Saturday, August 8, 2015

ሰበር ዜና ሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፀረ ወያኔ /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ተቃውሞ ስትናጥ አደረች !

ሰሞኑን የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ፍ/ቤት በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደውን ኢፍተሃዊ ውስኔ በመቃወም ሪያድ ከተማ ውስጥ ትላንት አርብ ኦገስት 7 2015 ምሸት ኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ተቃውሞውን አሰምቷል ። ቁጥሩ ከፍተኛ እንደሆነ ህዝብ የተገኘበት  ይህ ታላቅ ተቃውሞ የአካባቢውን ድባብ ለውጦት እንደ ነበር ለማወቅ ተችሏል። የተከሰተው ነገር በራሳችን እንደደረሰ ተሰምቶን በሶስት ቀን ውስጥ በተጠራ የተቃውሞ ጥሪ ይህን ያህል ህዝብ አንድነቱን ጥብቆ ለተቃውሞ በነቂስ መውጣቱ የትግሉ አንዱነት ጥንካሬ መገለጫ መሆኑን የገለጹት ሼክ ሲዒድ አህመድ ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ከባድ ፈተና እንደ ተጋረጠበት አውስተው ይህ ፈተና አዲስ ሆኖብን ሳንደናገጥ ትግሉን በበሰለና በስለጠነ መንገድ በማጠናከር እስከ ድል መቀጠል እንደሚገባ በቁጣ የወጣውን ህዝብ ሙስሊም በማረጋጋት በአባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል ።
ሼክ ሰዒድ በማስከተል አቡበከር በአንድ ወቅት በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ወህኒቤት ግፍ እይተፈፀመበት  « ፍ/ቤቱም የኛ ፤ ፖሊሱም የኛ ፤ አቅቤ ህጉም የኛ ፤ መርማሪውም የኛ ስለሆነ የፈለከውን የመከላከያ ምስከር ብታመጣ ብትወጣ ብትወርድ ከፍርድ አታመልጥም እኛ ነን የምንፈርድብህ » ተብሎ በስረአቱ ካድሬዎች በምጸት ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት ተነግሮት የነበረውን በተግባር ማየቱን ሼኩ ለተስብሳቢው በመጥቀስ በመሪዎቻችን ላይ የተፈፀመው ደባ ሊያስደንቀን እንደማይገባ ገልጸው የፍ/ቤቱን ኢፍታሀዊነት ለተሰብሳቢው በተጨባጭ  አስረድተዋል። በውቅቱ በቁጣ ገንፍሎ የወጣውን ህዝብ ለማስተናገድ ተይዞ የነበረው ቦታ በመጨናንቁ የነበረውን የሪያድ የአየር ሙቀት በመቋቋም ከ ምሽቱ 1 ስዓት ጀምሮ እስከ ሊሊቱ 9 ስዓት ድረስ በዘለቀው በዚህ  ፀረ ጭቆና ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች  ህዝበ ሙስሊሙን በገዛ ሃገሩ መቆሚያ መቀመጫ ያሳጣውን የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረዓት እንዲያጠፋላቸው እያለቀሱ  ለፈጣሪያቸው  ፀሎት  «  ዱአ » አድርሰዋል ።                                       የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ፍ/ቤት በህዝበ ሙስሊም ተወካዮች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ሰረዓቱ በመላ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ላይ እየፈጸመ ያለው ሃይማኖታዊ ጭቆና ግፍና በድል አንዱ አካል መሆኑን የገለጹት እንዚህ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከእንግዲህ ትዕግስታቸው መሞጠጡን ጠቅሰው  በዚህ አምባ ገነን ስረዓት ላይ የጀመሩትን ትግል እስከ መጨረሻ አጠናክረው ለመቀጠል በመወሰን የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።                                                                                                     በሳውዲ አረቢያ ድምጻችን ይሰማ ደጋፊዎች እያካሄዱ ባለው ሃይማኖታዊ ፀረ ጭቆና ትግል የህወሃትን/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ስረዓት የቦንድ ሽያጭና መስል የስረአቱን እንቅስቃሴ በማሽመድመድ  የታወቁ  ግንባር ቀደምና ጠንካራ መሆናቸው  ይነገራል። «ማሳሰቢያ ሊንኩን ተጭነው ያድምጡ  ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ

Saturday, April 25, 2015

በሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራውን IS IS ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡደን አወገዙ ።

ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ  ሚያዚያ 25 / 2007 ምሸት  የክርስትና የእስልምና እምንት ተከታይ የሃይማኖት አባቶች ጨምሮ መላው የሪያድ ነዋሪዎች በተገኙበት የሃዘን መግለጫ ላይ እራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራው አሸባሪ ቡደን በንጹሃን ዜጎቻችን ላይ የፈፀመውን  አረመኔያዊ ድርጊት አውግዘዋል ። አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊ ዎች እራሱን አይ ኤስ አይ ኤስ እያለ የሚጠራው አረመኔ ቡደን እንጀራ ፍለጋ ከሃገር በስተሰደዱ ንጹሃን የክርስትና እምናት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ የወሰደው ዘግናኝ እርምጃ ቡዱኑ የለየለት አረመኔና የትኛውንም ሃይማኖት የማይወክል የዘመናችን ጭራቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፤አንድ የእስልምና ሃይማኖት መሪ « ኢማም » በበኩላቸው ሲናገሩ ኢስላም ማለት ሰላም ማለት መሆኑን ገለጸው ሶሪያና ኤራቅን ጨምሮ በስሜን አፍሪካ እንደሚነቀሳቀስ የሚነገርለት ይህ የጨካኞች ቡደን በስሜት የሚነዱ ሃይማኖታዊ መስረተም ሆነ ግንዛቤ የሌላቸው አለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኖች
ስብስብ መሆኑን ተናግረዋል። ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ አለማችንን በኃይማኖት ሽፋን በሽብር በማተራመስ ምድራችንን በንጹሃን ደም ለማጨቅየት ቡድኑ ያለውን አኩይ ፍላጎት የሚያመላክት ለመሆኑ እጀራ ፍለጋ ሲከራተቱ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመው ሴጣናዊ ተግባር አብነት ነው ብለዋል ። በንጹሃን ደም የጨቀየው አይ ኤስ አይ ኤስ በ 30 ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው እርምጃ ሃዘናቸው መሪር መሆኑን የገለጹ  በስልክ ያነጋገርኳቸው አንድ የስብሰባው ተካፋይ አባወራ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ሊቢያ ላይ የተቀሉት ወገኖቻችን አሞሞት በጭካኔው ወደር የማይገኝለት በዓለም ህዝብ ፊት በአደባባይ የተፈጸመ በመሆኑ በስደት ዓለም በወገኖቻችን ላይ እይደረሰባቸው ካለው ሁሉ ለየት ያለ በመሆኑ ህዘናችንን መሪር ቢያደርገውም በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ቀደም ሲል ህጋዊ በሆነ መንገድ በኮንተራት የመጡ ኢትዮጵያውያን እህቶች አስክሬን ኮሚኒቲው ከማስተናገዱም በላይ  በሳውዲ አረቢያ የተለያዩ ግዛቶች ተበትነው የሚገኙ በ አስርሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአሰሪዎቻቸው ከሚፈጸምባቸው ግፍና በደል እራስቸውን ለመታደግ  እግር ወዳመራቸው ሲያቀኑ ህይወታቸውን አጥተው ያለቀባሪና መርዶ ነጋሪ በሳውዲ ሆስፒታሎች ተቆልሎ የሚገኘውን  የዜጎቻችንን በድን ቤት የቁጠረው ብለዋል ። እኚህ አባት በማስከተል የሞቱበት ምንክንያት በወል ሳይታወቅና ለቤተሰብ መርዶ ሳይነገር ስረዓተ ቀብራቸው የተፈጸመውን ወገኖቻችንን አሁን ማንሳት በሃዘን ላይ ሃዘን ከማስተናገድ ባሻገር ትርጉም የለውም በሚል  ምሬታቸውን በለቅሶ ገልጸዋል። 
በሪያድና በጅዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እራሱን አይ ኤስ አይ ኤስ እያለ በሚጠራው አረመኔ ቡድን በታረዱ ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የተሰማቸውን ሃዘን ለመግለጽ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን መንግስት ለዜጎች ጥበቃ አለማድረጉን በጽኑ ኮንነዋል። በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲና በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በዜጎቻችን ላይ የደረሰውን አስደጋጭ ዜና ምክንያት በማድረግ የሃዘን መግለጫው ላይ የተሳተፉት ዲፕሎማቶች  ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ትዕይንት ከማስቆም ይለቅ ነገሩን በማድበስበስ ከሃላፊነት ለማምለጥ የሚጥሩ በመሆናቸው አብዛኛው ህብረተሰብ በነዚህ የመንግስት ሹማምንቶች ላይ ያለው እምነት መሞጠጡ ይነገራል፡፤ አንድ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ከሚታተም ጋዜጣ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉ በሪያድ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማት ሪያድና ጣይፍ ከተማ ውስጥ ህይወት አጥፍተዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው አንገታቸው በአደባባይ በስይፍ ስለተቆረጠው ኢትዮጵያውያን የኮንተራት ሰራተኞች ኤንባሲው አንደ ማንኛውም ሰው ዜናውን በሳውዲ ሚድያዎች ከመስማት ባሻገር ምንም አይነት መረጃ እንዳልነበረው መግለጻቸው አይዘነጋም ፡፤ይህን ተከትሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ አንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ሃላፊነታቸውን በብቃት አልተወጡ በሚል የስራ ግዜያቸውን ሳይጨርሱ ከስልጣናቸው  ተነስተው ወደ ሃገር መመለሳቸው ይታወቃል።
ይህ በዚህ እንዳለ በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤትና በሪያድ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ሰንደቅ ዓላማዎች ዝቅ ብለው እንዲውለበለቡ ከመደረጉም በላይ ከ 5000 የሚበልጡ የሁለቱም ት/ቤት ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ተማሪዎች አይ ኤስ አይ ኤስ ብሎ እራሱን በሚጠራው አሸባሪ ቡደን በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመውን አረምኔያዊ ድርጊት በማውገዝ በዚህ ግፈኛና አረመኔ ቡደን አንገታቸው ለተቀላው ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች ጸሎት በማድረስ የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።

Ethiopian Hagere Jed Bewadi

Friday, March 20, 2015

እናቶችን የሚያስለቅስ አገዛዝ - የፍርድ ድቤት ዉሎ (ለገሰ ወልደሃና)

የካትት 10/2007 ዓም የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀበት የነዘመነ ምህረት ችሎት፣ በቀጠሮው መሠረት፣ ዛሬ መጋቢት 10/2007 ዓም ተሰይሟ።
ዘመነ ምህረት፣ መለሰ መንገሻና ሌሎች ወደ 25 የሚጠጉ ወጣቶች በማእከላዊ ፓሊሶች ታጅበው 8:ሰአት 20 አካባቢ ፍርድ ቤት ግቢ ገቡ። እንደተለመደው በርቀት እጃቻችንን በማውለብለብ ሰላም አልናቸው። እነሱም ባልታሰረው እጃቸው አፀፋውን መለሱልን።
ዘመነ ምህረት ብዙም አልተጎሳቆለም። መለሰ መንገሻ ግን በጣም ከስቷል። ሰውነቱ ቢጫ ሆኗል። እንደዛም ሆኖ ፈገግታ ግን አልተለያቸው። ችሎት ከመግባታቸው በፊት የተቀመጡበት አግዳሚ ወንበር ላይ ሆነው፣ በምልክት ለመነጋገር ሞክረን ለመግባባት ችለን ነበር። ነገር ግን ፓሊሶች ከኛ ጋር የሚያደርጉት የምልክት መግባባት አይተው፣ ፊታቸውን አዙረው አስቀመጧቸው ። ተስፋ ሳንቆርጥ ሞከርን። አልተሳካም።

የችሎት ሁኔታ እንደሚታወቀው በዝግ የታየ በመሆኑ የነበረውን ሁኔታ ማወቅ አይቻልም። ዘመነና መለሰ መንገሻ ችሎት የገቡት ተለያይተው ነው። ከዚህ መረዳት የሚቻለው የተከሰሱበት መዝገብ ይለያያል ማለት ነው ። ሁለቱም ችሎት ሲገቡ ሌሎች ወጣቶች አብረዋቸው ገብተዋል።
የዛሬው የችሎት ሁኔታ ተጨማሪ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፓሊስ ጠይቆ ለመጋቢት 08/7007 ዓም ተቀጥሯል።
አንድነት ዘመነ ምህረት፣ የዘመነ ምህረት የበኩር ልጅ፣ በፍርድ ቤት አልተገኘም። የሕጻን አንድነትን ቦታ ተክተው፣ ከሰሜን ጎንደር ተጉዘው የመጡት፣ የቆራጡ ታጋይ ዘመነ ምህረት እናት ነበሩ። እኚህ እናት ታማሚ ናቸው። የወለደ አንጀታቸው አልችል ብሏቸው ህመማቸውን ችለው፣ ከሰሜን ጎንደር፣ ከ700 ኪሎሜትር በላይ ተጉዘው፣ «ልጄ በህይወት መኖሩን ካላየሁ አላምንም» ብለው፣ አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተገኝተዋል። በጣም ያሳዝናሉ።
የመጡበትን ምክንያት የልጃቸውን በህይወት መኖር አለመኖር ለማረጋገጥ ነበር። በካቴና ታስሮም ቢሆን አይተዋል። በውስጣቸው ምን እንደተሰማቸው ባላውቅም። ጥልቅ የሆነ ሀሳብ ገብቷቸዋል። ለሰው ከመናገር ዝምታን ። ከኚህ የጀግና እናት ጋር ትንሽ ለመጨዋወት ሞክረን ነበር ። እንባቸው እየቀደማቸው ማውራት አልቻልንም። በመጦሪያቸው ጊዜ መንከራተት በጣም ያማል። እስኪ የኝህ እናት ፀሎት ተሳክቶ ዘመነ ተፈቶ ከመንከራተት ያድናቸው ዘንድ እንፀልይላቸው ። (ምንጭ: Millions of voices for freedom)

ድምጻዊ ብረሃኑ ተዘራ ሰሞኑን የለቀቀው ነጠላ ዜማ የስረአቱን ካድሬዎችና ቱባ ባለስልጣናቱን አስበርገገ ።

ኢትዮጵያን ሀገሬ ጅዳ በዋዲ

ከሁለት ሳምንት በፊት « ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ አንድነት ይብጀናል ዛሬ » በሚል ነጠላ ሃገራዊ ዜማው የተደናገጡ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ድህንነት አባላት ክተትል ይደረግበት የነበረው ድምጻዊ ብረሃኑ ተዘራ ሰሞኑንን ወደ አሜሪካ ማቅናቱን ለማወቅ ተችሏል። የህዝብን ፍላጎት በሆነ ነገር በመጨበጥ መግታት እንደ ማይቻል የሚናገረው ድምጽዊ ብርህኑ ተዘራ በተለይ ከኢሳት ድምጽ ጋር ሰሞኑን ባደረገው ቃለ ምልልስ ሲገልጽ « በመንግስት የተከለከለ አንድ ነገር በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው በመጥቀስ ህዝቡ በተቃራኒ ጎራ መቆሙን አውስቷል ይህንንም ተከትሎ ሃገራዊ አንድነትና እውነታን ማንም መገደብ ስለማይቸል « ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ አንድነት ይብጀናል ዛሬ » የሚል ነጠላ ዜማው ወቅታዊና የህዝብን ስሜት የሚገልጽ በመሆኑ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ ተደማጭነትን 

ማግኘቱን አክሎ ገልጾል፡ በዚህ ነጠላ ዜማ ውስጥ

« አይደለም አየሩ አይደለም ተራራው ፣

ሲርብ የሚያበላው ሃገር ማለት ሰው ፣

ለሆዱ ያደረ ወዳጁን የረሳ ፣

ነፃነት ምኑ ነው ቢነገር ቢወሳ ፣

» በሚለው የስንኝ ቋጠሮ የተበሳጩ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎችና ቱባ ባለስልጣናት አርቲስቱ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ተደማጭነት ካለው የኢሳት ድምጽ ጋር ቃለ ምልልስ በማድረጉና ዛሬ አሌክስ አንደር ቨሪጂንያ ውስጥ የህዝብን ትግል መቀላቀሉን በሚያበስረው ዝግጀት በአሁኑ ግዜ ጥላቸውን በማያምኑ የመንግስት ሃይሎች ጥርስ ውስጥ የገባው አርቲስት ወደ ሃገር ሲመለስ ወከባ ሊፈጸምበት እንደሚችል ምስጢራዊ ምንጮች ይገልጻሉ። በአጭር ግዜ ውስጥ የአብዛኛውን ኢትይጵይዊ ትኩረት የሳበው የአርቲስት ብረሃኑ ተዘር ነጠላ ዜማ ኢትዮጵያ በመዲናይቱ አዲስ አበባና በተለያዩ ክፍለ ህገራት ምግቤቶች ቡና ቤቶችና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ተሽክርካሪዎች ውስጥ ጭመር ሳይቀር በስፋት በመደመጥ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡

«ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ፤

አንድነት ይበጀናል ዛሬ ፤

መቼም አይሻረም ኢትዮጵያዊነቱ፤

መኖር ግን አይሻም ያለነጻነቱ ፤

እኮ ! ማነው ሰጪ ማነውስ ከልካይ፤

ሰው እንዳሻው ቢኖር በሃገሩ ላይ ፤
እያለ የሚያዜማው ድምጽዊ ብርሃኑ ክኢስት ለቀርበለት ጥያቄ አያሌ የሃገር ፍቀር ዘፈኖችን እንደዘፈነ ግልጾ ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ የሚለውን ነጠላ ዜማ ከለቀቀ ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ ይህዝብን ተኩረት ማግኘቱ አግርሞትን እንደ ደጫረበት በመናገር ከአቅሙ በላይ የሆኑ ምስጋናዎች ከህዝብ ስለተቸረው በህዝብ ውስጥ ያለውን እውነታ በሙያው ማንጸባረቅ በመቻሉ መደሰቱን ገልጾ ክብርና አድናቆትን ለቸሩት ሀገር ውስጥና በውጭ ሃገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናውን አቅርቧል ። ድምጻው ብረሃኑ ተዘራ ዛሬ በአሜሪካ ቨርጅኒያ ግዛት ውስጥ አዲስ ያወጣውን ነጠላ ዜማ ሲዲ በነጻ እንደ ሚያድል ለመረዳት ተችሏል፡ ይህ በዚህ እንዳለ ከዝግጀቱ በኃላ አርቲስት ብረሃኑ ወደ ህገር ይመለስ አይመለስ እስካሁን በግልጽ የተባለ ነገር ባይኖረም ምናልባት ከመንግስት ጥቃት እራሱን ለመከላከልና በነጻነት ለመኖር አርቲስቱ የሌሎች የህዝብ ትግል አጋሮቹን ፈለግ ሊከተል ይችላል ተብሎ ይታመናል። Ethiopian Hagere Jed bewadi

Monday, February 23, 2015

ሐዋሳ ከተማ በእሣት ስትጋይ አደረች « EBC የቀድሞው ኢ ቲ ቪ በዚህ ዙሪያ ምንም ያለው ነገር የለም »


በሐዋሳ ለጊዜው የጉዳቱ መጠን ያልታወቀ የእሣት ቃጠሎ መድረሱን በአደጋው ያዘኑ ገለጹ፡፡ ከስፍራው እንደተሰማው ለሰኞ አጥቢያ የተነሳው ቃጠሎ ምናልባትም በከተማዋ ታሪክ ከፍተኛው ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አደጋው ሲደርስ የእሣት አደጋ “አገልግሎት” በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ አስነስቷል፡፡

ለሰኞ አጥቢያ ሌሊት ላይ ነፍሳት ባረፉበት ወቅት የደረሰው የእሣት አደጋ መነሻው በትክክል ባይታወቅም ማምለጥ የሚቻልበት ባለመሆኑ አሟሟቱ የከፋ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የተለያዩ ወገኖች በምስል ይፋ ያደረጉት ቃጠሎ እንደሚመለክተው የእሣቱ መጠን በቀላሉ የሚቆጣጠሩትና አደጋውን የሚቀንሱበት እንዳልነበረ ያስረዳል፡፡
በሐዋሳ ታሪክ ከፍተኛ ነው የተባለው ይህ ቃጠሎ በህይወት ላይ ያደረሰው አደጋ በትክክለኛው ቁጥሩ ባይገለጽም ከሥፍራው የደረሰን አጭር መልዕክት እንደሚያስረዳው ከሰባት የማያንሱ መሞታቸውን ከ23 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቃጠሎ ደርሶባቸው የተጎዱ እንዳሉ፤ ሌሊት የተነሳ ቃጠሎ በመሆኑ መረጃ ለመሰብሰብ ቢያስቸግርም ደረሰ የተባለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ቀውስ ከዚህ የበለጠና ምናልባትም ኅሊናን የሚጎዳ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡
በዚሁ በደረሰን አጭር መልዕክት እሣቱን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የከተማዋ የእሣት አደጋ ብርጌድ “እውን ሐዋሳ የእሣት አደጋ ብርጌድ አላት?” የሚያሰኝ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ለመባሉ ምክንያቱ በዝርዝር አልተገለጸም፡፡ ምናልባትም አደጋው ሌሊት ላይ መከሰቱ በሰው ህይወት ላይ የተመዘገበውን አኻዝ ከሚገመተው በላይ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
የዝግጅት ክፍላችን በደረሰው የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት የተሰማውን ልባዊ ሐዘን በዚህ አጋጣሚ ይገልጻል፡፡
********************************************
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Monday, January 26, 2015

[ፎቶ] በሰላሌ አውራጃ ሁለት ግለሰቦች በመንግስት ሃይሎች ተገለው በአደባብይ ተሰቀሉ

 በሰላሌ አውራጃ በዳራ ወረዳ በጎሮ መስቀል መንደር ሁለት ግለሰቦች በመንግስት ሃይሎች ተገለው እሬሳቸው በመሃል ከተማ የተጎተተና ብሎም ህዝብ አይቶ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ በአደባብይ ተሰጥተው መዋላቸውን ተዘግቧል። « የወያኔ ጦር በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽመው የጦር ወንጀል » 




Friday, January 23, 2015

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ሰራተኞች ድምጽ አልባው እሮሮ !

ንብረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደሆነ በሚነገርለት ካፍቴሪያ ውስጥ የሚፈጸመው ግፍ አይሏል ። ከዛሬ 10 ዓመት በፊት እዚህ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ውስጥ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ሰማርተው እያገለገሉ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን አብዛኛዎቹ በወጣትነት እድሚያቸው የተቀጠሩ ናቸው ። ታዲያ ለወጣትነት እድሜ ጉልበታቸው ሳይሰሱ ነገን በተስፋ በመናፈቅ ተመጣጣኝ ባልሆነ ክፍያ በቀን ከ 8 ሰዓት በላይ አውዳአመታትን ሳይቀር ያለ እረፍት በስራ በማሳለፍ ኮሚኒቲውን አገልግለዋል። ሰራተኞቹ በተሰማሩበት የስራ መስክ በሚከፈላቸው ደሞዝ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ቤትሰብ አፍርተዋል ። እነዚህ ወገኖች እንደመነሻ በተቀጠሩበት አነስተኛ ደሞዝ ከግዜ ወደ ግዜ እይከበደ የመጣውን የስደት ዓለም ህይወት መቋቋም ተስኗቸው ገሚሱ በብስጨት በደረሰበት የጤና መታወክ ለህለፍት ሀይወት ሲዳረግ በስኳር በሽታ አይኑ ታውሮ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ ቤተሰቡን የበተነም እንዳለ ይነገራል። የተቀሩት እንደ ስራ ባልደረቦቻቸው አስከፊው ዕጣ ደርሷቸው ከስራ ገበታ ስኪፈናቀሉ በደም ግፊት እና ተጓዳኝ በሆኑ በሽታዎች የተጎስቆለ አካላቸውን በቁም እያስታመሙ አቤት ቢባል አድማጭ በሌለበት ሰማይ ስር የመጣውን ሁሉ ችለው ከእጅ ወደ አፍ የሆነቸውን ኑሮ ለማሸነፍ በውዴታ ግዴታ ኮፍቴሪያውን ማገልገላቸውን ቀጥለዋል።
ሁሌም ሃዘን እንጂ ደስታ ውስጣቸውን የማይሰማው እነዚህ ወገኖች የወጣትነት ፊት ገጽታቸው ተቀይሮ ያለ እድሜያቸው የተሸብሽው ቆዳቸው ከሰውነት ጓዳና በመውጣት ውስጣቸው ፍጹም፡ ሰላም እንድሌለ ያሳብቃል። ኮሚኒቲውን ለቀው እንዳይሄዱ ጉልበታቸው ዝሎ አቅም አልባ ሆነዋል ! የእድሜውም ጉዳይ በሌላ በኩል በዕንቀርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆኖባቸዋል ። ብቻ በአጠቃ ላይ በ 4 አመት አንዴ ግዜ እየጠበቁ ከኮሚኒቲው መተዳደሪያ ደንብ እና ስረዓት ውጭ በኤንባሲው አስተባባሪነት በብሄር እይተቦደኑ ያለችሎታቸው የአመራሩን ቦታ በሚጨብጡ የኮሚቲኒው አስተዳዳሪዎች በሚደርሰባቸው ዛቻ እና ማስፈራሪያ ከደሞዝ ጭማሪ ይልቅ ከስራ ገበታቸው እንዳይፈናቅሉ በስጋት ተሸብበው ፈጣሪ መህረቱን እንዲያወርድላቸው ይማጸናሉ። ለነዚህ የኮሚቲው አንጋፋ ሰራተኞች ክብር ብሎ ነገር አይታሰብም ምግብ በላህ ሻይ ጠጣህ የለስላሳ ማቀዝቀዣ ለመክፈት አሰብክ ተብሎ የጎሪጥ ክትትል እየተደረገባቸው ከሚሰነዘርባቸው አሳፍሪና አስዛኝ ክስ ባሻገር ህይወታቸውን ሙሉ በማገልገላቸው ብቻ ለሞራል የሰርተፍኬት ሽልማት እንኳን አጊተው አያውቁም። አንዳንዴም በተጠቀሱት አመራር አባላት እንደ ሰራተኛ ሳይሆን እንደ ሌባ በአይነ ቁራኛ ይጠበቃሉ። አፋቸውን በሁለት እጆቻቸው ግጥም አድርገው ካልያዙ የመናገር ሰበአዊ መብታቸው ተገፎ አመራር ዘለፉችሃል በሚል ክስ በዝቅተኛ ደሞዛቸው ላይ ከፍተኛ ቅጣት ይጣላል አሊያም ከስራ ገበታቸው ይታገዳሉ፡፡አልፎ አልፎም አይጥ በበላ ዳዋ እንዲሉ በሁለት አመት አንዴ ከአንድ ገጽ በማይበልጥ ብጣሽ ወረቀት ለማህበሩ አባላት ለይስሙላ በሚቀርብ ሪፖርት በኮሚኒቲው ካፍቴሪያ ካዝና ላይ ለተፈፀመው ነውረኛ ተግባር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠያቂ ሆነው ጣት ይቀሰርባቸዋል።
ሳውዲ አረቢያ ምድር ላይ ይህ ሁሉ ግፍ እና በደል በነዚህ ኢትዮጵያውያን ላይ እይተፈፀመ ያለው በባእዳኑ ሳውዲያን ሳይሆን እነሱን የሚመስል ባህሪ ባላቸው ጨካኝ ኢትዮጵያውያን መሆኑ ነገሩን አነጋጋሪ እና ውስብስብ ያደርገዋል። ወትሮስ ለማን አቤት ሊባል ! ዛሬ እነዚህ ግፉሃን ልጆቻቸውን ማስተማር ተስኗቸው ተጨማሪ ግቢ ፍለጋ ከካፍቴሪያው የስራ ሰአት ውጭ በመከራተት አስቀያሚ የስደት ዓለም ህይወታቸውን መግፋት ግድ ቢሆንባቸውም ሁሉም ነገር ግን ጨልሞል።በተላይ የሳውዲ አረቢያ ሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት የአሰሪ እና ሰራተኛ ደንብ አስመልክቶ ባወጣው ህግ ማናኛውም የውጭ ሃገር ዜጋ አሰሪው ከሚያሰማራው የስራ መስክ ውጭ የትም ሄዶ መስራት እንደማይችል ከተነገረ ወዲህ ለነዚህ ወገኖች የስውዲን አረቢያን ህይወት ያለተጨማሪ ግቢ መግፋት የማይታሰብ በመሆኑ ለከፋ ስቃይ እና መከራ ተዳርገዋል ።
Ethiopian Hagere Jed Bewadi