Friday, January 23, 2015

በስዊድን የኢትዮጵያ አምባሳደር በተቃዎሟቸው ኢትዮጰያውያን ላይ የመሰረቱትን ክስ የስዊድን ፖሊስ ውድቅ አደረገው።

ቀደም ሲል የኢህአዴግ መንግስት ፤ በስዊድን-ስቶኮሆልም  አዘጋጅቶት የነበረው የቦንድ ሽያጭ ዝግጅት ላይ ኢትዮጰያውያን ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸው ይታወቃል።

<<ከአባይ በፊት ዘረኝነት ይገደብ>> በሚል መርህ ተቃውሞውን ያደረጉት ኢትዮጰያውያን፤  ዜጎች ያለፍርድ እየታሰሩና እየተገደሉ ባለበት ሁኔታ  ገንዘብ ለመሰብሰብ መሯሯጥ፤ በሀገርና በህዝብ ላይ መቀለድ እንደሆነ በመናገር  ነበር- ተቃውሟቸውን  ጫማና እንቁላል በመወርወር የገለጹት።
ኢትዮጰያውያኑ -አምባሳደሯን መኪና ላይ የ እንቁላል መዓት በመወርወር ተቃውሟቸውን ሲገልጹ፤አምባሳደር ወይንሽት ከመኪናቸው መውጣት ተስኗቸው ተስተውለዋል። በኦትዮጰያውያኑ ጫማና እንቁላል የተወረወረባቸው በስዊድን የኢትዮጰያ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ፤ <<ስራዬን መስራት እስከማልችል ድረስ በደል ደርሶብኛል>> በማለት  ለስዊድን ፖሊስ ክስ ይመሰርታሉ።
የአምባሰደሯን ክስ ተከትሎ የስዊድን ፖሊስ  ባቀረበላቸው ጥሪ መሰረት ቃል ለመስጠት የሄዱት የኢትዮ-ስዊድን ግብረ-ሀይል አስተባባሪ አክቲቪስት መቅደስ ወርቁ እና የኢትዮጰያ ዲሞክራቲክ መድረክ ምክትል ሊቀ-መንበር አቶ ሞላ፤ ኢትዮጰያ ውስጥ ስላለው የመብት ረገጣና በስፋት ለስዊድን ፖሊስ በማብራራት፤ ተቃውሞው የተደረገው የሰብዓዊ መብት ጥሰትን፣ዘረኝነትን እና ሙስናን ለመቃወም እንደሆነ አስረድተዋል።
ጉዳዩን የተመለከተው የስዊድን ፖሊስም በስዊድን ህግ መሰረት የዚህ ዓይነት ተቃውሞ ማድረግ መብት እንጂ ወንጀል እንዳልሆነ በመጥቀስ እና ክሱ ውደ ፍርድ ቤት የሚያመራበት አንዳችም የህግ ምክንያት እንደሌለ በማብራራት የአምባሰደሯን ክስ ውድቅ እንዳደረገው አክቲቪስት መቅደስ ተናግረዋል። የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ከወራት በፊት በዋሽንግተን ዲሲ የልብስ መደብር ውስጥተቃውሞ ባቀረቡባቸው አክቲቪስቶች ላይ የመሰረቱት ክስ ሰሞኑን በአሜሪካ ፍርድ ቤት ውድቅ መደረጉ ይታወቃል።

Tuesday, January 20, 2015

የማለዳ ወግ... አርቲስት ሜሮንና አስቴር ተናገሩ ፣ እኛስ ! ነብዩ ሲራክ

የማለዳ ወግ... አርቲስት ሜሮንና አስቴር ተናገሩ ፣ እኛስ ! 
* በስደት የግፉአኑን መከራ ለመቅረፍ ምን እየሰራን ነው ?
* የውዴታ ግዴታ የለብንምን?

ሜሮንና አስቴር ...
ያን ሰሞን አርቲስት ሜሮን ጌትነት " አትሂድ " ባለችው የተዋጣለት ግጥሟ ታሸበሽብ ታረግድለት የነበረውን የኢህአዴግ አመራርና ስርአቱን በሰላ ብዕሯ መሸነቋቆጧ ከጫፍ እስከ ጫፍ የሃበሻ መነጋገሪያ ሆኖ ከርሟል ። የሜሮን ፋና ወጊ ፣ በጥበብ የተከሸነ ፣ ነፍስ አሽር ግጥም በድምጽ ብቻ ሲሰራጭ ገዥውን ፖርቲ የመከላከያ ሰራዊት መለዮ ከነኮፊያው ሳይቀር እየደነቀረች የተለያዩ ወቅታዊ ደጋፊ ዝግጅቶችን ስታቀርብ የምናውቃት አርቲስት ሜርን ጌትነት ድምጽ መሆኑን ለማመን ቸግሮንም ነበር ። ብዙም ሳይቆይ ግን ዛሬ በእሳት ዶግ አመድ በሆነው የጣይቱ ሆቴል ጥበብ ይዘንብበት በነበረው የጃዝ አንባ ዳራሽ መድረክ ላይ ግጥሙን ስታነብ የተቀረጸችው ፍንትው ያለ መረጃ ቀረበ ።

"ጉድ " አልን ... " እውነት ሜሮን ናትን " ስንል አይሆን መስሎን የተጠራጠርነው ገሃድ ሆኖ እውነቱ ተገለጠ ፣ ጥበቧን የወደዱላት " ጥበብ የህዝብ ስሜት ጉዳት ሲገልጥበት እንዲህ ነው ፣ አበጀሽ ሜሮናችን " በሚል የቆየ ብሽቀታቸውን ትተው የአድናቆት ፍቅር ስሜት ቀየሩት ፣ በቅኔ በውዳሴም በክብር " ሜሮን ሜሮን " እያሉ ከፍ ከፍ አደረጓት ! ሜሮን ጨክና ትደግፈው ይደግፉት የነበረውን የኢህአዴግ መንግስት ቅኔ ዘርፋ መሸንቆጧን ያልወደዱላት ምላሽ ቅኔ ሳይቀር ተቀኘን ብለው ትንታጓን ሜሮንን የስድብ ውርጅብኝ አወረዱባት ! " ይህች ደግሞ ምን ጎደለብኝ ብላ ነው? " ሲሉ የህዝብ ህመም ፣ የህዝብ ሮሮና ዋይታን የህዝብ ልጆች ጥበበኞች የመግለጽ ሃላፊነት እንዳለባቸው እያወቁት እንዳላቀቁ ሆነው ዘለፏት ፣ ተሳለቁባት !
የጥበብ ሰዎች እንደ ሃገሬው በከፋው የእኛ ፖለቲካ ዘባተሎ እየተገፉ " ሃብታችን የህዝብ ፍቅር ነው! " እንዳላሉ መሸነጋገላቸው አስተዛዛቢ ሆኖ መንጎድ ያዘ ፣ ህዝብና ጥበብ በፖለቲካ ቅኝት ተለያዩ ! አርቲስቱ ትዝብት ላይ ወደቁ ... ይለይለት ያላ የሚመስለው መንግስት ያን ሰሞን ህወሃት ኢህአዴግ ያለፈበትን የትግል ጉዞውን ያዩለት ዘንድ አርቲስት የጥበብ ሰዎችን ወደ ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የትጥቅ ትግል መጠንሰሻ ወደ ደደቢት ሲወስዳቸው ነገሩ ሁሉ ግልጥልጥ ማለት ያዘ !
በጉዞው ጉብኝቱ ስለሆነው ሁሉ አናወጋም ...በዚያው በጉብኝቱ በተደረገው ውይይት የተነሱ በርካታ ውይይቶች አንዱ ግን እናነሳለን ! ቀልብ ሳቢ ከነበሩት ውይይቶች መካከል የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች በተካፈሉበት አንድ ውይይት የሰላ ጥያቄ ለመከላከያ የበላይ ለጀኔራል ሳሞራ የኑስ የሰላ ጥያቄ ያቀረበችውን የአስቴር በዳኔ ጥያቄ ይጠቀሳል ፣ በእርግጥም የአስቴር በደኔ ጥያቄ ፍጹም ይሆንል ያልተናል ፣ ያልተጠበቀና ያልታሰበ ነበር ፣ የአስቴር ይህን ሁሉ አመት አውራ ሁናችሁ መግፋታችሁ ያዋጣ ይሆን የሚል አንድምታ ያለው ምክር የተቀላቀለበት ጥያቄ ለጀኔራል ሳሞራ ቀርቦ ምላሽ የተባለው ምልሽ ተሰጠው ...
እናም የአስቴር ጉዳይ ፣ የአስቴርን እያንሾካሾከ ከራሱ ጋር የሚፋተገው የእኔ ቢጤ ፈሪ ጥያቄው የእሱ ጭምር ሆኖ እያለ የህዝብ ልጇ የብርቱዋ አርቱስት አስቴር በዳኔ ጥያቄ እያለ እንደ ሜሮን ሾተላይ ግጥም እየተቀባበለ መመልከቱ እውነት ነው ፣ በእርግጥም ጥያቄው የብዙሃን ጥያቄ ነበርና የአርቲስት አስቴር በዳኔ ጥያቄና መልስ የያዘው ተንቀሳቃሽ ምስል የተደገፈ መረጃ እንደ ሜሮን ግጥም ከጫፍ እስከ ጫፍ በሰፊው ተናኘ !
እኛስ እንደ ዜጋ !
ከሜሮን ሰሞነኛ መነጋገሪያ ግጥም ለጥቆ አርቲስት አስቴር በዳኔ ለኢህአዴግ መንግስት ቁንጮ ባለስ ልጣናት ያቀረበችው ጥያቄ እንደ ሜሮን ሁሉ በድጋፍና በጥላ ቻ የታጀበ ነበር ። እኔ የምለው እኛስ የት ነው ያለነው ነው? ይህን ብየ የማጠይቀው ! መልስም አለኝ !
አዎ አርቲስት አስቴርና አርቲስት ሜሮን ያሻቸው የፈቀዱትን ተናግረዋል ፣ በቃ ! ሁለቱም እህቶች ስሜታቸውና ማስተላፍ ያለባቸው መልዕክት ያመኑበትን ሲሆን በአደባባይ ነው የተናገሩት ! እኛ ግን እነሱ ያመኑበትን ለመቀበል ምክንያቱ ግልጽ ሆኖ እያለ አግድመን እየተራኮትን ያለነው ! አርቲስቶች ባነሱት በብዙሃን የሃገሬ ሰው ውስጥ የሚንቀለቀል መሰረታዊ እውነትና ጥያቄ ውስጥ ራሳችን ማየት ተስኖናል ። እንደ ዜጋ በከባቢያችን ከእኛ የሚገባውን ጥቂቱን ሃላፊነት ሳንወጣ ማግለል ፣ ማንቋሸሽ ፣ ማጥላላትና መኮፈስን ለምደነዋል ! ግን ለምን ? አልልም ! እስከ መቸ እንዲህ ሁነን እንቀጥላለን ? ግን እላለሁ !
የሃገር ቤቱ ፖለቲካ እሳት ሆኖ ይፋጃል ቢባል ፣ በአረቡ አለም በስደት የሚገኙ እህቶቻችን መከራ እንዲያቆም በስደት ያለን የተሻለ ኑሮ የምንገፋው እንደ ዜጋ ለግፉአኑ የቻልነውን ማድረግ የሞራል ግዴታ እያለብን ለማድረግ ፈቃደኞች አይደለንም ! መከራና ሰቆቃው ከቀን ወደ ቀን እየከፋ መጥቷል ፣ የመንግስት ሹማምንት ከሞቀው ወንበራቸው ተነስተው ለተጎጅ ወገኖቻቸው እንዲተጎ እንኳ የሰላ ሂስ ሰንዝረን ቀርቶ ተሽቆጥቁጠን በየበአላቱ ስናጅባቸው ለተገፊው ወገን እንዲደርሱለት አንመክራቸውም ! በስደት የግፉአኑን መከራ ለመቅረፍ ምን እየሰራን ነው ? የውዴታ ግዴታ የለብንምን ?
አንዳንዶቹም ሹሞቻቸን ከማስተማር ከምመከር ወጥተን ጥሩ ነገር እንደሰሩ እናሞካሻቸዋለን ፣ የሰላ ሂስ የምናቀር በውን " የግንቦት 7 ፣ የኦነግ ፣ የአረናና የማንቴስ ተቃዋሚ አባላት " እያልን ለጥቅም ማግበስበሱ እኩይ ምግባር መትጋት ይቀናናል ፣ አድርባይ አጎብዳጅነቱን ትተንና ላንመለስበት ንስሃ ገብተን ፣ መቸ ይሆን ወደ ትክክለኛው መንገድ የምንጓዘው? መቸ ነው ለፖለቲካ ወገንተኛነትን ፈንግለን ለወገናችን መከራ መቆም ፣ ለሰብዕና ብለን እውነትን የምንከተለው ?
ከሰብአዊ ሰው በወጣ የአድርባይነት ካባ ደርበን የሚ ገፋውን ህይዎታችሁን መታዘብ ዘልቆ ያማል ! እንደ አርቲስት ሜሮን እውነትን ሸፋፍነን ብንከርምም ቀኑ ሲደርስ ፣ ውስጥ አልቀበል ሲል ለእውነት መስዋዕት ለመሆን የምንተጋበት ውበትን እውነት ብለን የምንገልጥበት ቀን ናፍቆኛል ። እንደ አርቲስት አስቴር ደፍረን የህዝብ የወገናችን "የህሊና ድምጽ " መሆኑ ቢሳነን ፣ የሚፈሩትን ሹሞች ሳንፈራ በግምባር የምናጠይቅበት ስለ እውነት የምናፈጥበት ሞራል ባይኖረን ... እንደ አቅማችን ፣ እንደ ራሳችን ፣ እንደ ቤታችም ፣ እንደ ጉዳታችን ሆነን የግፉአን ስደተኛ እህቶ ቻችን መከራ እንዲያቆም የምተጋበት ቀን ናፍቆኛል ! እውነቱን በገሃድ መገላለጥ ፣ ለየቸገረው ስደተኛ እርዳታን ድጋፍ የማድረጉ ሃላፊነት ከማናችንም የሚጠበቅ የውዴታ ግዴታ መሆኑን ልብ ልንለው ይገባል ! ያ ሲሆን ማየት ደግሞ በጣሙን ናፍቆኛል !
እስኪ ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ 
ጥር 12 ቀን 2007 ዓም

Friday, January 16, 2015

ለኢቦላ መከላከል የዘመቱት የበሽታው ተጠቂ ሆነው እየተመለሱ ነው:;



በምእራብ አፍሪካ የተነሳው የኢቦላ ቫይረስ ለመቆጣጠር በሚደረገው ጥረት ውስጥ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የተላኩት የጤና ባለሙያዎች የኢቦላ በሽታ ተጠቂ እየሆኑ መመለስ መጀመራቸው የጤና ጥበቃ እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ምንጮች ገለጹ:;
በዚሁ መሰረት በበሽታው ተይዘዋል ተብለው ከገቡት ውስጥ አንዱ መሞቱ ሲረጋገጥ ቤተሰቡ ከአከባቢው እንዳይንቀሳቀስ በማድረግ ናሙናዎች ተወስደው ወደ አሜሪካን ላቦራቶሪ በመላክ ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል::በሃገር ቤት ያሉ ሃኪሞች የጭንቅላት ወባ ነው ቢሉም ሕዝቡ ግን የጭንቅላት ወባ ከሆነ ሬሳ ምደባበቅ እና ቤተሰቡን ማገት ለምን አስፈለገ ሲል እየጠየቀ ይገኛል:: minilik salsawi 

Thursday, January 15, 2015

ሰበር ዜና ሳውዲ አረቢያ ሪያድ ከተማ በሄር ግጭት ታመስች ! በግጭቱ ሁለት ኢትዮጵያውያን በጩቤ ተወግተው ሲሞቱ 4 ቆስለዋል።


ሰሞኑንን በሪያድ ከተማ ልዩ ስሙ መንፉሃ እይተባለ የሚጠራ አካባቢ በኢትዮጵያውያን መሃከል በተቀሰቀሰ የእርስ በእስር ግጨት ህይወት መጥፋቱን ምንጮች ገለጹ። ግጭቱ ካገረሽ ወዲህ በተለይ የዛሬ ሳምንት አርብ ምሽት በተጠቀሰው አካባቢ ከ 10 የሚበልጡ ሳንጃ የታጠቁ ኢትዮጵያውያን «ሻራ ኢሽሪን » እየተባለ በሚጠራ መንገድ ዳር ወደ ሚገኝ የቴለፎን ማስደወያ «ካቢኔ» በማቅናት ላይ በነበሩ 4 ባላጣዎቻቸው ላይ አድፍጠው ጥቃት ለመፈጸም ባደረጉት ሙከራ በተከስተ ትንቅንቅ በአካባቢው በተነሳ ሁከት አንድ እድሜው በ 30 ዎቹ የሚገመት ወጣት አንገቱ ላይ በሳንጃ ተወግቶ ወዲያ ሲሞት ሆዱ ላይ የተወጋ ኢትዮጵያዊ ወጣት ነፍሱን ለማዳን በተደረገ ርብረብ ወጣቱ በክፉኛ ሁኔታ ተጎድቶ ስለነበር ሆስፒታል እንደደረሰ ህይወቱ ማለፉን ለማወቅ ትችሏል። 

ይህ በዚህ እንዳለ አካባቢው ፈጥነው በደረሱ የሳውዲ ፖሊሶች ቁጥጥር ስር የዋሉ በእርስ በእርስ ግጨቱ የተሳታፊ 4 ኢትዮጵያውያን በሰውነታቸው ላይ ከደረሰው መለስተኛ ጉዳት አገግመው በአሁኑ ሰዓት ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ ። በኢትዮጵያኑ መሃከል በሚከስት ግጨት በደም የተጨማለቀ በጠራራ ፀሃይ በሳንጃ አንጀቱ የተዘረገፈ ሬሳ መንፉሃ ውስጥ ማየት የተለመደ መሆኑን የሚገልጹ የአይን እማኞች የዛሬ አመት የሳውዲ ጸጥታ ሃይሎች በኢትዮጵያኑ ላይ በወሰዱት እርምጃ በጉሩፕ ይከስት የነበረ የዕለት ተዕለት ዘግናኝ ትእይንት ለወራት ጋብ ብሎ ቢቆይም ሰሞኑንን በአዲስ መልክ በማገርሸቱ የአካባቢውን ነዋሪ ክፉኛ አስደንግጦል ብለዋል። 
በሳውዲ አረቢያ በኢትዮጵያውያን መሃክል በሚከስት ግጨት ህይወቱ የሚያልፈውን ወገን ለማታደግ የአካባቢው የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች በሪያድ ከኢትዮጵያ ኤንባሲ ጋር በመተባበር ከአመት በፊት የጀመሩት ጥረት በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን ድክመት መስተጓጎሉ የሚናገሩ ውስጥ አዋቂ ምንጮች በአሁኑ ሰዓት ጭካኔ የተሞላበት የኢትዮጵያውያኑ የእርስ በእርስ ግጨት ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ በመምጣቱ መንፉሃ በሚኖሩ ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን ላይ ስጋት መደቀኑ ይነገራል። ቀደም ብሎ ከሳውዲ አረቢያ ወደ ሃገራቸው ከተመለሱ በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከግማሽ በላይ በባህር አቋርጠው ወደ ሳውዲ አረቢያ መግባታቸውን የሚናገሩ ወገኖች መንፉሃ እንደወትሮው በኑሮ ውድነት ሃገራቸው ውስጥ መኖር ተስኗቸው መሄጃ ባጡ ኢትዮጵያውያን ዳግም መጨናነቋን ይናገራሉ። 
እልባት ያላገኘው ይህ የኢትዮጵያኑ የብሄር ግጨት በሰላማዊ ወገኖቻችን ላይ የሚያደርሰውን ተጽእኖ ግምት ወስጥ በማስገባት በዚህ ዙሪያ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰንን ሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ስልክ በመደውል ለማግኘት ያደረኩት ሙከራ ባይሳካም አባሳደር መሃመድ ሃሰን አፈጉባኤ አብዱላ ገመዳ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለጉብኝት ከመግባታቸው በፊት ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ሃገር መመለሳቸውንና ኤንባሲው በግዜያዊነት በዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር እይተመራ መሆኑን አንድ ስማቸውን መጥቀስ ፈቃደኛ ያልሆኑ የኤንባሲው                                                                                          ሰራተኛ ከስጡኝ መረጃ ማረጋጋጥ ፡ተችሏል።
Ethiopian Hagere Jed Bewadi ይህ ሰሞኑንን ሪያድ መንፉሃ እና አካባቢውን ሲያብጥ የከረመው ዘግናኝ የብሄር ግጭጥ ተዕይንት ነው ።

Wednesday, January 7, 2015

በሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ዓውደ ዓመቱን አስመልክተው ያስተላለፉት አጭር መልዕክት !

እንኳን ለብረሃነ ልደቱ በስላም አደረሳችሁ ።
በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽቤት እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዘንድሮ ታህሳስ 29 /2007 በመላው ሀገራችን የኦርቶዶክስ እመነት ተከታዮች ዘንድሮ ተከብሮ የሚውለውን የጌታች መደሃኒታችን እየሱስ ከርስቶስ ልደት በዓል ምክንያት በማድረግ ዝግ ሆኖ እንደሚውሉ ተገለጾል ። በተመሳሳይ መልኩ የጅዳ ዓለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት በነገው ዕለት ዝግ መሆኑን ከት/ቤቱ አመራሮች የተገኘው መረጃ ያመለክታል። ዛሬ በመላ ሃገራችን ተከብሮ የሚውለውን እና ተከታታይ አናጻራዊ አውደ ዓመታትን በሳውዲ አረቢያ የምንኖር መእመናን በጋራ ተሰባስበን ለፈጣሪያቸው መስጋና የምናደርስበት የጸሎት ስፍራ እንዲፈቀድልን በተደጋጋሚ ጥያቄ ማቅረባችን ይታወሳል።
ይህ ጥያቄያችን እስካሁን መልስ ማግኘት ባለመቻሉ ሳውዲ አረቢያ የተለያዩ ግዛቶች እንደ ጨው ተበትነው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የእምነቱ ተከታዮች  በያሉበት በየቤታቸው እንደ አመቺነቱ ተሰባስቦው በዓሉን ለማክበር በሚያደርጉት ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ አደጋዎችን መጋፈጥ ግድ ሆኖባቸዋል። በመሆኑ ህዝበ ከርስቲያኑ ማህበረሰብ  በአውዳ ዓመቱ ከሚደርስበት አደጋ ለመታደግ የሚያስችሉ ዘላቂ መፍትሄዎች ተነድፈው ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት  ለጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ጸሎታችን በቤታችን በሚል ረእስ ጥያቄ ማቀረባችን አይዘነነጋም ። ጥያቄው የቱንም ያህል ውስብስብ እና አስቸጋሪ ቢሆነም ቆንስላው እና ኤንባሲው የዜጎቻቸውን ደህንነት የመጠበቅ ሃላፊነት እንዳለባቸው ተገንዝበው አንጻራዊ መላሽ ከመስጠት ይልቅ ዝምታን መርጠዋል። ዛሬም ሳንታክት ጥያቄያችንን እንደገና በማንሳት ሳውዲ አረቢያ ውስጥ እንድሚኖሩት ፊልፒን ፡ ሲሪላንካ ፡ ህንድ ...ወዘተ የውጭ ሃገራት ዜጎች እኛም በኤምባሲያችን ስር ባሉ የኮሚኒቲ ተቋሞት ውስጥ የጸሎት ቦታ እንዲፈቀድልን በድጋሜ አበክረን እንጠይቃለን ። 
እኛ በሳውዲ አረቢያ የምንኖር የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች ከሙስሊም ወገኖቻችን ጋር ባለን መልካም ግንኙነት ያልተደሰቱ የቆንስላው አንዳንድ ሹመኞች ይህን ህጋዊ መስረት ያለውን የመብት ጥያቄ  ለመቀልበስ በተለያዩ የሶሻል ሚድያ ገጾቻቸው እያነፈሱ ካለው ጥላቻ  ታቅበው የእግዛብሄን መንገድ መከተል እንደሚገባቸው እናሳስባለን። እነዚህ ወገኖች በየትኛውም አቅጣጫ እያደረጉ ሴጣናዊ  ሙከራ የቱንም ያህል ሃይማኖቱንም ሆነ ሰላማችንን ሊጎዳ እንደማይችል ጠንቅቀን ብንረዳም የህዝብ ከርስቲያኑን የጸሎት ቦታ ጥያቄን እንደ ነገር ትንኮሳ በመፈረጅ ህዝበ ሙስሊሙ ወገናችን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በሚኖረው የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኑ ላይ ጥላቻ እንዲያድርበት እየተፈጸመ ያለው ደባ በይቀራት ሊታለፍ የማይችል ፀረ ሰላም ድርጊት መሆኑን በየትኛውም አቅጣጫ የተሰለፉ ወገኖች ሊረዱ ይገባል።
በሰላም ስም እይነገዱ ህዝብን በህዝብ ላይ ለማነሳሳት የሚቃጣቸው እንዚህ ወገኖች ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በኤንባሲው ስር በሚገኙ የኮሚኒትው ንብረቶች ላይ ህዝበ ክርስቲያኑ መበት እና ስልጣን እንዳይኖረው እስከ ማግለል ርቀው ሄደዋል። ለዚህም በኮሚኒው ውስጥ ታቀፈው የነበሩ አንጋፋ አመራር አባላት በክርስትና ሃይማኖቱ ተከታይነታቸው ብቻ ቅጽል ስም እየሰጦቸው ከኮሚኒው ቅጥር ግቢ እንዲርቁ አድረገዋቸዎል። እንዚህ ጅዳ ቆንስላ እና ሪያድ ኤንባሲ የመሸጉ የዘመናችን ጭቃ ሹሞች ለህዝበ ክርስቲያኑ ባላቸው ጥላቻ ሰሞኑን በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ታትሞ የወጣውን የእንኳን አደረሳችሁ መለዕክት ያዘለውን ማስታወቂያ በጨቀየው ጽንፈኛ አስተሳሰባቸው ለመተቸት ሲቃጣቸውም ተስተውሏል። ህዝበ ክርስቲያኑ በሳውዲ አረቢያ ጅዳ እና ሪያድ ኮሚኒቲ ለመሸጉ ጸረ ሰላም ወገኖች ሳይበገር የጀመረውን ሰላማዊ የጸሎት ስፍራ ጥያቄ ከፍ በማድረግ እንደማንኛውም ዜጋ በጅዳ ቆንስላ እና በሪያድ ኤንባሲ ስር በሚገኙ ተቋማት ውስጥ አባልነታችን ማግኘት የሚገባንን መብት ለማስከበር የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን መቀጠል ይገባናል ። በአንጻሩ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ ዓውደ አመቱን አስመልክታችሁ ቢሮዎቻችሁን ከመዝጋት ባሻገር በስራችሁ በሚገኙ የኮሚኒቲ ተቋማት ለኦርቶዶክስ ምዕመናኑ የጸሎት ቦታ በመፍቀድ ታሪክ መስራት ይጠበቅባችሃል ። ታህሳስ 28/ 2007 በሳውዲ አረቢያ ፀሎታችን በቤታችን አስተባባሪ ኮሚቴ ጅዳ !

Monday, September 1, 2014

ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤል ተሰደደ ( በጌታቸው ሺፈራው )


  • 461
     
    Shar
ብስራት ወ/ሚካኤል
በተለያዩ ጋዜጦች፣ መፅሔቶች የራሱ “አዲስሚዲያ” ብሎግን ጨምሮ በተለያዩ ድህረ-ገፆች አዘጋጅ እና ፀሐፊ ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤል መሰደዱ ታወቀ፡፡ ጋዜጠኛው ቀደም ሲል የፍኖተ-ነፃነት ጋዜጣ አዘጋጅ፣የኢቦኒ መፅሔት ዋና አዘጋጅ፣ በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ኢሳው መፅሔት ባልደረባና አምደኛ፤ በኢትዮ-ምህዳር ጋዜጣና በቅርቡ ወደህትመት የገባው ቀዳሚ ገፅ ጋዜጣ ላይም የተለያዩ የፖለቲካ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰትና ማኀበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ በራሱና በብዕር ስም እንደሚፅፍ ይወቃል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተመሰረተውና በመንግስት ከፍተኛ ቁጥጥርና ጫና ላይ የወደቀው የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) መስራች አባል፤ በኋላም የማኀበሩ ትምህርትና ስልጠና ኃላፊ በመሆን እያገለገለ እንደነበር ይታወቃል፡፡ 

ጋዜጠኛው ከዚህ በፊትም በመንግስት ደህንነት ኃይሎች በምሽት እገታ እንደገጠመው፣ ከስልክ ጠለፋ እስከ ዛቻና ማስፈራራት ይደርስበት እንደነበር ከዚህ ቀደም የወጡ መረጃዎች ቢያመለክቱም፤በተለይ ከጥቅምት 2006 ዓ.ም. ከአዲሱ ጋዜጠኞች ማኀበር መመስረት ሂደት ጀምሮ እና በሚያዚያ ወር 2006 ዓ.ም. 3 ጋዜጠኞችን እና 6 የዞን 9 ብሎገሮች በመንግስት ከታሰሩ በኋላ የመንግስት ደህንነቶች ክትትል ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ ተጠናክሮ መቀጠሉንና ቀጣዩ እስር እሱ ላይም ሊፈፀም እንደሚችል በመረዳት ለቅርብ ጓደኞቹ አሳውቆ ነበር፡፡ 

ብስራት ባለፈው ነሐሴ 16 ቀን 2006 ዓ.ም. አርብ ጠዋት አዲስ ባወጣው የስልክ መስመር የማዕከላዊ ስልክ ጥሪ ካስተናገደ በኋላ ለጊዜው ከአዲስ አበባ ውጭ መሆኑን በማሳወቅ ለሰኞ እንደሚቀርብ ምላሽ ከሰጠ በኋላ ባለፈው እሁድ ድንገት ሀገር ጥሎ መሰደዱ ታውቋል፡፡ 

በቅርቡ ከታሰሩት ጋዜጠኞችና ብሎገሮች የእስር ስም ዝርዝር ውስጥ የማኀበሩ አመራሮች መኖራቸውና በቀጣይም መንግስት በአመራሮቹ ዙሪያ መረጃ እየሰበሰበ መሆኑ ምንጮች አረጋግጠው እንደነበረ ይታወቃል፡፡ ቀደም ሲል የማኀበሩ ፕሬዘዳንት ጋዜጠኛ በትረ ያዕቆብ፣ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊው ጋዜጠኛ ዘሪሁን ሙሉጌታ፣ ገንዘብ ያዥ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ስዩም እና መስራች አባል ጋዜጠኛ ተሰማ ደሳለኝ መሰደዳቸው አይዘነጋም፡፡ በአጠቃላይ ጋዜጠኛ ብስራት ወ/ሚካኤልን ጨምሮ በ2006 ዓ.ም. ብቻ 25 የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ሲሰደዱ፤3 የውጭ ዜጎች ጋዜጠኞችን ጨምሮ 20 ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ደግሞ በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡





ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ጋዜጠኛ ነበዩ ሲራክን ለማፈን የተቃጣው ሴራ ከሸፈ ።

ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ በመላው አረብ አለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ላይ የሚፈጸመውን ግፍ እና በደል በማለዳ ወጉ መረጃዎችን በማቀበል የሚታወቀው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በማያውቀው ጉዳይ  ተከሶ ዛሬ ፍ/ቤት መቀረቡን ውስጥ አውቂ ምንጮች ገለጹ ።      ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ኦገስት  27/8/2014 ማለዳ 4:00  በደረሰው የከስ ጥሪ የመጣውን ሁሉ በጸጋ ለመቀበል ህግ እና ስረአት አክብሮ ወደ     ፍ/ቤት መሄዱን የሚናገሩ    ምንጮች   በአካባቢው የሚገኙ የሳውዲ ህግ አሰከባሪዎች ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ተመስረተበት ስለተባለው   ወንጀል ምንም አይነት     መረጃ እንደሌላቸው አውስተው ጥሪውን ወዳስተላለፈለት ፖሊስ ጣቢያ ሄዶ ሪፖረት እንዲያደርግ መላኩን ይገልጻሉ ። 
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እረፍ ሲነሳው የከረመውን የሃስተ ክስ ለማጣራት መደበኛ ስራውን አቋርጦ ዛሬ እሁድ ለ31/8/2014 ማለዳ ደግሞ ፍ/ቤት ቢቀርበም ተመሳሳይ መልስ ስለተሰጠው ጥሪውን ወዳ ስተላለፈለት በተለምዶ ሽማልያ ስለላ የሚባል ፖሊስ ጣቢያ በማቅናት ሪፖርት ቢያደርግም ተረኛ የሳውዲ ፖሊስ መኮንኖች ስለጉዳይ ምንም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልጸው ጋዜጠኛውን በነጻ እንዳሰናበቱት ለመረዳት ተችሏል ። ጋዜጠኛ ነበዩ ሲራክ በማለዳ ወጎቹ ያቀርባቸው በነበሩ አሳዛኝ እና አሰቃቂ የእቶቻችን የአረበ አለም ህይወት ገጽታ በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን ዘንድ አድናቆት እና ክበርን ያተረፈ ታላቅ ግዜጠኛ መሆኑ ቢታወቀም በዚህ ስራው ባልተደሰቱ ምስለኔዎች ቀደም ብሎ በቀረበበት የሃሰት ከስ ለእስር ተዳርጎ እንደነበር የሚያስታውሱ ወገኖች ጋዜጠኛውን በእጅ አዙር ለማዋከብ የሚደረገው ጥረት አንዱ አካል ሊሆን እንደሚቸል ይናገራሉ። ይህ ጋዜጠኛ በወቅቱ በተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች እና የኢትዮጵያ ህዝብ ተዕጸኖ ነጻ ቢወጣም በአረብ አለም ስለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ምን አይነት ዘጋባ እንዳያቀረብ በተላልፈበት ከባድ ማስጠንቀቂያ ከጀርመን ድምጽ ዘጋቢነቱ በመራቅ እስካሁንም የህሊና እረኛ መሆኑን ይናገራሉ ። 

በአሁኑ ግዜ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ ስለሚፈጸመው ግፍ እና በደል መናገር ወንጀል ሆኗል የሚሉት ምንጮች ። በተለይ በኮንተራት ሰራተኛ እህቶቻችን ሬሳ ዶላር የሰበሰቡ አንዳንድ የአሰሪ እና ሰራተኛ ኤጀንሲ ባለቤቶች ሃላፊነት የማይሰማቸውን ደካማ የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሻቸው እያሸከረከሩ በወገኖቻችን ላይ ስለሚደርሰው ግፍ እና በደል በአደባባይ በሚናገሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፍተኛ ተጸዕኖ ማሳደር መቻላቸውን ይገልጻሉ። እንዚህ ምንጮች አያይዘው ሲገልጹ ምን እንኳን በኮነትራት ሰራተኛ ኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ግፍ እና በደል ሃገር አቀፍ ተቃውሞ በማስነሳቱ መንግስት ከግል ጥቅማቸው ባሻገር የወገኖቻቸው ህይወትን ማየት በተሳናቸው የአሰሪ እና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ላይ በወስደው አንጻራዊ እርምጃ የአያሌ ኢትዮጵያውያንን ህይወት ከስቃይ መታደግ ቢቻልም እነዚህን ወንጀለኞቸ ለፈርድ በማቅረብ ረገድ የውጨ ጉዳይ ሚንስተሩ ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም ገብተው የነበረውን ቃል ማጠፋቸው ግፉ የተፈጸመበትን ድፈን የኢትዮጵያን ህዝብ እጀግ በጣም አሳዝኗል ብለዋል:: እንደሚታወቀው በተጠቀሱት ኤጀንሲዎች አማካኝነት ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ ወደ ተለያዩ አረብ ሃገራት በኳንተራት ቪዛ ገበተው ያሉበት ሁኔታ እሳክሁን በወል ከማይታወቀው በመቶሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችን ባሻገር በሰው እጅ ተገለውም ሆነ በተለያየ ምክንያት ህይወታቸው አጥተው የኤንባሲ አሊያም የቆንስላ ባለስልጣናት ለወላጆቻቸው ሳያሳውቁ መርዶ ነጋሪ በሌለበት አረብ በረሃ ስረአተ ቀብራቸው የተፈፀመ እህቶቻችን ማንነት በሚስጠር መያዙ ይነገራል። 
ምንጭ Ethiopian Hagere Jed Bewadi