Thursday, June 16, 2016

ኤርትራ “200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድዬ 300 አቆስለኩ” አለች

 ቢቢሲ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴርን ገልጾ እንደዘገበው ኤርትራ በ2 ቀን ጦርነት 200 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገድላ 300 ማቁሰሏን አስታወቀች::
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ባለፈው እሁድ ባወጣው መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት በጾረና በኩል ጥቃት ፈጸመብኝ ማለቱ ይታወሳል::
እንደሚኒስትሩ መግለጫ እሁድ እና ሰኞ ዕለት በተደረገው ጦርነት 200 ሰዎችን መግደሉን ይገልጽ እንጂ ከራሱ በኩል የተጎዱ ወይ የሞቱ ወታደሮች እንዳሉ የገለጸው ነገር የለም::

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ለኤርትራ መንግስት እስካሁን ለፈጸመው ትንኮሳ ተመጣጣኙን እርምጃ ሰጥተነዋል:: ወደፊትም እንደ ኤርትራ መንግስት እንቅስቃሴ ጦራችንን እናንቀሳቅሳለን ማለቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም::
የመንግስት ጉዳዮች ሚኒስትሩ አቶ ጌታቸው ረዳ በዚህ ሳምንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫም ከኤርትራ ጋር ወደለየለት ጦርነት መግባት የኢትዮጵያ ምርጫ አይደለም ማለታቸው ይታወሳል::
ኢትዮጵያና ኤርትራ ከ1998 – 2000 ዓ.ም ድረስ ባደርጉት የድንበር ግጭት ከ100 ሺህ ሰዎች በላይ ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ የታሪክ መዛግብት ይመሰክራሉ::(ዘ-ሐበሻ) ቢቢሲን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው 

Wednesday, June 15, 2016

ሰይፉ ፋንታሁን ታሰረ – ነገ ሊፈረድበት ነው


ሰይፉ ፋንታሁን በቀረበበት ሀሰተኛ ወሬ የማሰራጨት ክስ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ሰይፉ በመናገሻ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤት ዛሬ በቀረበበት ወቅት ‹‹አዎ ድርጊቱን ፈፅሜያለሁ›› በማለት የእምነት ቃሉን እንደሰጠ ምንጮቻችን ገልፀውልናል፡፡ ፍርድ ቤቱም ተከሳሹ የቀረበበትን ክስ መፈፀሙን በማመኑ የፍርድ ውሳኔ ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ሰጥቶ ተከሳሹ በቁጥጥር ስር እንዲቆይ አዟል፡፡ በዚህ መሰረት ሰይፉ ፋንታሁን በአሁኑ ወቅት በጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ይገኛል፡፡ በነገው ዕለት በሚውለው ችሎት የእስር ወይንም የገንዘብ ቅጣት ሊጣልበት ይችላል፡፡
ለክስ የዳረገው ጉዳይ በቴዎድሮስ ተሾመና ቴዎድሮስ ተሾመ ድርሰቴን ሰርቆኛል ብለው ክስ በመሰረቱት ግለሰብ ዙሪያ በሬዲዮ ያሰራጨው ወሬ ነው፡፡ የሁለቱ ግለሰቦች ክስ በፍትሀብሄር እየታየ በነበረበት ሰዓት ሰይፉ በችሎት ያልተባለን ነገር ተብሏል ብሎ በማውራቱ ነው የተከሰሰው፡፡
ከዚህ ቀደም ሳያት አህመድ በዚሁ ፍርድ ቤት ሰይፉ ላይ ክስ አቅርባ እንደነበርና ጉዳዩ በሽምግልና ተድበስብሶ እንዲቀር መደረጉ ይታወሳል፡፡

Wednesday, December 30, 2015

ሳውዲ አረቢያ - ሪያድ አለም አቅፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ላይ የተጀመረው ዘረፋ ተጦጡፎል ። 37 ሚሊዮን ሪያል እጅ ከፍንጅ ተያዘ ።

ሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ባለፉት ሁለት አስረት አመታት ዘርፈ ብዙ ችግሮችን አሳልፎል ። በተለይ ት/ቤቱ በየሁለት አመት እተመራረጡ እራሳቸውን የት/ቤቱ አስተዳደር ቦርድ ብለው በሚሾሙ ቡድኖች ሁሉም ነገር ለወላጆች ሚስጠር ከሆነ ወዲህ በት/ቤቱ ካዝና ላይ ስለሚደርሰው አደጋ ማውጋት ቀላል እና የተለመደ ሆኗል። ወላጅ በየአመቱ የት/ቤቱ ህንጻ የኪራይ መጠን ጨመረ እይተባለ በነዚህ ወገኖች ከአቅሙ በላይ እንዲከፍል የሚገደደውን ወረሃዊ ክፍያ እየገፈገፈ ልጆቹን ከማስተማር ባሻገር ለምን ብሎ መጠየቅ በፍጹም መብት የለውም ። የወላጆች ኮሚቴ ፈርሷ የት/ቤቱ ፈላጭ ቆራጭ ቦርድ ከሆነ ወዲህ ሲሹም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል እንዲሉ የቦርድ አስተዳደሩ ከባእዳን አከራዩች ጋር በመመሳጠር ሁለት መቶ ሃምሳ ሺህ የነበረውን የት/ቤት ህንጻ አመታዊ ኪራይ መጠን ወደ 1. 4 ሚልዮን ( 6.5 ሚልዮን ብር ) እንዲያሻቀብ በማድረግ ወላጆች ከአቅማቸው በላይ ወረሃዊ ክፍያ እንዲከፍሉ እና ለ 2528 ተማሪዎች የመማር መስተማር ሂደት እየተሰተጓጎለ መምጣት ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆኑ ይነገራል። ይህ ባለበት ሁኔታ ሰሞኑንን አስተዳደር ቦርድ ባቀረበው ሪፖርት በሻንጣ የታጨቀ 37 ሚልዮን ሪያል ወይም ( ከሁለት ቢልዮን ብር በላይ ) እጅ ከፍንጅ መያዙ በወላጆች ዘንድ ክፉኛ ድንጋጤን ፈጥሯል።
እንደ አስተዳደር ቦርዱ ሪፖርት የት/ቤቱ ገንዘብ ያዥ አቶ ሰለሞን የተባሉ ግለስብ ከወላጆች ይሰበስብ የነበረውን ወረሃዊ የተማሪዎች ክፍያ በቀድሞ የቦርድ አመራር ትእዛዝ ካዛና ውስጥ ያስቀምጥ እንደነበር እና ካዝናው ምንም አይነት ቁጥጥርም ሆነ ለአመታት ኦዲት ተደርጎበት እንደማያውቅ የሚያትተው ሪፖርት የቀድሞው ቦርዱ የስራ ጊዜውን ጨርሶ ከመሰናበቱ በፊት ወደ ካዛና እንዳይጠጉም ሆነ የገንዘብ ስም እንዳያነሱ የተደረጉበት ምክንያት ግራ ስላጋባቸው ገንዘብ ያዡ ለዕረፍት የሳውዲን ምደር ለቀው ከመውጣታቸው በፊት ባደረጉት ክትትል የተጠቀሰውን የት/ቤት ገንዘብ ሻንጣ ውስጥ እንደ ታጨቀ ማግኘታቸውን አረጋግጠዋል።
ይህን ያህል ገንዘብ ያለምንም ዋስትና የት/ቤቱ ገንዘብ ያዥ እጅ እንዲቀመጥ የተደረገበት አግባብ እስካሁን በውል ባይታወቅም እጅ ከፍንጅ የተያዘው ጥሬ ገንዘብ ከዚህ በላይ ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ተጨማሪ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሳይዘረፍ እንዳልቀረ ይጠራጠራሉ ። በወቅቱ የት/ቤቱን ህንጻ በ 50 ሚልዮን ሪያል ለመግዛት በወላጆች ሃስብ ቀርቦ እንደነበር የሚያስታውሱ እነዚህ ውስጥ አውቂ ምንጮች ት/ቤቱ ካፒታል የለውም በሚል ሰበብ የአስተዳደር ቦርዱ ወላጆች ያቀረቡትን ሃስብ ውድቅ በማድረግ ት/ቤቱ በኪራይ እንዲቀጥል የወሰነበት ምክንያት የተጠቀሰውን ገንዘብ ለመዝረፍ ታስቦ እንደነበር ይገልጻሉ። በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ከወላጆች እጅ ከወጣ ወዲህ ገቢና ወጪው በትክክል አይታወቅም የሚሉ ምንጮች ፤ በመቶ ሺህ ሪያል ( እስከ ሩብ ሚልዮን ብር) የሚቆጠር ጥሬ ገንዘብ በቦርድ አባላት ትእዛዝ በነጭ ወረቀት በቀላሉ ውጪ የሚደረግበት አሰራር እንዳለ ይናገራሉ።
ከ 2500 በላይ ኢትዮጵያውያን ህጻናት ተቀብሎ እንደሚያስተናገድ ስለሚነገርለት ዝነኛ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት ከ 100 ለማይበልጡ ወላጆች ሪፖርቱን ያቀረበው አስተዳደር ቦርድ ቀደም ብሎ ሲሰራበት የነበረውን የፋይናስ ቁጥጥር በመለወጥ በአዲስ መልክ ዘረጋሁ ባለው ኔት ዎርክ ሲስተም ለት/ቤቱ ገቢ መሆን ከሚገባው ገንዘብ ውስጥ 100.000 ሪያል ወይም ( ከሩብ ሚልዮን ብር በላይ ) ጉድለት ማግኘቱን በመግለጽ ለዚህም ተጠያቂ የሆነው ግለሰብ 50.000 ሪያል ምህረት ተደርጎለት የቀረውን ገንዘብ በሂደት እንዲከፍል መወሰኑ አብዛኛውን ወላጆች አሳዝኖል። በሪያድ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት የቦርድ አባል ሆኖ ሃገርቤት ህንጻ ያላነፀ ፡ ዘመናዊ ተሽከርካሪዎችን ገዝቶ ያላከ ፡ አክሲዮን ያልገዛ የለም የሚሉት ምንጮች ግልጽነት እና ተጠያቂነት በሌለበት አሰራር ዛሬም ወላጆች በማያውቁት የአስተዳደር ቦርድ የሚዘወረው የት/ቤቱ ካዝናም ሆነ ት/ቤቱ ዋስትና እንደሌላቸው ይጠቁማሉ።
በተለያዩ ጊዜያት በአካባቢው የመንግስት ሹማምንቶች ተመርጠው የአስተዳደር ቦርድ በሚሆኑ አካላት የሚተዳደረው የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት ዘንድሮ ተማሪ የመቀበል አቅሙን ለማሳደግ በሚል ሽፋን ኮሚኒቲ ጊቢ ውስጥ የሚገኙ ትርፍ ቦታዎች ላይ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች ለማስገንባት ለይስሙላ በሚነቀሳቀሰው የቦርድ አመራር እና የት/ቤቱ አስተዳደር መሃከል የእከክልኝ ልከክለህ ግንኙነት ግንባታውን ለማስፈፀም ምንም አይነት ጫራታ እንዳልወጣ የሚናገሩ ወኖች ከአምናው በከፋ ዘንድሮም በረቀቀ መንገድ ት/ቤቱ ካዝና ላይ ከፍተኛ የሆነ ዘረፋ መፈፀሙን ይናገራሉ ።
በሪፖርቱ ለትርፍ ሰዓትና ተለያዩ ወጪዎች 70.000 ሪያል ( 392000 ብር ) መመንዘሩን ከመግለጽ ውጭ ዝርዝር መረጃ ያላስቀመጠው የት/ቤቱ አስተዳደር ቦርድ የት/ቤቱን ፈቃድ ለማሳደስ ተጠይቆ የነበረውን እጅ መንሻ 20.000 ሪያል ( መቶ ሺህ ) ብር ማስቀረቱን ሽፋን መስጫ በማድረግ ወላጆችን ለማደናገር ሞክሯል የሚሉ ምንጮች በቀጣይ አመት የት/ቤቱ ህንጻ ካልተለወጠ እስከነ አካቴው ፈቃዱ ሊሰረዘ እነደሚችል እና የት/ቤቱ የመማር ማስተማር ሰረአት ሊስተጓጎል እንደሚችል ከቀረበው ሪፖርት ለመረዳት መቻሉን ገልጸዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ ህልውናው አደጋ ላይ እየወደቀ የመጣውን የህዝብ ት/ቤት ለባለ ሃብቶች ለመሸጥ እቅድ እንዳለ ከአስተዳደር ቦርዱ አመራር አባላቱ ሾልኮ ከወጣ ሚስጥራዊ መረጃ ማረጋገጥ ተችሏል።
ይህ በዚህ እንዳለ ለስራ ጉዳይ ሃገር ቤት የሄዱት የት/ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ አብዱል ባሴጥ አብዱል ጀማል ተመልሰው ሳውዲ እንዳይገቡ የተፈፀመው ሴራ ከ 37 ሚልዮን ሪያሉ ጋር ግንኙነት ይኑረው አይኑረው እስካሁን በውል ባይታወቅም ርዕሰ መምህሩ ላይ በላግ ( wonted )ያስደረገውን አካል ለመያዝ በሳውዲ ፖሊስ እየተጣራ መሆኑና ወደፊት በህግ እንደሚጠየቅ ርዕሰ መምህሩ የሰጡትን መረጃ ዋቢ በማድረግ ውስጥ አዋቂ ምንጮች አክለው ገልፀዋል። ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ

Tuesday, September 22, 2015

በኢትዮጵያ አየር መንገድ መስተንግዶ እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየታቸውን የሚገልጹ ኢትዮጵያውያን ደንበኞች ቅሬታ አሰሙ።


ከቅርብ ግዜ ወዲህ ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚጓዙ መንገደኞችን በአሮጌው ተርሚናል በኩል በማስተናገድ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዜጎች በማንነታቸው ተለይተው እየተዋከቡ መሆኑን መንገደኞቹ የደረሰባቸውን በደል ዋቢ በማድረግ ምንጮች ይገልጻሉ በተለይ ወደ ሳውዲ አረቢያ የሚጓዘው ኢትዮጵያውያዊ አብዛኛው ሙስሊም ማህበረሰብ እንደመሆኑ መጠን ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚደረግባቸው የሚገልጹ እነዚህ ምንጮች ዜጎች በገዛ ሃገራቸውና አየር መንገዳቸው እንደ ሁለተኛ ዜጋ መታየታችው የመንግስት እጅ እንዳለበት አመላካች መሆኑን ይጠቁማሉ። በአሮጌው ተርሚናል የሚስተናገድ እንዚህ የአየር መንገዱ ተገልገላይ ኢትዮጵያውያን ደንበኞች ኢዘውት በሚወጡትና በሚገቡት እቃዎቻቸው ላይ ያለአግባብ ጥብቅ ፍተሻ ይደረጋል ለቤተሰብ ዘመድ አዝማድ ስጦታ የሚውል እቃዎቻቸው ላይ ከፈተኛ ቀረጥ ይጣላል የመንገደኛው ሻንጣ ቁልፍ ተሰብሮ ይዘረፋል ሻንጣዎቹ እስክነ አካቴው የውሃ ሽታ ሆነው ይቀራሉ በዚህ ተርሚናል የሚስተናገዱ ደንበኞች በአየር መነግዱ ሰራተኞች ክብር አይሰጣቸውም መብቱን ለማስከበር ለምን ? ብሎ የጠየቀ መንገደኛ የሰደባል ይገለመጣል አልፎ አልፎ በጥፊና በካልቾ የሚሰተናገድበት አስዛኝ አጋጣሚ እንደሚከሰት የአይን እማኞች ገልፀዋል። ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው እና የከፋው ሳውዲ አረቢያ « መካ » ለሃጅ የፀሎት ሥረዓት በቤተሰብ አጀብ የሚሸኙ የጸሎት ተጓዥ ምእመናን ወደ አሮጌው ተርሚናል ከገቡ በሃላ እንደ ፀሎት ተጓዥ ሳይሆን አንደ አንድ መንገደኛ ማግኘት የሚገባቸውን ክብር አጥተው ስረዓት በሌላቸው አንዳንድ የአየር መንገዱ አስተናጋጆችና የፀጥታ አባላት እንደ ሚዋከቡ በደሉ የደረሰባቸውን ዜጎች ዋቢ በማድረግ ይገልጻሉ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ በአሮጌው ተርሚናል እያደረገ ካለው የወረደ መስተንግዶ ይልቅ « ጅዳ » ሳውዲ አረቢያ አየር ማረፊያ በባዕዳኑ የአየር መንገዱ ሰራተኞችና የፀጥታ ሃይሎች የሚደረጉላቸው አቀባበልና / መስተንግዶ ምንም እንደ ማይገናኝና የትየለሌ መሆኑንን ሰሞኑን ጅዳ ከገቡ ምዕመናን የሃጅ ጸሎት ተጓዥ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ማረጋገጥ ተችሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገዱ መስተንግዶ መንግስት ሃገር ውስጥ በጋራ እና በተናጠል ህዝበ ሙስሊሙ ተቋም ላይ ከሚፈጽመው በደል አይለየም የሚሉ አንዳንድ ወገኖች በአሮጌው ተርሚናል በኩል የሚያልፍ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም እንደ ዜጋ ቀርቶ አንድ ቆዳው ነጣ ያለ መንገደኛ የሚሰጠውን ክብር ያህል ቦታ የለንም ይላሉ። የኢትዮጵያ አየር መንገዱ መስተንግዶ በኢትዮጵያዊን ሙስሊም ወገኖቻችን ላይ ብቻ ያነጣጠር ይሁን እስካሁን ማረጋገጫ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም «ከተላብ የተገኘ ስሊጥ አብረህ ተወቀጥ » እንዲሉ በኮንተራት ስራም ሆነ በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተጠቀሱት ሃገርት የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ሳይቀሩ በደሉ እየተፈፀመባቸው መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የሃገሪቱን ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ አርማው በማድረግ ከግማሽ መዕተ አመት በላይ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው ይህ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ ህዝብ የሆነው አየር መንገድ በገዥው ፓርቲ .../.... ስረአት ካድሬዎች እጅ ከወደቀ ወዲህ ዜጎች በማንነታቸው እየተለዩ የዜግነት ክብራቸውን የሚያጡበት ብቻ ሳይሆን የአየር መንገዱ ሰራተኞች ጭምር በብሄር ማንነታቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸው እየተለዩ ግፍና በደል የሚፈፀምባቸው ማዕከል እየሆነ መምጣቱ ይታወቃል። ህወሃት/.... ስረዓት የዜጎችን ከሃገር ወደ ሃገር የመዘዋወር ህገመንግስታዊ መበት በመጣስ ከሳውዲ አረቢያ ቤተዘመድ ጥየቃ ለረእፍት ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ዜጎች የዕረፍት ግዜያቸውን ጨርሰው ሲመለሱ የሚኖሩበትን ሃገር የመኖሪያ ፈቃድ መታወቂያ « ኢቃማ » ካላመጣችሁ አታልፉም በሚል ምክንያት በአየር መንግዱ ውስጥ በተሰገሰጉ የፀጥታ ሃይሎች እስከ 10 ሺህ ሪያል የሚደርስ ጉቦ በግልጽ እንደሚጠየቁ ለመረዳት ተችሏል። በሳውዲ አረቢያ ህግ ማንኛውም የወጭ ሃገር ዜጋ ፓስፖርቱን ከአሰሪው እጅ ሲቀበል የመኖሪያ ፈቃዱን ለኣሰሪው ማስረከብ እንደሚገባ ይደነግጋል። Ethiopian Hagere Jed Bewadi

Sunday, August 30, 2015

እራሱን ጽናት እያለ በሚጠራው ጀሌ ላይ በቀረበው ጽሁፍና ማስተባበያ ለቀረበበት «ዘረፋ» ግልጽ የሆነ ማስረጃ !‏‏

ድምጻችን ይሰማን ለሁለት በመስንጠቅ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመናድ ሀወሃት/.... እንቅልፍ አጥቶ ማደር የጀመረው ዛሬ እንዳልሆነ የታወቃል ።ህወሃት/.... የሃይማኖት ነጻነት ትግሉ በተጀመረ ማግስት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ዘብጥያ በማውረድ ለይስሙላ ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ መብት በመተላለፍ የህዝቦችን መብት በጠመንጃ አፈሙዝ ጨፍልቆ ለጸሎት አደባባይ የወጣውን አዛውንት ሴት ወጣት ሳይል ያገኘውን ሁሉ በደም በጨቀዩ ልዩ ኮማንዶዎቹ በጥየት ረሽኗል ከሞት የተረፈውን በቆመጥ ደብድቦ በክሚዎን በማጋዝ ወዳልታወቀ ስፍራ ወስዶ አስሮ በማሰቃየት ላይ ይገኛል። ታዲያ ይህን ሁሉ ግፍና ስቆቃ የተቀበለው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ሰላማዊ ተቃውሞውን የበለጠ በማጠናከር ሳይገድል እየሞተ ለአምባ ገነኖች የአላማ ጽናቱን በተግባር አሳይቷል በማሳየትም ላይ ይገኛል። ይህ የህዘበ ሙስሊሙ አንድነትና ለሃይማኖቱ ነጻነት ያለው ቁርጠኝነት እንቀልፍ የነሳው ሀወሃት መራሹ የኢ.... ስረአት የበግ ልምድ ለብሶ ውሎና አድሩን ህዝበ ሙስሊሙ ጉያ ውስጥ በማድርግ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ዑለማዎች የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በኃይል አሊያም በግዜያዊ ጥቅም በማግባባት ለዚህ እርኩስ ሴጣናዊ ተግባሩ ማስፈፀሚያ ግበአት እንዲሆኑ ለማድረግ ሃገር ውስጥና በውጩ አለም እየዞረ  ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልቦጠጠው ተራራ የለም። ለአብነት ያህል የፖለቲከኛውን ጁሃር መሃመድ አሳዛኝ ታሪክ ወደ ጎን ትተን በእስቷዝ ሃስን ታጁ ስም አዲስ አበባ ላይ ቀደም ሲል የተበተነውን ከፋፋይ የሆነ ባለ10 ገጽ ጽሁፍ ማስታወስ ከበቂም በላይ በቂ ማስረጃ ነው ።በእስቷዝ ሃስን ታጁ ጽሁፉ ላይ «ሰላማዊ ትግሉን የተቀላቀሉ ወጣቶች አላዋቂ፣ስሜተኛ፣ጃሂል አድርጎ ለማቅረብ ከተደረገው ጥረት ባሻገር የተቃውሞ አካሔድ ሌላ መንገድ ቢፈለግለት በሚል አሳፍሪ አቋም በተለይም የጁሙዓ ተቃውሞዎች መቋረጥ እንዳለባቸውና ኮሚቴዎቻችን ይቅርታ ጥይቀው እንዲወጡ » ህወሃት/.... ህዝበ ሙስሊሙን ተመስሎ በዑለማዎቻችን አንደበት ያሻውን መልዕክት በድፈረት ይስተላለፈበት ! ፈታኝ የትግል ዘመን የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው

ዛሬ ከዚህ አፍራሽ ተዕልኮ ባልተለየ የኢ.... ካድሬዎች አይናቸውን በጨው ታጥበው ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ሪያድ ከተማ ውስጥ ብዙሃኑ ተመስለው ሊያሰሙን በሞከሩት ጩኋት በአካባቢው ያሉትን ስመጥር የሃይማኖት አባቶችና እሩቅ ያሉትን የህዝበ ሙስሊሙን ነጻ ሚዲያዎች ቀልብ አሳስተው ለዚህ መስሪ ተግባራቸው ግበአት በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙ አንድንተ ላይ አደጋ ከመጋረጥ አልፈው በአቋራጭ የግል ኑሮቸውን ለማደርጀት ሲያደርጉ የነበረው ጥረት በሃገር ሽማግሌና በኃይማኖት አባቶች ውሻ በቀደድው ጅብ እንዳይገባ ሲነገራቸው የነበረውን ምከር አሻፈረን ብለው በህዝበ ሙስሊሙ ትግል ሽፋን ንጹሃን ለማደናገር ሞክረዋል። እንዚህ ወገኖች ጅዳ መካና መዲና ላይ እውነተኛ በሆኑ የትግሉ ባለቤቶች ሲተፉ እኔ ከሞትኩ ስርዶ አይበቀል እንዳለችው እንሰሳ ከፋፋዩን ዶሴያቸውን ሸንክፈው ሪያድ ከተማ ውስጥ በማድብት ጠንካራ ተብሎ በሚነገርለትን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት ለመፈታተን ያለሸረቡት ሴራ እንደሌለ ሰሞኑን በድምጽ ከተገኘ መረጃ ለማወቅ ተችሏል።በጣም የሚያሳዝነው በወቅቱ ለህዝብ  በቀረበው መረጃ የተደናገጡ ከጥቅማቸው ባሻገር የህዝበ ሙስሊሙ የትግል አንድነት ማየት የተሰናቸው እንዚህ ጀሌዎች ብዙሃኑን ተመስለው የሚያሰሙትን ጩህት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በማስተጋባት ከአይሌ እህቶቻችን ቦርሳ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በትግል ሽፋን ስለሚሰበስቡት በመቶሺ የሚቆጠር ገንዘብ አግባብ አለመሆኑ በነዚህ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ቢመከሩም አባታዊ ምክርን ሰምቶ ከመቀበል ይልቅ እንዚህን አባቶች ከመኮነን አልፈው ያልሆነ ስም በመስጠት እየፈጸሙ ያለውን ነወረኛ ተግባር በማድበስበስና ለህዝብ የቀረበውን መረጃ ከህቅ የራቀ አሰመስለው በማናፈስ « ውሻ በበላበት አፉ » እንዲሉ የህዝብ ሚዲያዎችን እስከ መዝለፍ ርቀው የሄዱበት ተግባራቸው ሰሞኑን ሪያድ በሚኖሩ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽምግሌዎች እርቃኑን መቅረት መቻሉ የጀሌዎቹን ማንነት ከመቸውም ግዜ በላይ ግልጽ አድርጎታል ዛሬ እነዚህ ጀሌዎች በፈጸሙት ነገር ሁሉ ተፀጽተው የበደሉትን ሁሉ በአደባባይ ይቀርታ በመጠየቅ ከጥፋታቸው ለመመለስ ቃል መግባታቸውን በደረሰን የድምጽ መረጃ አረጋግጠናል !
ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ

Thursday, August 20, 2015

ሰበር ዜና፡- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ

ፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የቆዩት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)፣ የሰማያዊና የአረና ፓርቲ አመራሮችና ሁለት ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ወሰነ፡፡
የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች በነፃ የተሰናበቱት፣ የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ ተሳትፎአቸውን ማረጋገጥ ባለመቻሉ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አስታውቋል፡፡
በውሳኔው መሠረት አቶ ሀብታሙ የሚጠየቁበት ወይም ሌላ የሚፈለጉበት ጉዳይ ከሌለ በዛሬው ዕለት እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺና አቶ የሺዋስ አሰፋ ከዚህ ቀደም ችሎት በመድፈር የተፈረደባቸውን ቅጣት እንዳጠናቀቁ እንዲፈቱ ወስኗል፡፡ ምንጭ ሳተናው ድህረገጽ 

እስራኤል ለስለላ የላከችው ዶልፊን በሃማስ ቁጥጥር ስር ውሏል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 14 ፣ 2007 ( ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነት የሻከረ እና መተማመን የጎደለው ነው።
በተለይ ደግሞ ከፍልስጤማውያን ጋር ዘወትር አተካሮ በመፍጠር ለበርካታ አመታት በግጭት የታጀበ ግንኙነታቸውን ዛሬም ድረስ ይዘውት ቆይተዋል።
ታዲያ የእስራኤል መንግስትም "ግዛቴንና ህዝቦቼን" ከጥቃት ለመከላከል በሚል ዘወትር የፍልስጤማውያንን እንቅስቃሴ በተለያዩ መንገዶች ይከታተላል።
ከሰሞኑ በጋዛ ሰርጥ በፍስጤማውያን የባህር ሃይል ኮማንዶዎች የተገኘውና በቁጥጥር ስር የዋለው ዶልፊን ግን ግርምትን ፈጥሯል።
ዶልፊኑ በባህር ክልሉ የፎቶ ካሜራ ተገጥሞለት በአካባቢው የእስራኤልን ባላንጣዎች እንቅስቃሴ ሲቀርጽና ሲሰልል ነበር ነው የተባለው።
ዶልፊኑ ባልተለመደ እና ቦታን ለማመልከት በሚመስል ሁኔታ በቦታው ላይ ብቅ ጥልቅ በማለት ያደረገው እንቅስቃሴ የባህር ላይ ቃኝዎችን ትኩረት በመሳቡ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተዘገበው።
ሰላዩ ዶልፊን በስፍራው ያለውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በተገጠሙለት ካሜራዎች እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በመቅዳት ለእስራኤሉ የስለላ ተቋም ሞሳድ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ይሰራ ነበርም ተብሏል።
ዋነኛ ተልዕኮውም በአካባቢው የሚካሄደውን የባህር ሃይል ስልጠና እና ተያያዥ ጉዳዮችን ቀርጾ መላክ እና መልዕክቶችን ማስተላለፍ እንደነበር ነው ከፍልስጤማውያኑ ጋዜጣ ል ቁድስ የተገኘ መረጃ የሚያሳየው።
የፍልስጤሙን ታጣቂ ቡድን ሃማስን ሰሞነኛ እንቅስቃሴ በመቅዳት እስራኤል በቡድኑ አንድ ክንፍ ላይ ልትወስድ ላሰበችው እርምጃ የሚያግዝ መረጃ ማቅረብን ታሳቢ አድርጎ የተካሄደ የስለላ ተግባር ነበር ተብሏል።
ሞሳድ በእንስሳት በሚደረጉ ስለላዎች በተደጋጋሚ ይጠረጠራል፤ ከዚህ ቀደም በግብጽ፣ በኢራን ፣ በቱርክ፣ በሱዳን እና በሌሎችም ሃገራት መሰል ስለላዎችን አካሂዷል በሚል ይታማል።
ድርጅቱ ለእስራኤል ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ በሚል በእርግቦች፣ በሽኮኮ፣ በሻርኮች እና ሽመላ በሚባሉ የአዕዋፍ ዝርያዎች ሃገራት ላይ በተላያዩ ጊዜያት ስለላውን አካሂዷል።
ምንጭ፤ www.thedailybeast.com

ተተርጉሞ የተጫነው፤ በምናለ ብርሃኑ