Friday, March 21, 2014

ቤተክርስቲያን መምህር ግርማን ፎርጂድ ደብዳቤ በማሰራጨት ወነጀለች


(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን “መልአከ መንክራት ግርማ ወንድሙ” በሚል ስያሜ የተበተነው ደብዳቤ ሕገ ወጥ በመሆኑ የሚመለከተው ሁሉ ይህን ግንዛቤ እንዲወስድ አሳሰበች፡፡ “መምህር ግርማ ወንድሙ ከፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ እንዲያገለግሉ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል” በሚል መምህር ግርማ እያሰራጩት ያለው ደብዳቤ ከቤተክርስቲያኒቱ ጽህፈት ቤት ተፈርሞ ያልወጣ የማጭበርበር ደብዳቤ ነው ሲል በአባ ገርማ (ሊቀጳጳስ/ዶ/ር) የብጹዕ ወቅዱስ ፓትርያርል ልዩ ጽህፈት ቤት የውጭ ግኙነት ሃላፊ ስም መጋቢት 10 ቀን 2006 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ተገልጿል።

ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መምህር ግርማ የበተኑትንና በመላው ዓለም ከፓትርያርኩ ተዘዋውሬ ሃብተ ፈውስን እንድሰጥ ተፈቅዶልኛል የሚለውን ደብዳቤ ማስተናገዷ የሚያወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የፓትሪያርኩ ልዩ ጽህፈት ቤት የወጣውን ደብዳቤ በማስተናገድ ፍርዱን ለአንባቢ ትተዋለች።
ቀጥሎም ፎርጂዱን ደብዳቤ እንዳትቀበሉት ሲል የወጣውን እና መምህር ግርማ ያሰራጩት የተባለውን ደብዳቤ በተከታታይ ለግንዛቤ አቅርበናቸዋል።
ዘ-ሐበሻ መምህር ግርማን በዚህ ህገወጥ የሆነ ደብዳቤ አሰራጭተዋል በሚል በቀረበባቸው ውንጅላ ዙሪያ ለማነጋገር ያደረገችው ሙከራ ባይሳካም እንዳገኘናቸው ሃሳባቸውን ለማቅረብ እንሞክራለን። ሆኖም ግን አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች መምህር ግርማ ነሐሴ 25/2005 ዓ.ም ደብዳቤ ተጽፎልኛል ብለው ደብዳቤውን ከበተኑት ከ7 ወር በኋላ ቤተክርስቲያን ጉዳዩን ማስተባበሏ ከበስተጀርባው አንድ ጉዳይ ሊኖር እንደሚችል ይናገራሉ።
የመምህር ግርማ ደብዳቤ ፎርጂድ ነው አትቀበሉት ሲል የተጻፈው ደብዳቤ
መምህር ግርማ በአቡነ ማቲያስ ሃብተ ፈውስን እንድሰጥ ተፈቅዶልኝ ደብዳቤ ተጽፎልኛል ሲሉ የበተኑት ደብዳቤ፦

Monday, March 17, 2014

በኩዌት ኢትዮጵያት የአሰሪዋን ልጅ ወግታ ገደለች ተባለ!! Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ




በኩየትም መከራችን እየበዛ ነው። ወገን ነገር አለሙ እየተበላሸ ይመስላል። ባለፈው በሳውዲ አረቢያ ረብሻ ከመነሳቱ በፊት የሆነውም ያልሆነውም ነገር በኢትዮጵያዊያን ላይ እየተጋነነ መነሳቱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ኩዌት ልክ የዚያን ግዜ አይነት ነገር ጀምራለች።
የኛ ልጆች ጭራሽ ንፁህ ናቸው ማለትም እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። ነገር ግን ለምን እንዴት በምን ሰበብ እውነትስ ይሁን ውሸት ምንም ነገር ሊደፈደፍባቸው እንደሚችልም መገመት አያስቸግርም። ለምን ቢባል በቅርቡ ከኩዌት እየተሰሙ ያሉ ዜናዎች የውጡልን ዘመቻ በህገ ወጦች ላይ በርትቷል የኛ ልጆችም የጥቃቱ ሰለባ እየሆኑ ነው።
ኢትዮጵያዊያን የገደሉት ሰው ልክ ካለፈው አመት ጀምሮ አስር ደርሷል ያለው ይሄው ዘገባ የኩዊት መንግስት የጉዳዩ አሳሳቢነት ረጋ ብሎ ማየት ይጠይቃል በሚል ለሁለት ወር የቤት ውስጥ ሰራተኛ ላታስገባ በአዋጅ አሳውቋል ይለናል ምንጫችን የሆነው "አክባር24" news
ወጣቱ በህግ ቁጥጥር ስር ውላ አቃቤ ህግ ምርመራ እያደረገ ነው።
ገዳይ ናት የተባለችው ወጣት ፎቶግራፍ

Saturday, March 15, 2014

በጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ላይ የተከፈተውን ስም ማጥፋት ዘመቻ በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙ « ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እረፍት ላይ ነው »


ሰሞኑንን የታላቁ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከድህረ ገጽ መራቅን ተከትሎ በተለዩዩ የፌስ ቡክ ገጾች የሚነገሩ መላምቶች ከእውነት የራቁ እና ፍጹም የታላቁን ጋዜጠኛ ባህሪ የማይወክሉ በኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞች ላይ የተሰነዘረ ተራ ስም ማጥፋት ዘመቻ መሆኑንን በሪያድ እና ጅዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ገለጹ ። ደከመኝ ሰልቸኝ ሳይል የማለዳ ወግ በሚል ር ዕስ በአረብ አለም የሚገኙ ወገኖቹን እሮሮ በማሰማት የህዝብን ፍቀር እና ክብረን ያገኘው ታላቁ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከማርች 4 2014 ጀምሮ እረፈት ላይ መሆኑን የሚናገሩ ምንጮች ይህን አጋጣሚ ተጠቅመው አንዳንድ ግለሰቦች በግል ጥላቻ በዚህ ታላቅ ጋዜጠኛ ላይ እይናፈሱ ባለው ወሬ ህዝቡ እንዳይደናገር አክለው ገልጸዋል። 

ታላቁ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በቤት ሰራተኝነት ወደ ሳውዲ አረቢያ በሚመጡ እህቶቻችን ላይ የሚፈጸመው መረን የለቀቀ ግፍ እና በደል እንዲቆም እያሰተላለፈ ባለው የማለዳ መልዕክቱ ይህ ታላቅ ጋዜጠኛ በወገኖቻችን ህይወት በሚነገዱ ጥቂትለሰቦች በአይነ ቁራኛ እንደሚጠበቅ ይታወቃል ። በተለይ ከኢትዮጵያ በኮንተራት ወደ ሳውዲ የመጡ እህቶቻችንን በሃይል ለባእዳን አሳልፈው በመስጠት በወሲብ ንግድ ላይ በማሰማራት በወገኖቻችን ስበዕና ላይ ግፍ ሲፈጽሙ እና ሲያስፈጽሙ የነብሩ ግለሰቦች ለ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የተለያዩ ሰሞችን በመስጠት ከህዝበ ሙስሊሙ ወግናችን ጋር ለማጋጨት ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልበጠሱት ቀጠል የለም። በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በስው አክባሪ ነቱ እና በኢትዮጵያዊ ጨዋነቱ የሚታወቀው ይህ ታላቅ ጋዜጠኛ በመካከለኛው ምስራቅ በተለይ ጅዳ እና ሪያድ ከተማ ውስጥ በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመውን ስቃይ እና በደል ለህዝብ በአደባባይ ከመግለጽ እንዲቆጠብ በተጠቀሱት ጋጥወጦች በድምጽ እና በጽሁፍ መሳፈራሪያዎች ቢደርሱትም ቅንጣጥ ያህል ሳይሸበር ሳይማር ላስተማረው ህዝብ መስወአት ለመሆን የህዝብን እሮሮ በማሰማት አንገቱን ለስይፍ ግንባሩን ለጥየት የሰጠ ያልተነገረለት ጀግና መሆኑን ከልጅ አስከ አዋቂ ለሃገር እና ለወገን ተቆርቋሪ የሆነ ሁሉ ይመስክርለታል።፡፤ 

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እየፈጸመ ላለው ታልቅ ተግባር ክብር እና ምስጋና ይገበዋል የሚሉ በጅዳ እና በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች እንደነዚህ አይነቶችን ይህዝብ ልጆች ለማበረታት የክበር ሽልማቶች መዘጋጀት እንዳለባቸውም አመልክተዋል። ከእንግዲህ በአረቡ አለም በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመው ስቃይ እና በደል ማብቂያ ሊበጅለት የሚሉ የአንድ በዕድሜ ባለጸጋ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ አባት ሳውዲ አረቢያ የተቀደሰችዋ መካ ከተማ ውስጥ ላለፉት 40 አመታት መኖራቸውን ገልጸው በወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመው ስቃይ እና በድለ ቀደም ብሎ ይሰማ እንዳልነበር አስታውሰው ዛሬ በጀርመን ድምጽ አማርኛ ፕሮግራም እና በተለያዩ ድህረ ገጾች መነበቡ «አልህምዱሊላሂ» ፈጣሪን ሊመሰገን ይገበዋል በለው ይህን ሁሉ ላደረገው ለታላቁ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ እና መስል ወገኖቻችን እድሜን እና ጤናን እንደሚመኙ አክለው ገልጸዋል። ይህን ተከትሎ በአንዳንድ ወሮ በሎች በጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ላይ በግልጥላቻ ሰሞኑንን ሰለሚናፍሰው ወሬ የተለመደ እና ቦታ እንደማይሰጡት ገልጸው በፌስ ቡክ ገጽ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችን ስም የሚያጠፉት ወገኖች በእህቶቻችን ላይ በድል እና ግፍ ሲፈጸም የከረሙ ሴጣኖች በመሆናቸው እነዚህ ግለሰቦች የኢትዮጵያን ሙስሊሙም ሆነ ክርስቲያኑን ማህበረሰብ ስለማይወክሉ ከወዲሁ ሊወገዙ እንደሚገባቸው ተናግረዋል ። 

 ሰሞኑንን ታላቁን ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከድህረ ገጽ መጥፋን ተከትሎ አንዳንድ ግለስቦች በተለያዩ የእስልምና ሃይማኖት ተከታይ ወገኖቻችን ስም በከፈቱት የፌስ ቡክ ገጽ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በሳውዲ አረቢያ ህግ የተከለክሉ ነገሮችን ፈጽሞ የታሰረ አስመስለው ውዠንበር በመንዛት ላይ ይገኛሉ። በመሆኑም የነዚህ ግለሰቦች ተዕለኳ ምን እንደሆነ ለግዜው ግልጽ ባይሆንም ታላቁ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በአሁኑ ግዜ እረፍት ላይ መሆኑንን በመረዳት ህዝብ በተለያዩ አቅጣጫዎች በሚነዙ በሬ ወለደ ውዠንብሮች እንዳይደናገጥ ውስጥ አውቂ ምንጮች ገልጸዋል ። 

Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ     ( እረፍት ላይ የሚገኘው አንገቱን ለሰይፍ ግንባሩን ለጥየት የሰጠ ታላቁ ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ) ።

Sunday, March 9, 2014

ድንፋታ…. እና የኢትዮጵያ እርጋታ



የግብጽ የተለያዩ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ እየገነባችው ባለችው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የተለያዩ ማስፈራሪያዎችን መሰንዘር የዘወትር ተግባራቸው አድርገው ይዘውታል። 

በቅርቡም የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …… ታህሪር ሳተላይት ቻናል ከተባለ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ከፍተኛ የማስፈራራት እና የዛቻ ንግግር ሲያደርጉ ተሰምተዋል። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የግብጽን ህዝብ ጥቅም በማንኛውም መልኩ ከማስከበር ሃገራቸው ወደ ኋላ እንደማትል እና ኢትዮጵያ ከግብጽ ጋር ስምምነት ላይ መድረስ የማትችል ከሆነ እርምጃ እንደሚወስዱ ተናግረዋል። «ከማንኛውም አደጋ ራሳችንን እንጠብቃለን፣ ከኢትዮጵያም ጋር ድርድር እናደርጋለን ነገር ግን ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገው ድርድር ውጤቱ ካላማረ ለሚፈጠረው ቀውስ ኢትዮጵያ ሃላፊነቱን ትውስዳለች ብለዋል። የኢትዮጵያ መንግስት ግን እነዚህ እና የመሳሰሉ የማስፈራሪያ እና የዛቻ ንግግሮች የትም እንደመያደርሱ በተላያዩ መንገዶች ትዕግስት የተሞላበት አስተያየት ሲሰጥ ነው የሚደመጠው። 

የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲም በጉዳዩ ላይ ለድሬቲዩብ የሰጡት አስተያየትም ከዚህ የተለየ አይደለም። በመጀመሪያ ይላሉ አምባሳደር ዲና « በመጀመሪያ ኢትዮጵያ በግብጽም ሆነ በታችኛው የተፋሰሱ ሃገራት ላይ አደጋ የሚያመጣ ምንም አይነት እቅድ የላትም፤ ይህም በተደጋጋሚ ሲገለጽ የቆየ ጉዳይ ነው»። 

ቃል አቀባዩ የግብጽ ባለስልጣናት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት እስካልደፈሩ ድረስ የፈለጉትን የማለት መብት እንዳላቸውም ተናግረዋል። ከዚህ በተጨማሪ ግብጾች እራሳቸው ከሶስትዮሹ የቴክኒክ ኮሚቴ ድርድር ወጥተው በተለያዩ የአረብ ሃገራት አደራዳሪነት አዲስ ውይት ይጀመር ይላሉ ነገር ግን ኢትዮጵያ ከሶስትዮሹ የቴክኒክ ኮሚቴ ድርድር ውጪ ማንኛውንም አይነት አደራዳሪም ሆነ ድርድር እንደማትቀበል ነው አምባሳደሩ የገለጹልን።

የግብጽ ባለስልጣናት በተለያዩ ግዚያት የሚናገሯቸው ንግግሮች «ህገወጥ ናቸው» ያሉት አምባሳደሩ አሁን እየተከተሉት ያለው አቋም የግብጽን ህዝብ የሚጎዳ ተግባር ከመሆኑ ባሻገር ይህንኑ የሚያደርጉበት የራሳቸው ውስጣዊ እና ውጫዊ ምክንያቶች አሏቸው ብለዋል። 

ተጀምሮ ከነበረው የሶስትዮሽ ድርድር ምንም እንዃ ግብጽ እራሷን ብታገልም ዞሮ ዞሮ ድርድሩ ለግብጽ ህዝብ የሚጠቅም በመሆኑ የግብጽ መንግስት ወደ ድርድሩ ይመለሳል የሚል ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል። ምንጭ ( www.DireTube.com )

ሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ከሴቶቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል




የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ቡድን እንደዘገበው ዛሬ በተካሄደው የሴቶች 5ሺሜትር ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ የሰቶች ጉዳይ ባመቻቸው እድል የፓርቲው ሴቶች የሮጡ ሲሆን በሩጫውም ላይ የተለያዩ መፈክሮች ማለትም ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ትፈታ፤ አቡበከር ይፈታ፣ እስክንድር ይፈታ፣ አንዷአለም ይፈታ፣ ነፃነት እንፈልጋለን እና ሌሎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች አሰምተዋል::



ከመነሻው የጀመረው የተቋውሞ ድምጽ እስከ ማብቂያው የቀጠለ ሲሆን ሩጫቸውን ጨርሰው ሊገቡ ሲሉ በፖሊሶች ተቆርጠው በአሁኑ ሰዐት ታስረው ይገኛሉ። በሩጫው ወቅት ተቋውሞ ሲያሰሙ የሚያሳይ ቪድዮ እና ፎቶ እንደደረሰን ምንለቅ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን::



የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሴት አባላት እና ከእናርሱ ጋር የነበሩ ሴቶች በዛሬው እለት በተካሄደው ሩጫ ላይ ተሳትፈው ሃሳባቸውን በመግለጽ ላይ አንዳሉ በሩጫው መጨረሻ ላይ በፖሊስ ታፍሰው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡


ይህ በእንዲህ እንዳለ በአከባቢው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ጌታነህ ሴቶቹ መታሰራቸው ምንም አግባብነት እና ህጋዊ መሰረት የለውም በማለታቸው ከሴቶቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የእስረኞች ስም ዝርዝር
1 ንግስት ወንድይፍራ(የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ)
2 ወይንሸት ሞላ (የምክርቤት አባል)
3 ወይኒ ንጉሴ(አባል)
4. እመቤት ግርማ(አባል)
5. ሜሮን አለማየሁ (አባል)
6. ምኞት መኮንን(አባል)
https://fbcdn-vthumb-a.akamaihd.net/hvthumb-ak-prn1/t15/s130x130/1623250_1429394780635494_1429394033968902_18540_2529_b.jpg 
ለጊዜው የሴቶች ጉዳይ እና የህግ ጉዳይ ኮሚቴ የሆኑት ኢየሩስ ተስፋው እና ኤልሳ ወሰኔ ያሉበትን ልናውቅ አልቻልንም፡፡
ከነዚህ ሴቶች በተጨማሪም በቦታው የነበሩት የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት አቶ ብርሀኑ ተ/ያሬድ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊው አቶ ጌታነህ ባልቻ እና የህዝብ ግንኑነት ኮሚቴ አቶ አቤል ኤፍሬም ናቸው፡፡
እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ አቤል ኤፍሬም በአካባቢው ስለነበሩ ብቻ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያሉበትን ለማጣራት የሰማያዊ ወጣት ክንፍ አባላት በእንቅስቃሴ ላይ መሆናችንን እያስታወቅን የደረስንበትን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናስታውቃለን፡

ትግሉን በእስራት እና በግድያ ማስቆም አይቻልም        ( ምንጭ ዘ ሀበሻ )

ሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው ከሴቶቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል





የሰማያዊ ፓርቲ ወጣት ቡድን እንደዘገበው ዛሬ በተካሄደው የሴቶች 5ሺሜትር ሩጫ ላይ የሰማያዊ ፓርቲ የሰቶች ጉዳይ ባመቻቸው እድል የፓርቲው ሴቶች የሮጡ ሲሆን በሩጫውም ላይ የተለያዩ መፈክሮች ማለትም ጋዜጠኛ ርዕዮት ዓለሙ ትፈታ፤ አቡበከር ይፈታ፣ እስክንድር ይፈታ፣ አንዷአለም ይፈታ፣ ነፃነት እንፈልጋለን እና ሌሎች ማህበራዊና ፖለቲካዊ ጥያቄዎች አሰምተዋል::



ከመነሻው የጀመረው የተቋውሞ ድምጽ እስከ ማብቂያው የቀጠለ ሲሆን ሩጫቸውን ጨርሰው ሊገቡ ሲሉ በፖሊሶች ተቆርጠው በአሁኑ ሰዐት ታስረው ይገኛሉ። በሩጫው ወቅት ተቋውሞ ሲያሰሙ የሚያሳይ ቪድዮ እና ፎቶ እንደደረሰን ምንለቅ መሆኑን በትህትና እንገልጻለን::


የሰማያዊ ፓርቲ የሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሴት አባላት እና ከእናርሱ ጋር የነበሩ ሴቶች በዛሬው እለት በተካሄደው ሩጫ ላይ ተሳትፈው ሃሳባቸውን በመግለጽ ላይ አንዳሉ በሩጫው መጨረሻ ላይ በፖሊስ ታፍሰው ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደዋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአከባቢው የነበሩት የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ብርሃኑ እና የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ጌታነህ ሴቶቹ መታሰራቸው ምንም አግባብነት እና ህጋዊ መሰረት የለውም በማለታቸው ከሴቶቹ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የእስረኞች ስም ዝርዝር
1 ንግስት ወንድይፍራ(የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ)
2 ወይንሸት ሞላ (የምክርቤት አባል)
3 ወይኒ ንጉሴ(አባል)
4. እመቤት ግርማ(አባል)
5. ሜሮን አለማየሁ (አባል)
6. ምኞት መኮንን(አባል)

ለጊዜው የሴቶች ጉዳይ እና የህግ ጉዳይ ኮሚቴ የሆኑት ኢየሩስ ተስፋው እና ኤልሳ ወሰኔ ያሉበትን ልናውቅ አልቻልንም፡፡
ከነዚህ ሴቶች በተጨማሪም በቦታው የነበሩት የፓርቲው ህዝብ ግንኙነት አቶ ብርሀኑ ተ/ያሬድ ፤ የድርጅት ጉዳይ ሀላፊው አቶ ጌታነህ ባልቻ እና የህዝብ ግንኑነት ኮሚቴ አቶ አቤል ኤፍሬም ናቸው፡፡
እንዲሁም የሰማያዊ ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል አቶ አቤል ኤፍሬም በአካባቢው ስለነበሩ ብቻ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ያሉበትን ለማጣራት የሰማያዊ ወጣት ክንፍ አባላት በእንቅስቃሴ ላይ መሆናችንን እያስታወቅን የደረስንበትን ይፋ የምናደርግ መሆኑን እናስታውቃለን፡
ትግሉን በእስራት እና በግድያ ማስቆም አይቻልም        ( ምንጭ ዘ ሀበሻ )

Thursday, March 6, 2014

ብልጡ አልጀዚራ ኢቲቪን ሸወደው ( በከበደ ካሳ )


በከበደ ካሳ
በኳታር መንግስት ሃብት የተቋቋመውና ስነ አፈጣጠሩ ሲጠናም የምዕራቡን አለምና የእስራኤል ሚዲያን የአረብ ሀገራት ጉዳይ አዘጋገብ ለመገዳደር የተፈጠረው የአልጀዚራ ቴሌቪዥን ጣቢያ ስትራግል ኦቨር ናይል በሚል ርዕስ አንድ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅቶ ነበር። ጣቢያው ይህን ፊልም በቴሌቪዥኑ ያስተላለፈው ሲሆን በድረ ገፁ ላይ ስለጫነውም በርካቶች ተመልክተውታል።
የዘጋቢ ፊልሙ ይዘት በናይል ወንዝ የተነሳ በላይኛውና በታችኛው የተፋሰሱ ሀገራት መካከል ስለነገሰ ውጥረት ሲሆን ትኩረት ያደረገው ደግሞ ከላይኛው ተፋሰስ ኢትዮጵያ ላይ፤ ከታችኛው ተፋሰስ ደግሞ ግብፅ ላይ ነው። ይህን ፊልም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ከሞላ ጎደል እንደወረደ በሚባል ደረጃ ወደ አማርኛ ተርጉሞ አቅርቦታል። ‘ጠብቁን’ የሚል ማስታወቂያ መሰራቱና ፊልሙ በተደጋጋሚ መታየቱ የአባይ ፍጥጫ ከሚለው ጩኸታም ርዕሱ ጋር ተዳምሮ በርካታ ኢትዮጵያዊያን እንደተከታተሉት ለመገመት አይከብድም።
ይህን ዘጋቢ ፊልም የተከታተሉ የምቀርባቸውን ሰዎች ስለ ዘገባው ያላቸውን አስተያየት ጠይቄያቸው ነበር። የሚበዙቱ እንዳደነቁት ነግረውኛል። ሁሉም ለማለት በሚቻልበት ደረጃ በምስል አጠቃቀሙ፤ በትረካው ፍሰትና በታሪክ አወቃቀሩ በጥቅሉ በአቀራረብ ደረጃ ምርጥ የሚባል ዘጋቢ ፊልም እንደሆነ ይስማማሉ። እኔም በዚህ ረገድ ልዩነት የለኝም። ሆኖም አንዳንድ ያሳሰቡኝን ጥያቄዎች ሳነሳ የጠየቅኋቸውም እንደኔው ግር ይላቸዋል አለያም “እውነትክን ነው፤ ከኢትዮጵያ ጥቅምና አቋም ጋር ይጋጫል” ይሉኛል።
በእኔ እምነት ዘገባው ከኢትዮጵያ ይልቅ ለግብፅ ጥቅም ያደላ፤ ሶስተኛ ወገን ለኢትዮጵያ ሳይሆን ለግብፅ እንዲጨነቅላት/እንዲያዝንላት የሚያደርግና ኢትዮጵያ ከምትከተለው አብሮ የመልማት ወይም በጋራ የመጠቀም እሳቤ ይልቅ ለፍጥጫና ግጭት መንስዔነት የቀረበ ነው። ይህን የምለው አልጀዚራ የአረብ አለም ሚዲያ ነው፤ ግብፅ ደግሞ የአረቡ አለም እምብርት ነች ከሚል አጠቃላይ ፍረጃ ተነስቼ ሳይሆን ከራሱ ከዘገባው ይዘት በመነሳት ነው። የማነሳቸው መከራከሪያዎችም በፊልሙ ውስጥ ቃል በቃል የሰፈሩ ናቸው።
ይህ ዘጋቢ ፊልም ለኢትዮጵያ አይበጅም ስል ምክንያት ከማደርጋቸው አንዱ የአባይ/ናይል ወንዝ ከኢትዮጵያ ይልቅ ለግብፅ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ አድርጎ ማቅረቡ ነው። እንደ ፊልሙ አባይ ለግብፅ የህልውና ጉዳይ ሲሆን ለኢትዮጵያ ግን የልማት ወይም የእድገት ጉዳይ ነው። በዘገባው ላይ እንደተገለፀው ካይሮ የተፈጠረችውና ያደገችው በናይል ወንዝ የተነሳ ነው። ያለ ናይል አካባቢው ሰው ሊኖርበት የማይችል በረሃ ነው። ማንኛውም ግብፃዊ በወንዙ ዙሪያ የመስፈር ፍቅሩም ከፍተኛ ነው። ስለሆነም “ሄሮዲተስ ግብፅን የአባይ ስጦታ ብሎ ገልጧታል። ትክክለኛ አገላለፅ ነው” ሲል ይደመድማል።
“በ1959ኙ ስምምነት መሰረት ግብፅ ከአባይ ወንዝ 55.5 ቢሊዮን ሜትሪክ ኪውብ ውሃ ይደርሳታል። ሆኖም ግን ከዚያን ግዜ ጀምሮ የግብፅ ህዝብ በሶስት እጥፍ አድጎ 80 ሚሊዮን በመድረሱ የውሃ እጥረት አጋጥሟታል።” ተብሏል በፊልሙ ውስጥ። ቃለ ምልልሱ ያካተታቸው የግብፅ ወታደራዊ ተንታኝ “በህልውናና በደህንነት መካከል ልዩነት አለ፤ እኛ ሙሉ በሙሉ የአባይ ዉሃ ጥገኞች ነን። ሌላ የዉሃ ምንጭ የለንም። ስለዚህ ሃቁ ያለው በአባይ ዉሃ ላይ ስጋት የሚፈጥር ነገር ሲኖር በግብፆች ህልውና ላይ ያነጣጠረ ነው ማለት ነው። ይህ ደግሞ በእኛ ላይ የዉሃ ጥምና የሞት አደጋን እንዳያስከትል ያሰጋናል” ይላሉ።ስለተጠቃሚነት የተጠየቁት ኢትዮጵያዊ ወ/ሮ አጀበች ደግሞ በመብራት እጦት መሰቃየታቸውን ይናገራሉ። የነዚህ ንግግሮች ድምር አባይ/ናይል ለግብፃዉያን የህይወት ምንጭ፤ ለኢትዮጵያዉያን ግን የመብራት ምንጭ ነው የሚል ነው።
እኔ ወንዙ ለግብፅ በምን ያህል ደረጃ ያስፈልጋታል? የሚል ክርክር ውስጥ መግባት አልፈልግም። ወንዙ ከነሱ ህልውና ጋር አይተሳሰርም ብዬም አልከራከርም። ከግብፅ በላይ ለእኛ ያስፈልገናልም አልልም። ግን ሶስት ጥያቄዎችን አነሳለሁ።
አንደኛው ናይል ለግብፆች የሞት የሽረት ጉዳይ ስለመሆኑ ማውራቱ ለኢቲቪ ምን ይፈይድለታል? የሚል ነው። ይህንንማ ግብፃውያን ከውልደት እስከሞታቸው የሚሰበኩት አይደለም እንዴ። ይህንንማ በራሳቸው ሚዲያ ሁሌ የሚደጋግሙልን አይደል እንዴ? ትክክል አለመሆናቸውን ለማሳየት ነው እንዳልል እንዲያ የሚል ነገር አልሰማሁበትም።
ሁለተኛው ጥያቄዬ ምን የሚያሰጋ ነገር ስለመጣ ነው የግብፆችን ስጋት ማንፀባረቅ ያስፈለገበት? የሚል ነው። ኢትዮጵያ የዉሃው መጠን አይቀንስም፤ ማንም ሳይጎዳ ወንዙን በጋራ መጠቀም እንችላለን እያለች ባለችበት ሁኔታ የነሱን“በዉሃ ጥም እናልቃለን” ስጋት ማውራት ‘እንትን ያለበት ዝላይ አይችልም‘ እንደሚባለው አያስመስልምን? ይህ ነገር በተለይ ኢትዮጵያና ብሪታኒያ ወንዙን ግብፅን ለማንበርከክ ይጠቀሙበት ነበር ተብሎ ከቀረበው ታሪክ ጋር ሲዳመር የግብፅ ስጋት ተገቢ ነው ወደሚል ማደማደሚያ አያደርስም? በፊልሙ ውስጥ ቀደምት የኢትዮጵያ ገዢዎች ከግብፅ ወርቅ ለማግኘት ሲሉ አባይን እንገድበዋለን እያሉ ያስፈራሩ እንደነበርና ብሪታኒያም የግብፆችን የፀረ ቅኝ ግዛት እንቅስቃሴ ለመግታት ስትል በጥቁር አባይና በነጭ አባይ መካከል ግድብ መስራቷ ተመልክቷል። አልጀዚራ በተዘዋዋሪ እየተናገረ ያለው አሁንም ኢትዮጵያ ግድቡን ግብፅን ለማንበርከክ ልትጠቀምበት ትችላለች ነው።
ሶስተኛው ጥያቄዬ ሁለቱ ሀገሮች በፍትሃዊ አጠቃቀም ላይ ስምምነት ባልደረሱበት ሁኔታ ይህን ፊልም ያየ ሶስተኛ ወገን ምን ሊያስብ ይችላል? ነው። በፊልሙ ላይ ግብፆች ገና ከአሁኑ በዉሃ እጥረት እየተሰቃዩ እንደሆነ ለማሳየት ታስቦ የገቡ ምስሎች ብዙ ናቸው። በርካታ ግብፃውያን ጀሪካኖችን ይዘው በአንድ ቧንቧ ዙሪያ ሲራኮቱ ይታያሉ። ይህ ግን አጠቃላዩን የግብፅ ሁኔታ ገላጭ አይደለም። ይልቁንም ግብፆች የሚታወቁትና ራሳቸውም የማይክዱት በዉሃ አጠቃቀማቸው አባካኝ እንደሆኑ ነው። እንግዲህ ሶስተኛ ወገን ሲባል ለጋሽ ድርጅቶችን፤ ሃያላን መንግስታትን፤ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትን ያካትታል። ይህን ፊልም ሲመለከቱ የሚያዝኑት ለማን ይሆናል? መብራት ለምትፈልገውና ሌሎች አማራጮች አሏት ተብላ በፊልሙ ለተፈረጀችው ኢትዮጵያ? ወይስ ህይወቷ በሙሉ በናይል ላይ የተንጠለጠለና የመጠጥ ዉሃ አጥታ የምትሰቃይ ተደርጋ ለተሳለችው ግብፅ?
ሁለተኛው የመከራከሪያ ነጥቤ ዘጋቢ ፊልሙ አባይ/ናይልን ከትብብር ይልቅ የግጭት ምንጭ አድርጎ ስሎታል የሚል ነው። ይህን የምመዝነው ኢትዮጵያ ከያዘችው አባይ/ናይል የትብብር እንጂ የግጭት ምንጭ ሊሆን አይችልም ከሚለው አቋም ተነስቼ ነው። የዘጋቢ ፊልሙ ርዕስ በእንግሊዘኛው ስትራግል ኦቨር ናይል የሚል ሲሆን ኢቲቪ የተረጎመውም የአባይ ፍጥጫ በሚል ነው። የፊልሙ ችግር ከዚህ ይነሳል። የአልጀዚራን ቀልብ የሳበው ኢትዮጵያ የምትከተለው አባይ/ናይል ለሁላችንም በቂ ነው የሚለው የትብብር መንፈስ ሳይሆን ግብፅ የምትሰብከው የዜሮ ድምር ውጤት ነው። በግልፅም “ናይል የህይወትም የግጭትም ምንጭ ነው” ይላል። የህይወት ምንጭ የተባለው ለግብፅ ሲሆን የግጭት ምንጭ የተባለው ለሁለቱ ሀገራት መሆኑ ነው። የትብብር ምንጭ መሆን እንደሚችል ግን አያረጋግጥም።
ኢትዮጵያና ግብፅ ያላቸው ባላንጣነት እድሜ ጠገብ መሆኑን የሚገልፀው ይህ ፊልም ሁለቱም ሀገራት የስልጣኔ ምንጭ ከሆኑበት የጥንቱ ታሪካቸው ጀምሮ ተቀናቃኝ ሆነው መኖራቸውን ያሳያል። አፄ ኃይለስላሴ እና ገማል አብደል ናስር ሁለቱም ራሳቸውን የአፍሪካ ግንባር ቀደም መሪ አድርገው ስለሚወስዱ በያዟቸው ተቃራኒ የፖለቲካ አስተሳሰብ ልዩነት /ኢምፔሪያሊስትና ፀረ ኢምፔሪያሊስት/ ውስጥ ሆነው በተቀናቃኝነት መኖራቸውን ያትታል። ውጥረቱ በደርግ መንግስት ወቅትም መቀጠሉንና የዚህም ምንጩ መንግስቱ ኃይለማርያም ፊቱን ወደ ሶቪየት ሲያዞር አንዋር ሳዳት ደግሞ ወደ ምዕራባውያን በማዞሩ ሁለቱ ሀገሮች በሁለቱ የአለም ጎራዎች ማዶና ማዶ መሰለፋቸው እንደሆነ ያስታውሳል። አሁን ደግሞ ኢትዮጵያ አስቸጋሪ ፈተና ውስጥ ገብታለች ይላል የአልጀዚራው ጋዜጠኛ።እንደዘገባው “አሁን ኢትዮጵያ በሁለት አማራጮች የተወጠረች ሀገር ሆናለች። በአንድ በኩል ወንዙን ለልማት የማዋል በሌላ በኩል ደግሞ ከታችኞቹ የአባይ ተፋሰስ ጎረቤቶቿ ጋር ያላትን ግንኙነት በማሻከር መካከል ያሉትን አማራጮች በትኩረት ታያቸዋለች።”
እዚህም ላይ ዘገባው እውነትን አልያዘም ብዬ አልከራከርም። ጥያቄዬ ይህ እውነት ትብብርን በምንሻው በእኛ በኢትዮጵያውያን መዘገቡ ፋይዳው ምንድን ነው? የሚል ነው። የኔ ጥያቄ ለምን ያለፉትን የግጭት መንስዔዎቻችንን ከምናጎላ አዳዲሶቹን የትብብር አማራጮቻችንን አንተነትንም? የሚል ነው። አሁን አፄዎቹ የሉም፤ ደርግም ተገርስሷል። በምትኩ ያለው ‘በጠላቶች ተከብቤያለሁ’ ከሚል የቆየ ስሜት ራሱን አውጥቶ ከጎረቤቶቹ ጋር በጥቅም የተሳሰረ፤ ይህንንም ወደ ሌላ ታላቅ ምዕራፍ ለማሸጋገር እየሰራ ያለ መንግስት ነው። ታዲያ ፊልሙ ምነዋ ይህን ተግባራችንን ዘነጋው? ምነውስ ከጎረቤቶቻችን ጋር ያለንን ግንኙነት ሳናሻክር አብረን መበልፀግ ይቻላል የሚለውን ሶስተኛውን አማራጭ ሳያቀርበው አለፈ?
ወደ ሶስተኛው ምክንያቴ ልለፍ። በዚህ ዘጋቢ ፊልም ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም የሚጎዱ ነገር ግን በአግባቡ ምላሽ ያልተሰጠባቸው ሃሳቦች አሉ። አንደኛው ግብፃዊው የፖለቲካ ተንታኝ አብዱል ዋሂብ ያነሱት ሃሳብ ነው። “የቀድሞ ስምምነቶችን ማክበር አለብን። ይህ ለአለም አቀፋዊ የሀገራት ድንበርም የሚያገለግል አካሄድ ነው። ለምሳሌ ከነፃነት በፊት የነበሩ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ድንበሮችን መቀየር አንችልም። እነዚህ በቅኝ ገዢዎች የተከለሉ ድንበሮች ከነፃነትም በኃላ ህጋዊ ሆነው እንዲያገለግሉ ከስምምነት ተደርሷል። ስለዚህ በአባይ ዉሃ አጠቃቀም ዙሪያ የተፈረሙትንም ስምምነቶች በተመሳሳይ መልኩ ማየት ነው።” ይላሉ። የ1929ኙን ስምምነት መሆኑ ነው። ጋዜጠኛው ደግሞ “የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ግን እነኚህ ስምምነቶች የቅኝ ግዛት ቅሪት ስለሆኑ ተቀባይነት የላቸውም ሲሉ ይከራከራሉ” ይላል።
የኢትዮጵያ መከራከሪያ ግን ይህ ሊሆን አይችልም። የስምምነቱ አካል ስላልሆንኩ ለመቀበል የሚያስገድደኝ ምንም አይነት ህግ የለም ነው የምትለው ኢትዮጵያ። የቅኝ ግዛት ቅሪት በሚለው ከሆነማ አብዱል ዋሂብ እንዳሉት የድንበር ማካለሉን ተቀብለን ስምምነቶቹን እንቢ የምንልበት ምክንያት አይኖርም። አልጀዚራ ይህ ጠፍቶት ሳይሆን ኢትዮጵያ የያዘችውን ትክክለኛና ምክንያታዊ አቋም አለባብሶ ለማለፍ ስለፈለገ ነው።
በሌላ መልኩ “በአለም አቀፉ ህግ መሰረት የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ግድብ ከመስራታቸው በፊት የታችኞቹን ተፋሰስ ሀገራት የማማከር ግዴታ ስላለባቸው ለግብፅ ማሳወቅ አለባቸው” ይላሉ። ይህም እንደ ሃቅ ተቀባይነት አግኝቶ ያለፈ ነው በዘጋቢ ፊልሙ። እውነታው ግን ይህን አይነት አስገዳጅ አለም አቀፍ ህግ ያለመኖሩ ነው። ይልቁንም ህጉ የሀገራትን ሉዓላዊ መብት የሚያከብርና ፍትሃዊና በሌላው ላይ ትርጉም ያለው ጉዳት ያለማድረስ መርሆችን የሚያበረታታ መሆኑ ነው።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ1997 ያወጣው ለመጓጓዣነት የማያገለግሉ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች አጠቃቀም ስምምነት እኩል/ሚዛናዊ ተጠቃሚነትና ከፍተኛ ጉዳት ያለማድረስን ነው መሰረት የሚያደርገው። እኩል/ሚዛናዊ ተጠቃሚነት ደግሞ የህዝብ ብዛትን፤ የቆዳ ስፋትን፤ ሊታረስ የሚችል መሬትን፤ ሌሎች አማራጭ ምንጮችንና የዉሃውን ደህንነት መጠበቅ የሚባሉ ጉዳዮችን ያቀፈ ነው። ስትራግል ኦቨር ናይል ግን እነዚህን ጉዳዮች ዘወር ብሎ አላያቸውም።
ሌላው ግብፆች የሚመኩበትና እስካሁንም አወዛጋቢ የሆነው በአፄ ሚኒሊክና በብሪታኒያ መንግስት መካከል ተፈርሟል የሚባለው ስምምነት ነው። ይህንን የግብፆችን መከራከሪያ ነጥብ ሳያስተባብሉ እንደወረደ ከማቅረብ በላይ የኢቲቪን ወገንተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ጉዳይ አይኖርም። ፊልሙ ላይ እንዲህ ይላል። “እንግሊዝ እ.አ.አ በወርሃ ግንቦት 1902 ከአፄ ሚኒሊክ ጋር አንድ ስምምነት ተፈራረመች። በዚህ ስምምነት አፄ ሚኒሊክ የአባይ ወንዝ ወደ ግብፅ የሚያደርገውን ፍሰት የሚያሰናክል ወይም የዉሃውን መጠን የሚቀንስ ምንም አይነት ግድብ እንደማይገነቡ ቃል ገቡ።” የሚገርመው በቅርቡ በናይል ቲቪ በተካሄደ የቀጥታ ስርጭት ውይይት ላይም የቀድሞው የግብፅ የዉሃ ሚኒስትር ዶ/ር ናስር አደም ይችን ነጥብ አንስተዋታል።
አፄ ሚኒሊክ ፈርመውታል የተባለው ስምምነት ፕሮፌሰር አሊ አብዱላህ አሊ እንደሚሉት ቢያንስ በሁለት መሰረታዊ ነጥቦች የተነሳ በአሁኑ ወቅት ተቀባይነት የለውም። አንደኛ ስምምነቱን የሁለቱ ሀገራት የወቅቱ የዘውድ ም/ቤቶች አላፀደቁትም። ሁለተኛ የስምምነቱ የአማርኛና የእንግሊዝኛ ትርጉም ግጭት ፈጥሮ ስለነበር አፄ ሚኒሊክ በወቅቱ አልተቀበሉትም። አልጀዚራ ያዘጋጀውና ኢቲቪ የተቀበለው ዘጋቢ ፊልም ይህንን የግብፅን የክስ ነጥብ ያሳይና የኢትዮጵያን መከራከሪያ ነጥብ ግን አያስቀምጥም። በዚህም በህግ የመርታት አዝማሚያው ለግብፅ ያጋደለ እንዲመስል አድርጓል።
የመጨረሻውን ነጥቤን ላንሳ። እንደፊልሙ ከሆነ የኢትዮጵያን የአፈር ማዕድን ጠራርጎ የሚሄደው ደለል ለግብፃዊያን ሲሳያቸው ነው። ፊልሙ “ለም አፈር ለግብፃውያን ዋና ስጦታ ነው” ይልና ምክንያቱን ሲያብራራ መሬታቸው በለም አፈር ይበለፅግላቸውና አጥጋቢ ምርት ያገኛሉ ይላል። ይህን ከተቀበልን ኢትዮጵያ ‘ግድቤ ደለልን በመቀነስ የታችኞቹን ሀገራት ተጠቃሚ ያደርጋል’ የምትለው ድለላ /lip service/ ነው ማለት ነው። አልጀዚራ ይህን ይበል እንጂ እውነታው ግን እሱ አይደለም። ግብፅ የአስዋን ግድብን ከገነባች በኋላ ደለሉ በግድቡ የታችኛው ክፍል ላይ ስለሚተኛ ተጠቃሚ ሳይሆን ተጎጂ ነው የነበረችው። ስለዚህም የኢትዮጵያ አቋም ትክክል ተብሎ ነበር መወሰድ ያለበት።
ልብ በሉ፤ አሁን ልክ አይደለም የምለደው አልጀዚራን አይደለም፤ ኢቲቪን ነው። አልጀዚራማ ከሚዲያው ጥቅም ተነስቶ የሚፈልገውን መልዕክት አቅርቧል። እኔ የምተቸው የኢትዮጵያ የሆነውን ኢቲቪን ነው። ዘገባው ከላይ ያስቀመጥኳቸው የይዘት ጉድለቶች ሳሉበት ለምን ኢቲቪ አስተላለፈው? ነው የኔ ጥያቄ። ለአንድ ደቂቃ ማስታወቂያ በሺዎች የሚቆጠር ብር የሚቀበለው ኢቲቪ ለምን የአየር ሰዓቱን በዚህ ማቃጠል አስፈለገው? ነው የእኔ ጥያቄ። የኢትዮጵያን ጥቅም ማስጠበቅ የሚችል የፀዳ ዘጋቢ ፊልም በውስጡ ባለው የዶክመንታሪ ክፍል መስራት የሚችለው ኢቲቪ ለምን የአልጀዚራን ዥጉርጉር ፊልም መኮረጅ አስፈለገው? ነው የኔ ጥያቄ።
እያንዳንዱ ሚዲያ ሲቋቋም የራሱ ተልዕኮ ይዞ ነው። ለጥቅሙ የሚቆምለት ወገንም አለው። አልጀዚራ የኳታርን ብሔራዊ ጥቅም በሚጎዳ ተግባር ውስጥ እጁን አያስገባም። በአንፃሩ የኳታርን ሲያልፍ ደግሞ የአረቡን አለም አጀንዳዎች ከፍ ከፍ አድርጎ ያሰማል። ኢቲቪ የሚከተለው የሚዲያ ፍልስፍና ልማታዊ ጋዜጠኝነት ነው። በልማታዊ ዴሞክራሲ የፖለቲካ ኢኮኖሚ ውስጥ እንደመሆኑ በተለይ እንደ ኢቲቪ ያለ የህዝብ ሚዲያ ግልፅ ተልዕኮዎችን ይዞ መንቀሳቀሱ የማይቀር ነው። እናም የኢትዮጵያን ሕዳሴ ማብሰር ዋና ተልዕኮው ነው።
     ሁለቱ ተቋሞች በተልዕኮም በሚከተሉት ፍልስፍናም የማይታረቁ ባህሪዎች አሏቸው። ኢቲቪ ከአልጀዚራ ያገኘውን ዘገባ እንደወረደ ለአድማጭ ተመልካቹ የሚዘረግፍ ከሆነ ተሸውዷል ማለት ነው። አሁንም የሚታየኝ ይሄው ነው። ግድ የላችሁም፤ አልጀዚራ በውብ ምስሎቹና በማራኪ አቀራረቡ የተነሳ ኢቲቪን ሸውዶታል። ግን ለሌላ ግዜ ትምህርት ይሆነዋል ብዬ አስባለሁ።