በባህር ዳር ከተማ ቀበሌ 13 ሜትሮሎጂ ጀርባ በተለምዶ ዝንጀሮ ወንዝ በሚባለው አካባቢ የከተማው አስተዳደር የመኖሪያ ቤቶችን በግሬደር ማፍረሱን ተከትሎ በአካባቢው ነዋሪዎችና በታጣቂዎች መካከል በተነሳ ግጭት ሁለት ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ የፍኖተ ነጻነት ምንጮች ከሶስት በላት ሰዎች መሞታቸውን የአይን ምስክሮችን ጠቅሰው ዘግበዋል፡፡ ከስፍራው የደረሰን መረጃ እንደሚያመላክተው ግጭቱ እየተባባሰ የመጣ ሲሆን ተኩሱ አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡ ዘግይቶ ከባህርዳር የደረሰን ዜና እንደሚያስረዳው ከሆነ በአካባቢው መንግስት ክላሽን ኮቭ ቦንብ እና ክላሽ የታጠቁ የፌደራል ሰራዊት እና መትረየስ የተጠመደባቸው ጆፕ ተሽከርካሪዎች ወደ አካቢው በማቅናት ላይ ናቸው ። See more at: http://www.fnotenetsanet.com/
No comments:
Post a Comment