Saturday, August 8, 2015

ሰበር ዜና ሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፀረ ወያኔ /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ተቃውሞ ስትናጥ አደረች !

ሰሞኑን የህወሃት/.... /ቤት በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደውን ኢፍተሃዊ ውስኔ በመቃወም ሪያድ ከተማ ውስጥ ትላንት አርብ ኦገስት 7 2015 ምሸት ኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ተቃውሞውን አሰምቷል ቁጥሩ ከፍተኛ እንደሆነ ህዝብ የተገኘበት  ይህ ታላቅ ተቃውሞ የአካባቢውን ድባብ ለውጦት እንደ ነበር ለማወቅ ተችሏል። የተከሰተው ነገር በራሳችን እንደደረሰ ተሰምቶን በሶስት ቀን ውስጥ በተጠራ የተቃውሞ ጥሪ ይህን ያህል ህዝብ አንድነቱን ጥብቆ ለተቃውሞ በነቂስ መውጣቱ የትግሉ አንዱነት ጥንካሬ መገለጫ መሆኑን የገለጹት ሼክ ሲዒድ አህመድ ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ከባድ ፈተና እንደ ተጋረጠበት አውስተው ይህ ፈተና አዲስ ሆኖብን ሳንደናገጥ ትግሉን በበሰለና በስለጠነ መንገድ በማጠናከር እስከ ድል መቀጠል እንደሚገባ በቁጣ የወጣውን ህዝብ ሙስሊም በማረጋጋት በአባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል
ሼክ ሰዒድ በማስከተል አቡበከር በአንድ ወቅት በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ወህኒቤት ግፍ እይተፈፀመበት  « /ቤቱም የኛ ፖሊሱም የኛ አቅቤ ህጉም የኛ መርማሪውም የኛ ስለሆነ የፈለከውን የመከላከያ ምስከር ብታመጣ ብትወጣ ብትወርድ ከፍርድ አታመልጥም እኛ ነን የምንፈርድብህ » ተብሎ በስረአቱ ካድሬዎች በምጸት ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት ተነግሮት የነበረውን በተግባር ማየቱን ሼኩ ለተስብሳቢው በመጥቀስ በመሪዎቻችን ላይ የተፈፀመው ደባ ሊያስደንቀን እንደማይገባ ገልጸው የፍ/ቤቱን ኢፍታሀዊነት ለተሰብሳቢው በተጨባጭ  አስረድተዋል። በውቅቱ በቁጣ ገንፍሎ የወጣውን ህዝብ ለማስተናገድ ተይዞ የነበረው ቦታ በመጨናንቁ የነበረውን የሪያድ የአየር ሙቀት በመቋቋም ምሽቱ 1 ስዓት ጀምሮ እስከ ሊሊቱ 9 ስዓት ድረስ በዘለቀው በዚህ  ፀረ ጭቆና ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች  ህዝበ ሙስሊሙን በገዛ ሃገሩ መቆሚያ መቀመጫ ያሳጣውን የህወሃት/.... ስረዓት እንዲያጠፋላቸው እያለቀሱ  ለፈጣሪያቸው  ፀሎት  «  ዱአ » አድርሰዋል                                        የህወሃት/.... መንግስት /ቤት በህዝበ ሙስሊም ተወካዮች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ሰረዓቱ በመላ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ላይ እየፈጸመ ያለው ሃይማኖታዊ ጭቆና ግፍና በድል አንዱ አካል መሆኑን የገለጹት እንዚህ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከእንግዲህ ትዕግስታቸው መሞጠጡን ጠቅሰው  በዚህ አምባ ገነን ስረዓት ላይ የጀመሩትን ትግል እስከ መጨረሻ አጠናክረው ለመቀጠል በመወሰን የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።                                                                                                     በሳውዲ አረቢያ ድምጻችን ይሰማ ደጋፊዎች እያካሄዱ ባለው ሃይማኖታዊ ፀረ ጭቆና ትግል የህወሃትን/....ግን ስረዓት የቦንድ ሽያጭና መስል የስረአቱን እንቅስቃሴ በማሽመድመድ  የታወቁ  ግንባር ቀደምና ጠንካራ መሆናቸው  ይነገራል። «ማሳሰቢያ ሊንኩን ተጭነው ያድምጡ  ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ

No comments:

Post a Comment