Monday, October 7, 2013

አዲሱ ፕሬዚዳንት በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲሱ ፕሬዚዳንት በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 27 ፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዲሪ አራተኛ ፕራዚዳንት በመሆን የተመረጡት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ የቀድሞ ፕሬዘደንት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስና ጠቅላይ ሚኒስትር ሐይለማርያም ደሳለኝ ተገኝተዋል።

በተጨማሪም ከህዝብ ተወካዮችና ከፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትና አምባሳደሮች በአቀባበል ስነ ስርዓቱ ላይ ከተገኙት እንግዶች መካከል ይጠቀሳሉ።

አዲሱ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላት ተሾመም በይፋ ስራቸውን ጀምረዋል ይሆናል። 
ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ማን ናቸው?
ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ውርቱ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ አርጆ ወረዳ በ1949 ዓ.ም ተወለዱ።
የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርጆ እና በአዲስ አበባ ተከታትለዋል።
በ1974 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በፖለቲካል ፍልስፍና እንዲሁም በአለም አቀፍ ግንኙነት ከዚያም በፍልሰፍና የዶክቶሬት ድግሪያቸውን።
ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በተለያዩ መስኮች ያከናወኑ እና በመምህርነትም ያገለገሉ ሲሆን ፥ አማርኛ ፣ ኦሮምኛ ፣ እንግሊዘኛ ፣ ቻይንኛ እንዲሁም ፈረንሳይኛ ቋንቋን መናገር እና መጻፍ ይችላሉ።
ከ1993-1994 ዓ.ም የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስትር ፣ ከጥቅምት 1994 እስከ 1998 ዓ.ም በፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት እንዲሁም ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በቱርክ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።

ዶክተር ሙላቱ በትዳር ህይወታቸው የአንድ ወንድ ልጅ አባት ናቸው።

No comments:

Post a Comment