ድምጻችን ይሰማን ለሁለት በመስንጠቅ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመናድ ሀወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ እንቅልፍ አጥቶ ማደር የጀመረው ዛሬ እንዳልሆነ የታወቃል ።ህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የሃይማኖት ነጻነት ትግሉ በተጀመረ ማግስት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ዘብጥያ በማውረድ ለይስሙላ ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ መብት በመተላለፍ የህዝቦችን መብት በጠመንጃ አፈሙዝ ጨፍልቆ ለጸሎት አደባባይ የወጣውን አዛውንት ሴት ወጣት ሳይል ያገኘውን ሁሉ በደም በጨቀዩ ልዩ ኮማንዶዎቹ በጥየት ረሽኗል ፤ ከሞት የተረፈውን በቆመጥ ደብድቦ በክሚዎን በማጋዝ ወዳልታወቀ ስፍራ ወስዶ አስሮ በማሰቃየት ላይ ይገኛል። ታዲያ ይህን ሁሉ ግፍና ስቆቃ የተቀበለው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ሰላማዊ ተቃውሞውን የበለጠ በማጠናከር ሳይገድል እየሞተ ለአምባ ገነኖች የአላማ ጽናቱን በተግባር አሳይቷል በማሳየትም ላይ ይገኛል። ይህ የህዘበ ሙስሊሙ አንድነትና ለሃይማኖቱ ነጻነት ያለው ቁርጠኝነት እንቀልፍ የነሳው ሀወሃት መራሹ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት የበግ ልምድ ለብሶ ውሎና አድሩን ህዝበ ሙስሊሙ ጉያ ውስጥ በማድርግ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ዑለማዎች የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በኃይል አሊያም በግዜያዊ ጥቅም በማግባባት ለዚህ እርኩስ ሴጣናዊ ተግባሩ ማስፈፀሚያ ግበአት እንዲሆኑ ለማድረግ ሃገር ውስጥና በውጩ አለም እየዞረ ያልፈነቀለው ድንጋይ
ያልቦጠጠው ተራራ የለም። ለአብነት ያህል የፖለቲከኛውን ጁሃር መሃመድ አሳዛኝ ታሪክ ወደ ጎን ትተን በእስቷዝ ሃስን ታጁ ስም አዲስ አበባ ላይ ቀደም ሲል የተበተነውን ከፋፋይ የሆነ ባለ10 ገጽ ጽሁፍ ማስታወስ ከበቂም በላይ በቂ ማስረጃ ነው ።በእስቷዝ ሃስን ታጁ ጽሁፉ ላይ «ሰላማዊ ትግሉን የተቀላቀሉ ወጣቶች አላዋቂ፣ስሜተኛ፣ጃሂል አድርጎ ለማቅረብ ከተደረገው ጥረት ባሻገር የተቃውሞ አካሔድ ሌላ መንገድ ቢፈለግለት በሚል አሳፍሪ አቋም በተለይም የጁሙዓ ተቃውሞዎች መቋረጥ እንዳለባቸውና ኮሚቴዎቻችን ይቅርታ ጥይቀው እንዲወጡ » ህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ህዝበ ሙስሊሙን ተመስሎ በዑለማዎቻችን አንደበት ያሻውን መልዕክት በድፈረት ይስተላለፈበት ያ ! ፈታኝ የትግል ዘመን የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው ።
ዛሬ ከዚህ አፍራሽ ተዕልኮ ባልተለየ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች አይናቸውን በጨው ታጥበው ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ና ሪያድ ከተማ ውስጥ ብዙሃኑ ተመስለው ሊያሰሙን በሞከሩት ጩኋት በአካባቢው ያሉትን ስመጥር የሃይማኖት አባቶችና እሩቅ ያሉትን የህዝበ ሙስሊሙን ነጻ ሚዲያዎች ቀልብ አሳስተው ለዚህ መስሪ ተግባራቸው ግበአት በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙ አንድንተ ላይ አደጋ ከመጋረጥ አልፈው በአቋራጭ የግል ኑሮቸውን ለማደርጀት ሲያደርጉ የነበረው ጥረት በሃገር ሽማግሌና በኃይማኖት አባቶች ውሻ በቀደድው ጅብ እንዳይገባ ሲነገራቸው የነበረውን ምከር አሻፈረን ብለው በህዝበ ሙስሊሙ ትግል ሽፋን ንጹሃን ለማደናገር ሞክረዋል። እንዚህ ወገኖች ጅዳ መካና መዲና ላይ እውነተኛ በሆኑ የትግሉ ባለቤቶች ሲተፉ ፤ እኔ ከሞትኩ ስርዶ አይበቀል እንዳለችው እንሰሳ ከፋፋዩን ዶሴያቸውን ሸንክፈው ሪያድ ከተማ ውስጥ በማድብት ጠንካራ ተብሎ በሚነገርለትን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት ለመፈታተን ያለሸረቡት ሴራ እንደሌለ ሰሞኑን በድምጽ ከተገኘ መረጃ ለማወቅ ተችሏል።በጣም የሚያሳዝነው በወቅቱ ለህዝብ በቀረበው
መረጃ የተደናገጡ ከጥቅማቸው
ባሻገር የህዝበ ሙስሊሙ የትግል አንድነት ማየት የተሰናቸው እንዚህ ጀሌዎች ብዙሃኑን ተመስለው የሚያሰሙትን ጩህት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በማስተጋባት ከአይሌ እህቶቻችን ቦርሳ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በትግል ሽፋን ስለሚሰበስቡት በመቶሺ የሚቆጠር ገንዘብ አግባብ አለመሆኑ በነዚህ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ቢመከሩም አባታዊ ምክርን ሰምቶ ከመቀበል ይልቅ እንዚህን አባቶች ከመኮነን አልፈው ያልሆነ ስም በመስጠት እየፈጸሙ ያለውን ነወረኛ ተግባር በማድበስበስና ለህዝብ የቀረበውን መረጃ ከህቅ የራቀ አሰመስለው በማናፈስ « ውሻ በበላበት አፉ » እንዲሉ የህዝብ ሚዲያዎችን እስከ መዝለፍ ርቀው የሄዱበት ተግባራቸው ሰሞኑን ሪያድ በሚኖሩ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽምግሌዎች እርቃኑን መቅረት መቻሉ የጀሌዎቹን ማንነት ከመቸውም ግዜ በላይ ግልጽ አድርጎታል ። ዛሬ እነዚህ ጀሌዎች በፈጸሙት ነገር ሁሉ ተፀጽተው የበደሉትን ሁሉ በአደባባይ ይቀርታ በመጠየቅ ከጥፋታቸው ለመመለስ ቃል መግባታቸውን በደረሰን የድምጽ መረጃ አረጋግጠናል ፤ !
ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ
No comments:
Post a Comment