የጉዞ
ትዝብት ! ፖሊሳዊ ክህሎት እና ንቃት የሌለው የፖሊስ ሰራዊት በኢትዮጵያ !
ፖሊስ በህዝብ እና በሃገር ድህነት ላይ የሚደርሱ አደጋዎች ቀደሞ ብሎ የማምከን ግንባር ቀደም ሃልፊነት እና ግዴታ እንዳለበት ማንም ሊክደው የማያችል እውነታ ነው። ይህን እውነታ መተግበር እየተሳነው የመጣው የኢትዮጵያ ፖሊስ አልፎ አልፎ ከህዝብ የሚቀርቡለትን መረጃዎች መተግበር ተስኖት በተዘዋዋሪ ሰላሜን ጸጥታዬን ያስጠብቅልኛል ብሎ ተስፋ በጣለበት ህዝብ ላይ የወንጀል ድርጊት የሚፈ ተባባሪ እየሆነ መምጣቱ ለፖሊስ ሰራዊቱ ሌላ የሰለጠነ ብቃት ያለው የፖሊስ ሃይል እንደሚያስፈልገው ሃገራችን ውስጥ በተደጋጋሚ በፖሊስ ሰራዊቱ እንዝላልነት የሚከሰቱ ወንጀሎች እየተበራከቱ መምጣታቸው ያመለክታሉ ።
የጅማ
ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሰሞኑንን የ3 ህጻናት ወላጅ የሆነችውን ባለቤቱን በአሰቃቂ ሁኔታ በስለት ወግቶ የገደለውን
አባወራ የምርመራ ውጤት እንደ ጀብዱ ሊያስደምጠን የሞከረው የኢትዮጵያ ፖሊስ ቴሌቪዥን ፕሮግራም ስርጨት በግናብር ቀደም መጠየቅ
የሚገባቸውን የሰራዊቱን አባላት ያፈጠጠ ስህተት ለማድበስበስ በተጠቀሰው ወረዳ የፖሊስ ምርመራ ውጤት የህዝቡ ቀልብ ለመሳብ ሲያስደምጠን
በነበረው ትረካ « የዝግጀት ክፍሉን አላውቂ ሳሚነት ለመረዳት ይግድ
ነብይ መሆን አያሻም። አዎ « ፖሊስ በቡድን እና በተናጥል የሚፈጸሙ
ወንጀሎችን ቀድሞ የመከላክል ሃልፊነት እና ግዴታ አለበት » የሚለውን
እውነታ በቅጡ መገንዘብ የተሳናቸው የማስታውቂያ ሚንስቴር የሞቀ ህንጻ
ላይ ተኮፍሰስው በስማ በለው ያረቀቁትን ልብወለድ በሳምንቱ መጨረሻ «እሁድ» የሰራዊቱን ፋቲክ ተጀቡነው እንደገደል ማሚቱ የሚያስተጋቡትን የዝግጀት ክፍሉን ጋዜጠኞች የሙያ ብቃት መቃኘት ይግድ ቢሆንም ዝግጀት ክፍሉ
ቀጣይ ዝግጀቶች እናድሉት ስለገለፀ ……. ስለተፈጸመው ወንጀል እንደሚከተለው
ለማቋደስ ወሰንኩ ።



በጅማ ከተማ የወረዳው 2 ፖሊስ መርማሪው በማስከተል ሲናገሩ ሞች ወሮ ሂሩት ለፖሊስ ያቀረቡትን የነብስ አድን ጥሪ በማስታወስ ፖሊስ ባልና ሚስት የማስታረቅ እንጂ የማፋታት ስራ እንደማይሰራ ጠቅሰው
«ጅብ ከሄደ ውሻ ጮህ እንዲሉ » በሞች ወ/ሮ ሂሩት የቀረበውን የነብስ
አድን ጥሪ ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የወ/ሮዋ ህይወት በአስቃቂ ሁኔታ ከጠፋ በኃላ ወንጀለኛውን ተከታትሎ በመያዝ ፖሊሳዊ ግዳጃቸውን በበቃት መወጣታቸውን ይናገራሉ። ይህ አባባላቸው በከተማይቱ
ጅማ ህዝብ ዘንድ ከወ/ሮ ሂሩት ግድያጋ ተያይዞ የመነጋገሪያ አጀንዳ እንደሆነ በተጨባጭ አረጋግጫለሁ፡፤ ፖሊሳዊ ብቃት በሌላቸው
የፖሊስ አባላት የሚመራውን የፖሊስ የምርመራ ውጤት በኢቲቭ የፖሊስ ፕሮግራም
መነገሩ አስፋሪነቱ አጠያያቂ ባይሆንም እንደ ጋሪ ፈረስ
ለመዘገብ የደፍረው ዝግጀት ክፍሉ ጉዳዩን በስፋት ለማየት ባለመታደሉ ያሳዝናል። በሞች ወ/ሮ ሂሩት ላይ ለተፈጸመው ወንጀል በጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የወረዳ
2 ፖሊስ ጽ/ቤት ቀጠተኛ ሃላፊነት እና ተጠያቄነት ሊኖርባቸው እንደሚገባ የሁሉም እምነት ነው።
« አካላዊ እና መንፈሳዊ ብቃት የሌለው ፖሊስ ሠራዊት ለህዝብ ህይወት እና ንብረት አሌንት የመሆን የሞራል ብቃት የለውም
!
Ethiopian Hagere ( from Ethiopia )
No comments:
Post a Comment