ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ሚያዚያ 25 / 2007 ምሸት የክርስትና የእስልምና እምንት ተከታይ የሃይማኖት አባቶች ጨምሮ መላው የሪያድ ነዋሪዎች በተገኙበት የሃዘን መግለጫ ላይ እራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራው አሸባሪ ቡደን በንጹሃን ዜጎቻችን ላይ የፈፀመውን አረመኔያዊ ድርጊት አውግዘዋል ። አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊ ዎች እራሱን አይ ኤስ አይ ኤስ እያለ የሚጠራው አረመኔ ቡደን እንጀራ ፍለጋ ከሃገር በስተሰደዱ ንጹሃን የክርስትና እምናት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ የወሰደው ዘግናኝ እርምጃ ቡዱኑ የለየለት አረመኔና የትኛውንም ሃይማኖት የማይወክል የዘመናችን ጭራቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፤አንድ የእስልምና ሃይማኖት መሪ « ኢማም » በበኩላቸው ሲናገሩ ኢስላም ማለት ሰላም ማለት መሆኑን ገለጸው ሶሪያና ኤራቅን ጨምሮ በስሜን አፍሪካ እንደሚነቀሳቀስ የሚነገርለት ይህ የጨካኞች ቡደን በስሜት የሚነዱ ሃይማኖታዊ መስረተም ሆነ ግንዛቤ የሌላቸው አለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኖች
ስብስብ መሆኑን ተናግረዋል። ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ አለማችንን በኃይማኖት ሽፋን በሽብር በማተራመስ ምድራችንን በንጹሃን ደም ለማጨቅየት ቡድኑ ያለውን አኩይ ፍላጎት የሚያመላክት ለመሆኑ እጀራ ፍለጋ ሲከራተቱ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመው ሴጣናዊ ተግባር አብነት ነው ብለዋል ። በንጹሃን ደም የጨቀየው አይ ኤስ አይ ኤስ በ 30 ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው እርምጃ ሃዘናቸው መሪር መሆኑን የገለጹ በስልክ ያነጋገርኳቸው አንድ የስብሰባው ተካፋይ አባወራ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ሊቢያ ላይ የተቀሉት ወገኖቻችን አሞሞት በጭካኔው ወደር የማይገኝለት በዓለም ህዝብ ፊት በአደባባይ የተፈጸመ በመሆኑ በስደት ዓለም በወገኖቻችን ላይ እይደረሰባቸው ካለው ሁሉ ለየት ያለ በመሆኑ ህዘናችንን መሪር ቢያደርገውም በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ቀደም ሲል ህጋዊ በሆነ መንገድ በኮንተራት የመጡ ኢትዮጵያውያን እህቶች አስክሬን ኮሚኒቲው ከማስተናገዱም በላይ በሳውዲ አረቢያ የተለያዩ ግዛቶች ተበትነው የሚገኙ በ አስርሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአሰሪዎቻቸው ከሚፈጸምባቸው ግፍና በደል እራስቸውን ለመታደግ እግር ወዳመራቸው ሲያቀኑ ህይወታቸውን አጥተው ያለቀባሪና መርዶ ነጋሪ በሳውዲ ሆስፒታሎች ተቆልሎ የሚገኘውን የዜጎቻችንን በድን ቤት የቁጠረው ብለዋል ። እኚህ አባት በማስከተል የሞቱበት ምንክንያት በወል ሳይታወቅና ለቤተሰብ መርዶ ሳይነገር ስረዓተ ቀብራቸው የተፈጸመውን ወገኖቻችንን አሁን ማንሳት በሃዘን ላይ ሃዘን ከማስተናገድ ባሻገር ትርጉም የለውም በሚል ምሬታቸውን በለቅሶ ገልጸዋል።
በሪያድና በጅዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እራሱን አይ ኤስ አይ ኤስ እያለ በሚጠራው አረመኔ ቡድን በታረዱ ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የተሰማቸውን ሃዘን ለመግለጽ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን መንግስት ለዜጎች ጥበቃ አለማድረጉን በጽኑ ኮንነዋል። በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲና በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በዜጎቻችን ላይ የደረሰውን አስደጋጭ ዜና ምክንያት በማድረግ የሃዘን መግለጫው ላይ የተሳተፉት ዲፕሎማቶች ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ትዕይንት ከማስቆም ይለቅ ነገሩን በማድበስበስ ከሃላፊነት ለማምለጥ የሚጥሩ በመሆናቸው አብዛኛው ህብረተሰብ በነዚህ የመንግስት ሹማምንቶች ላይ ያለው እምነት መሞጠጡ ይነገራል፡፤ አንድ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ከሚታተም ጋዜጣ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉ በሪያድ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማት ሪያድና ጣይፍ ከተማ ውስጥ ህይወት አጥፍተዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው አንገታቸው በአደባባይ በስይፍ ስለተቆረጠው ኢትዮጵያውያን የኮንተራት ሰራተኞች ኤንባሲው አንደ ማንኛውም ሰው ዜናውን በሳውዲ ሚድያዎች ከመስማት ባሻገር ምንም አይነት መረጃ እንዳልነበረው መግለጻቸው አይዘነጋም ፡፤ይህን ተከትሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ አንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ሃላፊነታቸውን በብቃት አልተወጡ በሚል የስራ ግዜያቸውን ሳይጨርሱ ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ሃገር መመለሳቸው ይታወቃል።
ይህ በዚህ እንዳለ በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤትና በሪያድ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ሰንደቅ ዓላማዎች ዝቅ ብለው እንዲውለበለቡ ከመደረጉም በላይ ከ 5000 የሚበልጡ የሁለቱም ት/ቤት ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ተማሪዎች አይ ኤስ አይ ኤስ ብሎ እራሱን በሚጠራው አሸባሪ ቡደን በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመውን አረምኔያዊ ድርጊት በማውገዝ በዚህ ግፈኛና አረመኔ ቡደን አንገታቸው ለተቀላው ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች ጸሎት በማድረስ የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere Jed Bewadi
No comments:
Post a Comment