Thursday, October 10, 2013

በቀድሞው የኢትዮጵያ ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የበላይ ጠባቂነት ይመራ የነበረው ት/ቤት የባለቤትነት ውዝግብ በኤምባሲው የበላይነት በሰላም ተጠናቀቀ!



በቀድሞው የኢትዮጵያው ፕሬዘዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የበላይ ጠባቂ ነት ሲተዳደር በነበርው የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤት ላይ የተነሳው የባለቤት ነት ጥያቄ ውዝግብ አነጋጋሪንቱ እንዳለ ሆኖ ሰሞኑንን ተቀስቅሶ የነበረው ውዝግብ በኤምባሲው የበላይ ነት መጠናቀቁን ምንጮች ከሪያድ ይገልጻሉ ። ከእንግዲህ ወላጆች በት/ቤቱ ጉዳይ ምንም አይነት መብት እንደሌላቸው ኦክቶበር 4 2013 ምሸት ኤምባሲው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳርሽ ባዘጋጀው የወላጆች ስብሰባ ላይ በእንግድነት የተገኙት አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ለተሰብሳቢው ባሰሙት ንግግር ከንግዲህ ይህ ጥያቄ ልድርድር የማይቀርብ መሆኑንን አረጋግጠዋል ብለዋል።
ሰሞኑንን የሳውዲ አረቢያ መንግስት ለወጭ ሃገር ዜጎች የሰጠው የግዜ ገደብ መጠናቀቅን ተከትሎ ዲያስፖራው በራሱ ጉዳይ ተጨንቆ ባለበት ዋዜማ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን በማን አለብኝነት የት/ቤቱን መስተዳድር እና የቦርድ አባላት እጅ በመጠምዘዝ በዲያስፖራው ንብረት አስነዋሪ ተግባር በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ አንዳንድ የአካባቢው ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎች አክለው ገልጸዋል። በተለይ ከዛሬ 20 አመት በፊት ከ200 በማይበልጡ ህጻናት የመማር ማስተማር መረሃግብሩን «ህ» ብሎ በይፋ መጀምሩ የሚነገርለት በቀደሞው የኢትዮጵያው ፕ/ት ግርማ ወ/ጊዮርግስ የበላይ ጠባቂነት እንደሚመራ የሚነገርለት ይህ በሪያድ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤት ግንባር ቀደም ሰለባ መሆኑ ወላጆችን እንዳስደንገጠ እነዚሁ ውስጥ አዋቂ ምንጮች አክለው ገልጸዋል። 

ይህ ት/ቤት ለኢንቨስተሮች ቢተላለፍ ጥሩ ውጤት እንደሚያመጣ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ የሚሰብኩት አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ት/ቤቱን ከጥቂት ግብረአብሮቻቸው ጋር በእጅ አዙር ለመቆጣጠር ቀደም ብለው ሊፈጽሙት ያሰቡት ሴራ በህብረትሰቡ ጥረት መክሸፉን የሚገልጹት ውስጥ አዎቂዎች ዛሬ በሳውዲ የመኖሪያ ፈቃድ አለመስተካከል እና መሰል ተዛምጅ ጉዳዮች ግራ ተጋብቶ ህብረትሰቡ ጭንቀት ውስጥ ያለብትን ወቅት እንደመልካም አጋጣሚ ተጠቅመው የዲያስፖራውን ልጆች ከት/ምህርት ገበታ በግፍ ከማፈናቀል በማፈናቀል ባስነሱት ግርግር በሚልዮን የሚቆጠረውን የኮሚኒት ገንዘብ ወደ ግል ኪሳቸው ለምክተት ያደረጉት ጥረት መክሸፉን « በሳውዲ የደህንነት ሃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉትን የአምባሳደሩን የቅርብ ዘመድ በመጥቀስ» ይገልጻሉ።
ይህ ከ2ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ከአቅም በላይ በሆነ ወረሃዊ ክፍያ ወላጆችን እየመዘበረ የሚገኘው ኮሚኒትው የመካበት የነበረ ት/ቤት ጥሩ ግቢ እንዳለው በተርዱ የሪያድ ዲፕሎማቶች ጣልቃ ገብነት አደጋ ውስጥ መወደቁን የሚናገሩ ወላጆች ት/ቤት በመግዛት ከኪራይ ከፋይነት ነጻ የሚያደርጋቸውን እቅድ በኚሁ የኢትዮጵያው አንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን መደናቀፉ ግራ የሚያጋባ እና ወክሎ ለላካቸው ልማታዊ መንግስት አሳፍሪ መሆኑንን ይናገራሉ ። በ 90 የመማሪያ ክፍሎች 120 በሚበልጡ መምህራኖች በመታገዝ የመማር ማስተማሩን ስረአት እያካሄደ እንደሆነ የሚነገርለት ይህ ት/ቤት ከወላጆች እጅ ወጥቶ የጥቂት ዲፕሎማቶች እና ተላላኪዎቻቸው ኪስ ማደለቢያ ከሆነ ወዲህ የትምህርት ጥራቱ ከአመት አመት በማሽቆልቆል አምና ማትሪክ ፈተና ከወስዱ ተማሪዎች ውስጥ አብዛኛው ዝቅተኛ ውጤት በማምጣት ትምህርታቸውን መቀጠል ባለመቻላቸው በሰው ሃገር ልጆቻቸው በየመንገዱ ሲጋራ አጫሽ ቦዘኔ ለመሆን መገደዳቸውን በመምሬት የሚገልጹት ወላጆች በት/ቤቱ የመማር ማስተማር ሂደት ላይ ያላቸው ተስፋ መሞጠጡን አረጋግጠዋል። 

የአዳዲስ መምህራን ቅጥር እና የነባር መምህራን የስራ እደገት የሚወሰነው በችሎታ ሳይሆን በዝምድና እና ከዲፕሎማቱ ጋር ባላቸው የጠበቀ ግንኙነት መሆኑንን የሚገልጹት የት/ቤቱ መምህራኖች በበኩላቸው ቅሬታቸውን ሲያሰሙ የት/ቤቱ ቦርድ ተጠሪነቱ በቀጥታ ለዲፕሎማቱ በመሆኑ የደሞዝ ጭማሪ በመነፈጋቸው በትርፍ ግዜያቸው መንደር ለመንደር እየዞሩ ተማሪዎችን በክፍያ የማስጠናት ስራ ላይ ለመሰማራት መገደዳቸውን ገልጸዋል። አርብ ኦክቶበር 4 2013 ምሽት ኤንባሲው ባዘጋጀው በዚህ የወላጆች ስብሰባ ላይ በዲፕሎማቱ የተዘጋጀው አደናጋሪ እና ተአማኒነት የጎደለው የኦዲት ልብ ወልድ ሪፖርት መቀረቡ የወላጆች ተጸኖ የፈጠረው ጭንቀት መሆኑንን የሚናገሩት ታዛቢዎች 250 ሺህ ሪያል የነበረው የት/ቤቱ አመታዊ የኪራይ ክፋያ በአጭር ግዜ ውስጥ በአራት እጥፍ አድጎ 1.2 ሚልዮን ሪያል አሊያም በሃገራችን ምንዛሪ «5.4 ሚልዮን ብር » መድረሱን የሚናገሩ እንዚህ ታዛቢዎች በአንባሳደሩ ሳንባ የሚተነፈሰው የት/ቤቱ ቦርድ ከባዕዳን አከራዩች ጋር ተማስጥረው ፈጸሙ የተባለውን አሰነዋሪ ድርጊት ጥርጣሬ ያጠናክራሉ ። 

በለሌላ በኩል በት/ቤቱ የትምህርት ጥራት ላይ የቀረበውን የወላጆች ወቀሳ አምነው የተቀበሉ የት/ቤቱ ረእሰ መምህር አቶ አቡል ባስጥ ጀማል ዘንድሮ በትምህርት ጥራት ላይ የነበረውን ድክመት አምነው በመቀበል ት/ቤቱ ይመራ የነብረው በቆየ «የሲናግፖር» ካሪኩለም መሆኑንን ጠቅሰው በዚህ ዙሪያ አዲስ ጥናት መዘጋጀቱን በማውሳት ወደፊት ከወላጆች ጋር ለመስራት ቃል ቢገቡም አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከወላጆች ባለቤት ነት እጅ የወጣው ይህ አለም አቀፍ ኮሚኒቲ ት/ቤት የአምባሳደር መሃመድ ሃሰን እና የጥቂት ዲፕሎማቶች ኪስ ማደለቢያ ከመሆን ባሻገር በት/ቤቱ የትምህርት ጥራት ላይ ከእንግዲህ ምንም አይነት ለውጥ ሊመጣ እንደምያችል ስጋታቸውን በማስቀመጥ ፡ የረዕሰ መምህሩን አባባል ከጊዜያዊ ጭንቀት ለማምለጥ ለወላጆች የተነገረ የተለመደ መደለያ ቃል መሆኑንን ገልጸዋል። ኤምባሲው በጠራው በዚህ የወላጆች ስብሰባ ላይ በፈቃደኝነት ከ300 መቶ በላይ ወላጆች መታደማቸውን የሚገልጹት ምንጮች መድረኩ ሙሉ ለሙሉ በዲፕልማቱ እና እንሱ ለይስሙላ ባስቀመጦቸው ተላላኪዎች በመይዙ ወላጆች ሃሳብቸውን እንዳሻቸው ለመግለጽ እድል ባለማግኘታቸው በወቅቱ አዳራሽ ውስጥ ግጭት ተነስቷ እንደነበር ታውቋል። ይህ በዚህ እንዳለ አንዳንድ ወላጆች ት/ቤቱን በበላይነት የሚቆጣጠር ኮሚቴ ከተጠራው የወላጆች ጉባኤ ለማስመረጥ ተይዞ የነብረውን እቅድ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን አቅጣጫ በማስለወጥ እንደ ፌስ ቡክ ባሉ ሶሻል ሚዲያዎች የተሳስቱ መረጃዎችን በመስጠት የሃሰት ወሬ እየነዙባቸው መሆኑንን አውስተው አንባሳደሩ መንግስት አምኖ ከጣለባቸው ሃላፊነት ውጭ በግል እና በቡድን በኮሚኒቲው ንብረት ላይ የሚፈጽሙት አስነዋሪ ተግባር አደባባይ መውጣቱ አበሳጭቷቸው ባሰሙት ጥራዝ ነጠቅ ንግግር የስብሰባውን ተሳታፊ በመዝለፍ ለዲያስፖራው ያላቸውን ንቀት ዳግም አረጋግጠዋል ብለዋል። 

እንዚህ ታዛቢዎች አንባሳደሩ ከግል ጥቅማቸው ውጭ ምንም አይነት የህዝብ ተቆርቋሪነት የማይሰማቸው በመሆኑ የሃገራችንን በጎገጽታ የሚያጎድፍ እና ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ በመካከለኛ ምስራቅ እና አካባቢው የሚኖሩ ዜጎቻችንን ህልውና ለአደጋ የሚያጋልጥ የኢትዮጵያውያንን ባህል የሚያጎድፍ ድርጊቶች በሚዲያዎች ሲናፈሱ እንደ አንድ ሃገር መንግስት ተወካይ ጉዳዩ አንገብግቦቸው ማስቆም አለመቻላቸው ሊያስጠይቃቸው ይገባል ብለዋል። አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰንን በስም እንጂ በአይን አይተዋቸው የማያቁት የሪያድ ነዋሪዎች የትዮጵያ ኮሚኒት ግቢ ውስጥ በተለያዩ ግዜያት ያለበቂ ህክምና የሚሞቱ እህቶቻችን ጉዳይ አንድም ቀን እንቅልፍ ነስቷቸው የማያውቅ ጨካኝ ሰው መሆናቸውን ይናገራሉ ። እኚህ አምባሳደር በስራቸው ለሚንቀስቀሱ እንደነ ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን አይነቱን ሰዎች የኤንባሲ ከለላ በመስጠት ህገወጥ፡ ወጥ በሆነ መንገድ በሚልዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ወደ ኢትዮጵያ አሾልኮ በማስገባት በደሃው ሃዝባችን ጉሮሮ ላይ አጥንት የሚሸነቅሩ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የጎደላቸው የዘመናችን ጨካኝ ዲፕሎማት መሆናቸው ይገልጻሉ። በአጠቃላይ አምባሳደር መሃመድ ሃሰን እና ተላላኪዎቻቸው ማህበረሰብን በጎሳ ከፍለው በጠላትነት እንዲተያይ ማድረጋቸውን የሚናገሩ ምንጮች በትቤቱ የሚደረገውን የኤንባሲውን ጣልቃ ገብነት ጨምሮ በተለያዩ ግዜያት ዲያስፖራው ለመንግስት የሚያቀርባቸውን ጥያቄዎች በአግባቡ ተቀብለው በማስተናገድ ባለመቻላቸው ዲያስፖራውን ከመግስት ጋር ለማጋጨት እየሄዱ ያለበት የተሳስተ አቅጣጫ መረን የለቀቀ በመሆኑ በሪያድ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ማህብረሰብ ቀደም ሲል በሃገሩ ጉዳይ ላይ የነበረው ልማታዊ ተነሳሽነት ወደ ነበረበት እንዲመለስ አምባሳደር ድ/ር መሃመድ ሃሰን እና አንዳንድ ለማህብረሰቡ ክብር የለሌላቸው ዲፕሎማት ከሪያድ እንዲያነሱላቸው ጠይቀዋል ። 

Ethiopian Hagere ሳውዲ አረቢያ (ጅዳ በዋዲ )

No comments:

Post a Comment