መሪ በውጭ ሃገር የሚኖሩ ወገኖቻችን በሃይማኖት በብሄር በቋንቋ ሳይለያዩ በአንድ ድምጽ አደባባይ በመውጣት በሳውዲ አረቢያ መንግስት ላይ ላደረጉት ጫና መስጋና ሊቸራቸው እንደሚገባ የገለጹበት አጋጣሚ በደማቅ ጭብጨባ እና ሆታ ለደቂቃዎች የአዳርሹን ድባብ ለውጦት እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች አንባሳደር ውብሸት በውጭ የሚኖሩ ፀረ ሰላም ሃይሎች ብለው እንዚህን ወገኖቻችንን በመፈረጅ መንግስታቸው ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው ጸረ ሰላም ድርጊት እያካሄዱ ያሉትን ቅጥረኞች በቅርብ እይተከታተሉ መሆኑንን በመግለጽ ከመደርክ አስተባባሪዎቹ አድናቆት የተቸራቸውን የኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እንቅስቃሴ በማውገዝ ታዳሚውን ክፉኛ አሳዝነዋል። 

በወቅቱ አንዳንድ ወገኖች መድረክ አጊተው እንደነበር የሚናገሩ ምንጮች አንድ የህገር ሽማግሌ አባት የገቢ ማሰባሰባሰቢያ ፕሮግራሙን የተቀደሰ አላማ በማለት ገልጸው ሁላችንም ኢትዮጵያውያን ነን ዛሬ የሳውዲዎቹ ጥቃት ያነጣጠረው መኖሪያ ፈቃድ በሌለው ወገኖችን ላይ ብቻ ሳይሆን የሃበሻ ደም ባለው ላይ ሁሉ ስለሆነ መንግስት ለደህነታችን ዋስትና ምን እየሰራ ነው በሚል ለልኡካን ቡድኑ ያቀረቡላቸው ጥያቄ ተድበስብሷ እንደታለፈ ገልጸዋል ። ጉዳዩ በብሄራዊ ደረጃ መታየት እንደሚገባው የሚናገሩ ኢትዮጵያውያን የሪያድ ነዋሪዎች በወገኖቻችን ስም በየጓሮው ያለ ደረሰኝ የሚሰብሰበው ገንዘብ አሁን ሪያድ ውስጥ ላለው ወገናችን በምንም አይነት መልኩ ሊደርስ እንደማይችል ገልጾው ገንዘቡ የስደተኞቹን ጉዳይ ለመስፈጸም የጸህፍሀት መስሪያዎች እና መሰል ተዛማጅ ነገሮች የገንዘብ እጥረት አለብን እያሉ ለሚያዛጉት በሪያድ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማቶች ኪስ ማደለቢያ ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል። 

በስልክ ያነጋገርኳቸው አንድ ሪያድ ከተማ የሚኖሩ የሃይማኖት አባት በበኩላቸው ገቢ በማሰባሰቡ ጽንሰ ሃሳብ ላይ ተቃውሞ እንደሌላቸው ተናግረው የወገኖቻችንን ህይወት ለመታደግ ለአለም አቀፍ የዕርዳታ ድርጅቶች በዚህ ዙሪያ ተሳታፊ እንዲሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ጠንክሮ መስራት እንደሚገባው እና ከሰደት ተመላሽ ወገኖቻችንን ለማቋቋም ካሰፈለገ በብሄራዊ ደረጃ ህጋዊ በሆነ መንገድ የገቢ ማሰባሰቢያው ፕሮግራም መደረግ ተገቢ መሆኑን መክረው አሁን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ በዲፕሎማቱ እየተድረገ ያለው የገበያ ግርግግር የተለመደ በመሆኑ በአብዛኛው ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም ብለዋል። በወገኖቻችን ስም በሚደረግ በዚህ የገቢ መሰባሰቢያ ፕሮግራም በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ት/ቤት 2 ሺህ ተማሪዎች ከያንድንዱ 10 ሳ ሪያል ለመሰብሰብ ዲፕሎማቱ እቅድ መያዛቸውን የሚገልጹ ምንጮች አርብ ምሽት በተድረገው ፕሮግራም ከልማት ማህበራት ከእድሮች ከኮሚኒቲው ማህበር እና ጉዳዩ ካልገባቸው አንዳንድ ወግኖች እስከ 3 መቶሺህ ሪያል በወገኖቻችን ስም መሰብሰቡን ለመረዳት ተችሏል ብለዋል። 

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳርሽ እንደዚህ አይነት የግቢ መሰባሰቢያ ፕሮግራም ሲደረግ ለሁለተኛ ግዜ መሆኑን የሚናገሩ ወገኖች ቀደም ሲል ላለፉት 11 ወራት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ አነስተኛ ኮንቴነር ውስጥ በር ተቆልፎባቸው ሲሰቃዩ ለነበሩ 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ ከ200 ለሚበልጡ እህቶቻችን የአይሮፕላን ትኬት መግዣ ፤ በተዘጋጀ የግቢ ማሰባሰቢያ ፕሮራም ላይ እስከ 1መቶ ሺህ ሪያል « ግማሽ ሚልዮን ብር » ተገኝቶ እንደበር በማስታወስ የተጠቀሰው ገንዘብ ለታቀደለት አላማ ሳይውል በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ መጠለያ ውስጥ የነብሩትን ወገኖቻችን ስበዕና ያልፈጠረባቸው በነዚህ አረመኔ ዲፕሎማቶች ለሳውዲ አረቢያ ፖሊስ ተላልፈው በመስጠታቸው ለከፋ ችግር እንደዳረጓቸው ገልጸዋል። እነዚህ የሪያድ ምንጮች አክለው ሲገልጹ የተጠቀሱት ወገኖች ለረጅም ግዜያት የሪያድ ኮሚኒት ግቢ ሲሰቃዩ የነበሩ መሆናቸው ግምት ውስጥ ገብቶ ከህዝብ በተሰብሰብው ገንዘብ የአይሮፕላን ትኬት ቀርቦላቸው በክብር ለሃገራቸው መብቃት ሲገባቸው በገዛ ዲፕሎማቶቻችን እንደዚህ አይነት ኢሰባዊ ድርጊት መፈጸሙ በምድርም በሳማይም የሚያስጠይቅ ወንጀል መሆኑን በምሬት ይገልጻሉ። 

ይህ በዚህ እንዳለ ቀደም ብሎ በኢትዮጵያውያኑ ስም የተሰበሰብው 1 መቶ ሺህ ሪያል ወይም « ግማሽ ሚልዮን ብር » ዲፕሎማቱ ኪሳቸው መክተታቸውን የሚናገሩ ወገኖች 12 ነፍሰጡሮችን ጨምሮ እስከ ከ200 የሚጠጉ ወገኖቻችንን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ጊዚያዊ መጠለያ በኖሩባቸው ግዜያቶች ከኮሚኒቲው ካፍቴሪያ እየወስዱ ሲበሉ ለከረሙት ቀልብ ወሃ እና መብራት ሂሳብ መወራረዱን ዲፕሎአምቱ በድፍረት መናግራቸው በጣም እንዳሳዘናቸው ጠቅሰው « ውሻ በላበት አፉ ይጮሃ እንዲሉ» እንዚህ አረመኔ በሪያድ የሚኖሩ ዲፕሎማቶች ሰሞኑንን በዚሁ አዳርሽ ለሁለተኛ ግዜ ያለደረስኝ ሲሰበሰብ የከረሙት 3 መቶ ሺህ ሪያል ወይም « 15 ሚልዮን ብር » ለስደተኛው ወገናችን በቀጥታ መድረሱን እንጠራጠራለን ብለዋል ።

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ