Thursday, October 31, 2013

አሳዛኝ ዜና -በጀርመን ህክምና እየተከታተለ የሚገኘው ኮሜዲያን አብርሐም አስመላሽ አረፈ።


21
አብርሃም አስመላሽ
አርቲስት አብርሃም አስመላሽ ባደረበት ህመም ምክንያት ላለፊት ጥቂት ወራት በጀርመን ኑረንበርግ ከተማ አካባቢ የእክምና እርዳታ ሲደረግለት ቆይቶ ባለፈው አርብ ጥቅምት 15 ቀን 2006 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
በአብዛኛው በገጠርኛ ዘይቤ አቀራረቡና በኮሜዲ ስራዎቹ የሚታወቀው አርቲስት አብርሃም አስመላሽ በዲስክ መንሸራተት ህመም ምክንያት ለረጅም ጊዜያት ሲሰቃይ ቆይቷል።
አርቲስት አብርሃም ከዲስክ መንሸራተት በተጨማሪ በጉበትና በኩላሊት እንዲሁም በሳምባ ምች በሽታዎች ሲታመም የነበረ ቢሆንም ከወዳጆቹና ከጥቂት የስራ ባልደረቦቹ ባገኘው የገንዘብ እርዳታ ህክምና አግኝቶ ከተወሰኑት በሽታዎች ሊድን ችሎ ነበር።
ይሁንና የዲስክ መንሸራተት መሙን በግሉ ከፍሎ መታከም ባለመቻሉ ህብረተሰቡን ለህክምና የሚሆን የገንዘብ እርዳታ በመጠየቅ ላይ እንደነበር ይታወሳል።
በዚህ የዲስክ መንሸራተት ህመም ምክንያት አርቲስት አብርሃም እንደልቡ መንቀሳቀስ ባለመቻሉ ለረጅም ጊዜያት በህዝብ ከሚታወቅባቸው የመነባንብና የኮሜዲ ስራዎቹ ሊርቅ ተገዶ ነበር።
በተለይ ”እረኛውና” ፣ ”ጠበል ቅመስ” በሚል ስራዎቹ የሚታወቀው አርቲስት አብርሃም አስመላሽ ከሃያ ያላነሱ ዓመታትን በኢትዮጵያ ራዲዮ ቅዳሜ መዝናኛ የተለያዩ ማህበረሰብ ነክ በመነባንቦችንና የኮሜዲ ስራዎችን ሲያቀርብ እንደነበር በተለያዩ ጊዜያት በሰጣቸው ቃለመጠይቆች ላይ ገልፃል።
አዲስ አበባ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ ተወልዶ ያደገው አርቲስት አብርሃም አስመላሽ የገጠርኛ ዘይቤ አቀራረቡን ለበግ ንግድ ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢው ወደሚገኘው ”ደንሴ ተራራ” ይመጡ ከነበሩ የመንዝና የወሎ አካባቢ ነጋዴዎች ቀስሞ እንዳደገ ይገልፃል።
አርቲስት አብርሃም ከተለያዩ አካባቢዎ ወደ ”ደንሴ ተራራ” ይመጡ ከነበሩ የገጠር የሀገሪቱ አካባቢ ነዋሪዎች ለየት ያለ የአማርኛ አነጋገር በመመሰጡ የተነሳ ”ሌሎች ሰዎች በገበያዎች በጎችን ሲሰርቁ እኔ ግን የአማርኛ አነጋገር ዘይቤያቸውን ነበር ስሰርቅ ያደግኩት ”ሲል ገልፆ ነበር።
አርቲስቱን ከሞት ለመታደግ የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የድረሱለት ጥሪ ቢያሰሙም ከጥቂት ግለሰቦች በስተቀር ማንም ምላሽ የሰጠው አልተገኘም።
አርቲስት አብርሃም አስመላሽ ወደ ቀድሞው ጤንነቱ ቢመለስ ኖሮ ለህትመት ያልበቁ በርካታ ስራዎችን የማሳተም እቅድ እንደነበረው ገልፆ ነበር።
አርቲስት አብርሃም ትዳር እንዳልመሰረተና ያፈራው ልጅም እንደሌለው ገልፆ የነበረ ሲሆን በህመም ተይዞ ለህክምና እርዳታ እጁን እስከዘረጋበት ጊዜ ድረስ መነኩሴ እናቱን በመርዳት ብቻ ይኖር እንደነበር ገልፃል።
ለአርቲስቱ ቤተሰቦችና አድናቂዎች መፅናናትን እንመኛለን!
zehabesha.com

Wednesday, October 30, 2013

አቶ በረከት ስምኦን የኢቲቪ ቦርድ ሰብሳቢነቱን ለአቶ ሬድዋን ሁሴን አስረከቡ



October 30th, 2013


የሹመቱ አግባብነት ጥያቄ አስነስቷል

አፈጉባዔ አባዱላ ጠ/ሚኒስትሩ በሹመቱ ላይ ማብራሪያ ለመስጠት አይገደዱም አሉ
የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ኃላፊነት ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ያቀረቡትን ሹመት ተቀብሎ አጸደቀ። በዚሁ መሠረት ድርጅቱን ለረዥም ጊዜ በቦርድ ኃላፊነት ባገለገሉት አቶ በረከት ስምኦን ምትክ አቶ ሬድዋን ሁሴን የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ተሹመዋል።

ጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ትናንት ለም/ቤቱ በላኩትና የአማካሪ ም/ቤት አስቀድሞ ሳይመክርበት በድንገት በቀረበው ደብዳቤ መሰረት ለኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ስምንት አባላት ያሉት የስራ አመራር ቦርድ አባላትን መሾማቸውን አሳውቀዋል። በዚሁ መሠረት በቅርቡ የመንግሰት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት አቶ ሬድዋን ሁሴን የድርጅቱ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው ሲሾሙ በቅርቡ ለረዥም ጊዜ ካገለገሉበት የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኃላፊነታቸው ተነስተው በጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት የሕዝብ ተሳትፎ አደረጃጀት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው የተሾሙት አቶ ደስታ ተስፋው አባል፣ በቅርቡ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የምክትል ጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ በመሆን የተሾሙት አቶ አማኑኤል አብርሃም አባል፣ አቶ ዓቢይ መሐመድ ከሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባል፣ አቶ ገበየሁ በቀለ ከአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ አባል፣ ዶ/ር አብዲሳ ዘርዓይ ከአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ አባል፣ መጋቢ ዘሪሁን ደጉ ከእምነት ተቋማት አባል፣ አቶ ዘርዓይ አስገዶም ከኢቲቪ አባል በመሆን ተሹመዋል።

የተሰናባቹ የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት የስራ አመራር ቦርድ አባል መሆናቸውን የተናገሩ አንድ የም/ቤት አባል ሹመቱን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ሹመቱ ግልጽነት የጎደለው መሆኑን በመጥቀስ ማብራሪያ ጠይቀዋል። እንደእሳቸው አባባል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተጠሪ የሆኑ የመንግስት የሚዲያ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት እና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መሆናቸውን በማስታወስ ለሁለቱ ተቋማት 4ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሹመት መስጠቱን አስታውሰዋል። አሁን የቴሌቪዥን ቦርድ በድክመት ባልተገመገመበት ሁኔታ ለብቻው ተለይቶ በተናጠል እንዴት ሹመት ሊሰጥ እንደቻለ ጠይቀዋል። “ምናልባት ሰብሳቢው ቦታውን ለውጦ ከሆነ ያ ቦታ የተካው ሰው መያዝ ሲገባው የስራ አመራር ቦርድ አባላት ድክመት ባልገመገምንበት ሁኔታ ቦርዱ እንደ አዲስ ሊሰየም የተፈለገበት ምክንያት አልገባኝም” ሲሉ አባሉ አስቀምጠዋል። በተጨማሪም የቀድሞ ቦርድ ቁጥሩ ዘጠኝ የነበረ ሲሆን አሁን ቁጥሩ ለምን ወደ ስምንት ዝቅ አለ ሲሉ የጠየቁ ሲሆን ሌሎች የም/ቤቱ አባላትም ከእምነት ተቋም ተወካይ ቦርዱ ውስጥ የገባበት ምክንያት እንዳልገባቸው፣ ከዚህ ይልቅ ከሲቪል ማህበር ቢሆን ይሻል እንደነበር እንዲሁም የሴቶች ተሳትፎ በሹመቱ ውስጥ መዘንጋቱ በጥያቄ መልክ ተነስቷል።

አቶ አባዱላ ገመዳ የም/ቤቱ አፈጉባዔ በሰጡት ምላሽ ጠ/ሚኒስትሩ በማንኛውም ጊዜ ሚኒስትሮችን ሲያነሱ ማብራሪያ እንደማይጠየቁ ሁሉ የቦርድ አባላትንም ሲሰየሙ ማብራሪያ ለመስጠት እንደማይገደዱ ተናግረዋል። የአሁኑ ቦርድ አሰያየም ፖለቲካን ብቻ ሳይሆን የሙያ አቅምንም መሰረት ያደረገ ነው ካሉ በኋላ የሴቶች ተሳትፎ መጓደልን በተመለከተ መልዕክቱን እንደሚያደርሱ ገልፀዋል።

Monday, October 14, 2013

የኢትዮጵያን ፖሊስ ሰራዊት ግንባር ቀደም በሃላፊነት የሚያስጠይቅ አስቃቂ የግድያ ወንጀል «በጅማ ከተማ» ።


         የጉዞ ትዝብት ! ፖሊሳዊ ክህሎት እና ንቃት የሌለው የፖሊስ ሰራዊት በኢትዮጵያ !




ፖሊስ በህዝብ እና በሃገር ድህነት ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ቀደሞ ብሎ የማምከን ግንባር ቀደም ሃልፊነት እና ግዴታ እንዳለበት  ማንም ሊክደው የማያችል እውነታ ነው። ይህን እውነታ መተግበር እየተሳነው የመጣው የኢትዮጵያ ፖሊስ አልፎ አልፎ ከህዝብ የሚቀርቡለትን መረጃዎች መተግበር  ተስኖት በተዘዋዋሪ ሰላሜን ጸጥታዬን ያስጠብቅልኛል ብሎ ተስፋ በጣለበት ህዝብ ላይ የወንጀል ድርጊት የሚፈ ተባባሪ እየሆነ መምጣቱ ለፖሊስ ሰራዊቱ ሌላ የሰለጠነ ብቃት ያለው የፖሊስ ሃይል እንደሚያስፈልገው ሃገራችን ውስጥ በተደጋጋሚ በፖሊስ ሰራዊቱ እንዝላልነት የሚከሰቱ ወንጀሎች እየተበራከቱ መምጣታቸው ያመለክታሉ ።


የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሰሞኑንን የ3 ህጻናት ወላጅ የሆነችውን ባለቤቱን በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ወግቶ የገደለውን አባወራ የምርመራ ውጤት እንደ ጀብዱ ሊያስደምጠን የሞከረው የኢትዮጵያ ፖሊስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ስርጨት በግናብር ቀደም መጠየቅ የሚገባቸውን የሰራዊቱን አባላት ያፈጠጠ ስህተት ለማድበስበስ በተጠቀሰው ወረዳ የፖሊስ ምርመራ ውጤት የህዝቡ ቀልብ ለመሳብ ሲያስደምጠን በነበረው ትረካ  « የዝግጀት ክፍሉን አላውቂ ሳሚነት ለመረዳት ይግድ ነብይ መሆን አያሻም።  አዎ « ፖሊስ በቡድን እና በተናጥል የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ቀድሞ የመከላክል ሃልፊነት እና ግዴታ አለበት  » የሚለውን እውነታ በቅጡ መገንዘብ የተሳናቸው  የማስታውቂያ ሚንስቴር የሞቀ ህንጻ ላይ ተኮፍሰስው በስማ በለው ያረቀቁትን ልብወለድ በሳምንቱ መጨረሻ «እሁድ» የሰራዊቱን ፋቲክ ተጀቡነው እንደገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡትን  የዝግጀት ክፍሉን ጋዜጠኞች የሙያ ብቃት መቃኘት ይግድ ቢሆንም ዝግጀት ክፍሉ ቀጣይ ዝግጀቶች እናድሉት ስለገለፀ ……. ስለተፈጸመው ወንጀል እንደሚከተለው  ለማቋደስ ወሰንኩ ።
ታሪኩ እንዲህ ነው ። ቀኑ በጅማ ከተማ የወረዳ 2 ነዋሪ የዕለት እተዕለት እንቅስቃሴውን ለመጀምር በማለዳ ተነስቶ ጉዳይ ያለው ወደ ጉዳዩ ስራ ያለው ወደ ስራው በየፊናው  የሚንቀሳቀስበት ሰአት ነው። በዚህ ቅጽበት በተጠቀሰው ወረዳ  አንድ አስደንጋጭ ዜና ተሰማ ። ከአንድ አመት በፊት በሁለት ባል እና ሚስት መሃከል በተፈጠረ አለመግባባት ባል የ3 ልጆቹን እናት የሆነች የ6 አመት የትዳር ጎደኛውን የምትሰራበት የውበት ሳሎን መዕከል ድረስ ተከታትሎ በመ ሄድ በያዘው ስለት አንገቷ ላይ 3 ቦታ ወግቷ ገድሎ መሰወሩን የፖሊስ የምርመራ ውጤት ይገልጻል።  ገና ከማለዳው የአካባውን ነዋሪ ጉድ ያሰኘው ይህ ጭካኔ የተሞላበት ወንጀል በጅማ ከተማ ለወረዳ  2 ፖሊስ ጽ/ቤት ፖሊስ ጆሮ ይደርሳል ። ጉዳዩን ለማጣራት ወንጀሉ የተፈጸመበት ቦታ ድረስ ሄደው ፎቶ ማንሳታቸውን ወንጀለኛው  ማነው ? የሚለውን ለማወቅ በአካባቢው ያገኙትን መረጃዎች አሰባሰበው  ክትትል መጀመራቸውን የሚናገሩት የወረዳው  ተረኛ መርማሪ ነፍሰ ገዳዩን በዛው ቅጽበት  እራሱን የማጥፋት ሙከራ ሲያደርግ ደርሰው በቁጥጥር ስር ማዋሉን በኩራት ይናገራሉ። ፖሊስ በተጠቀሰው ወንጀለኛ  ላይ የሚያደርገውን ምርመራ በማጠናከር ከአካባቢው ማህበረሰብ  ባገኘው መረጃ መስረት ከአንድ አመት በፊት በመሃከላቸው በተነሳ አለመግባባት በቤተሰብ ደረጃ ተሞክሮ ስላልተቻለ ላይገናኙ ተማምለው  እንደ ተለያዩ የሚገልጸው የምርመራ ውጤት  ወንጀለኛው በቁጭት የልጆቹን እናት ለመግደል ክትትል ያደርግ እንደነበር መረጃ እንደነበረው አክሎ ይገልጻል። ከዚህ ባሻገር   «ሂሩትን ገድያት ስለመጣሁ ፖሊስ ቢመጣ ያለሁበትን ቦታ እንዳትጠቁሙ ብሎ ከፖሊስ ለመስወረ እንዲተባበሩት ወንጀለኛው  ለዘመዶቹ መግለጹን ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ አባወራው ከተያዘ በሃላ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል የልጆቹን እናት መግደሉን ከምርመራው ውጤት ማረጋገጡን ይገልጻል ።  እዚህ ላይ ልብ ያለው ልብ ይበል  ሞች ወ/ሮ ሂሩት ቀደም ብለው ለፖሊስ የቀድሞው ባለቤታቸው ሊገድላቸው ክትትል እያደረገባቸው መሆኑን  ለፖሊስ በመግለጽ ሊፈጸምባቸው ከሚችል ግድያ እንዲታደጋቸው በተደጋጋሚ  አመልክተው እንደነበር መርማሪው ፖሊስ ሳይሸሽጉን በማን አለብኝነት   የተናገሩትን እንኳ የጅማ ህዝብ ድፍን የኢትዮጵያ ህዝብ እሁድ ረፋድ ቀን ኦክቶበር 13 2013 በተላለፈው የፖሊስ ራዲዮ ፕሮግራም በሚገባ አድምጠናል።


በጅማ ከተማ የወረዳው 2 ፖሊስ መርማሪው በማስከተል ሲናገሩ  ሞች ወሮ ሂሩት ለፖሊስ ያቀረቡትን የነብስ አድን ጥሪ በማስታወስ  ፖሊስ ባልና ሚስት የማስታረቅ እንጂ የማፋታት ስራ እንደማይሰራ ጠቅሰው «ጅብ ከሄደ ውሻ ጮህ እንዲሉ » በሞች ወ/ሮ ሂሩት የቀረበውን  የነብስ አድን ጥሪ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የወ/ሮዋ ህይወት በአስቃቂ ሁኔታ ከጠፋ በኃላ ወንጀለኛውን ተከታትሎ በመያዝ  ፖሊሳዊ ግዳጃቸውን በበቃት መወጣታቸውን ይናገራሉ። ይህ አባባላቸው በከተማይቱ ጅማ ህዝብ ዘንድ ከወ/ሮ ሂሩት ግድያጋ ተያይዞ የመነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ በተጨባጭ አረጋግጫለሁ፡፤ ፖሊሳዊ ብቃት በሌላቸው የፖሊስ አባላት የሚመራውን የፖሊስ የምርመራ ውጤት በኢቲቭ የፖሊስ ፕሮግራም  መነገሩ አስፋሪነቱ አጠያያቂ ባይሆንም  እንደ ጋሪ ፈረስ ለመዘገብ የደፍረው ዝግጀት ክፍሉ ጉዳዩን በስፋት ለማየት ባለመታደሉ ያሳዝናል።  በሞች ወ/ሮ ሂሩት ላይ ለተፈጸመው ወንጀል በጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወረዳ 2 ፖሊስ ጽ/ቤት ቀጠተኛ ሃላፊነት እና ተጠያቄነት ሊኖርባቸው እንደሚገባ የሁሉም እምነት ነው።                                                                          « አካላዊ እና መንፈሳዊ ብቃት የሌለው ፖሊስ ሠራዊት ለህዝብ ህይወት እና ንብረት አሌንት የመሆን የሞራል ብቃት የለውም ! 


Ethiopian Hagere  ( from Ethiopia )

Thursday, October 10, 2013

በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የበላይ ጠባቂነት ይመራ የነበረው ት/ቤት የባለቤትነት ውዝግብ በኤምባሲው የበላይነት በሰላም ተጠናቀቀ!



በቀድሞው የኢትዮጵያው ፕሬዘዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የበላይ ጠባቂ ነት ሲተዳደር በነበርው የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤት ላይ የተነሳው የባለቤት ነት ጥያቄ ውዝግብ አነጋጋሪንቱ እንዳለ ሆኖ ሰሞኑንን ተቀስቅሶ የነበረው ውዝግብ በኤምባሲው የበላይ ነት መጠናቀቁን ምንጮች ከሪያድ ይገልጻሉ ። ከእንግዲህ ወላጆች በት/ቤቱ ጉዳይ ምንም አይነት መብት እንደሌላቸው ኦክቶበር 4 2013 ምሸት ኤምባሲው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳርሽ ባዘጋጀው የወላጆች ስብሰባ ላይ በእንግድነት የተገኙት አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ለተሰብሳቢው ባሰሙት ንግግር ከንግዲህ ይህ ጥያቄ ልድርድር የማይቀርብ መሆኑንን አረጋግጠዋል ብለዋል።
ሰሞኑንን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለወጭ ሃገር ዜጎች የሰጠው የግዜ ገደብ መጠናቀቅን ተከትሎ ዲያስፖራው በራሱ ጉዳይ ተጨንቆ ባለበት ዋዜማ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን በማን አለብኝነት የት/ቤቱን መስተዳድር እና የቦርድ አባላት እጅ በመጠምዘዝ በዲያስፖራው ንብረት አስነዋሪ ተግባር በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ አንዳንድ የአካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል። በተለይ ከዛሬ 20 አመት በፊት ከ200 በማይበልጡ ህጻናት የመማር ማስተማር መረሃግብሩን «ህ» ብሎ በይፋ መጀምሩ የሚነገርለት በቀደሞው የኢትዮጵያው ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርግስ የበላይ ጠባቂነት እንደሚመራ የሚነገርለት ይህ በሪያድ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤት ግንባር ቀደም ሰለባ መሆኑ ወላጆችን እንዳስደንገጠ እነዚሁ ውስጥ አዋቂ ምንጮች አክለው ገልጸዋል። 

ይህ ት/ቤት ለኢንቨስተሮች ቢተላለፍ ጥሩ ውጤት እንደሚያመጣ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚሰብኩት አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ት/ቤቱን ከጥቂት ግብረአብሮቻቸው ጋር በእጅ አዙር ለመቆጣጠር ቀደም ብለው ሊፈጽሙት ያሰቡት ሴራ በህብረትሰቡ ጥረት መክሸፉን የሚገልጹት ውስጥ አዎቂዎች ዛሬ በሳውዲ የመኖሪያ ፈቃድ አለመስተካከል እና መሰል ተዛምጅ ጉዳዮች ግራ ተጋብቶ ህብረትሰቡ ጭንቀት ውስጥ ያለብትን ወቅት እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የዲያስፖራውን ልጆች ከት/ምህርት ገበታ በግፍ ከማፈናቀል በማፈናቀል ባስነሱት ግርግር በሚልዮን የሚቆጠረውን የኮሚኒት ገንዘብ ወደ ግል ኪሳቸው ለምክተት ያደረጉት ጥረት መክሸፉን « በሳውዲ የደህንነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉትን የአምባሳደሩን የቅርብ ዘመድ በመጥቀስ» ይገልጻሉ።
ይህ ከ2ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ከአቅም በላይ በሆነ ወረሃዊ ክፍያ ወላጆችን እየመዘበረ የሚገኘው ኮሚኒትው የመካበት የነበረ ት/ቤት ጥሩ ግቢ እንዳለው በተርዱ የሪያድ ዲፕሎማቶች ጣልቃ ገብነት አደጋ ውስጥ መወደቁን የሚናገሩ ወላጆች ት/ቤት በመግዛት ከኪራይ ከፋይነት ነጻ የሚያደርጋቸውን እቅድ በኚሁ የኢትዮጵያው አንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን መደናቀፉ ግራ የሚያጋባ እና ወክሎ ለላካቸው ልማታዊ መንግስት አሳፍሪ መሆኑንን ይናገራሉ ። በ 90 የመማሪያ ክፍሎች 120 በሚበልጡ መምህራኖች በመታገዝ የመማር ማስተማሩን ስረአት እያካሄደ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ት/ቤት ከወላጆች እጅ ወጥቶ የጥቂት ዲፕሎማቶች እና ተላላኪዎቻቸው ኪስ ማደለቢያ ከሆነ ወዲህ የትምህርት ጥራቱ ከአመት አመት በማሽቆልቆል አምና ማትሪክ ፈተና ከወስዱ ተማሪዎች ውስጥ አብዛኛው ዝቅተኛ ውጤት በማምጣት ትምህርታቸውን መቀጠል ባለመቻላቸው በሰው ሃገር ልጆቻቸው በየመንገዱ ሲጋራ አጫሽ ቦዘኔ ለመሆን መገደዳቸውን በመምሬት የሚገልጹት ወላጆች በት/ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ያላቸው ተስፋ መሞጠጡን አረጋግጠዋል። 

የአዳዲስ መምህራን ቅጥር እና የነባር መምህራን የስራ እደገት የሚወሰነው በችሎታ ሳይሆን በዝምድና እና ከዲፕሎማቱ ጋር ባላቸው የጠበቀ ግንኙነት መሆኑንን የሚገልጹት የት/ቤቱ መምህራኖች በበኩላቸው ቅሬታቸውን ሲያሰሙ የት/ቤቱ ቦርድ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለዲፕሎማቱ በመሆኑ የደሞዝ ጭማሪ በመነፈጋቸው በትርፍ ግዜያቸው መንደር ለመንደር እየዞሩ ተማሪዎችን በክፍያ የማስጠናት ስራ ላይ ለመሰማራት መገደዳቸውን ገልጸዋል። አርብ ኦክቶበር 4 2013 ምሽት ኤንባሲው ባዘጋጀው በዚህ የወላጆች ስብሰባ ላይ በዲፕሎማቱ የተዘጋጀው አደናጋሪ እና ተአማኒነት የጎደለው የኦዲት ልብ ወልድ ሪፖርት መቀረቡ የወላጆች ተጸኖ የፈጠረው ጭንቀት መሆኑንን የሚናገሩት ታዛቢዎች 250 ሺህ ሪያል የነበረው የት/ቤቱ አመታዊ የኪራይ ክፋያ በአጭር ግዜ ውስጥ በአራት እጥፍ አድጎ 1.2 ሚልዮን ሪያል አሊያም በሃገራችን ምንዛሪ «5.4 ሚልዮን ብር » መድረሱን የሚናገሩ እንዚህ ታዛቢዎች በአንባሳደሩ ሳንባ የሚተነፈሰው የት/ቤቱ ቦርድ ከባዕዳን አከራዩች ጋር ተማስጥረው ፈጸሙ የተባለውን አሰነዋሪ ድርጊት ጥርጣሬ ያጠናክራሉ ። 

በለሌላ በኩል በት/ቤቱ የትምህርት ጥራት ላይ የቀረበውን የወላጆች ወቀሳ አምነው የተቀበሉ የት/ቤቱ ረእሰ መምህር አቶ አቡል ባስጥ ጀማል ዘንድሮ በትምህርት ጥራት ላይ የነበረውን ድክመት አምነው በመቀበል ት/ቤቱ ይመራ የነብረው በቆየ «የሲናግፖር» ካሪኩለም መሆኑንን ጠቅሰው በዚህ ዙሪያ አዲስ ጥናት መዘጋጀቱን በማውሳት ወደፊት ከወላጆች ጋር ለመስራት ቃል ቢገቡም አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከወላጆች ባለቤት ነት እጅ የወጣው ይህ አለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን እና የጥቂት ዲፕሎማቶች ኪስ ማደለቢያ ከመሆን ባሻገር በት/ቤቱ የትምህርት ጥራት ላይ ከእንግዲህ ምንም አይነት ለውጥ ሊመጣ እንደምያችል ስጋታቸውን በማስቀመጥ ፡ የረዕሰ መምህሩን አባባል ከጊዜያዊ ጭንቀት ለማምለጥ ለወላጆች የተነገረ የተለመደ መደለያ ቃል መሆኑንን ገልጸዋል። ኤምባሲው በጠራው በዚህ የወላጆች ስብሰባ ላይ በፈቃደኝነት ከ300 መቶ በላይ ወላጆች መታደማቸውን የሚገልጹት ምንጮች መድረኩ ሙሉ ለሙሉ በዲፕልማቱ እና እንሱ ለይስሙላ ባስቀመጦቸው ተላላኪዎች በመይዙ ወላጆች ሃሳብቸውን እንዳሻቸው ለመግለጽ እድል ባለማግኘታቸው በወቅቱ አዳራሽ ውስጥ ግጭት ተነስቷ እንደነበር ታውቋል። ይህ በዚህ እንዳለ አንዳንድ ወላጆች ት/ቤቱን በበላይነት የሚቆጣጠር ኮሚቴ ከተጠራው የወላጆች ጉባኤ ለማስመረጥ ተይዞ የነብረውን እቅድ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን አቅጣጫ በማስለወጥ እንደ ፌስ ቡክ ባሉ ሶሻል ሚዲያዎች የተሳስቱ መረጃዎችን በመስጠት የሃሰት ወሬ እየነዙባቸው መሆኑንን አውስተው አንባሳደሩ መንግስት አምኖ ከጣለባቸው ሃላፊነት ውጭ በግል እና በቡድን በኮሚኒቲው ንብረት ላይ የሚፈጽሙት አስነዋሪ ተግባር አደባባይ መውጣቱ አበሳጭቷቸው ባሰሙት ጥራዝ ነጠቅ ንግግር የስብሰባውን ተሳታፊ በመዝለፍ ለዲያስፖራው ያላቸውን ንቀት ዳግም አረጋግጠዋል ብለዋል። 

እንዚህ ታዛቢዎች አንባሳደሩ ከግል ጥቅማቸው ውጭ ምንም አይነት የህዝብ ተቆርቋሪነት የማይሰማቸው በመሆኑ የሃገራችንን በጎገጽታ የሚያጎድፍ እና ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ በመካከለኛ ምስራቅ እና አካባቢው የሚኖሩ ዜጎቻችንን ህልውና ለአደጋ የሚያጋልጥ የኢትዮጵያውያንን ባህል የሚያጎድፍ ድርጊቶች በሚዲያዎች ሲናፈሱ እንደ አንድ ሃገር መንግስት ተወካይ ጉዳዩ አንገብግቦቸው ማስቆም አለመቻላቸው ሊያስጠይቃቸው ይገባል ብለዋል። አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰንን በስም እንጂ በአይን አይተዋቸው የማያቁት የሪያድ ነዋሪዎች የትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ በተለያዩ ግዜያት ያለበቂ ህክምና የሚሞቱ እህቶቻችን ጉዳይ አንድም ቀን እንቅልፍ ነስቷቸው የማያውቅ ጨካኝ ሰው መሆናቸውን ይናገራሉ ። እኚህ አምባሳደር በስራቸው ለሚንቀስቀሱ እንደነ ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አይነቱን ሰዎች የኤንባሲ ከለላ በመስጠት ህገወጥ፡ ወጥ በሆነ መንገድ በሚልዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ወደ ኢትዮጵያ አሾልኮ በማስገባት በደሃው ሃዝባችን ጉሮሮ ላይ አጥንት የሚሸነቅሩ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የጎደላቸው የዘመናችን ጨካኝ ዲፕሎማት መሆናቸው ይገልጻሉ። በአጠቃላይ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን እና ተላላኪዎቻቸው ማህበረሰብን በጎሳ ከፍለው በጠላትነት እንዲተያይ ማድረጋቸውን የሚናገሩ ምንጮች በትቤቱ የሚደረገውን የኤንባሲውን ጣልቃ ገብነት ጨምሮ በተለያዩ ግዜያት ዲያስፖራው ለመንግስት የሚያቀርባቸውን ጥያቄዎች በአግባቡ ተቀብለው በማስተናገድ ባለመቻላቸው ዲያስፖራውን ከመግስት ጋር ለማጋጨት እየሄዱ ያለበት የተሳስተ አቅጣጫ መረን የለቀቀ በመሆኑ በሪያድ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ማህብረሰብ ቀደም ሲል በሃገሩ ጉዳይ ላይ የነበረው ልማታዊ ተነሳሽነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ አምባሳደር ድ/ር መሃመድ ሃሰን እና አንዳንድ ለማህብረሰቡ ክብር የለሌላቸው ዲፕሎማት ከሪያድ እንዲያነሱላቸው ጠይቀዋል ። 

Ethiopian Hagere ሳውዲ አረቢያ (ጅዳ በዋዲ )

Monday, October 7, 2013

አዲሱ ፕሬዚዳንት በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲሱ ፕሬዚዳንት በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዲሪ አራተኛ ፕራዚዳንት በመሆን የተመረጡት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞ ፕሬዘደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስና ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከህዝብ ተወካዮችና ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትና አምባሳደሮች በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ከተገኙት እንግዶች መካከል ይጠቀሳሉ።

አዲሱ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላት ተሾመም በይፋ ስራቸውን ጀምረዋል ይሆናል። 
ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ማን ናቸው?
ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ውርቱ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ አርጆ ወረዳ በ1949 ዓ.ም ተወለዱ።
የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርጆ እና በአዲስ አበባ ተከታትለዋል።
በ1974 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በፖለቲካል ፍልስፍና እንዲሁም በአለም አቀፍ ግንኙነት ከዚያም በፍልሰፍና የዶክቶሬት ድግሪያቸውን።
ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በተለያዩ መስኮች ያከናወኑ እና በመምህርነትም ያገለገሉ ሲሆን ፥ አማርኛ ፣ ኦሮምኛ ፣ እንግሊዘኛ ፣ ቻይንኛ እንዲሁም ፈረንሳይኛ ቋንቋን መናገር እና መጻፍ ይችላሉ።
ከ1993-1994 ዓ.ም የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስትር ፣ ከጥቅምት 1994 እስከ 1998 ዓ.ም በፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት እንዲሁም ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በቱርክ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።

ዶክተር ሙላቱ በትዳር ህይወታቸው የአንድ ወንድ ልጅ አባት ናቸው።

Sunday, October 6, 2013

በምስራቅ ጎጃም ስለተቃጠሉ ስምንት አብያተ ክርስቲያናት መንግስት ባስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሠጥ እንጠይቃለን!!!!

በምስራቅ ጎጃም ስለተቃጠሉ ስምንት አብያተ ክርስቲያናት መንግስት ባስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሠጥ እንጠይቃለን!!!!

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

መንግስት በሚያስተዳድረው ሐገር ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን፣ ተቋማትን፣ የሀገር ሉዓላዊነትን፣ ታሪክን፣ ባህልን፣ የእምነት ነፃነትንና ደህንነትን ማስጠበቅ ተቀዳሚ ተግባሩ ነው፡፡ ይሁን እንጂ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በምስራቅ ጎጃም በአዋበልና አነደድ ወረዳ የሚገኙ ስምንት አብያተ ክርስትያናት ከሚያዚያ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ብቻ በእሳት ተቃጥለው በቤተክርስቲያናቱ ውስጥ የሚገኙ ነዋየ ቅድሳት፣ ልዩ ልዩ አልባሳት፣ ብዙ መጽሐፍትና ንብረት ወድሟል፡፡

እጅግ የሚያሣዝነው የአካባቢው ነዋሪዎች በመንግስት በኩል ምክንያቱ ታውቆ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሠድ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም ሰሚ ጆሮ አላገኙም፡፡ ጉዳዩንም የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲያውቀው በክልሉ ቴሌቪዥን በዜና መልክ እንዲገለፅ ያደረጉት ጥረት አልተሳካም፡፡ በአንድ አካባቢ በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ በቤተክርስትያን ላይ የማውደም ተግባር ስምንት ጊዜ ሲፈፀም በሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሀን አንድም ቀን አለመገለፁና በመንግስት በኩል መፍትሔ አለመስጠቱ ፓርቲያችንን ከልብ አሳስቦታል፡፡ በመሆኑም እነዚህ ከታች የተዘረዘሩት አብያተ ክርስቲያናት፡-
1. አንጋጫ ኪ/ምህረት 2. ዳገት ሚካኤል 3. የደርበን ሚካኤል
4. ዋሻ መድሀኒዓለም 5. መንክር ማሪያም 6. ቀዝቀዝ ገብርኤል
7. ደማም እየሱስ 8. ምስለ ዋሻ ጊዮርጊስ

አንዳንዶቹ ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ የወደሙ ሲሆን የተወሰኑት በአካባቢው ሕብረተሰብ ጥረት በከፊል ተቃጥለው የተወሰነ ንብረት ሊተርፍ ችሏል፡፡ ፓርቲያችን በህግ ተመዝግቦ ህጋዊ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ተወዳደሮ የመንግስት ሥልጣን ከመያዝ በተጨማሪ በተለያየ ጊዜ በሐገርና በህዝብ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን መከታተልና በሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲያገኙ ጥረት ማደረግ ስለሆነ በመንግስት በኩል ጉዳዩ ትኩረት ተሰጥቶት የቃጠሎው ምክንያት ተጣርቶ ድርጊቱን የፈፀመው አካል በህግ ተጠያቂ እንዲሆንና ይህም ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዲገለፅ እያሳሰብን እንዲህ ዓይነቱ በሕዝብ አመኔታ የሚጣልባቸው ተቋማትን የማውደም ተግባር ወደፊትም እንዳይደገም በመንግስት በኩል አስፈላጊው ጥበቃ እንዲደረግ በአፅንኦት እንጠይቃለን፡፡
መስከረም 26 ቀን 2006 ዓ.ም
አዲስ አበባ

Friday, October 4, 2013

ሰበር ዜና በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒተ ሊቀመንበር በሳውዲ ደህነቶች ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ተከትሎ ዲፕሎማቱ ተደናገጡ

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሊቀመንበር እና የአንባሳደር መሃመድ ሃሰን የቅርብ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ሰሞኑንን በሳውዲ ጸጽታ አህይሎች በቁጥጥር ስራ መዋላቸውን ውስጥ አውቂ ምንጮች ገልጸዋል። 

አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ምንጩ ከየት እንዳልሆነ ያልታወቀ 2 ሚልዮን ሪያል « በኢትዮጵያ ምንዛሪ ከ10 ሚልዮን ብር በላይ በእጃቸው መገኘቱን ተከትሎ በሳውዲ የደህንነት ሃይሎች ለጥያቂ ይፈለጋሉ ተበለው እንደ ተያዙ የሚናገሩት እነዚ ምንጮች ጉዳዩ በቀጥታ ከኢትዮጵያው አንባሳደር ክቡር መሃመድ ሃሰን ጋር ግንኙነት እንዳለው ይገልጻሉ ። አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ለረጅም አመታት ሲኖሩ ቀዋሚ የሆነ የገቢ ምንጭ እንዳልነበራቸው የሚጠቅሱት ታዛቢዎች ከቅርብ ግዜ ውዲህ በሚልዮን የሚቆጠሩ ሪያሎችን ማገላበጥ መጀመራቸው ጉዳዩ የሳውዲን የደህንነት ህይሎች ባቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ መንግስትንም የሚያሳስብ ጉዳይ ነው ብለዋል ። 

አንባሳደር መሃመድ ሃሰን መንግስት ከጣለባቸው ሃላፊነት ውጭ፡ በማንኛውም ንግድ ስራ ላይ እንደማይሰማሩ የሚመስክሩላቸው ወገኖች በአቶ ሙስጠፋ ሁሴን አማካኝነት ከፍተኛ ሪያሎችን ህገወጥ፡በሆነ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ አሾልኮ በማስገባት ከተጠቀሱት ግለስብ ጋር ቀጥተኛ የሆነ የጥቅም ግንኙነት ሊኖራቸው እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ። በተለይ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የስራተኛ እና አሰሪ ኤጀንሲ ባለቤት በመሆን ሃላፊነት በጎደለው መልኩ አያሌ ኢትዮጵያውያን እህቶቻችንን ወደ ሳውዲ አረቢያ በማስመጣት ንግድ ስራ ላይ ተሰማረተው እንደነብሩ የሚነገር ላቸው አቶ ሙስጠፋ ሁሴን በሳቸው ኤንጄንሲ አማካኝነት የመጡ እህቶቻችን በአሰሪዎቻቸው በተፈጸምባቸው አሰቃቂ ግፍ እና በደል ለሞቱ 3 እህቶቻችን ግባር ቀደም ተጠያቂ መሆናቸው ይነገራል።

አቶ ሙስጠፋ ሁሴን በኮሚኒቲ የሊቀመንበር ነት ዘመናቸው ከኮሚኒተው ስራ አመራር ሳያማክሩ «ጌታውን የተማመነች በግ እንዲሉ » የአንባሳደር የቅርብ ዘምድ በመሆናቸው ብቻ ከኮሚኔው መተዳዳሪያ ደንብ ውጭ በግላቸው ውሳኔ የኮሚኒትውን ካፍቴሪያ ካዝና ጨምሮ ቀዋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን እንዳሻቸው ሲዘውሩ እንደ ነበር ይታወቃል ። በሙስሊም የሃይማኖት አባትነታቸው ሽፋን የህዝብን አመኔታ እና ፍቅርን ለማግኘት ያደረጉት ሙከራ የተሳካላቸው አቶ ሙስጠፋ ሁሴን በሪያድ አስዳጊ በሌላቸው ህጻናት ስም አንባሳደር መሃመድ ሃሰን በሰጦቸው የድጋፍ ደብዳቤ ከተለያዩ የሳውዲ በጎ አድራጊ ገለስቦች እና ተቋማት ከፍተኛ ሪያል በመሰብሰብ ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በመባል ይታማሉ ። 

ይህ በዚህ እንዳለ አቶ ሙስጠፋ ሁሴን ካዝና ውስጥ፡የተገኘው 2 ሚልዮን ሪያል ከኮሚኒቲው ማህበር ካፍቴሪያ እና ከኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤት የተዘረፈ ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ የኮሚኒተው አባላት ግምታቸውን ይገልጻሉ። አቶ ሙስጠፋን ሁሴን ከእስርቤት ለማስለቀ ኤንባሲው ያደረገው ሙከራ እሳክሁን እንዳልተሳካ የሚናገሩት የኤንባሲው ምንጮቻችን ጉዳዩ አንባሳደሩን ጨምሮ በኮሚኒትው ዘረፋ የሚታሙትን ዲፕሎማቶች ቤት ሊያንኳኳ እንደሚችል ይናገራሉ ። 


Ethiopian Hagere ሳውዲ አረቢያ ጅዳ በዋዲ

ምክትል ጠ/ሚሩ በአቶ መለስ ዜናዊ አሰራር ላይ የመጀመሪያውን ትችት አቀረቡ

ምክትል ጠ/ሚሩ በአቶ መለስ ዜናዊ አሰራር ላይ የመጀመሪያውን ትችት አቀረቡ

መስከረም ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አቶ መለስ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ብዙ ስራዎችን መሸከማቸው አፈጻጸም ላይ ድክመት ማምጣቱን በመገምገም የማሻሻያ እርምጃ መወሰዱን ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን አስታወቁ፡፡ አቶ ደመቀ ከመንግስታዊው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉትና ትላንትናና ዛሬ ታትሞ በወጣው ቃለምልልሳቸው ላይ አቶ መለስ ብዙ ስራዎችን መሸከማቸው አንዳንድ ዘርፎችን በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሸ ችግር እንዳጋጠመ አምነዋል፡፡ “

ባለፉት ዓመታት ሥራዎቻችንን ስንገመግም ጠቅላይ ሚኒስትራችን ብዙ ስራ ተሸክመው ይሰሩ በነበረበት ወቅት ዋና ዋና የልማት ስራዎች ላይ በማተኮር አንዳንድ የሚኒስቴር መ/ቤቶችና የልማት መስኮች በሚፈለገው ደረጃ ያለመፈተሽ በዝርዝር ዕቅድ ግምገማና ድጋፍ ያለማድረግ ክፍተቶች እንደነበሩ እንደ ችግር በጋራ ያገኘናቸው ነጥቦች አሉ”፡፡ ብለዋል ምክትል ጠ.ሚኒስትሩ ጋዜጣው ከአቶ መለስ ሕልፈት በኋላ በተካሄደው የስልጣን ሽግሽግ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ደረጃ የክላስተር አስተባባሪዎች መሾማቸው በአራቱ ብሔራዊ ድርጅቶች መካከል ያለውን አለመተማመን የሚያሳይና ምክትል ጠ/ሚኒስትርነቱን ስልጣን ለሁሉም ለማዳረስ የተደረገ ነው ስለመባሉ ጥያቄ ቅርቦላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ “አቶ መለስ ታግሎ የሚያታግል ጠንካራ መሪ ነው፡፡እሱን ማጣት ትልቅ ጉድለት ነው፡፡

ጉድለቱን ዝም ተብሎ እዚያና እዚህ በዘመቻ የሚሞላ አይደለም” ሲሉ የተናገሩት አቶ ደመቀ፣ ከአቶ መለስ ህልፈት በኋላ አንድ ሰው በቀጥታ አቶ መለስን ባይተካም የጋራ አሰራርን በማጠናከር የተለያዩ የስራ ክፍፍሎች በማድረግ የጋራ አቅም አጎልብቶ እንዴት የህዳሴውን ጉዞ አጠናክሮ መቀጠል ይቻላል የሚለው በስፋት የተመከረበት ጉዳይ እንደነበር አብራርተዋል፡፡ አያይዘውም በሁለት ምክትል ጠ/ሚኒስትር ደረጃ በመሰየም የተለያዩ ክላስተሮችን እንዲያስተባብሩ ማድረግ ያለመተማመን መገለጫ አይደለም በማለት ወቀሳውን አስተባብለዋል፡፡ እነዚህን ችግሮች በመፍታት ድጋፍ ለማድረግ በምክትል ጠ/ሚኒስትር ደረጃ የክላስተር አደረጃጀት ማስፈለጉን የጠቀሱት አቶ ደመቀ የበለጠ አቅም ለማሳደግ፣የተሟላ የመሸከም ብርታት ለመስጠት ይህ የጋራ አሰራር መተግበሩን አስረድተዋል፡፡

Tuesday, October 1, 2013

ቃለመጠይቅ – ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር (“ላይፍ” መፅሄት)

ምንሰማው እውነት ከሆነ ከመቀሌው አባይ በስተጀርባ ቴዎድሮስ ሃጎስ አለ። ከአዲሳባው አባይ ስር እነ ጌታቸው አሰፋ፣ እነ ደብረፅዮን መሰለፋቸው ይሰማል። ሳሞራ የአዲሳባውን አባይ ተቀላቅሎአል። አዜብ ‘አርፈሽ ቁጭ በይ! የመለስን ፋውንዴሽን ተከታተይ’ ተብላለች። እብድ ስለሆነች ያልተጠበቀ ነገር እንዳትፈፅም በመስጋት ሰንሰለቷን ሁሉ በጣጥሰውባታል። የዘረፋ ቀዳዳዎቿን እየዘጉባት ነው። ያም ሆኖ አዜብ አርፋ ትቀመጣለች ተብሎ አይታመንም። መሞከሯ አይቀርም። የግል አስተያየቴን ለመስጠት ያህል፣ የመቀሌ – አዲሳባ ሽኩቻ ይፋ ሳይወጣ ውስጥ ውስጡን ሊጠናቀቅ ይችላል። ሁለቱ ተቀናቃኝ ወገኖች ሽጉጥ ከተኮሱ ቤተመንግስቷን ለዘልአለሙ እንደሚያጧት ያውቃሉና ሽጉጥ ወደ መምዘዝ የሚገቡ አይመስለኝም። ከሁለቱ ቡድኖች አንደኛው እስኪያሸንፍ ሃይለማርያም ወንበሩን በታማኝነት ይጠብቅላቸዋል። ማን በአሸናፊነት ሊወጣ እንደሚችል አብረን እናየዋለን። የአዲሳባው ቡድን የሚበረታ ይመስለኛል። ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም ከሁለቱም ቡድኖች ገለልተኛ ሆኖ የአስታራቂነት ሚና ለመጫወት እሞከረ ነው። ምናልባት እሱን በማንገስ ልዩነታቸውን ይፈቱ ይሆናል።… ሙሉውን የ “ላይፍ” መፅሄት ቃለ-መጠይቅ ለማንበብ @እዚህ ይጫኑ…