ሰበር ዜና ሪያድ መንፉሃ ውስጥ፡ ማምሻውን ውጥረት ነግሷል ! በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ኢትዮጵያውያኑ እጃቸውን በሰላም እንዲሰጡ ወረቀት በትኗል!
DECEMBER 25, 2013
ዛሬ በኢትዮጵያ ሰዓት አቋጣጠር ከቀትር 6 ሰዓት ጀምሮ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራው የሃበሾች መንደር ከ 15 ሺህ በሚበልጡ ቆመጥ፡ እና አሜሪካ ሰራሽ ኦዚ በታጠቁ የሳውዲ ኮማንዶዎች መከበቡን የሚናገሩ የአካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች ብዛት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መታፈሳቸውን ይገልጻሉ ፡፤ በአካባቢው ውጥረት መስፈኑንን የሚገልጹ የአይን ምስክሮች ማንኛውም ሰው ወደተጠቀሰው መንደር መግባት እንጂ መወጣት እንዳማይችል ይገልጻሉ።
ይህን ተከትሎ ማምሻውን አያሌ ኢትዮጵያውያን ቀደም ሲል የተፈጸመው አይነት ጭፍጨፋ ይፈጸምብን ይሆን የሚል ስጋት ውስጥ እንደሆኑ የሚናገሩ ምንጮች ዛሬ አመሻሹ ላይ መንፉሃ ዳግም ወደ ጦር ቀጠናነት መለወጡ ያስደነገጣቸው የሃበሻ ሱቆች እና ምግቤቶች በግዜ ለመዝጋት መገደዳቸውን ተከትሎ ኢትዮጵያዊያኑን ነዋሪ ለበለጠ ጭንቀት እንደዳረጋቸው ይናገራሉ። የፀጥታ እስከባሪዎቹ ማመዘኛ ህጋዊ መሆን ያለመሆን ነው የሚሉ ምንጮች የሌላ ሃገር ዜጎች መንፉሃ ውስጥ፡በነጻነት ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውን ጠቅሰው በኢትዮጵያውያኑ ላይ ያነጣጠረው ይህ ሁለተኛ ዙር የሳውዲ መንግስት እርምጃ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸውንም ጭምር ፈቃዶቻቸውን እይቀደዱ ከሃገር ለማባረር እቀድ መኖሩን ማሳያ ነው ብለዋል ።


በኢንባሲው ህግወጥ ትብለው የተፈረጁት ኢትዮጵያውያን ጥያቂያቻቸውን በማጠናከር
1/ነፃ የሙያ ቅየራ /profishinal change/ ይፈቀድልን ።
2/ የመኖሪያ ፈቃዶቻችንን ከግለሰብ ወደ ተለያዩ መ/ቤቶች እንድናደርግ ይፈቅድልን ።
3/ ያለ ምክንያት ሚደረግ የመኖሪያ ፈቃድ በላግ ይቁምልን ።
4/ፖሊሲ ባልተፈፀመ ወንጀል ይዞ ማሰር ያቁምልን ።
5/ለዕድሳት የሚሰጡ የመኖሪያ ፈቃዶቻችን በጊዜ ታድሰው ይመለሱልን ።
ይህ ሁሉ የማይቻል ከሆነ መኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን የተከበረው ኤምባሲ መሉ የኢቃማ ወጪያችውን ከነ ሞራል ካሳ የሳውዲ መንግስትን ጠይቆ በሰላማዊ መንገድ ወደ ሐገራቸው የሚመለሱበትን ሆነታ ሊያመቻችላቸው ይገባል የሚሉ ወገኖች የመኖሪያ ቤቶቻቸውን ካርታ አሲዘው አሊያም ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶቻቸውን ሸጠው ሳውዲ አረቢያ ሰርቼ እለወጣለሁ በሚል ተስፋ ከ 1 መቶ ሺህ እስከ 2 መቶ ሺህ ብር አውጥተው የገዙትን መኖሪያ ፈቃዶቻቸውን ሰርዘው ሃገር እንዲገቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ እያሰማ ያለው ጩኽት ወገናዊነት የጎደለው በመሆኑ በኢትዮጵያውያኑ ዘንድ ከፍተኛ ተቋውሞ መቀስቀሱን አክለው ገልጸዋል።
በዚህ ዙሪያ በሪያድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት እንደሆኑ የሚነገርላቸውን የአንባስደሩን አማካሪ ዲፕሎማት አቶ ዘላለም እና አንባሳደር መሃመድ ሃሰንን ለማነጋገር ያደረኩት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም !
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ
posted by Aseged Tamene
No comments:
Post a Comment