Thursday, June 12, 2014

በሪያድ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት በገንዘብ እጥረት 3000 ህጻናትን በትኖ ሊዘጋ ነው ! ወላጆች ለልጆቻቸው መበተን ዲፕሎማቱን ተጠያቂ ያደርጋሉ !

በስድት አለም የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ህጻናት በተመጣጣኝ ዋጋ ተቀብሎ በማስተማር ከፈተኛ ስተዋጾ እያበረከተ የሚገኘው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ላለትፉት ሁለት አስርት አመታት ሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚመኩበት እና የሚኮሩበት ተቋም ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል። ከቅርብ ግዜ ወዲህ በወላጆች እና በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች መሃከል በተፈጠረው አለመግባባት ት/ቤቱ እንደተቛም ህልውናውን ጠብቆ ወደፊት መቀጠል እንደተሳነው የሚናገሩ ምንጮች ።  ሰሞኑን የት/ቤቱ የኪራይ ዘመን እና የት/ቤቱ ህጋዊ  ፈቃድ የግዜ ገደብ በመጠናቀቁን ተከትሎ በተቋሙ ህልውና ላይ የጋረጠው  አደጋ  አሳስቢ መሆኑን በመጥቀስ  ከወራት በፊት በማን አለብኝነት ት/ቤቱን በበላይነት ተቆጣጥረው እንዳሻቸው ሲዘውሩት የከረሙት በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሹማምንቶች በትምህርት ቤቱ ዙሪያ ተከሰቱ የተባሉትን የተወሳሰቡ ችገሮች ደረጃ በደረጃ መቅረፍ ተስኗቸው እራስቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን የፌታችን አርብ ጁን 13 2014 አስቸኳይ የወላጆች ስብሰባ መጥራታቸውን ይገልጻሉ።
  
በአምባሳደር መሃመድ ሃሰን አቀነባሪነት በዲያስፖራው ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር አስፈጻሚነት ወላጆች በት/ቤቱ ጉዳይ አንድነት እንዳይፈጥሩ በብሄር ከፋፍለው በማጋጨት ዲፕሎማቱ ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ  በሾማቸው የቦርድ አባላት ያለምንም ኦዴት የት/ቤቱ ገቢ እና ወጪው ሳይታወቅ በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ « ሪያል» ዘረፋ እንደተፈፀመበት የሚናገሩ እንዚህ ምንጮች ዛሬ ት/ቤቱ አመታዊ ኪራይ መክፈል ተስኖት ጉዳዩን ወደ ወላጆች ማምጣት እራስን ከተጠያቂነት ለማዳን ከሚደረግ እሩጫ ተለይቶ የማይታይ መሆኑንን ይናገራሉ። 3000 የሚሆኑ የስደተኛውን ማህበረሰብ ልጆች እንደሚያስተናገድ የሚነገርለት ይህ ት/ቤት ከእያንዳንዱ ተማሪ በወር እስከ 3 መቶ ሪያል በነፍስ ወከፍ እንደሚሰበስብ የሚገልጹት ውስጥ አዋቂዎች የት/ቤቱ ወረሃዊው ገቢ ብቻ   ት/ቤቱ የራሱ የሆነ ህንጻ በማስገንባት ከኪራይ ነጻ መሆን ያስችለው እንደነበር አስታውሰው ከባለቤቱ በላይ አዋቂ ሆነው ት/ቤቱን በሞግዜትነት በሃይል ሲያስተዳደሩ የከረሙት እነዚህ ዲፕሎማቶች የት/ቤቱ ወላጆች እና የአካባቢው ማህበረሰብ  በአንድ ወቅት ት/ቤቱን ከኪራይ ጥገኝነት ለመላቀቅ የራሴ ነው ብለው የሚመኩበትን ት/ቤት ለማስገንባት እንቅስቃሴ ላይ እያሉ በአምባሳደር መሃመድ ሃስነ ተዕዛዝ መታገዳቸውን ይናገራሉ ። 
ይህ በዚህ እንዳለ ለዚህ ተግባር የሚውል ከወላጆች ከአካባቢው ማህበረሰብ  ለመሰብሰብ ታቅዶ ከነበረው 10 ሚልዮን ሪያል « በአሁኑ የኢትዮጵያ ምንዛሪ ከ50 ሚልዮን የሚበልጥ ብር » ውስጥ ግማሽ ያህሉ መሰብሰቡን የሚያስታውሱ ወላጆች ለገዘቡ ደህነት ሲባል በወቅቱ  በአምባስደር መሃመድ ሃሰን ስም ከ 3 አመት በፌት አንድ ሳአውዲ አረቢያ የሚገኝ ባንክ ቤት ገቢ መሆኑን ይገልጻሉ። ዛሬ ት/ቤቱ እንደዚህ አይነት የተወሳሰቡ ችገሮች ውስጥ ባለበት ወቅት አመታዊ የኪራይ ገንዘብ አጥቶ አደጋ ላይ መውደቁን ለወላጆች ለማርዳት ዲፕሎማቱ እያሰሙ ያለው ጩሀት ተቀባይነት የሌለው እና ከ3000 በላይ የሆኑ ህጻናትን ሜዳ ላይ በትኖ ት/ቤቱን ለመዝጋት የሚደረገው ጥረት ከጀርባው  ድብቅ አጀንዳ ያለው መሆኑ ይነገራል ።
ከዚህ ባሻገር ዘንድሮ የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያወጣውን አዋጅ ለመተግበር  ማንኛውም መምሀር የመኖሪያ ፈቃዱ በት/ቤቱ ሰር እንዲሆን ለማስቻል ት/ቤቱን በእጅ አዙር በባለቤትነት የተቆጣጠሩት ዲፕሎማቶች በጀመሩት ዘመቻ ከት/ቤቱ ካዝና አህዙ በትክከል የማይታወቅ ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ያለምንም ማስረጃ ህገወጥ በሆነ መንገድ ወጪ መደረጉን የሚገልጹት ለጉዳይ ቅርበት ያላቸው ወገኖች  ለመምህራኑ ጉዳይ ማስፈፀሚያ ተመድቦል ተብሎ ለይስሙላ በቦርድ አባላቱ ከተነገረው 70 ሺህ ሪያል እና ለኮሚኒቲው ካፍቴርያ ድጎማ በብደር መልክ ተሰጥቷል ተብሎ ከት/ቤቱ ካዝና በሚስጠር ውጪ ከተድረገው ከ2 መቶ ዘጠናሺህ ሪያል ወይም « ከግማሽ ሚልዮን ብር » በተጨማሪ  ቁጥሩ በወል የማይታውቅ ጥሬ ገንዘብ የት እንደገባ እና ለምን አገልግሎት እንደዋለ በግልጽ እንደማይታወቅ  ይገልጻሉ ። 

ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በተለያዩ ዝቅተኛ ስራዎች ላይ ተመደበው ከሚሰሩ የውጭ ሃገር ዜጎች ያነስ ደሞዝ እይተከፈላቸው የስደት አለሙን ህይወታቸውን ለማሸነፍ የሚባዝኑት የት/ቤቱ መምህራን እና ሰራተኞች የመኖሪያ ፈቃዶቻቸውን በት/ቤቱ ሰር ለማድረግ ከያንዳንዱ መመህራን የወር ደሞዝ እስከ ሁለትሺህ እና ከዛ በላይ መቆረጡን ያረጋገጡ ምንጮች  መምህራኑ ህጋዊ ለመሆን ባላቸው ጉጉት ከሆድ ከማታልፍ ደሞዛቸው በየወሩ የህን ያህል ከፈሉ እይተባለ የሚጣልባቸው እዳ ከወር ደሞዛቸው ዝቅተኝነት  ጋር ተዳምሮ በኖራቸው ያስከተለውን  ቀውስ ለመታደግ ተጨማሪ ገቢ ፍለጋ በትርፍ ግዜያቸው የተለያዩ ተማሪዎችን በክፍያ በማስጠናት አሊያም ያለ እረፍት በተለያዩ የጉለብት ስራዎች ላይ ለምሰማራት መገደዳቸው በት/ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ አሉታዊ ተፀእኖ በማሳደሩ ወላጆች በት/ቤቱ ላይ የነበራቸው ተስፋ መጨለሙ ይነገራል። ይህ በዚህ እንዳለ የሳውዲ አረቢያ ት/ሚንስቴር መ/ቤት ቀደም ብሎ ማንኛውም  ተቋም በስሩ ት/ቤቶችን መከፈት ከፈለገ  ጥራቱን የጠበቀ በሳውዲ አረቢያ የት/ሚ/ር ህግ መሰረት የተለያዩ  ማስፈርቶችን ያሞላ ከኪራይ ነጻ የሆነ የግል ህንጻ ሊኖረው እንደሚገባ  ባወጣው መመሪያ መስረት በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒ ት/ቤት ዲዛይኑ  ለመጋዘን መዋል የሚገባው የመጸዳጃ  እና የተማሪ እረፍት ቦታዎችን ያላሞላ ከመሆኑም በላይ ህጻናቱ ይማሩበታል የሚባለው ህንጻ በማርጀቱ በተማሪዎቹ ህይወት ላይ ሊያስከትል የሚችለውን አሰቃቂ አደጋ  ከግመት በማስገባት   የሳውዲ እሳት አደጋ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ከፍል ከሳውዲ ትምህርት ሚ/ር ጋር በመተባበር የት/ቤቱ  ፈቃድ እንዲሰረዝ መወሰናቸውን ተከትሎ ት/ቤቱ በቀጣይ የትምህረት ዘመን የመማር ማስተማር ሂደቱን መቀጠል እንደማይቸል  ከት/ቤቱ የሚወጡ ሚስጥራዊ መረጃዎች ያመለክታሉ ። Ethiopian Hagere ጀድ በዋዲ      በውስጥ መስመራችን ያደረሰን 

Wednesday, June 4, 2014

አባ ዱላና ከንቲባ ድሪባ የቁም እስረኛ ሆኑ፣ ፓስፖርታቸው ተቀማ

“የኢህአዴግ በርዕዮተ ዓለም መበላላት ይፋ እየሆነ ነው”

አባ ዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኞች መሆናቸው ከተለያዩ ምንጮች እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልከተዋል። የጎልጉል ምንጮች ግን ኦህዴድ ውስጥ በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ግምገማ ሲጠናቀቅ በርካታ ባለስልጣኖች ክስ እንደሚመሰርትባቸው ተናግረዋል።

Photo: አባ ዱላና ከንቲባ ድሪባ የቁም እስረኛ ሆኑ፣ ፓስፖርታቸው ተቀማ
“የኢህአዴግ በርዕዮተ ዓለም መበላላት ይፋ እየሆነ ነው”
http://www.goolgule.com/aba-dulla-and-deriba/

አባ ዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኞች መሆናቸው ከተለያዩ ምንጮች እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልከተዋል። የጎልጉል ምንጮች ግን ኦህዴድ ውስጥ በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ግምገማ ሲጠናቀቅ በርካታ ባለስልጣኖች ክስ እንደሚመሰርትባቸው ተናግረዋል።

በቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አባ ዱላ ገመዳና በአቶ ድሪባ ላይ ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገር ጥለው እንዳይወጡ በሚል ነው። ጎልጉል በቅርቡ ካገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣኖች እንዳሉ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። ውሳኔው የተላለፈው ሰሞኑን የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን ለመተግበር የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መካተታቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ነው። ከሁለቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ ከፍተኛ የክልልና የዞን የኦህዴድ አመራሮችም በደህንነት ቅርብ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ ተሰምቷል። ካገር መውጣት የማይችሉም አሉ።

አባ ዱላ /ጃርሳው/

አባ ዱላ ኦሮሚያን ሲረከቡ በማክረር አካሄድ የሚታወቁት አቶ ጁነዲን ያዋቀሩትን ካቢኔ በመበተን ሥራቸውን አንድ ብለው ጀመሩ። አዲስ ካቢኔ ሲገነቡ የመረጡት አዲስ የዩኒቨርስቲ ተመራቂዎችንና በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የተቀናቃኝ (የተቃዋሚ) ፓርቲ አባላትን በማስኮብለል ነበር። ህወሃት ለሁለት በተበረገደበት ወቅት ለአቶ መለስ ቡድን ድጋፍ በመስጠት ቅድሚያ የያዙት አባ ዱላ ባስቀመጡት ውለታ መሰረት ኦሮሚያ ላይ ያሻቸውን እንዲያደርጉ የሟቹ መለስ ድጋፍ ነበራቸው። በዚህም ድጋፍ ሳቢያ ኦሮሚያ ላይ የሚፈልጉትን ሲያደርጉ ከተባረሩት መካከል የአሁኑ ፕሬዚዳንት ሙክታር ከዲር ይገኙበታል።

“አትደግፉን ነገር ግን የክልሉን ልማት አታደናቅፉ” በማለት አዲስ የመለመሏቸው የተለያየ አመለካከት ያላቸው አዳዲስ የኦህአዴድ አባላት ኦሮሚያን ከአባ ዱላ እጅ ተረከቡ። አባ ዱላ ፍጹም ነጻነት ይሰጡ ስለነበር ካድሬው ወደዳቸው። ስማቸው ተቀይሮ መለያ ተሰጣቸው፤ “ብራንድ” ሆኑ – “ጃርሳው” ተባሉ። በካቢኔያቸውና በሳቸው መካከል የነበረው ፍቅር በነደደበት ወቅት አባ ዱላ ክልሉን እንደሚለቁ ተሰማ። ባለፈው ምርጫ አባ ዱላ ለፌዴራል እንጂ ለክልል እንደማይወዳደሩ ይፋ ሲደረግ ካድሬው ገነፈለ። “የኢህአዴግ ምክር ቤትን ውሳኔ አንቀበልም” በማለት ተቃወመ። ከአንዴም ሁለት ጊዜ ስብሰባ ቢካሄድም ከስምምነት ላይ ሊደረስ ባለመቻሉ ተበተነ። በመጨረሻም ራሳቸው አባ ዱላ በመሩት ስብሳባ ካድሬውን ተማጽነው ነገሩ ረገበ። ይሁን እንጂ ቅርሾ ግን ነበር። ይህንኑ አስመልክቶ “ኦህዴድ/ኢህአዴግ በመደብ ትግል መተላለቅ ጀመረ” በማለት ዘግበን ነበር።

አባ ዱላ ኦሮሚያን ሲመሩ ቆይተው ሲመሻሸ “ይህንን ቤት ይዤ ለመታገል አይመቸኝም” በማለት ቦሌ ያስገነቡትን አስገራሚ ህንጻ ለኦህዴድ አስረከቡ። በከፍተኛ ሙስና ይታሙ ስለነበር ተናዘውና ገብረው ታለፉ። ለፌዴራል ተወዳድረው አፈ ጉባኤ ለመሆን በቁ። በወቅቱ የወ/ሮ አዜብ ድጋፍ ቢኖራቸውም የሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲን የቀኝ እጅ የሆኑ ባለስልጣኖች ግን ጠምደዋቸው ነበር። ሙክታር አህመድ አንዱና ዋናው ነበሩ። ከላይ በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ አባ ዱላን ከሚቃወሙ መካከል በግንባር ቀደምትነት የሚቀመጡ ናቸው።

በዚህ አጣብቂኝ ውስጥ አልፈው እዚህ የደረሱት አባ ዱላ ሰፊ ቁጥር ያላቸውን ተማሪዎች ህይወት የቀጠፈውን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አስመልክቶ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ተማሪዎችን ከወ/ሮ አስቴር ማሞ ጋር በመሆን አነጋግረው ነበር። በወቅቱ የተማሪዎቹ ጥያቄ ፍትሃዊ እንደሆነ ሲመሰክሩ፣ ይህንኑ ምስክርነታቸውን ለተለያዩ የአገር ውስጥና የውጪ አገር ሚዲያዎች አሳውቀውም ነበር። አያይዘውም ነፍስ ያለ አግባብ ያጠፉ እንደሚጠየቁ ቃል ገቡ።

የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት አባ ዱላ ይህንን ከተናገሩ በኋላ ከፍተኛ ወቀሳ ተሰንዝሮባቸዋል። “ረብሻውን ያስነሱት ራሳቸው የኦህዴድ ካድሬዎች ናቸው” ከሚል ድምዳሜ የደረሰው ኢህአዴግ ችግሩ ከተፈጠረ በኋላ ሰፊ የስለላ ስራ አከናውኗል። “ጥፋተኞቹን ለህግ እናቀርባለን” በማለት መግለጫ ያወጣው ኢህአዴግ በቀጣይ የሚያስራቸውና የሚከሳቸው ባለስልጣኖች አሉ። ምንጮቹ በተለይ አባዱላና የአዲስ አበባ ከንቲባ የሆኑት አቶ ድሪባ ኩማ ላይ ስለሚወሰደው ርምጃ ያሉት ነገር ግን የለም። ክስ ከተመሰረተባቸውና ምርመራው በሰንሰለት ታች ድረስ ከዘለቀ የኦህአዴድ የታችኛው መዋቅር ሊናጋ እንደሚችል ግን ግምታቸውን አኑረዋል። ለምሳሌ ያነሱት ሽፈራው ሽጉጤን ነው። ሽፈራው ሽጉጤ በሙስና እንዲከሰሱ ከተወሰነ በኋላ የታለፉት “የሲዳማ ብሔረሰብ ይነሳል” በሚል እንደሆነ ያወሱት ምንጮች “ክስ ተመስርቶ ምርመራው ቢካሄድባቸው ወ/ሮ አዜብም አሉበት ሲሉ አስቀድመው በምክር ቤት ይፋ በማድረጋቸው ዝምታ ተመርጧል”።

ኦህዴድን ወደ ታች ማዘዝ እንደ ቀድሞው አይቀልም

አዲስ አበባን የሚያሰፋው አዲሱ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዲሆን ሀሳብ ሲቀርብ ድፍን የኦህዴድ ምክር ቤትና ካቢኔ ተቃውሞ አሰምቷል። በክልሉ ምክር ቤት ደረጃም የተያዘው አቋም ተመሳሳይ ነው። ይህንን እውነት የሚያነሱ ክፍሎች ኢህአዴግ/ህወሃት ስንቱን አስሮና ለፍርድ አቅርቦ ይችለዋል ሲሉ ጥያቄ ይሰነዝራሉ” ቀደም ሲል በምርኮኞች ስብስብ የተቋቋመው ኦህዴድና አሁን ያለው ኦህዴድ የተለያዩ መሆናቸውን ኢህዴግ ችግር ሊገጥመው እንደሚችልም ግምታቸውን ያስቀድማሉ።

አሁን ያለው ኦህአዴድ ከምርኮ አስተሳሰብ የተላቀቀ። አዲስ ትውልድ የተካተተበት፣ በጎሳ አስተሳሰብ የተቃኙ፣ ህወሃት በሚፈልገው መጠን ከመታዘዝ በላይ ወደ ራሳቸው ደምና ጎሳ የተሳቡ፣ ይህንኑ አስተሳሰብ እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ የተከሉ በመሆናቸው የተወሰኑ የበላይ አመራሮችን በማሰር ችገሩ ሊፈታ እንደማይችል ሰፊ አስተያየት እየተሰጠ ነው። ለዚህም ይመስላል ኢህአዴግ በመደብ መተላላቅ መጀመሩ ይፋ እየሆነ የመጣው።

የመጨረሻው መጀመሪያ

ለጊዜው ይፋ ሆኑ መረጃዎች እንደሚያመክቱት አባዱላና አቶ ድሪባ ኩማ ካገር መውጣት አይችሉም። የተጀመረው ግምገማ ተጠናቆ የሚሆነው ሳይታወቅ በቅርብ ክትትል ስር ናቸው። የጎልጉል ምንጮች እንደጠቆሙት የዞንና ወረዳ መዋቅሮች ላይ ርምጃ ለመውሰድ  ስጋት አለ። ካድሬው ዘንድም መደናገጥ ተፈጥሯል። ህወሃት ውስጥም የአቋም መለያየት ተከስቷል፡፡ በአንድ ወገን ካድሬው እንዳይሸፍትና በቀጣዩ ምርጫ ኢህአዴግን አሳልፎ እንዳይሰጠው ርምጃው የተለሳለሰ መሆን አለበት እየተባለ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ግለ ሂስ በማካሄድ ነገሩን የማርገብና ምርጫውን የማለፍ ስልታዊ አካሄድ አለ። ይሁን እንጂ ኦህዴድ እየተለማመደ ያለው አካሄድ ሌሎችን ትምህርት በሚሰጥ መልኩ ካልታረመ ወደ ፊት ችግሩን ያገዝፈዋል የሚል አቋም የሚያራምዱ መኖራቸው ታውቋል። ህወሃት በዚህ ደረጃ አቋም ለመያዝ አለመቻሉና በርዕዮተ ዓለም መከፋፈል መጀመሩ ለዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ የዘራው መርዝ መልሶ ራሱን ሊያጠፋው አፉን መክፈቱ የሚጠቁም ነው፡፡ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት “ኢህአዴግ በርዕዮተ ዓለም መበላላት መጀመሩ ይፋ እየሆነ ነው” የሚለው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚነሳ ዓቢይ ጉዳይ ሆኗል፡፡
***********************
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Saturday, May 31, 2014

አረብሳት ከኢትዮጵያ የሞገድ አፈና እየተደረገብኝ ነው አለ

አረብሳት ከኢትዮጵያ የሞገድ አፈና እየተደረገብኝ ነው አለ
ተቀማጭነቱን በሳዑዲ አረቢያ ያደረገውና በርካታ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚያሰራጨው የአረብ ሳተላይት ኮሙኒኬሽን ተቋም (አረብሳት) ካለፈው ሳምንት ጀምሮ እየተፈጸመበት ያለው ዓለማቀፍ የሳተላይት ሞገድ አፈና (Jamming) ምንጩ ከኢትዮጵያ መሆኑን እንዳረጋገጠ ገለጸ፡፡
ሳትኒውስ የተባለው የአገሪቱ የዜና ምንጭ ከትናንት በስቲያ እንደዘገበው፣ አረብሳት በሚያስተላልፋቸው በርካታ የቴሌቪዝን ጣቢያዎቹ ላይ መታየት የጀመረውን የስርጭት መስተጓጎል መነሻ ለማወቅ ባደረገው በረቂቅ ቴክኖሎጂ የታገዘ ጥናት፣ ከኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚነሳና ሆን ተብሎ የሚፈጸም የሳተላይት ሞገድ አፈና (Jamming) እየተደረገበት መሆኑን ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡ ይህን መሰሉ ህገወጥ ድርጊት መፈፀሙ መሆኑ እጅግ እንዳሳዘነው ያስታወቀው አረብሳት፤ ከኢትዮጵያም ሆነ ከኤርትራ የሚተላለፍ ምንም አይነት ስርጭት ሳይኖረው፣ የሳተላይት ሞገድ አፈና መደረጉ እንቆቅልሽ እንደሆነበት ገልጿል፡፡ 
የሳተላይት ሞገድ አፈናው፣ ምናልባትም ከሁለቱ አገራት የአንዱ ተቀናቃኝ የሆኑና ከአረብሳት ሳተላይቶች አቅራቢያ በሚገኙ ሳተላይቶች አማካይነት የሚሰራጩ የቴሌቪዝን ጣቢያዎችን ለማፈን የታለመ ሊሆን እንደሚችል ያለውን ግምትም ሰጥቷል፡፡
እየተፈጸመበት ያለውን ህገወጥ ተግባር ለመመከት በብሄራዊና በአለማቀፍ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን የገለጸው አረብሳት፣ ጉዳዩን ለዓለማቀፉ የቴሌኮምኒኬሽን ህብረት እና ለአረብ ሊግ ማሳወቁንም ጠቅሷል፡፡አረብሳት ጉዳዩን በቀጣይ ከመረመረ በኋላ፣ ከአለማቀፍ የህግ  ተቋማትና የአገሪቱ የህግ አካላት ጋር በመቀናጀት ወደ ህግ እንደሚያመራና እየተቃጣበት ባለው የሳተላይት ሞገድ አፈና ለደረሰበትም ሆነ ለሚደርስበት ጉዳት ካሳ እንደሚጠይቅ  ማቀዱን ተናግሯል፡፡ከሁለት አመታት በፊት ከኢትዮጵያ ተመሳሳይ የሳተላይት ሞገድ አፈና እንደተፈጸመበትም አስታውሷል።                          ምንጭ አዲስ አድማስ 

Tuesday, May 27, 2014

የመደብ ወይስ የብሄር ጭቆና?!

እንዲህ ተጠይቋል

“ባለፉ ስርዓታት የነበረ የማሕበረ ፖለቲካ መዋቅር የመደብ የትግል (ጭቆና) መሰረት ያደረገ ነበር ወይስ ብሄር?”
ባለፉ ስርዓታት ጭቆና ነበረ (አሁንም አለ)። በኢትዮጵያ ታሪክ በህዝብ የተመረጠ ህዝብን ለማገለግል የተነሳ መንግስት አልነበረም (የለም)። ስለዚህ ጭቆና አለ። ጭቆናው ምን መሰረት ያደረገ ነው? ብሄር ወይስ መደብ? በኔ እምነት ጭቆናው ከሁለቱም ዉጭ ነው። በኢትዮጵያ የመደብ ጭቆና አልነበረም (የለም)፤ የብሄር ጭቆናም አልነበረም (የለም)። የነበረው (አሁንም ያለው) ጭቆና የኤሊት (Elite) ጭቆና ነው።
እስካሁን ድረስ የመደብ ፖለቲካ የለንም። የመደብ ፖለቲካ ከሌለ የመደብ ጭቆናም የለም። የብሄር ጭቆናም አልነበረም፣ የለም፣ ሊኖርም አይችልም። የመደብ ጭቆና ግን ለወደፊቱ ሊኖር ይችላል።
ያለፉ የኢትዮጵያ ገዥዎች ስልጣን ለመያዝ እንዲሁም በስልጣን ለመቆየት ሲሉ በህዝቦች ላይ በደል አድርሰዋል። በደል ሲያደርሱ ብሄር ወይ መደብ መሰረት አድርገው አይደለም። መደብ ጭራሽኑም አልነበረም፣ የለም። ብሄር ነበር፤ ግን ጭቆናው ብሄር መሰረት ያደረገ ሳይሆን ስልጣን መሰረት ያደረገ ነበር፣ ነው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ Class Based Or Nation Based Struggle ሳይሆን Elite vs People Based Power Struggle ነው።
ገዥዎች ስልጣን መያዝና እስከ ህልፈታቸው በስልጣን መቆየት ይፈልጋሉ። ለስልጣናቸው ሲሉ ታድያ ይደግፈናል የሚሉትን የሕብረተሰብ ክፍል ይጠቅማሉ፤ ለስልጣን አደጋ ነው በሚሉት ህዝብ ወይ ግለሰብ ደግሞ ጉዳት ያደርሳሉ፤ ስልጣናቸውን ለማጠናከር። ግን በፖለቲካ አንድን የሕብረተሰብ ክፍል መጥቀም አይቻልም፣ ይከብዳልና። ስለዚህ በሕብረተሰቡ ስም የተወሰኑ ግለሰቦች እንዲጠቀሙ ይደረጋል። ግለሰቦቹ ሲጠቀሙ የመጡበትን ሕብረተሰብ እንደተጠቀመ ተድርጎ ይታሰባል: ለፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ሲባል። ህብረተሰቡ በስልጣን ላይ ያለ ስርዓት “የኛነት” ስሜት ያሳድራል። ለዚህም ፕሮፓጋንዳ ይሰራል። ምክንያቱም የተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ ነው መጥቀም የሚቻለው። ለስልጣን የሚረዳው ግን አብዛኝው ህዝብ ነው። ተጠቃሚ ግለሰቦች ታማኝ የስርዓቱ አገልጋዮች ይሆናሉ። በነሱ ታማኝነት ስርዓቱ ዕድሜው ያራዝማል።
ለስልጣን አደጋ የሚሆን ግለሰብ ወይ ማሕበረሰብ ደግሞ የጥቃት ዒላማ ይሆናል። የስልጣን ዒላማ የሚሆነው በመደቡ አልነበረም (በመደቡ ዒላማ ሊደረግ ይችላል ግን መደብ አልነበረም)። በብሄሩም አልነበረም። በግዜው ካልተመቱ የስልጣን ስጋት ይሆናሉ የተባሉትን ግለሰቦች ወይ የሕብረተሰብ ክፍሎች ይጠቃሉ፤ ብሄራቸው ምን ይሁን ምን። ግን በኢትዮጵያ ታሪክ አንዳንድ ብሄሮች የከፋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ለምን? በብሄራቸው ምክንያት? አይደለም። ለስርዓቱ ታማኝ አይደሉም፤ ስጋት ይሆናሉ ስለተባሉ ብቻ ነው።
በኢትዮጵያ ታሪክ የመጎዳትም የመጠቀምም መስፈርት ብሄር ወይ መደብ አይደለም፤ የፖለቲካ ታማኝነት (Political Patrimonial-ism) ነው። በኢትዮጵያ የፖለቲካ ልምድ መሰረት የፖለቲካ ታማኝነት የሚገናኘው ከብሄር ጋር ነው። ሙሉ በሙሉ ባይባልም አንድ ዓይነት ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች የበለጠ ይተማመናሉ (ምክንያቱም ፖለቲካችን መርህ መሰረት ያደረገ ሳይሆን ስሜት መሰረት ያደረገ ነው። በስሜት መነዳት ደግሞ አለመሰልጠን ነው)። አማርኛ ተናጋሪ ስልጣን ከያዘ አማርኛ የሚናገረውን (ሌላ ቋንቋ ከሚናገር) የበለጠ ያምናል። ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞን የበለጠ ያምናል። ትግርኛ ተናጋሪ ትግራዋይን የበለጠ ያምናል። በዚህ መሰረት አማራኛ ተናጋሪ ስልጣን ሲይዝ አማራዎችን ያስቀድማል (ለስልጣኑ ሲል)። ሌሎች ደግሞ ቅሬታ ያድርባቸዋል። ከዛ ለስርዓቱ ታማኝ አይሆኑም። ታማኝ ካልሆኑ በጠላትነት ይፈረጃሉ። በጠላትነት ሲፈረጁ ተጎጂ ይሆናሉ። እነዚህ የስርዓቱ ተጠቃሚ የሚደረጉ ታማኞች ግለሰቦች ናቸው። ብሄር ሙሉ ተጠቃሚ ማድረግ አይቻልምና። ተጎጂዎች ግን ብሄር ሙሉ ወይ የሀገር ህዝብ በሙሉ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለዚህ ተጠቃሚዎች ታማኝ ግለሰቦች ናቸው። ተጎጂዎች ግን ብሄር ሊሆኑ ይችላሉ። አንድን ብሄር ሌላኛው ብሄር እየበደለ ነው ይባላል። በዳዮቹ ግን ኤሊቶች (elites) ናቸው። ይህን ነገር ጉዳዩ የብሄር ጭቆና ያስመስለዋል። የብሄር ጭቆና ሊኖር ግን አይችልም።
ስለዚህ ባለፉ ስርዓታት (አሁንም ጭምር) በህዝቦች የሚደርስ በደል አለ። ይህንን በደል ብሄሮች የሚፈጥሩት አይደለም። ያለው በደል በብሄሮች ላይ የተፈፀመ የelites በደል ነው። ኦሮሞዎች የተበደሉ ኦሮሞ ስለሆኑ አልነበረም። ለተመሰረተው ስርዓት ተቀብለው አሜን ብለን እንዲገዙ ለማድረግ የተቃጣ ጥቃት ነው የተፈፀመባቸው። ስለዚህ ጥቃቱ ስልጣን መሰረት ያደረገ ነው። ዒላማው የፖለቲካ ታማኝነትን መሰረት ያደረገ ነው።
አማርኛ ተናጋሪ ንጉሶች ታማኝ ባልሆነ ማንም ሰው እርምጃ ይወስዳሉ። ለዚህም ነው በሁሉም ህዝቦች (አማራን ጨምሮ) በደል የደረሰው። ትግርኛ ተናጋሪ ገዥዎች ታማኝ ባልሆነ ማንኛውም ሰው እርምጃ ይወስዳሉ፤ ለስልጣን ሲሉ። ምሳሌ ህወሓት የትግራይ ልጆች በሆኑ እነ ስየ አብርሃ፣ አውዓሎም ወልዱ፣ አስገደ ገብረስላሴና ሌሎች ታጋዮች ላይ መጥፎ እርምጃ የወሰደው እነኚህ ሰዎች ትግርኛ ተናጋሪ ስላልነበሩ አይደለም። ለስርዓቱ ታማኝ ስላልሆኑ እንጂ።
ስለዚህ በኢትዮጵያ ምድር የደረሰውን እንዲሁም እየደረሰ ያለው ጭቆና ብሄር ወይ መደብ መሰረት ያደረገ ሳይሆን የፖለቲካ ታማኝነት መሰረት ያደረገ ነው። ስለዚህ የኢትዮጵያውያን ጭቆና የብሄር ወይ የመደብ ሳይሆን የፖለቲካ ነው።
Aseged Tamene

Friday, May 23, 2014

የታንዛኒያ አልቢኖ ጎሳ አስገራሚ ኑሮና በህይወታቸው የተጋረጠው አስቃቂ ፈተና ….

(አድማስ ሬዲዮ አትላንታ እንዳቀናበረው)
በታንዛኒያ ከሚገኙት ጎሳዎች መካከል አልቢኖዎች ይጠቀሳሉ። አልቢኖዎች በተለይ የሚጠቀሱት የቆዳቸው ንጣት ከሌሎች ጠቆር ካሉ ታንዛኒያውያን ስለሚለያቸው ነው። ንጣታቸው የፊታቸው ቆዳ ብቻ ሳይሆን ጸጉራቸውም ጭምር ነው። ከህጻን እስከ አዋቂ ባጭሩ የአልቢኖ ጎሳ አባላት ሙሉ በሙሉ በለምጽ የተሸፈነ ዓይነት መልክ አላቸው። እናም ህይወታቸው በታንዛኒያ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል። እስቲ ታንዛኒያ እንሂድና እንያቸው ……
አንዲት አልቢኖ ሴት ፣ ህጻን ልጇን ይዛ ሳር ላይ እያሯሯጠች ታጫውታለች። ጓደኞቿ አጠገቧ ሆነው ያያሉ። ካሜራ የሚያነሱ ሰዎች ከበዋቸዋል - እነሱም ለካሜራው ፈገግ ማለትን ለምደዋል። እንደ ልዩ ሰው ስለሚታዩ ሁሉም ፎቶ ያነሳቸዋል።

ፎቶው ግን ለነሱ አስቸጋሪ አልነበረም። የተቸገሩትና ዘራችን ሊጠፋ ነው እስከማለት ያደረሳቸው ግን አሳ አጥማጆች፣ ማዕድን አውጪዎችና የውሸት ፈዋሾች ያሉበት ድረስ እየመጡ በድብቅ ስለሚገድሏቸው እንጂ። የሚገድሏቸውም የአልቢኖ ጎሳ አባላትና ለየት ያለ ነጭ መልክ ስላላቸው ብቻ ነበር።
ብዙዎቹ ታንዛኒያውያን የመናፍስት ጎሳ አባላት ወይም የማይታዩት ጎሳዎች ሲሉ ይጠሯቸዋል። አንዳንድ ጊዜማ ከውጭ ብቻ ሳይሆን ከራሳቸው ጎሳ አባላትም ግድያ ይፈጸምባቸዋል። ግድያው የሚፈጸመው የውስጥ አካላቸውን አውጥቶ ለመሸጥ ነው፣ ይህም የሚሆነው በታንዛኒያ የነዚህ የአልቢኖዎች የውስጥ አካል ገድ አለው፣ ሃብትና ዕውቀት ያስገኛል ተብሎ ስለሚታመን ነው።
የቸገረው የታንዛኒያ መንግስት ለነዚህ ለአልቢኖዎች ለብቻ መጠለያ በመስራት ልጆቻቸው እዚያ ገብተው ራሳቸውን በራሳችው እንዲመሩና እንዲያስተዳደሩ እስከማድረግ ደርሷል። ከዚያም አልፎ በታንዛኒያ መንግስት ፓርላማ ውስጥ አንድ የአልቢኖ ተወላጅ የፓርላማ አባል ሆኖም በ2008 ዓ.ም ተመርጦ ድምጻቸውን እንዲያሰማ ተደርጓል።
ችግሩ ግን በቀላሉ የሚለቅ አይደለም። አንዳንድ ጊዜ ራሱ የአልቢኖ ቤተሰብ አባወራ የራሱን ልጆች በመግደል የውስጥ አካላቸውን በሺዎች ለሚቆጠር ዶላር የሚሸጥበት ጊዜ ያጋጥማል።
አሳ አጥማጆች ፣ የአልቢኖዎች ጸጉር በማጥመጃ መረባቸው ላይ ከተቋጠር ብዙ ዓሳ እንይዛለን ብለው ስለሚያምኑ ለጸጉራቸው ሲሉ ይገድሏቸዋል። ማ ዕድን አውጪዎች ፣ የአልቢኖዎች አጥንት በርካታ አልማዝና እንቁ ያስገኝልናል ብለው ሰለሚያምኑ ይገድሏቸዋል። የውሸት ፈዋሾችና የሃሰት የመንደር ሃኪሞች የአልቢኖዎች ብልት፣ የሌላውን ለወሲብ አልታዘዝ ያለ ብልት ይፈውሳል ብለው ስለሚያምኑ ገድለውም ሆነ አስገድለው ብልቶቻቸውን ይወስዳሉ። እናም የአልቢኖ ጎሳዎች ይህን ሁሉ የመቋቀም ፈተና አለባቸው።
አልቢኖዎች 48 ሚሊዮን ከሚሆነው የታንዛኒያ ህዝብ መቶ ሺህ ያህል ቁጥር እንዳላቸው የአልቢኖዎቹ ተወካዮች ይናገራሉ። በየጫካው ተሰባጥረው የሚኖሩትንና ምንም መከላከያ የሌላቸው የነዚሁ አልቢኖዎች ዘር ከመጥፋቱ በፊት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተከፈቱላቸው መጠለያ ጣቢያዎች ለወደፊት ትውልዳቸው መቀጠል ሊጠቅም እንደሚችል የብዙዎች ግምት ነው።

አንዳንድ ጊዜ ራሳቸው አልቢኖዎች ርስ በርስ ተፈራርተው ይኖራሉ፣ አንዳንድ ጊዜ የአልቢኖ ሴቶች ሲያረግዙ ቶሎ ያስወርዳሉ፣ ምክንያቱም የሚወልዷቸው ህጻናት የዚሁ ችግር ቀማሽ ይሆናሉ ብለው ስለሚሰጉ ነው።
በ2013 ዓ.ም በአንድ ጉዳዩን በሚያጠና ድርጅት አማካኝነት ይፋ የወጣ ታሪክ እንደሚያወሳው፣ ከወላጆቿ የተለየች የ17 ዓመት ወጣት አልቢኖ ከ እናቷ ጋር እንድትገናኝ ተደረገ። ታሪኳ እንደዚህ ነው፣ ..
ይህች ወጣት እንደተወለደች አባቷ የፈጣሪ ስጦታ አገኘሁ ብሎ ደስ አለው፣ ከጊዜ በኋላ ግን እሷን ገድሎ አካሏን ለመሸጥ እንደሚፈልግ እናቷ ደረሰችበት። 13 ዓመት እስኪሞላትም እናት እየጠበቀቻትና አባትን እያዘናጋች አቆየቻት፣ 13 ዓመት ሲሞላት ግን ጥቃት እንዲያደርሱባት የመለመላቸውን ሰዎች ይዞ መጣ፣ በዚህ ጊዜ እናትና የ እናቷ ወላጆች ህጻኗ ላይ ሊደርስ የታቀደውን አፍኖ መውሰድና መገደል ለመከላከል ትግል ገጠሙ፣ በዚህ ጊዜ እሷ ስታመልጥ አያቶቿ ግን ህይወታቸው አለፈ።
ወጣቷ እንደምትለው ለጊዜው ታምልጥ እንጂ፣ ያን ጊዜ በ አ እምሮዋ የተቀረጸው ነገር ዛሬም ድረስ ያስጨንቃታል። ስለ አልቢኖዎች ብዙ ነገር ይባላል። አንዳንድ ታንዛኒያውያን “አልቢኖዎች እንደዚህ ነጭ የሆኑት ጥንት የአልቢኖዎች ሁሉ እናት የሆነችው ሴት ከፈረንጅ ጋር በመተኛቷ ነው” ብለው ያምናሉ።
ሆነም ቀረ እነዚህ ለየት ያለ መልክ ያላቸው የአልቢኖ ዝርያዎች በአጉል ዕምነት በተዋጡ ሰዎች እየተገደሉና የሰውነት አካላቸው እየተቆረጠ ለገበያ እየቀረበ ነው። ምናልባት ከጊዜ በኋላ አልቢኖዎች ከምድረ ገጽ ይጠፉ ይሆን?                     

በአባይ ጉዳይ ኃያላኑ በግብጽ ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው የጫናው መነሻ አነጋገሪ ሆኗል

ምዕራባውያን ሃያላን አገሮች ግብጽ በአባይ ዙሪያ የድርድር ጠረጴዛ ላይ እንድትቀመጥ ጫና እያደረጉ መሆኑ ተሰማ፡፡ ዜናውን የዘገበው አልአህራም ቃል በቃል ግብጽ ላይ ጫና ተፈጠረ ብሎ ባይጽፍም ከዜናው ለመረዳት እንደተቻለው ግብጽ ላይ ጫና እየተደረገባት ነው፡፡ ሃያላኑ ግብጽ ላይ እያሳደሩት ያለው ጫና መነጋገሪያ ሆኗል፡፡

እንደ ጋዜጣው ዘገባ ያለፈው ቅዳሜ የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ ጉዳይ ለመደራደር አገራቸው ፈቃደኛ መሆኗን ማሳወቃቸውን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ይህንን መግለጫ ከመስጠታቸው በፊት የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት የውሃ ሃብት ልዩ አስተባባሪ ከሆኑት አሮን ሳልዝበርግ እንዲሁም ከአውሮጳ ኅብረት ልዩ ልዑክ አልክሳንደር ሮንዶስ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡

በተለይ የአሜሪካው ተወካይ ሳልዝበርግ ወደ ግብጽ ከመሄዳቸው በፊት አዲስ አበባ ላይ ቆይታ አድርገው ከኢህአዴግ ባለሥልጣናት ጋር ግድቡን በተመለከተ ውይይት ማድረጋቸው አብሮ ተዘግቧል፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ በምን ነጥቦች ላይ እንደተደራደረ የተገለጸ ነገር ባይኖርም የአሜሪካው ባለሥልጣን ወዲያው ወደ ግብጽ እንደበረሩ ግብጽ ድርድር መፈለጓ መገለጹ የበርካታዎችን ትኩረት የሳበ ጉዳይ ሆኗል፡፡

በተያያዘ ዜና ሪፖርተር እሁድ ባስነበበው ጋዜጣ ላይ እስራኤል በኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት ሥራ የመሰማራት ዕቅድ እንዳላት ዘግቧል፡፡ እስካሁን ድረስ እስራኤል በኃይል ማመንጨት ሥራ ውስጥ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳለት ሲጠቀስ የቆየ ቢሆንም ከዚሁ ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎች ሲነሱ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም እንደ ሪፖርተር ዘገባ ከሆነ በኢትዮጵያ የፖታሽ ፕሮጀክት 30በመቶ ባለድርሻ የሆኑትን የሚስተር ኢዳን ኦፈር ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዘርፍ የመሰማራት ዕቅድ እንዳላቸው ጠቅሷል፡፡

እንደ ዜናው ከሆነ እስራኤል የምትሰማራበት የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ “የውኃ፣ የጂኦተርማል ወይም የንፋስ መሆኑን” በግልጽ እንዳላሳወቀች ነገር ግን ጥናቱ በኩባንያው ቴክኒክ ቡድን በኩል እንደሚካሄድ የኩባንያው ባለቤት መናገራቸውን ጨምሮ ዘግቧል፡፡ ሚስተር ኦፈር የሚመሩት ኢዝራኤሊ ኬሚካልስ የተባለው ኩባንያ በማዳበሪያና መሰል ምርቶች ላይ የተሠማራ ሲሆን የማዕድን ማውጣት ተግባሩን በእስራኤል፣ በአሜሪካ፣ በአውሮጳና ቻይን ያካሂዳል፡፡ ከኩባንያው አክሲዮን ሁለተኛው ከፍተኛ ባለድርሻ የካናዳው የፖታሽ ኮርፖሬሽን እንደሆነ ይታወቃል፡፡

የእስራኤል በኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ተግባር የመሰማራቷ ዜና ምናልባትም ከአባይ ግድብ ጀርባ የሃያላኑ አገራት ድጋፍና ጥበቃ እንዲሁም ቀጥተኛ ወይም ተዘዋዋሪ የሆነ ጥቅም የማስከበር ፍላጎት እንዳለ የሚሰነዘረውን ሃሳብ ያጠነክረዋል፡፡ አንዳንዶች እንደሚሉት የጫናው መነሻ ይህ የጡንቸኞቹ የጥቅም ጉዳይ እንደሆነ ያስረግጣል ይላሉ፡፡

በዚህና በተለያዩ ምክንያቶች በአባይ ግድብ ዙሪያ የሚነሱት መላምቶች ወይም መከራከሪያዎች ከሃያላኑ ጫና ጋር ተዳምረው መነጋገሪያ ርዕስ ሆኗል፡፡ግብጽ ጫናውን አስመልክቶ በይፋ የገለጸችው ተቃውሞ ወይም ቅሬታ የለም፡፡ ይሁን እንጂ በግብጽ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ ላይ ያሉትና የምዕራባውያን ቀጥተኛ ድጋፍ ያላቸው ፊልድ ማርሻል አል-ሲሲ “የውሃ ነገር” ለግብጽ “የህይወትና የሞት ጉዳይ” መሆኑን መግለጻቸውንና ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን መፍትሔ መፈለጉ “የግድ” እንደሆነ ማስታወቃቸውን ጎልጉል ዘግቦ ነበር፡፡

በዜናው መሠረት አል-ሲሲ “የሌሎችን ፍላጎትና ጥቅም የምንረዳ መሆናችንን ማሳየት ይገባናል፤ (የዚያኑ ያህልም) የራሳችንን ጥቅም ለማስጠበቅ ጽኑ መሆን አለብን፤ (ምክንያቱም) ውሃ ማለት ለእኛ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው” ማለታቸውን ጎልጉል ጨምሮ በማስታወቅ እጩው ፕሬዚዳንት ከዚህ በፊት ያልታየ መለሳለስ በማሳየት “ለኢትዮጵያና ለሌሎች አፍሪካ ወንድሞቻችን ተገቢውን ጥረት አለማድረጋችንን ማመን አለብን፤ በዚህ ዓይነቱ ጉዳይ ለመተባበርና መፍትሔ ለማግኘት ድርድርና የጋራ መግባባት ቁልፍ ናቸው” ማለታቸውን ጭምሮ ዘግቦ እንደ ነበር ይታወሳል፡፡

የአባይ ጉዳይ ኢትዮጵያንና ግብጽን ለዘመናት በተለያዩ እሰጥ አገባ ውስጥ የከተታቸው ነው፡፡ በአባይ ከሚፈሰው 90በመቶ የሚሆነው ውሃ የሚመነጨው እንዲሁም በአባይ ተጠርጎ ከሚወሰደው ለም አፈር 96በመቶ የሚሆነው የሚሄደው ከኢትዮጵያ ደጋማ ክፍል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ የአባይ ወንዝን አጠቃቀም በተመለከተ የሚያስተዳድሩት ሕጎች እኤአ በ1929 እና በ1959 በግብጽና በሱዳን እንዲሁም በግብጽና በብሪታኒያ በቅኝ ግዛት ዘመን በተፈረሙ ውሎች ሲሆን በውሉ መሠረት ግብጽና ሱዳን ከአባይ ወንዝ ኃብት በድምሩ 90በመቶ የሚሆነውን የመጠቀም መብት አላቸው (ይህም በየዓመቱ 55.5 ሜትር ኩብ የሚሆነው ለግብጽ 18.5 የሚሆነው ደግሞ ለሱዳን ማለት ነው)፡፡

ይህ ኢትዮጵያን የሚጎዳ ውልና አሠራር እንዳለ ሆኖ የዛሬ አራት ዓመት አካባቢ በታህሳስ ወር አቶ መለስ ይህንኑ የቅኝ ግዛት ዘመን ውል እንደገና በመቀበል ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ የተፈቀደላትን የድርሻ ኮታ ማግኘት ይገባታል በማለት ስምምነት መፈረማቸውን አልአህራም በወቅቱ ዘግቦ እንደነበር አይዘነጋም፡፡

ከጥቂት ቀናት በፊት ደግሞ ኢነርጂ ቢዝነስ ሪቪውን በመጥቀስ ሪፖርተር ለንባብ ባበቃው ዜና ላይ “በምሥራቃዊ ሱዳን በኩል ከከሰላ ግዛት ተነስቶ ወደ ኤርትራ በሚዘረጋ የ45 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር” በኩል ሱዳን ከኢትዮጵያ የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለኤርትራ ለመሸጥ እንቅስቃሴ ላይ መሆኗን ዘግቧል፡፡ ሱዳን ከዚሁ የአባይ ግድብ በርካሽ የምትገዛውን የኤሌክትሪክ ኃይል ምን ያህሉን በምን ያህል ትርፍ ለኤርትራ ለመሸጥ እንዳሰበች እስካሁን አለመታወቁን ጋዜጣው ጭምሮ አስታውቋል፡፡

አቶ መለስ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ዓመታት ኤርትራ ከኢትዮጵያ ያለቀረጥ ክፍያ በነጻ ያህል ከኢትዮጵያ የምትወስደውን ቡና በዓለም ገበያ ላይ በመሸጥ ከቡና አምራችና ሻጭ አገራት ውስጥ ተመዝግባ እንደነበር አይዘነጋም፡፡ ከዚህ ልምድ በመነሳት አሁንም ኤርትራ ከሱዳን የምትገዛውን ከአባይ ግድብ የሚመነጨውን የኤሌክትሪክ ኃይል በአቅራቢያዋ ለሚገኘው አጎራባቿ የሰሜን ኢትዮጵያ ክልል መልሳ በትርፍ ትሸጥ ይሆናል የሚለው አስተያየት ስላቃዊ ቢሆንም አነጋጋሪ እየሆነ መጥቷል፡፡
******************
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Tuesday, May 20, 2014

ራስ ምታት ያስቸግሮታል? እነዚህን ምግቦች ቢሞክሩስ?

በተለምዶ በእንግሊዝኛ ስያሜዉ ማይገሬን የሚባለዉ የእራስ ምታት አይነት በተለይም በአንደኛዉ የጭንቅላት ክፍል ላይ ከፍተኛ ህመም የሚፈጥር ሲሆን ፥ ዋና መነሻዉ በተለያየ ምክንያት የሚመጣ የነርቭ ስርዓት መዛባት ነዉ፡፡
ብዙዎቻችን በቅርብ በምናገኛቸዉ ምግቦች ይህንን የራስ ምታት አይነት ማስታገስ ይቻላል ይላል ኸልዝ ትዌንቲ ፎር ዶት ኮም ያወጣው መረጃ
1. የአበባ ጎመን፦ የነርቭ ስርዓትን ፣ ጡንቻንና ደም ግፊትን በማስተካከል የራስ ምታትን ይቀንሳል!
2. ወተት፣ ስኳር ድንች፦ በቫይታሚን ቢ2 ይዘታቸዉ የነርቭ እና ቀይ የደም ሴሎችን እድገትና በሽታ የመከላከል አቅምን ይጨምራሉ!
3. ገብስ ፦ በቫይታሚን ቢ6 ይዘቱ ሄሞግሎቢንን (የሰዉነት ኦክስጂን ተሸካሚ ንጥረ ነገር) በመገንባት የነርቭ ስርዓት እንዲገነባ እና በሽታ ለመከላከል ያግዛል!
4. የዶሮ ስጋ፦ በያዘዉ ቪታሚን ቢ3 የደም ዝዉዉርን በማፋጠን የደም ቧንቧን ክፍት ያደርጋል፣ በወር አበባ ጊዜ ለሚከሰት ራስ ምታት፣ ለድብርት እንዲሁም ለተያያዥ የህመም ስሜቶችም ፍቱን ነዉ!
5. እንቁላል፦ ሰዉነታችን በራሱ ማምረት የማይችለዉን ኦሜጋ 3 የተሰኘ አሲድ የያዘ ሲሆን ፥ ለአእምሮ ስራና እድገት እጅግ ተቃሚ ነዉ ፤ በተጨማሪም በድብርት እና ምክንያት አልባ ጭንቀት ለሚሰቃዩ ሰዎች ጠቃሚነቱ ተረጋግጧል።