Thursday, February 27, 2014

"ዓድዋ - ይከበር፣ ይዘከር - ለዘላለም !" ( የማለዳ ወግ ... ጉዞ ወደ ዓድዋ ! ነቢዩ ሲራክ )


የማለዳ ወግ ... ጉዞ ወደ ዓድዋ ! 
"ዓድዋ - ይከበር፣ ይዘከር - ለዘላለም !"

የአድዋ ድል የአድዋ ድል ለእኛ ለኢትዮጵያውያን የማንነታችን መሰረትና የህልውናችንም መገለጫ ብቻ ነው አልልም ። ዓድዋ ለመላው የጥቁር ህዝብ የነፃነት ተምሳሌትና የአርነት ምንጭ ስለመሆኑ የታሪክ መዛግብትም ሆኑ ባእዳን የታሪክ ልሂቃን ሳይቀር የሚመሰክሩት ሃቅ ነው ። በዓድዋ የጥቁር ዘር አትንኩኝ ባይበት ሲረጋገጥ የጥቁር ዘር ለነጻነቱ ቀናኢ መሆኑን ለአለም የታየበት መሆኑም የሚታበል አይደለም ! 

የዚህ ታላቅ ድል ባለቤቶች ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሆናችን አልፋና ኦሜጋ ሲያኮራን ይኖራል። የዓድዋን ታሪካዊ የድል በአል በመላ አለም በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አመት በመጣ ባሰለሰ ቁጥር በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል። በአሉ ሃበሾች በነጭ እብሪተኞች ላይ የተቀዳጀነው የዓድዋ ነውና ቀጣዩ ትውልድ ታሪኩን አክብሮና ጠብቆ እንዲኖር ያደገዋልና የበአሉ መከበር ታሪክን ከማወራረስ አንጻር ያለው ጠቀሜታ ከፍ ያለ ነው ። የዘንድሮው 118ኛ የዓድዋ ድል በአል ለማክበር በአገርና በቀረው አለም በምንገኝ ኢትዮጵያውያን በማህበራዊ ድህረ ገጾች ሰፋ ያለ የመታሰቢያ ማዘከሪያ ዝግጅትን በማድረግ ላይ መሆናችን እውነት ነው ። 

በአረቡ አለም በተለይም ከግማሽ ሚሊዮን የማያንስ ኢትዮጵያውያን በምንገኝበት በሳውዲ አረቢያ በአሉን አድምቀን እንድናስበው ስለማይደረግ እድሜ ለቴክኖሎጅ በአሉን በማህበራዊ ገጾቻችን ለማክበር ተፍ ተፍ በማለት ላይ እንገኛለን። በሪያድ ኢንባሲና በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎቻችን የዓድዋን ታላቅ ሃገር አቀፍ በአል በአዳራሾቻቸው ተሰባስበን እንድናከብረው ቢያደርጉን ምንኛ በኮራን ነበር ! ዳሩ ግና የኢንባሲና የቆንስል ሃላፊዎቻችን እንዲህ አስበው አናውቃቸውም እንደ ልማዳችን እናዝናለን ። ቢያንስ የገዥው ፖለቲካ ድርጅቶች እና በጎጥ ለተመሰረቱት የልማት ማህብራት የሚሰጡትን ያህል ለቱባው ኢትዮጵያዊነት ክብር ሰጥተው ዓድዋን ሻማ አብርተን የጀግኖቻችን ታሪክ ላንድ አፍታ እያነሳሳን እንድናዘክር ፣ እንድንማማርና እንድናመሰግን አያደርጉም ። እውነቱ ይህ ሆነና የስደት ፍሬ የሆኑ በአረብ ሃገር ተወልደው የሚያድጉ ልጆቻችን የዓድዋንና የመሳሰሉ ሃገር አቀፍ በአላት ይልቅ ስላደጉበት አገር በአላት የተሻለ እውቀት እንዲኖራቸው እየገፋናቸው በመሆኑ ሊታሰብበት ይገባል ። የበአሉን አከባበር ካነሳሁ አይቀር ቀልቤን ወደሳበው እና መነሻየ ወደ ሆነው በስድስት ትንታግ ጎልማሶች እየተደረገ ስላለው የዓድዋ ታሪካዊ የእግር ጉዞ ላምራ ...

በፍላጎት የተሰባሰቡ ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ስድስት ጎልማሶች
1ኛ / ጋዜጠኛና የፊልም ባላሙያው ብርሃኔ ንጉሴ 
2ኛ/ ጋዜጠኛ ኤርሚያስ ዓለሙ ከኢትዮጲካሊንክ 
3ኛ/ መሐመድ ካሣ (ኬር ኤቨንትስ ኤንድ ኮሙኒኬሽን - የባህልና የኪነ ጥበብ ፕሮሞተር) 
4ኛ/ ሙሉጌታ መገርሣ (ደብሊው) (የፊልም ባለሙያ) 
5ኛ/ አለምዘውድ ካሳሁን (የካሜራ ባለሙያ) 
6ኛ/ ያሬድ ሹመቴ (የፊልም ባለሙያ) 

በአንድ ውለው በአንድ አስበው ለታሪካዊው 118 የዓድዋ ድል መታሰቢያ ልዩ ዝግጅት አቅደው ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴው አመሩ። ጥር 10 ቀን 2006 ዓ.ም ከሌሊቱ 11፡30 በግምት ወደ 40 ቀን የሚወስደውን ረጅሙን ወደ ዓድዋ የሚያደርጉትን የ1,006 ኪሎ ሜትር ርቀት ጉዞ ከአዲስ አበባ ዳግማዊ አጤ ምኒልክ አደባባይ በአንድ እርምጃ ጀምረው ወደ ማጠናቀቁ ተቃርበዋል። 

ታላቁን የአድዋ ድል ለማዘከር "ዓድዋ - ይከበር፣ ይዘከር - ለዘላለም" የሚል መፈክር ይህን ጉዞ ለማድረግ ያነሳሳቸው ዋና አላማ 118ኛ የዓድዋን ድል ቀን በዓድዋ ለማዘከር እንደሆነም ሰምተናል። ትንታግ ጎልማሳ ወንድሞቻችን በትጋት የጀመሩትን ጉዞ ሊያጠናቅቁ የቀራቸው ጥቂት ቀናት ብቻ ነው። 

ከአጤ ምኒልክ አደባባይ የተጀመረውን ጉዞውን ልዩ የሚያደርገው ቀደምት አባቶቻችን የዓድዋ ድል ከ118 አመት ለማስገኘት እየተሰባሰቡ የዘመቱባቸውን ከተሞች ተከትሎ መሆኑ ታሪካዊውን የሃገር ወዳድ ወንድሞች ጉዞ ልዩ አድርጎታል። የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ ከፍ አድርገው በማውለብለብ ጉዟቸውነወ በመከወን ላይ የሚገኙት ተጓዦች በየደረሱባቸው ታሪካዊ ከተሞች ሞቅና ደመቅ ያለ አቀባበል እየተደረገላቸው መሆኑን ያን ሰሞን ተጓዦች መረጃውን አድርሰውናል።

እኒህ የብርታት ተምሳሌት የሚሆኑን ትንታግ ወንድም ተጓዦች ቃል አቀባይ ወንድም ተጓዦች ኮንቦልቻ እንደደረሱ በሰጠው ማብራሪያ እንዲህ በማለት ያስረዳል "... ማለዳ በአድዋ ድልድይ ተሻገሩ፡፡ ለገጣፎ - ለገዳዲ - ሰንዳፋ - በኪ - አለልቱ - ፍቼ - ሐሙስ ገበያ - ሸኖ - ሰምቦ - ጥያኪ - ጫጫ - ጠባሴ - ጅሁር መገንጠያ - ደብረ ብርሃን - አንኮበር መገንጠያ - ቀይት - ጉዳ በረት - ጣርማ በር - ደብረ ሲና - ጭራ ሜዳ - አስፋቸው - ሸዋ ሮቢት - አጣዬ - ከሚሴ - ሃርቡ - ፎንተኒና - አልፈው ኮምቦልቻ ደርሰዋል፡፡ በመንገድ ላይ አጤ ምኒልክ እና ሠራዊቱ (የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች) ለአገርና ለሕዝብ ዘብ የቆሙ ወታደሮች የደረሰባቸውን መከራ ይዘክራሉ፡፡ የአድዋ ድል የጥቁር ህዝቦች ድል ነው፡፡ በዚህ ድል አፍሪካዊያን ይኮራሉ፡፡ የዚህ ድል ባለቤት የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው፡፡ በዚህ የታሪክ ሰንሰለት ተምሳሌቱን ዳግም ለዓለም ለማወጅ ታሪካዊ ጉዞ እያደረጉ ናቸው፡፡ ተጓዦቹ - ሰንቃጣ ወይንም (ስንቅ አጣን) ሲደርሱ የታሪካዊ ጉዞ ፈተና ይቀምሳሉ፡፡ (ይራባሉ - ይጠማሉ፡፡) የስድስቱ ተጓዦች ለመራብ - ለመጠማት መዘጋጀታቸው ልዪ የሚያደርገው ስንቅ እያላቸው መሆኑ ነው፡፡ ስድስቱ የእግር ተጓዦች የካቲት 23 ቀን 2006ዓ.ም አድዋ ይደርሳሉ፡፡ 118ኛ የዓድዋ ድልን በአድዋ ተራራ ያከብራሉ፡፡ በርካታ ታሪካዊ መዘክሮችን አዘጋጅተዋል፡፡ ለምሳሌ ሶሎዳ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ባንዲራ በክብር ለማቆም አቅደዋል፡፡ የአድዋ ክብረ በዓል ላይ የበዓሉን ማብሰሪያም መድፍ ይተኮሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተጓዦቹ - ‹‹በየደረስንበት የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ አቀባበልና ድጋፍ እያደረገልን ነው፡፡ !›› ብሏል ! ጉዞው አሁንም ቀጥሏል ... እኒህ ወንድሞች ትጋትና ቁርጠኝነትን በትጋት እና በተግባት ለማሳየት ፣ የአባቶቻችን ታሪካዊ ተጋድሎ በክብር ለማስታወስ "ዓድዋ - ይከበር፣ ይዘከር - ለዘላለም !" ሲሉ የእግር ጉዞ አኩርቶኛል! በእርግጥም እኒህ ወንድሞቻችን ለአባቶች ተጋድሎ ተድበስብሶ እንዳይቀር እና አንጸባራቂውን ድል ለቀጣዩ ትውልድ በክብር ለማውረስ ስራ በመስራታቸው ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል! ይህን መሰል ፋና ወጊ ታሪክ ለመስራት መታደል በእርግጥም መታደል ነው !

አዎ እኔም በአድዋ ድል እኮራለሁና "ዓድዋ - ይከበር፣ ይዘከር - ለዘላለም !" እላለሁ ! 
የዓድዋን ድል በክብር እዘክራለሁ ! እናዘክራለን !

ክብር ለኢትዮጵያ ክብር ለደሙ ለቆሰሉና በክብር ለሞቱ ሰማዕነታት ፣ ለጀግኖቻችን !

ከሰብር ለእምየ ምኒሊክ እና ለእቴጌ ጣይቱ !

ክብር ለኢትዮጵያ !

ሰላም

ነቢዩ ሲራክ

Tuesday, February 25, 2014

የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረዕት ነጻ ፕሬሶችን አስጠነቀቀ !



ኢዜአ የነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበር ሊቀመንበርን ጠቅሶ ባስተላለፈው ዜና የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ዳግም በነጻ ፕሬሶች ላይ እርምጃ ለመውሰድ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጦል። እንደ ዜናው ዘገባ በአሸባሪነት ተፈርጀው በህግ ቁጥጥር ስራ  በሚገኙ ዙሪያ አንዳንድ ጋዜጦች የተዛባ ውዥንበር በህዝብ መሃል  በመንዛት ድብቅ አጀንዳቸውን ያራምዳሉ ብሏል። 

የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ሰሞነኛ ፉከራ  መጪውን ሃገራዊ ምርጫ ተከትሎ የተቃዋሚ ሃይሎች በህዝብ ዘንድ ድጋፍ እያገኙ እና እያንሰራሩ መመጣታቸው  እንዳስደነገጠው የሚናገሩ ወገኖች  ከብሄራዊ ምርጫ በፊት የህዝብ ልሳን የሆኑትን የነጻ ፕሬስ ጋዜጦችን በማጥፋት የህዝብን ድምጽ፡ለማፈን እያደረገ ያለው  ዘመቻ አንዱ አካል መሆኑንን  ይስማሙበታል ። በ1997 እ.ኢ.አ በኢትዮጵያ የተካሄደውን ብሄራዊ ምርጫ ተከትሎ በተነሳው ውዝገብ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት ኮሮጆ ገልብጦ ጠንካራ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችን በማጥፋት ብቻውን እሩጦ በዴሞክራሲ ሽፋን አለም አቀፉን ማህበረሰብ  ሲያደናገር የነበር ስረአት መሆኑንን የሚገልጹ የፖለቲካ ተንታኞች ሀግሪቱን ያለተቀናቃኝ ለ20 አመታት ረግጦ መግዛቱን በመጥቀስ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር መለሰ ዜናዊ ሞት በሃላ  በአባልቱ መሃከል የነበሩ  አለመግባባቶች ፈር እይለቀቁ መምጣታቸውን ተከትሎ    ድርጀቱ ከእንግዲህ እንደ መንግስት መቀጠል እንደማይችል  ይናገራሉ።  ይህ በዚህ እንዳለ  የነጻውን ፕሬስ አባላት በመግደል እና በማፈን የሚታወቀው ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መግስት ኢትዮጵያ ውስጥ አቋጥቁጦ የነበርን   ዲሞክራሲያዊ ስረአት በመቀልበስ  በአለም አቀፍ ደረጃ ከለየላቸው አንባ ገነን  መንግስታቶች ግንባር ቀደም  መሆኑ ይታወቃል።   

  አቶ   ታምራት ይህደጎ  ከቨርጅኒያ  

Monday, February 24, 2014

የመስጊድ ኢማሞች የሚሾሙት በመንግስት በራሱ መሆኑን መንግስት አመነ!!!



ሕዝቡ ሳያውቀው ሕገ መንግስቱ ተቀይሮ ይሆን?
ሰኞ የካቲት 17/2006

መንግስት ‹‹እኔ በሾምኳቸው የመስጊድ ኢማሞች (አሰጋጆች) አልሰገዳችሁም›› በሚል ንጹሀን ሙስሊም ግለሰቦች ላይ ክስ ያቀረበበት ሰነድ ተገኘ!!!

ከፍርድ ቤት የውስጥ ምንጮቻችን የተገኘውና በፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሀን አለባቸው ፊርማ በታህሳስ 4/2006 የተጻፈው ይኸው የክስ ሰነድ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ የቀረበ ሲሆን ሁለት መስጂድ ውስጥ በኢማምነት ያሰገዱ ሙስሊም ግለሰቦችንም ተከሳሽ አድርጎ አቅርቧል፡፡

ሰነዱ እጅግ አስገራሚውን ክስ ሲያብራራ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሽ በቁባ መስጂድ የአህባሽ ተከታዩን ኢማም ተከትሎ ለመስገድ ፍቃደኛ ያልሆነውን ህዝበ ሙስሊም ማሰገዳቸውንና በዚህ ተግባራቸውም ‹‹የሃይማኖት ሰላም ስሜት›› መንካታቸውን ገልጿል፡፡ ቃል በቃልም ሁለተኛ ተከሳሽ ‹‹መንግስት በሾመው ኢማም ቦታ ላይ በመቆም ሳይፈቀድለት የእነሱን ተከታዮች በማሰገድ ሰላማዊው ሙስሊም እንዳይሰግድ በማድረግ...›› ወንጀል መስራቱን ገልጿል፡፡

እስካሁን ‹‹መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ መንግስታዊ መርህ አልጣስኩም›› እያለ ሲከራከር የቆየው መንግስት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲጋለጥ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን መከራከሩ እንደማያዋጣው አውቆ በማን አለብኝነት ‹‹እኔ የሾምኩትን ኢማም አልተከተላችሁም›› በሚል ፍርድ ቤት ችሎት ማሰየም መጀመሩ ‹‹ህገ መንግስቱ አንድ ቀን ይከበር ይሆናል›› ለሚሉ ወገኖች ትልቅ መርዶ ይዞ መጥቷል፡፡ የአገሪቱ ‹‹የፍትህ›› አካላት የሆኑት ዳኞች እና አቃቤ ህጎች መንግስት የሾመውን ኢማም ተከትላችሁ አልሰገዳችሁም›› በሚል ኢ-ህገ መንግስታዊ ክስ ላይ በይፋ መሰየማቸውም ለሀገሪቱ የፍትህ ስርአት የቁልቁለት አዘቅት መሆኑ አያጠራጥርም!

ህዝበ ሙስሊሙ ከ1987 ጀምሮ በመንግስት ሹመኞች ቁጥጥር ስር የዋለውን መጅሊስ ተቀባይነት የነሳውና ለመሪ ተቋሙ መመለስም እስካሁን እየታገለ ያለው መጅሊሱ የመንግስት ካድሬዎች መጫወቻ በመሆኑ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በመጅሊሱ ስም የሚካሄዱት ሁሉም ተግባራት በመንግስት የሚሾፈሩ መሆናቸውም የአደባባይ ምስጢር ሆኖ ቆይቷል፡፡ የዛሬውን ዜና ልዩ የሚያደርገው ግን መንግስት ‹‹ሽብርተኝነት›› እና ሌሎች የማስመሰያ ስሞች ሳያስፈልጉት ‹‹እኔ የመረጥኩልህን እምነት አልተከተልክም፤ እኔ በሾምኩልህ ኢማም አልሰገድክም›› ሲል በግልጽ በሰነድ ጭምር ምስክር ጠርቶ ችሎት ፊት ሰዎችን ማቆሙ ነው፡፡ ይህም ይፋ መውጣቱ መንግስት የደረሰበትን የሃይማኖታዊ አፈና ደረጃ ለመላው ዓለምና ለሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት ይበልጥ ይፋ የሚያደርግ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡

አዎን! የመንግስት ሃይማኖታዊ ጭቆና በምንም መልኩ መደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ ግን ከሁለት አመታት በላይ ኢ-ፍትሀዊነትን ሲታገል የቆየው ህዝበ ሙስሊም የበለጠ በትግሉ ላይ እንዲጠናከር የሚያደርገው እንጂ ተስፋ የሚያስቆርጠው አይደለም፤ ህዝብ ተስፋ አይቆርጥም! ህዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖት ነጻነቱ እስኪከበርና የዜግነት መብቱን የሚጋፉ አሰራሮች እስኪቀረፉ ድረስ በጽናት መታገሉን ይቀጥላል፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!!!

ድምጻችን ይሰማ!

አላሁ አክበር!
የመስጊድ ኢማሞች የሚሾሙት በመንግስት በራሱ መሆኑን መንግስት አመነ!!!
#Ethiopia #Ethiomuslims #EPRDF #FreedomofReligion @Dimtsachinyisema
ሕዝቡ ሳያውቀው ሕገ መንግስቱ ተቀይሮ ይሆን?
ሰኞ የካቲት 17/2006

መንግስት ‹‹እኔ በሾምኳቸው የመስጊድ ኢማሞች (አሰጋጆች) አልሰገዳችሁም›› በሚል ንጹሀን ሙስሊም ግለሰቦች ላይ ክስ ያቀረበበት ሰነድ ተገኘ!!!

ከፍርድ ቤት የውስጥ ምንጮቻችን የተገኘውና በፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሀን አለባቸው ፊርማ በታህሳስ 4/2006 የተጻፈው ይኸው የክስ ሰነድ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ የቀረበ ሲሆን ሁለት መስጂድ ውስጥ በኢማምነት ያሰገዱ ሙስሊም ግለሰቦችንም ተከሳሽ አድርጎ አቅርቧል፡፡

ሰነዱ እጅግ አስገራሚውን ክስ ሲያብራራ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሽ በቁባ መስጂድ የአህባሽ ተከታዩን ኢማም ተከትሎ ለመስገድ ፍቃደኛ ያልሆነውን ህዝበ ሙስሊም ማሰገዳቸውንና በዚህ ተግባራቸውም ‹‹የሃይማኖት ሰላም ስሜት›› መንካታቸውን ገልጿል፡፡ ቃል በቃልም ሁለተኛ ተከሳሽ ‹‹መንግስት በሾመው ኢማም ቦታ ላይ በመቆም ሳይፈቀድለት የእነሱን ተከታዮች በማሰገድ ሰላማዊው ሙስሊም እንዳይሰግድ በማድረግ...›› ወንጀል መስራቱን ገልጿል፡፡

እስካሁን ‹‹መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ መንግስታዊ መርህ አልጣስኩም›› እያለ ሲከራከር የቆየው መንግስት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲጋለጥ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን መከራከሩ እንደማያዋጣው አውቆ በማን አለብኝነት ‹‹እኔ የሾምኩትን ኢማም አልተከተላችሁም›› በሚል ፍርድ ቤት ችሎት ማሰየም መጀመሩ ‹‹ህገ መንግስቱ አንድ ቀን ይከበር ይሆናል›› ለሚሉ ወገኖች ትልቅ መርዶ ይዞ መጥቷል፡፡ የአገሪቱ ‹‹የፍትህ›› አካላት የሆኑት ዳኞች እና አቃቤ ህጎች መንግስት የሾመውን ኢማም ተከትላችሁ አልሰገዳችሁም›› በሚል ኢ-ህገ መንግስታዊ ክስ ላይ በይፋ መሰየማቸውም ለሀገሪቱ የፍትህ ስርአት የቁልቁለት አዘቅት መሆኑ አያጠራጥርም!

ህዝበ ሙስሊሙ ከ1987 ጀምሮ በመንግስት ሹመኞች ቁጥጥር ስር የዋለውን መጅሊስ ተቀባይነት የነሳውና ለመሪ ተቋሙ መመለስም እስካሁን እየታገለ ያለው መጅሊሱ የመንግስት ካድሬዎች መጫወቻ በመሆኑ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በመጅሊሱ ስም የሚካሄዱት ሁሉም ተግባራት በመንግስት የሚሾፈሩ መሆናቸውም የአደባባይ ምስጢር ሆኖ ቆይቷል፡፡ የዛሬውን ዜና ልዩ የሚያደርገው ግን መንግስት ‹‹ሽብርተኝነት›› እና ሌሎች የማስመሰያ ስሞች ሳያስፈልጉት ‹‹እኔ የመረጥኩልህን እምነት አልተከተልክም፤ እኔ በሾምኩልህ ኢማም አልሰገድክም›› ሲል በግልጽ በሰነድ ጭምር ምስክር ጠርቶ ችሎት ፊት ሰዎችን ማቆሙ ነው፡፡ ይህም ይፋ መውጣቱ መንግስት የደረሰበትን የሃይማኖታዊ አፈና ደረጃ ለመላው ዓለምና ለሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት ይበልጥ ይፋ የሚያደርግ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡

አዎን! የመንግስት ሃይማኖታዊ ጭቆና በምንም መልኩ መደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ ግን ከሁለት አመታት በላይ ኢ-ፍትሀዊነትን ሲታገል የቆየው ህዝበ ሙስሊም የበለጠ በትግሉ ላይ እንዲጠናከር የሚያደርገው እንጂ ተስፋ የሚያስቆርጠው አይደለም፤ ህዝብ ተስፋ አይቆርጥም! ህዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖት ነጻነቱ እስኪከበርና የዜግነት መብቱን የሚጋፉ አሰራሮች እስኪቀረፉ ድረስ በጽናት መታገሉን ይቀጥላል፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!!!

ድምጻችን ይሰማ!

አላሁ አክበር!
Like ·  · 5 hours ago · 

የኩዬት መንግስት ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ወደ ሃገሩ ገብተው እንዳይሰሩ እገዳ ጣለ፡፡


የኩዬት የሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚንስቴር ኢትዮጵያውያን ወንድ እና ሴት የቤት እና የጉልበት ሰራተኞች ወደሃገሩ ገብተው እንዳይሰሩ ማገዱን አስታውቋል፡፡

የፓስፖርት እና የብሄራዊ ጉዳዮች ምክትል ሃላፊ ሜጀር ጀነራል ፈይሰል አል ናዋፍ እንዳሉት ለኢትዮጵያውያኑ ቪዛ መስጠት የታገደው በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች እየተፈጸመ ያለው የግድያ ፣ የስርቆት ፣ የድብደባ እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች በማስፈራራት ገንዘብ የመጠየቅ ወንጀሎች በመበራከታቸው ነው፡፡

እገዳው ተግባራዊ የሚሆነው ከየካቲት 12 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

አል-ሻባብ ቤተመንግሥቱን አጠቃ


የአልቃይዳ ግብረአበር ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች ሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ውስጥ በፕሬዚዳንቱ ቤተመንግሥት - ቪላ ሶማሊያ ላይ ከፍተኛ አደጋ መጣላቸው ተዘግቧል፡፡

በጥቃቱ አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣንን ጨምሮ ቢያንስ 17 ሰው ተገድሏል፡፡
በፕሬዚዳንቱ ላይ ጉዳት አልደረሰም፡፡

የዛሬው ጥቃት የአልሻባብ ጥቃት የተጣለው የሶማሊያ መንግሥትና የአፍሪካ ሕብረት ኃይሎች በቡድኑ ላይ አዲስ ጥቃት ለመክፈት እያቀዱ ባሉበት ወቅት ነው፡፡

ከዛሬው የጁምዐ ሶላት በኋላ አደጋ ጣዮቹ የቪላ ሶማሊያን ማለትም የፕሬዚዳንቱን ቤተመንግሥት ቅጥር ግቢ መግቢያ ከከበቡ በኋላ ወደ ውስጥ ዘልቀው ለመግባት በኃይል መሞከራቸውን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ጥቃት አድራሾቹ ለማሳሳቻ የተጠቀሙበትን ወታደራዊ የደንብ ልብስ ለብሰው እንደነበርም የፀጥታ ባለሥልጣናት አመልክተዋል፡፡

የካናዳ ዜግነት የነበራቸው የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ኃላፊ ከተገደሉት መካከል እንደሚገኙ ታውቋል፡፡

ለጥቃቱ አል-ሻባብ ኃላፊነቱን ወስዷል፡፡

ለዝርዝሩና ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡ 
http://amharic.voanews.com/content/villa-somalia-attacked-al-shabab-02-21-14/1856885.html

ዜና ድንቅ) የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት የጸረ ግብረሰዶም ህጉን ፈረሙበት!



የኡጋንዳ ፓርላማ ፣ አንዳንድ ግብረሰዶማዉያንን እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ እስራት ለመቅጣት ያሳለፈውን ህግ፣ ፕሬዚዳንት እንዳይፈርሙበት፣ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ከአንዳንድ የሰብ አዊ መብቶ ድርጅቶች ግፊት ቢደረግባቸውም፣ ዛሬ ፈርመውበታል።

(ዜና ድንቅ)  የኡጋንዳው ፕሬዚዳንት የጸረ ግብረሰዶም ህጉን ፈረሙበት!
       የኡጋንዳ ፓርላማ ፣ አንዳንድ ግብረሰዶማዉያንን እስከ ዕድሜ ልክ በሚደርስ እስራት ለመቅጣት ያሳለፈውን ህግ፣ ፕሬዚዳንት እንዳይፈርሙበት፣ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማና ከአንዳንድ የሰብ አዊ መብቶ ድርጅቶች ግፊት ቢደረግባቸውም፣ ዛሬ ፈርመውበታል።

አስቀድሞ ፓርላማው ግብረሰዶማዊ የሆነው ሰው ከህጻናት ጋር ሲፈጽም ከተገኘ ወይም ኤች አይ ቪ እንዳለበት እያወቀ ድርጊቱን ከፈጸመ በሞት ይቀጣ ሲል ህግ ቢያወጣም፣ ፕሬዚዳንቱ ፣ የሞት ቅጣቱ ካልቀረ አልፈርምም ሲሉ ቆይተዋል። በኋላ ቅጣቱ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት ተቀየረ። በዚህ መካከል የኡጋንዳ ሳይንቲስቶች "ግብረሰዶማዊነት የተፈጥሮ ጉዳይ ነው፣ ወይም በፍላጎት የሚፈጸም?" የሚለውን አጥንተው እንዲነግሯቸው ፕሬዚዳንቱ አዘዙ። ሳይንቲስቶቹም "ምንም እንኳን ግብረሰዶም መፈጸም በሽታ ነው ማለት ባይቻልም፣ በተፈጥሮ የሚመጣ ሳይሆን ሰዎች ፈልገውና ተለማመደው የሚያደርጉት ነው" ሲሉ ነገሯቸው።

አሁን በቃ ልፈርም ነው ሲሉ በመናገራቸው ወዲያው ፕሬዚዳንት ኦባማ "እንዳታደርገው ተጠንቀቅ" አይነት መልክት ላኩባቸው፣ እሳቸውም "እሺ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች፣ ነገሩ የተፈጥሮ ነው (ሰዎች ግብረሰዶማዊ ሆነው ነው የሚወለዱት) የሚለውን ነገር መጥተው ለኔና ለሳይንቲስቶቼ ያስረዱን" ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። ይህን ካሉ ቀናቶች አለፉ። እንግዲህ መጥቶ ያስረዳቸው የለም ማለት ነው። ዛሬ ህጉን ፈርመዋል። በኡጋንዳ ግብረሰዶማዊነት እስከ 10 ዓመት በ እስር ሲያስቀጣ፣ ነገሩ የተፈጸመው ከህጻን ጋር ከሆነ እስሩ እስከ ዕድሜ ልክ ይሆናል። በነገራችን ላይ በዚህ ህግ መሰረት ግብረሰዶም ፈጻሚዎች አይቶ ለፖሊስ ያልጠቆመም እንዲሁ እስር ይጠብቀዋል። (ዜናውን ዴይሊ ቢስትና አልጀዚራ ዛሬ አወሩት - ድንቅ መጽሔት ተረጎመው)
አስቀድሞ ፓርላማው ግብረሰዶማዊ የሆነው ሰው ከህጻናት ጋር ሲፈጽም ከተገኘ ወይም ኤች አይ ቪ እንዳለበት እያወቀ ድርጊቱን ከፈጸመ በሞት ይቀጣ ሲል ህግ ቢያወጣም፣ ፕሬዚዳንቱ ፣ የሞት ቅጣቱ ካልቀረ አልፈርምም ሲሉ ቆይተዋል። በኋላ ቅጣቱ ወደ ዕድሜ ልክ እስራት ተቀየረ። በዚህ መካከል የኡጋንዳ ሳይንቲስቶች "ግብረሰዶማዊነት የተፈጥሮ ጉዳይ ነው፣ ወይም በፍላጎት የሚፈጸም?" የሚለውን አጥንተው እንዲነግሯቸው ፕሬዚዳንቱ አዘዙ። ሳይንቲስቶቹም "ምንም እንኳን ግብረሰዶም መፈጸም በሽታ ነው ማለት ባይቻልም፣ በተፈጥሮ የሚመጣ ሳይሆን ሰዎች ፈልገውና ተለማመደው የሚያደርጉት ነው" ሲሉ ነገሯቸው።

አሁን በቃ ልፈርም ነው ሲሉ በመናገራቸው ወዲያው ፕሬዚዳንት ኦባማ "እንዳታደርገው ተጠንቀቅ" አይነት መልክት ላኩባቸው፣ እሳቸውም "እሺ የአሜሪካ ሳይንቲስቶች፣ ነገሩ የተፈጥሮ ነው (ሰዎች ግብረሰዶማዊ ሆነው ነው የሚወለዱት) የሚለውን ነገር መጥተው ለኔና ለሳይንቲስቶቼ ያስረዱን" ሲሉ ጥሪ አቀረቡ። ይህን ካሉ ቀናቶች አለፉ። እንግዲህ መጥቶ ያስረዳቸው የለም ማለት ነው። ዛሬ ህጉን ፈርመዋል። በኡጋንዳ ግብረሰዶማዊነት እስከ 10 ዓመት በ እስር ሲያስቀጣ፣ ነገሩ የተፈጸመው ከህጻን ጋር ከሆነ እስሩ እስከ ዕድሜ ልክ ይሆናል። በነገራችን ላይ በዚህ ህግ መሰረት ግብረሰዶም ፈጻሚዎች አይቶ ለፖሊስ ያልጠቆመም እንዲሁ እስር ይጠብቀዋል። (ዜናውን ዴይሊ ቢስትና አልጀዚራ ዛሬ አወሩት - ድንቅ መጽሔት ተረጎመው)

በኤልኩራን የነዳጅ ፍለጋ ጉድጓድ የነዳጅ ፍሰት ታየ



በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ኤልኩራን በተሰኘ አካባቢ የነዳጅ ፍለጋ ሥራ በማካሄድ ላይ የሚገኘው ‹‹ኒው ኤጅ›› የተሰኘው የእንግሊዝ ኩባንያ፣ በቆፈረው ‹‹ኤልኩራን ሦስት›› የተባለው ጉድጓድ ውስጥ የተፈጥሮ ዘይትና ጋዝ ፍሰት ታየ፡፡ 


ኩባንያው ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ጉድጓዱን በመቆፈር ላይ ይገኛል፡፡ የኩባንያው ዕቅድ 2,850 ሜትር ጥልቀት ያለው ጉድጓድ መቆፈር ነው፡፡ ታማኝ ምንጮች ለሪፖርተር እንደተናገሩት፣ ኩባንያው 1,200 ሜትር ጥልቀት ላይ ሲደርስ የተፈጥሮ ዘይትና ጋዝ ፍሰት በጉድጓድ ውስጥ ተመልክቷል፡፡ 

ከጉድጓዱ ውስጥ በቂ የሆነ ናሙና ለመውሰድና የነዳጅ ፍሰት ሙከራ ለማካሄድ ቁፋሮው መቋረጡን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አክለውም በመጀመሪያ በዕቅድ ከተያዘው 2,850 ሜትር በላይ ዘልቆ ለመቆፈር መወሰኑን አስረድተዋል፡፡ የነዳጅ ፍሰቱ መጠን ከፍተኛ እንዳልሆነ የተናገሩት ምንጮች፣ የፍሰቱን መጠን ለመጨመር የሚያስችሉ የተለያዩ የጂኦሳይንስ ሥራዎች መሠራት እንደሚኖርባቸው ጠቁመዋል፡፡

እ.ኤ.አ. በ1972 በኦጋዴን የነዳጅ ፍለጋ ሥራ ያካሂድ የነበረው ቴኔኮ የተሰኘ የአሜሪካ የፔትሮሊየም ኩባንያ በኤልኩራን አካባቢ በቆፈረው ጉድጓድ ውስጥ የነዳጅ ክምችት እንዳገኘ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ ይሁን እንጂ በወቅቱ ክምችቱ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማስገኘት የሚበቃ መጠን የለውም በማለት ተትቶ እንደነበር ያስረዳሉ፡፡ 

‹‹በዚያን ወቅት የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 14 ዶላር ነበር፡፡ በወቅቱ የነበረው የነዳጅ ፍለጋ ቴክኖሎጂ አሁን ካለው ጋር ሲነፃፀር ኋላቀር ነበር፡፡ አሁን በዓለም አቀፍ ገበያ የአንድ በርሜል ነዳጅ ዋጋ 120 ዶላር ነው፡፡ የነዳጅ ፍለጋ ቴክኖሎጂውም ተራቋል፡፡ ከዚህ አንፃር ኒው ኤጅ ያለውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም አዋጪ የሆነ የነዳጅ ክምችት መኖሩን ሊያረጋግጥ ይችላል፤›› ብለዋል፡፡ 

አንድ ከፍተኛ የፔትሮሊየም ባለሙያ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በኦጋዴን በተለይም በሂላላና ኤልኩራን አካባቢ የተፈጥሮ ዘይትና ጋዝ ፍሰት መመልከት የተለመደ ነው፡፡ ፍሰቱን መመልከት በራሱ አዋጪ (Commercial Deposit) ክምችት መኖሩን አያረጋግጥም፡፡ ‹‹ብዙ ተጨማሪ ሥራዎች ሊሠሩ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡ 

ኒው ኤጅ አፍሪካ ኦይል ከተሰኘው የካናዳ ኩባንያ ጋር በመጣመር በብሎክ 7፣ 8 እና አዲንላ አካባቢዎች የነዳጅ ፍለጋ ሥራ የሚያካሂድ ሲሆን፣ በደቡብ አፍሪካና ኮንጐ ብራዛቪል በነዳጅ ፍለጋ መስክ የተሰማራ ነው፡፡ ኒው ኤጅ እ.ኤ.አ. በ2007 የተመሠረተ ተቀማጭነቱ በለንደን የሆነ በአፍሪካ ላይ አተኩሮ የሚሠራ የነዳጅ ኩባንያ ነው፡፡ 
Reporter Amaharic 23 February 2014 በቃለየሱስ በቀለ

የ24 ዓመቱ ወጣት ለስራ በተሰጠው መሳሪያ ቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ፡፡

በርሱፈቃድ በጋሻው ተሾመ የተባለው የ24 አመት ወጣት ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በሚገኘው የህብረት ባንክ በጥበቃ ሰራተኝነት ለአንድ ወር ሲሰራ የቆየ ሲሆን ዛሬ 6 ሰዓት አካባቢ ባንኩ ለጥበቃ በሰጠው ጠመንጃ ሶስት ግዜ በመተኮስ ነው ራሱን ያጠፋው፡፡

በአካባቢው የነበሩ የአይን እማኞች ሟቹ ሁለት ግዜ በአገጩ ስር ተኩሶ ራሱን ከሳተ በኋላ በሶስተኛው ጥይት ጭንቅላቱን መትቶ ራሱን ሲያጠፋ ማየታቸውን ተናግረዋል፡፡
የ24 ዓመቱ ወጣት ለስራ በተሰጠው መሳሪያ ቦሌ መንገድ ላይ ራሱን አጠፋ፡፡
የሟች ባልደረቦች እንደሚሉት ከሆነ ሟች በጠዋት ወደስራ ሲመጣ አይኑ ቀልቶ እና የተረበሸ ይመስል እንደነበር እንዲሁም ‹‹በተደጋጋሚም ክርስቶስ አይወደኝም ›› ሲል እንደተሰማ ተናግረዋል፡፡


ምንጭ ድሬ ትዩብ

Saturday, February 22, 2014

ደም አፋሳሹ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም ተጠናቀቀ።

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚቴ ማህበር ስራ አመራር አባላት እና በቀድሞው የማህበሩ ሊቀመንበር ደጋፊዎች መሃከል በተፈጠረው የስልጣን ሽኩቻ በአባላቱ ላይ አጥልቶ የነበረው የእርስ በእስር ግጨት መቀልበሱን ምንጮች ከሪያድ አስታወቁ። ፌብረዋሪ 21 2014 ምሸት ሲጠበቅ የነበረው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ በሪያድ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደስታቸውን በመግለጽ ፈጣሪያቸውን አመስግነዋል ብለዋል፡፤ 

በጉባኤው ላይ ከኤንባሲው የተወከሉ ዲፕሎማቶች በታዛቢነት መገኘታቸውን የጠቀሱት አንድ የጉባኤው ተሳታፊ በስራ አመራሩ እና በሼክ መስጠፋ ሁሴን መሃከል ተከስቶ የነበረው ልዩነት በዲፕሎማቱ ብለሃት ከወዲሁ መቀልበሱን ጠቅሰው ስብሰባው ያለምንም ችገር እና ስጋት በሰላም መካሄዱን አረጋግጠዋል። አስተያየት ሰጪው አያይዘው ሲገልጹ ጥቂቶች በብዙሃኑ ደም ዎኝተው የበላይነታቸውን በአቋራጭ ለማረጋገጥ የነበራቸው ህልም መና መቅረቱ የኮሚኒቲው ማህበር ከህግ እና ስረአት ውጭ ለሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የማይበገር መሆኑንን ያረጋጋጠበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ብለዋል። በተለይ ይላሉ እኚህ አስተያየት ሰጪ ጉዳይ የሚዲያ ሽፋን አጊቶ በሚመለከታቸው አካላቶች ትኩረት ሳይሰጠው ቀርቶ ቢሆን ኖሮ አያሌ ወገኖች ዘግናኝ የሆነ ነገር ውስጥ ሊገቡ ይችሉ እንደነበር አውስተው ሶሻል ሚዲያዎች አደጋ ከመድረሱ በፌት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው የህዝቡን እሮሮ በማስተጋባት የኮሚኒቲውን አባላት ከአሰቃቂ ግጨት በመታደጋቸው ሊመስገኑ ይገባልም ብለውል። 

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በዲያስፖራው ዘንድ ተደማጭነት እና ክብር ያላቸው 3 ዲፕሎማቶች ኤንባሲውን ወክለው በታዛቢነት መገኘታቸውን የሚናገሩ ምንጮች ስብሰባው ያለምንም ስጋት እና ሁከት በሰላም እንዲካሄድ ለማስቻል ከፍተኛ አስተዋጾ ማድረጋቸውን አክለው ገልጸዋል። በስብሰው ወቅት የኮሚኒቲው ስራ አመራር የ20 ወራቱን የስራ ሪፖርት በማስደመጥ በአባልቱ መሃከል ከፍተኛ ውይይት መድረጉን የሚናገሩ እማኞች በስራ አመራሩ የቀረበው ሪፖርት በአብዛኛው አባላት ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበር ሳይሽሽጉ ተናግረዋል። 

በመጨረሻም የኮሚኒቲው ሊቀምንበር አቶ ቃሲም ያሲን በቀረብው ሪፖርት ዙሪያ ከአድማጮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ በመስጠት በጉባኤው ተሳታፊዎች ዘንድ ሰፊ ውይይት ከመደረጉም በላይ የኮሚኒቲው ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል በኮንተራት ለግለስቦች ቢተላለፍ የበለጠ ውጤታማ መሆን እንደሚችል ከአንድ አድማጭ የተሰነዘረውን ሃሳብ የኤንባሲው ተወካይ ክቡር አቶ ተመስገን ኡመር የኮሚኒቲው ንበረት ለዲያስፖራው ያለውን አጋርነት እና ጠቀሜታ በዝርዝር በማስቀመጥ የኮሚኒቲው ንብረቶች በኤንባሲው ስር እንደመሆናቸው መጠን አካሄዱ ህጋዊ መስረት ሊኖረው ስለማይችል የቀርበውን ሃሳብ ውድቅ በማድረግ ተቀባይነት እንደሌለው አረጋግጠዋል፡፤ የማህበሩ ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል የሆነው ካፍቴሪያ ዘንድሮም 61 ሺህ ሪያል ኪሳራ ማሳየቱን ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል።በዚህ ጉባኤ ላይ የሃይማኖት አባቶች የህገር ሽማግሌዎች ጨምሮ 1/ ክቡር አቶ አህመድ ጠላህ 2/ ክቡር አቶ ተመስገን ኡመር 3/ ክቡር አቶ መስፍን ድባቡ መገኘታቸውን የሚገልጹ የኮሚኒቲው አባላት ከስጋት እና ጭንቀት ይልቅ የጉባኤውን ምሸት በነጻነት ማሳለፋቸውን አስረድተዋል። ለጉባኤው የቀረበ የተባለው ሪፖርት ግልባጭ በእጃችን እንደገባ ሰሞኑን በዚህ ገጽ በስፋት ለመዳሰስ ይሞከራል።

Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ





Thursday, February 20, 2014

(የማለዳ ወግ ... በጭካኔ እየተገዳደልን ፣ ወዴት እየሔድን ነው ?) በነብዩ ሲራክ




ከሳምንት በፊት እዚህ ጅዳ ሻረ ሄራ በሚባል አካባቢ የሃበሻን ዘር ያሳዘነ የግድያ ድርጊት መፈጸሙን ሰማሁ ። ትውውቅ ባይኖረንም በአይን የማውቀው ወንድም አብዱ ሁሴን ይማም በጭካኔ መገደሉን የሰማሁት ድርጊቱ በተፈጸመ ከሰአታት በኋላ ከአንድ ወዳጀ በኩል በደረሰኝ የስልክ መልዕክት ነበር። በቀጣይ ቀናት ወጣቱ አብዱ የተቀጠፈበትን የጭካኔ ድርጊት የሚያወግዙ በርካታ መልዕክቶች ማስተናገድ ጀመርኩ። በመካከላችን ባሉ ጥቂት የሰው አውሬዎች እየሆነ ያለው እና ስማችን የመክፋቱ ነገር ያሳሰባቸው በርካታ ወገኖች በግድያው ማዘናቸውን በመግለጽ በርካታ መልዕክቶችን ልከውልኛል። በጭካኔ ተፈጸመ የተባለው ድርጊት ዘልቆ ነፍሱን አስጨንቆ ያሳዘነው አንድ ወንድም የላከልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል ....

" ጩኸት ሰሚ ሲያጣ እንዴት ያናዳል ... ሀበሻ የድሮወቹ የሉም ... ወድ የሆነውን የሰውን ደም በከንቱ የሚጠጡ እርኩስ መንፈስ የተጠናውታቸው ውሾች ናቸው .so ሰሞኑን በ ጅዳ አካባቢ ሸር ሄራ አካባቢ የተደረገውን ግፍ ልንገርክ ...በሀበሾች ጭካኔ የተገደለውን ልጅ በአካል አውቀዋለሁ አብዱ ሁሴን ይማም ይባላል ... በሳንጃ ገደሉት ! ልብ በል ... የሳውድ መንግስት ታዲያ እንዴት አያሳድደን ! እንደነዚህ አይነት እርኩሶች እያሉ እኛ ቤተሰብ እንዴት እንርዳ? ልጅስ እንዴት እናስተምር? ..ነብዩ ሰው እንዴት ...የሰውን ነፍስ ያጠፋል? ደግሞም ሳውዲ ውስጥ ? ከተሰራ ለሚገኝ ገንዘብ እጅግ ያሳዝናል ይጎመዝዛል ! ጌታ እውነቱን ይፍረድ ለሀበሻ ጩኸት በቃኝ እኔም ሀበሻ ነኝ!!! " ይላል ! 

ሰሞኑን "ኢትዮጵያዊ በኢትዮጵያዊ ላይ በግፍ የግድያ ወንጀል ተፈጸመ !" የሚለው ወሬ ከጓዳ እስከ አደባባይ ሲናኝ አስከፊውን ሂደት የታዘቡ ወገኖች ኢትዮጵያውያን ብቻ አልነበሩም። ጉዳዩን በቅርብ ከሚያውቁና ከሚከታተሉ የሃገሩ ሰዎችም መልዕክቶችና አስተያየቶች ደርሰውኝ በሃፍረትም ቢሆን ለማስተናገድ ተገድጀም ነበር ... የሟችን ጉዳይ በቅርብ የሚከታተሉ ፣ ኢትዮጵያን የሚወዱና ስለኢትዮጵያ የሚጽፉ ፣ አንድ ከፍ ያለ ሃላፊነት ያላቸው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያና ሃያሲ የሃገሩ ሰው አዝነውብን አግኝቻቸዋለሁ ። በቁም ነገር በቢሯች አስጠርተው ያሉኝ እንዲህ ነበር " ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ምንድ ነው እንዲህ የመሰለ የዘቀጠ በሃበሾች ያልተለመደ ጉዳይ ተደጋገመሳ ? ሀበሾች ምን ገባባችሁ? ከአመታት በፊት በሪያድ መንፉሃ ፣ ከወራት በፊት በመዲና በአብሃ እና በዙሪያው ያን ሰሞን ደግሞ በኪሎ ተማንያ እና በዙሪያው በሃበሾች መካከል መጨካከን የተሞላበት ድርጊት ታይቷል። ከሁሉም የሚያሳዝነው የግድያ ምክንያቶቹ ጊዜያዊ ጸብን ፣ ጥቅምንና ጥቃቅን የሰው ህይዎትን በጭካኔ ሊያስጠፉ የማይገባቸው ምክንያቶች ናቸው ። ግን ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ወደ የትስ እየተኬደ ነው? " ሲሉ በጥያቄ ላፋጠጡኝ ሳውዲ ወዳጀ የሚሆን መልስ ግን አልነበረኝም ! ብቻ የሆነው አሳዝኖ ፣ አሳፍሮ አንገቴን አሰበረኝ ...

እርግጥ ነው ፣ ባሳለፍናቸው አመታት በሪያድ መንፉአ አካባቢ አልፎ አልፎም በኢትዮጵያውያኑ መካከል በሚፈጠር ግጭት ቁጥራቸው ከፍ ያሉ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ዜጎች በሰላ ጩቤ አሰቃቂ ጥቃት ተፈጽሞባቸው የመቁሰልና የመገደል አደጋ ምክንያት እንደ ነበር የአይን እማኞች አጫውተውኝ ነበር ። በጩቤ ለመወጋጋቱ ዋንኛ ምክንያትም ደግሞ ተራ ከገንዘብና ከሴት ጋር የተያያዙ እዚህ ግቡ የማይባሉ መሆናቸው ማጤንና መገንዘብ ደግሞ በእጅጉ ያሳዝናል ...በቀደሙት ጥቂት አመታት በሳውዲና የመን ድንበር ከተሞች ይህ መሰሉ ወንጀል የከፋ እንደ ነበር አውቃለሁ። በተለይም በጀዛን ፣ በአብሃና በከሚስ ምሽት በሚባሉ አካባቢዎች በዙሪያው ባሉ የከተማና የገጠር ከተሞች በከተሙ ኢትዮጵያውያን መካከል ተፈጸሞ የምንሰማው ግድያ ፍጹም ጭካኔ ያልተለየው መሆኑ ይጠቀሳል ! ወደ አብሃና ከሚስ ምሸት ለስራ ባቀናሁባቸው ቀናት በእኛ ዙሪያ እየሆነ ያለውን ለመስማት የከበደ መረጃ በእጀ መድረሱን አስታውሳለሁ። በህገ ወጥ መንገድ ዜጎቻችን ከየመን ሳውዲ በሚያመላልሱ ለገንዘብ በገንዘብ እየሸጡ የሚተዳደሩ ደላሎችና አቀባባዮች በጎሳ ተቧድነውና ብሔርን ለይተው የሚከሰተውን ግጭት ከጩቤ ያለፈ እንደ ነበርም በቦታው ተገኝቸ ታዝቤያለሁ። በተለይም በአብሃ አካባቢ በግጭቱ ስለተቀጠፈው ህይዎት ፣ ፍርድን ይጠባበቁ ስለነበሩ የእኛ ገዳዮችም የፍርድ ሂደት በቅርብ እከታተል ነበር ። ከሁሉም የሚያሳዝነው የሰውን ልጅ ያህል ታላቅ ፍጡር በስለት የሚጠፋበትን ምክንያት መስማት እንደ ነበርም ትዝ ይለኛል። ከሃገር ቤት ያለ የዘር ፣ የግል ጥላቻና ጸብን መሰረት ያደረገው የደም መቃባት ፣ በገንዘብ መካካድ " ጓደኛየን ነጠቀኝ!" ፣ "የሰማንያ ሚስቴን ደፈረ !"፣ በሚሉትና በመሳሰሉት ክሶች የሚያጠነጥነው ብቀላ በፍትህ ሳይሆን በጭካኔ ለመወጣት የሚፈጸም ያረጀ ያፈጀ ይትበሃል ሳውዲ ተከትሎን መጥቶ ስማችን ማርከሱ ደግሞ ከሁሉም በላይ ያማል !

በያዝነው አመት ከጅዳ በ400 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው በሙስሊማን ቅዱስ ከተማ በመዲናም በዜጎቻች መካከል በተፈጠረ የቨዛ ሽያጭ እና ተጓዳኝ የገንዘብ መካካድ ያስከተለው አምባጓሮ በቅዱሷ ከተማ ቅዱስ የማይባል ግድያ ለመፈጸሙ ምክንያት ነበር ። ይህም የጭካኔ ወንጀል የተፈጸመበት ኢትዮጵያዊ ፣ ወንጀል ፈጻሚው ኢትዮጵያዊው መሆኑ ደግሞ ጉድ አሰኝቶ አሳፍሮን አልፏል። ከወራት በፊትም እዚሁ ጅዳ በተለያዩ አካባቢዎች በኢትዮጵያውያን መካከል የተነሱ አምባጓሮዎች በተመሳሳይ ጭካኔ በተሞላባቸው የግድያ ድርጊቶች የተከበቡ ወንጀሎች ምክንያት ነበሩ ማለት ይቻላል። እናም ጉዳዩ አሳሳቢ እየሆነ መጥቷል ....

ባሳለፍነው ሳምንት በጭካኔ የተገደለው ወንድም ወንጀል ተጠርጣሪ ፣ ተጠያቂ የቅርብ ጓደኛ ወዳጁ እንደነበረና ከቀናት በፊት በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ሰማን ! አብዱ በማጣታቸው ትልቁ የሃዘን መርግ የወደቀባቸው፣ የሚይዙት የሚጨብጡ ያጡት ፣ ቤታቸው የጨለመባቸው አንዲት ሴት ልጂና የስድስት ወር ነፍሰ ጡር ባለቤቱ ሃዘን የከበደ ነው...ስለአብዱን ቅንነት፣ ሰው አማኝ ፣ ትጉህና ታታሪነቱን የሚመሰክሩት ባልንጀሮቹም ሃዘናቸው መሪር ያደረገው የተፈጸመው የጭካኔ ወንጀል ብቻ ሳይሆን የወንጀሉ ቀዳሚ ተጠርጣሪ የቅርብ ወዳኛ መሆኑ ነበር ። በዚህም ሊያምኑት በከበደ ድርጊት እርር ድብን ብለው አዝነዋል! ዛሬ የማይሰማ የማያየን አብዱ ሁሴን በሰላሳዎቹ የእድሜ ክልል ይገኝ እንደነበር በቅርብ ጓኞቹ ጨምረው አጫውተውኛል ። የወንድም አብዱ ሁሴን ይማም የቀብር ስነ-ስርዓት ትናንት የካቲት 12 / 2006 ረቡዕ ከቀትር በኋላ በጅዳ ከተማ ተፈጽሟል ! አብዱ የሔደው ሁላችንም ወደ ማንቀርበት የላይኛው ቤት ነው ! ነፍሱን ይማረው ! " አላህ ይርሃሙ !"

ወንጀሉን በትኩሱ ለማቅረብ በፖሊስ ክትትክ መሆኑና ተጠርጣሪ ወንጀለኛው ባለመያዙ የማለዳ ወጌን እንዳዘገየው ቢያስገድደኝም መረጃውን ባሳለፍናቸው ቀናት ከበርካታ ነዋሪዎች አስተያየቶችን ለመሰብሰብ ሞክሬ ነበር ። በዚህ መሰል ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት ዙሪያ እየተነጋገረ የሚገኘውን አብዛኛው የጅዳ ነዋሪ " ህጋዊ ህገ ወጥ " ነገን ምን ይከተል ይሆን እያለ በጭንቀት በሰቀቀን እየጠበቀ ባለበት ሰአት የዚህ መሰሉ ድርጊት መፈጸም " እንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ !" ሆኖበት ተመልክቻለሁ! ለእኔም የሆነብኝ እንዲያ ነው ...

ድርጊቱ አሳዝኖኝ ለማውገዝ ያነሳሁት ብዕር መቋጫ የሚሆነው ሳውዲው ሃያሲ ወዳጀ ያጫወቱኝን ዘልቆ የሚሰማ ያልመለስኩት ጥያቄ ነው ። ሃያሲው ሃበሾች በዚህ መሰል ድርጊት እንደማንታወቅ ተናትነው ከቅርብ አመታት የሰበሰቧቸው መረጃዎች ቢያሳስቧቸው ቆጣ ብለው በንዴት ሲያጠይቁ "ግን ምንድን ነው እየሆነ ያለው? ወደ የትስ እየተኬደ ነው? " ነበር ያሉኝ ...እኔም ተጠርተን የማናውቅበት ወንጀል ሲደጋገም አሞኛልና ድርጊቱን አወግዘዋለሁ! ወደ መጨረሻም አሳፍሮ መልስ ያጣሁለትን የሃያሲውን ወዳጀ ጥያቄ ላጠይቅ ግድ አለኝ ... ግንስ ... በጭካኔ እየተገዳደልን ፣ እየተጠላላን ወዴት እየሔድን ነው ? ምንድን ነው እየሆነ ያለው? 

ቸር ያሰማን !

ነቢዩ ሲራክ

Wednesday, February 19, 2014

ዓለም ባንክ ኢህአዴግን በረበረው – ከዚያስ?


“ኢህአዴግ የተጭበረበረ ሪፖርት አቅርቦ” ነበር
world bank foto


ኢህአዴግ “አልመረመርም፣ አልበረበርም” በማለት ሲያንገራግር ከቆየ በኋላ በዓለም ባንክ ቀጭን ትዕዛዝ ለመበርበር መስማማቱን ገልጾ በተለያዩ አካላት ምርመራ ተካሂዶበታል። በተከታታይ ሲካሄድ የነበረው ምርመራ አካል የሆነው የመጨረሻ ምርመራ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ተጠናቋል። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች እንደተናገሩት ስድስት አባላትን ያካተተው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ኢህአዴግን መርምሮ ተመልሷል። የሚጠበቀው የመጨረሻው ሪፖርትና ሪፖርቱ የሚቀርብለት የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ነው። በቅርቡ የሚወጣውን ውሳኔ አቅጣጫ ለማስቀየር በማሰብ ኢህአዴግ ለመርማሪው ቡድን ራሱ የፈጠረውን “የተጭበረበረ ሪፖርት” አቅርቦ ነበር፡፡
ኢህአዴግ ምርመራውን በተቀነባበረ የፈጠራ ሪፖርት ለማምለጥ ሞክሮ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጮች “የመርማሪዎቹ ቡድን ሪፖርቱን አንቀበልም፣ የችግሩ ሰለባዎችና ክሱን የመሰረቱት ክፍሎች በሚኖሩበት ቦታ በመገኘት ነዋሪዎችን በተናጠል ለማነጋገር እንፈልጋለን” በማለት ኢህአዴግን እንደሞገቱት አስታውቀዋል። ኢህአዴግ በልማትና በህዝብ ስም የሚያገኘውን ከፍተኛ የዕርዳታ ገንዘብ የጦር ሃይሉን ለማደራጀት፣ የደህንነትና የፖሊስ ሃይሉን ለማስታጠቅና ርዳታ በሚለመንባቸው ዜጎች ላይ የተለያየ ወንጀል ፈጽሟል፣ አሁንም እየፈጸመ ነው በሚል መወንጀሉ ይታወሳል።
የምርመራው መነሻ ከዛሬ አስር ዓመት በፊት በቀድሞው ጠ/ሚኒስትርና የጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ፣ የህወሃትና የኢህአዴግ ሊቀመንበር አቶ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝና በየደረጃው ያሉ አስፈጻሚዎች በጋምቤላ ክልል የተከናወነው የጅምላ ጭፋጨፋ ነው። በወቅቱ የተካሄደው ጭፋጨፋ ከ400 በላይ የተማሩ የአኙዋክ ወንዶች ላይ ያተኮረ እንደነበር በተለያዩ ጊዜያት የወጡ ዓለም አቀፋዊ ሪፖርቶችና የጉዳዩ ሰላባዎች ይፋ ያደረጉት ጉዳይ ነው። አቶ መለስ ሞት ቀደማቸው እንጂ የዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የቀረበባቸውን የክስ ማስረጃ ተቀብሎ ክስ እንዲመሰረትባቸው ከድምዳሜ መድረሱም ይፋ ሆኖ ነበር። ኢህአዴግ በዚሁ ፍርድ ቤት ላይ የአፍሪካ መሪዎችን የማስተባባርና የፍርድ ቤቱን አካሄድ ማውገዝ የጀመረው አቶ ኦባንግ የሚመሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አቶ መለስ ላይ የመሰረተው ክስ እንዲከፈት መወሰኑን ተከትሎ እንደሆነ በወቅቱ ከየአቅጣጫው አስተያየት የተሰጠበት ጉዳይ ነው።
ከዚህ “ዘግናኝ” እንደሆነ ከሚነገርለት ጭፍጨፋ በኋላም በጋምቤላ ሰፋፊ ለም መሬትን በኢንቨስትመንት ስም ነዋሪዎችን በሃይል እያፈናቀለ በመሸጡ ኢህአዴግ ይከሳሳል። በተለይም የኦክላንድ ተቋምና (Oakland Institute) ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ያቀረቡዋቸው ሪፖርቶች ኢህአዴግ በስድብና “የአብዮታዊ ዴሞክራሲ መንገድ ተጻራሪዎች፣ ርዕዮተ ዓለሙ ላይ የተነሱ፣ አይኗ እየበራ ያለችውን ኢትዮጵያን ለማጥፋትና ወደኋላ ለመጎተት ልዩ ተልዕኮ ያላቸው፣ የነፍጠኛውን ስርዓት መልሶ ለመትከል የሚሰሩ፣ ጸረ ልማቶች፣ ወዘተ” በማለት ቢያጣጥላቸውም ቀን ጠብቀው ስራቸውን እየሰሩ ስለመሆናቸው እየተነገረ ነው።
ጎልጉል ጥቅምት2፤ 2005 ዓም /October 12, 2012/ ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ላይ መውደቁን፣ ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው inspection panelገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ፣ ዓለምአቀፉ ሁሉን ያካተተ የልማት ተቋም /Inclusive Development International (IDI)/ የተባለውን ተቋም ጠቅሰን “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ” በሚል ርዕስ መዘገባችን ይታወሳል።
ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት በመጣስ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ማስረጃ በመያዝ፤ በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ በመሰብሰብ ተጠያቂ የሚያደርገው IDI ከሰለባዎቹ ውክልና የተሰጠው ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቆም ነበር፡፡
የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ ተመልክቷል። ዝርዝሩ እዚህ ላይ ይገኛል፡፡
አቤቱታው ከቀረበ በኋላ ሁኔታውን ለማጣራትና ውሳኔ ላይ ለመድረስ ያመች ዘንድ ኢንስፔክሽን ፓናል በኢትዮጵያ በመገኘት ምርመራውን አካሂዶ ነበር፡፡ በክሱ መሠረት ፓናሉ በእርግጥ “የዓለም ባንክ ለልማት ሥራዎች የሚሰጠው የእርዳታ ገንዘብ በኢትዮጵያ በተለይም በጋምቤላ ክልል የሚኖሩትን ዜጎች ሰብዓዊ መብት በመጣስ ላይ” እና ለደኅንነትና ወታደራዊ ጥቅሞች ላይ አውሎታል በማለት የምርመራውን ውጤት የዓለም ባንክ ቦርድ ውሳኔ እንዲሰጥበት አቀረበ፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የውሳኔውና ሃሳብ አስመልክቶ “ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ” በሚል ሐምሌ 11፤ 2005ዓም /July 18, 2013/ በዘገብንበት ወቅት ከውጪ በሚመጣ ዕርዳታ ላይ ህልውናው የተመሰረተው ኢህአዴግ ገመዱ እየከረረበት መምጣቱን ጠቁመን ነበር፡፡
ኢህአዴግ የዓለም ባንክ ቦርድ ውሳኔውን እንዳያስተላልፍ የተለያዩ የውስወሳ (ሎቢ) ሥራዎችን ሲሰራ እንዲሁም የዓለም ባንክ የራሱን ማጣራት እንዳያደርግ ለማደናቀፍ ሲሞክርና ሲከላከል አምስት ወራት አስቆጠረ፡፡ በመጨረሻም ሐምሌ 11፤ 2005ዓም (July 18) ከፍተኛ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ከአዲስ አበባ፤ እንዲሁም በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኘው ኤምባሲ ከፍተኛ ዲፕሎማቶች በመሆን የዓለም ባንክን አመራሮች ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው እያለ ባንኩ ከአንድ ቀን በፊት ሙሉ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዘ። ውሳኔው ባንኩ በራሱ ገንዘብ ማንም ሊያዝበት እንደማይችል ያሳየበትና ለኢህአዴግም እጅግ አሳፋሪ ውሳኔ መሆኑ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተለው ዓለምአቀፉ ሁሉን ያካተተ የልማት ተቋም Inclusive Development International (IDI) እና ሌሎች ክፍሎች አስተያየት ሰንዝረው ነበር። የዜናው ዝርዝር እዚህላይ ይገኛል፡፡world-bank
ከዚህ ውሳኔ በኋላ የኅልውናው ጉዳይ ያሰጋው ኢህአዴግ የባንኩ መርማሪ ቡድን ሙሉ ምርመራ እንዳያካሂድ የተቻለውን ሁሉ ሲያደርግ ቆይቶ ነበር፡፡ ምርመራው ተካሂዶ ኢህአዴግ በእርግጥ ከዓለም ባንክ የሚሠጠውን ገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ረገጣ ማዋሉን ቡድኑ ካረጋገጠ፤ ኢህአዴግ በትንሹ 600 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያጣ፣ ጉዳቱ ከከፋም እስከ ቢሊዮኖች እንደሚደርስ ጎልጉል በዚሁ ዜናው ምንጮቹን ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል።
ከዚህ ሁሉ በኋላ ከሁለት ሳምንት በፊት ላይ ወደ አዲስ አበባ አቅንቶ የነበረው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ሥራውን በትክክል እንዳያካሂድ ኢህአዴግ የራሱን “የተጭበረበረ ሪፖርት አዘጋጅቶ” እንደጠበቃቸው ለጎልጉል መረጃ ደርሶታል። በዚሁ ሪፖርት መሰረት “ችግሩ ካለበት ጋምቤላ ክልል መሔድ አያስፈልግም” በማለት ኢህአዴግ የባንኩን መርማሪ ቡድን ተከራክሮ ነበር። የምርመራው ቡድን አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት አገር ጥለው የኮበለሉትን የቀድሞ የጋምቤላ ክልል መሪ አቶ ኦሞት ኦባንግን የተኩት አዲሱ ፕሬዚዳንትም ረዳቶቻቸውን በመያዝ አዲስ አበባ ተገኝተው ኢህአዴግ የያዘውን አቋም “እኛን እመኑ፤ ነዋሪውን ማነጋገር አያስፈልግም” በማለት ለዓለም ባንክ ቡድን አባላት አቅርበው ነበር።
ለጊዜው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉና ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ከአዲስ አበባ ለጎልጉል እንዳሉት ሶስት ቀን የፈጀ ክርክር ከተደረገ በኋላ የዓለም ባንክ መርማሪ ቡድን በቅድመ ሁኔታ ጋምቤላ የተፈቀደለት ቦታ ብቻ እንዲሄድ ከስምምነት ላይ ተደረሰ። ኢህአዴግ ባዘጋጀው “የተጭበረበረ ሪፖርት” ላይ እንደገለጸው አስቀድሞ ሰፈራን የሚያካሂደው የጤና አገልግሎት፣ ትምህርት ቤት፣ ንጹህ የመጠጥ ውሃ፣ መንገድ፣ የመኖሪያ ቤትና አስፈላጊ መስረተ ልማቶችን እንዳሟላ በስፋት ዘርዝሮ ነበር። በተመረጡት ቦታዎች ምስክርነት እንዲሰጡ የራሱን ሰዎች አዘጋጅቶ እንደነበርና በእድሜ የገፉ አባቶችና እናቶች አስተያየት እንዳይሰጡ ቅድመ ዝግጅት አድርጎ ነበር። በእድሜ የገፉት ሰላባዎች “የመጣው ይምጣ በማለት እውነቱን ለመናገር አይፈሩም፣ በቀላሉም አይደለሉም” የሚል ድምዳሜ ላይ መድረሳቸውን የሚናገሩት እኚሁ ሰው “የመርማሪው ቡድን በቀላሉ የሚታለል አልነበረም” በማለት የዓለም ባንክ ቡድን በቅርቡ ከሚያወጣው የውሳኔ ሪፖርት በፊት ዝርዝር ጉዳዮችን ከመናገር ተቆጥበዋል።
ከምርመራው ቡድን አባላት መካከል ሁለቱ በኬኒያና በደቡብ ሱዳን ስደት ላይ የሚገኙ የአኙዋክ ተወላጆችን በግንባር ተገኝተው ማነጋገራቸውን ጎልጉል አረጋግጧል፡፡ በተለይ አንደኛዋ እንስት መርማሪ ጭፍጨፋውን አምልጠው የተሰደዱትን ሰዎች ባነጋገሩበት ወቅት እንባቸውን መቆጣጠር አቅቷቸው ሲያለቅሱ እንደነበር የሚያስታውሱት የጎልጉል የመረጃ ምንጮች፣ “ኢህአዴግ displaced anuaksለማጭበርበር ያደረገው ሙከራ እንዳልተሳካለት፣ የመርማሪዎቹ ቡድን አስፈላጊው መረጃ እንደነበረው፣ ጉዳዩን አስቀድመው ለዚህ ሂደት እንዲበቃ ያደረጉት ክፍሎች የያዙት እውነትና ውክልናውን ወስዶ የክስ ማመልከቻውን ያዘጋጀው ተቋም በቂ ልምድና ሚዛን የደፋ ተግባር ያከናወነ በመሆኑ ኢህአዴግ በተለያዩ ጊዜያት የተዘገቡት ኪሳራዎች ይደርስበታል፣ አሊያም በቀድሞው መንገድ የመቀጠሉ ጉዳይ አሳሳቢ ይሆናል” ሲሉ ግምታቸውን ሰጥተዋል።
ከተለያየ አቅጣጫ አጣብቂኝ ውስጥ እየገባ ያለው ኢህአዴግ፤ አሜሪካ እንደ ቀድሞው ባዶ ቼክ እንደማትሰጥና ካሁን በኋላ ሁኔታዎችን እየመረመረች ገንዘብ እንደምትለቅ መወሰኗ ይህንንም በህግ ማጽናቷ በቅርቡ ሊያካሂድ ካሰበው “ምርጫ” አኳያ የሰሞኑ ራስ ምታት ሆኗል፡፡ ይህ የአሜሪካ ውሳኔ በአውሮጳውያኑም ዘንድ ተግባራዊ እንዲሆን እየተሰራ ባለበት ባሁኑ ወቅት ኢህአዴግ ፊቱን ወደ ቻይና የማዞር አዝማሚያ ሊያሳይ የፈለገ ቢመስልም የማያዋጣው እንደሆነ በስፋት ይታመናል፡፡ እንዲህ ዓይነቱ አቅጣጫው የጠፋበት አካሄድና ውጥረት በአገዛዙ ውስጥ ራሱን የቻለ የፖለቲካ ገመድ ጉተታ ፈጥሮ ችግሩን ሊያባብስ ይችላል እየተባለ ባለበት ወቅት የዓለም ባንክ ከዕርዳታና ድጎማ ጋር በተያያዘ የሚሰጠው ውሳኔ ሊፈጥር የሚችለውን ውጥረት ለመገመት ኢህአዴግ ምርመራው እንዳይካሄድ የተጠቀመውን ማደናቀፊያ መመልከቱ ብቻ በቂ እንደሆነ ይታመናል፡፡
የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ለምርመራ አዲስ አበባ ከመግባቱ በፊት ኢህአዴግ የቀድሞውን የክልሉን መሪ አቶ ኦሞት ኦባንግን በቁጥጥር ስር በማዋል ለሚከሰስበት ጉዳይ መስዋዕት አድርጎ ሊያቀርባቸው ዝግጅቱን አጠናቆ እንደነበር፣ አቶ ኦሞት ከደህንነትና ከቀድሞ ታጋይና የአሁኑ “ልማታዊ ኢንቨስተሮች” ጋር ባላቸው ትስስር የተነሳ መረጃ ደርሷቸው እንደኮበለሉ ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።
በአሁኑ ወቅት አውሮጳ እንደሚገኙ የሚነገረው አቶ ኦሞት ኦባንግ ከዓለም ባንክ ጋር በመገናኘት ከአኙዋኮች ጭፍጨፋ ጀምሮ እስከ አሁኑ ጊዜ ድረስ ለዘመናት የሚያውቁትን ምስጢር ሁሉ ለዓለም ባንክ በማጋለጥ ለራሳቸው ርካሽ የስደተኛ ጉዳይ መጠቀሚያነት ያውሉታል እየተባለ ከቅርብ ወገኖቻቸው ዘንድ ይሰማል፡፡
ኢህአዴግ በየመንደሩና በየክልሉ በተመሳሳይ የሚፈጽማቸውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና ህገወጥ ተግባራት በተደራጀ መልኩ በማሰባሰብ ዱካውን እየተከተሉ መታገል፣ ዓለም አቀፍ መስመሮችን በመከተል ትግልን ማሳለጥ፣ ኢህአዴግ በሚፈልገው መልኩ ደረጃን ዝቅ በማድረግ አላስፈላጊ ንትርክ ውስጥ አለመግባትና አልሞና አስተውሎ መራመድ የወቅቱ ጥያቄ እንደሆነ በተደጋጋሚ የሚናገሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ የዓለም ባንክ እዚህ ደረጃ የመድረሱ ዜና የአንድ ቀን ሥራ ውጤት እንዳልሆነ ሲናገሩ መቆየታቸው ይታወሳል፡፡
ሐምሌ 11፤2005ዓም /July 18, 2013/ “ኢህአዴግ በሩን እንዲከፍት የዓለም ባንክ አዘዘ” በሚል በዘገብንበት ወቅት አስተያየታቸውን የሰጡት አቶ ኦባንግ “እኛ በመሠረቱ ልማትን አንቃወምም፤ ሆኖም ግን በልማት ስም የሚሠጠው ዕርዳታ የዜጎችን ሰብዓዊ መብት ለመርገጥ የሚውል ከሆነ ህወሃት/ኢህአዴግ ተጠያቂ መሆን ይገባዋል፤ የግልጽነትና ተጠያቂነት ዕጥረት እንዲሁም የሙስና በሽታ እንዳጠቃው በራሱ መሪዎች የሚነገርለት ኢህአዴግ፤ የፈለገውን ነገር እንደፈለገው የማድረግ አምባገነናዊ አሠራሩ ራሱን አጣብቂኝ ውስጥ እንደሚከተው” በመጥቀስ ድርጅታቸው በጥናትና በዕቅድ ከሚያካሂደው ሁሉን ዓቀፍ ትግል መካከል ይህ አንዱ እንደሆነና “በተጠናከረ መልኩ በመንቀሳቀስ ጉዳዩን ዳር በማድረስ የተጎዱ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን መከራ” እንደሚታደጉ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡
ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ይህንን የዓለም ባንክ ጉዳይ አስመልክቶ ከአንድ ዓመት በላይ ሲዘግብበት የቆየ ሲሆን በየጊዜው የወጡት የዜና መዘርዝሮች ለአንባቢው ግንዛቤ መስጠት ይችሉ ዘንድ በቅደምተከተል አቅርበናቸዋል፡፡
ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል! ጥቅምት 2፤2005ዓም/October 12, 2012
ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል – የካቲት 9፤2005ዓም/February 16, 2013
የማነቂያው ገመድ ከርሯል፤ “ትግሉ ይቀጥላል” ኦባንግ ሜቶ – ሐምሌ 11፤2005ዓም/July 18, 2013
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ዕልቂት


ያዩ እንደሚሉት በርግጥም ዘግናኝ ነዉ።የሰዉ አንገት በገጀራ ይቀነጠሳል።እጅ፥ እግር፥ በጎራዴ ይቆረጣል።ሌላ አካል በጩቤ ይጨቀጨቃል። መንገዶች በደም አበላ ጨቅይተዋል-እየጨቀዩም ነዉ።አስከሬን በየጉርጓዱ ይከመራል።ከተንቀሳቃሽ ሥልክ እስከ ምግብ፥ ከሐብል እስከ ብስክሌት ያሉ ቁሳቁሶች ይመዘበራሉ። ቤቶች፥ መደብሮች፥ ቁሳቁሶች፥ መሳጂዶች ይነዳሉ።
የዋሽግተን-ሞስኮ፣ የለንደን-ቤጂንግ ሐያላን ከቁብ አልቆጠሯትም።ፓሪሶች እንዳይረሷት የድሮ ቅኝ ተገዢ ናት።እንደ ሊቢያ እንደ ኮትዲቯር፥ ወይም እንደ ማሊ ሐያል ተባባሪዎችን አስተባብረዉ እንዳያዘመቱባት ነዳጅ፣ ሥልታዊነት፣ መጥፋት ያለበት ገዢ ጠላት የለባትም።ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ።አፍሪቃዉያን የደቡብ ሱዳንን ያክል እንዳይጨነቁላት ነዳጅ፥ አዲስ ገበያ የላትም።ፈረንሳዮችም፣ አፍሪቃዎችም የሉም እንዳይባሉ በጥቂት ጦር አለን ሲሉ፣ የአዉሮጳ ሕብረት አለሁ ለማለት እያዘገመ ነዉ።የደሐይቱ ሐገር ሕዝብ ግን ይረገፋል።የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ እልቂት መነሻ፥ የዓለም ትኩረት ያልሳበበት ምክንያት መድረሻችን ነዉ። ላፍታ አብራችሁኝ ቆዩ።
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን እንደ ብዙዉ ዓለም ፖለቲከኛ ዲፕሎማት ሁሉ ዘግይተዋል።ግን ቢያንስ በቀደም የግጭት፥ እልቂት ጥፋቱን አሳሳቢነት ተናገሩ።
«ለትዉልዶች ተሳስሮ የኖረዉ ማሕበረሰብ ተከፋፋል እየተጫረሰ ነዉ።ማሕበረሰቡን ደም ያቃባዉ ግጭትን ለማቆም እርምጃ ካልተወሰደ ለአስርታት የሚዘልቅ ግጭት ያስከትላል።»
እልቂቱ፥ ያዩ እንደሚሉት በርግጥም ዘግናኝ ነዉ።የሰዉ አንገት በገጀራ ይቀነጠሳል።እጅ፥ እግር፥ በጎራዴ ይቆረጣል።ሌላ አካል በጩቤ ይጨቀጨቃል።ሴቶች ይደፈራሉ። መንገዶች በደም አበላ ጨቅይተዋል-እየጨቀዩም ነዉ።አስከሬን በየጉርጓዱ ይከመራል።ከተንቀሳቃሽ ሥልክ እስከ ምግብ፥ ከሐብል እስከ ብስክሌት ያሉ ቁሳቁሶች ይመዘበራሉ። ቤቶች፥ መደብሮች፥ ቁሳቁሶች፥ መሳጂዶች ይነዳሉ።
ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን ከኒዮርክ የእልቂት ፍጅቱን አስጊነት ሲናገሩ ፖላንዳዊዉ የካቶሊክ ቄስ ንዛኮን የተባለችዉ መንደር የምታስነግደዉን ግፍ ይታዘቡ ነበር።ስማቸዉ መጠቀሱን ያልፈለጉት ቄስ እንደሚሉት ከመንደሪቱ ሲደርሱ ጣራ-ግርግዳቸዉ የጋዩ ቤቶች፥ በደም የራሰ ዓመድ፥ ከሰል፥ ዝንቦች የወረሩት አስከሬን—-አዩ።የንዛኮን አስደንጋጭ ትርዒት ቄሱ እንደሚሉት በዚሕ አላበቃም።
«እዚያ እንደደረስን ሃያ-ሁለት ሰዎች ተገደሉ።ወደዚያዉ ሃያ-አምስት ቤቶች ጋዩ።ወደ መንደሪቱ መሐል ስንደርስ የተቃጠሉ ሞተር ብስክሌቶች፥ ብስክሌቶች፣የጋየ መድሐኒት ቤት አየን።ሰዎቹ በጣም መጥፎ ነገር ነዉ የፈፀሙት።»
ሙስሊሞች የሚበዙበት የሳሌካ አማፂያን ሕብረት የቀድሞዉን ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ አምባገነን ገዢ ፍራንሷ ቦዚዜን አስወግዶ ሥልጣን ከያዘበት ካለፈዉ ዓመት መጋቢት ወዲሕ ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ሠላም ኖሯት አያዉቅም።በቀድሞዉቹ አማፂያን እና አማፂያኑን በሚቃወሙት በቦዚዜ ታማኞች፥ ቦዚዜ ባስታጠቋቸዉ ወጣቶች መካካል ለወራት የተደረገዉ ዉጊያ ግጭት ሐገሪቱን ለዘራፊ ወሮበሎች አጋልጧቷል።
ወዲያዉ ግጭት ዉጊያዉ ፖለቲካዊ መልክ ባሕሪዉን ለዉጦ ሐይማኖታዊ ሆነ።ሙስሊሞች የሚበዙበትን አማፂያን የሚቃወሙት የክርስቲያኒያን ሚሊሺዎች የታጠቀዉንም፥ ያልታጠቀዉንም፥ ሴቱኑም ወንዱኑም፣ ልጁንም አዋቂዉንም ሙስሊም ሲያሰኛቸዉ በጥይት፥ ሲፈልጋቸዉ በቆንጨራ ይረሽኑት፥ ያርዱ፥ ይቆራርጡ፥ ያሰደዱት ገቡ።
ቻናል ፎር የተሰኘዉ የብሪታንያ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ባለፈዉ ሳምንት እንደዘገበችዉ ደግሞ ሰዎች እንደበግ እየታረዱ ነዉ።
«ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ዉስጥ የዘር ማጥፋት ዘር እየተዘራ ነዉ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስጠንቅቋል።የአይን ምስክሮች እንደሚሉት ደግሞ ሙስሊሞች እንደገበግ እየታረዱ ነዉ።»
የቀድሞዋ የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ቅኝ ገዢ ፈረንሳይ የሠላማዊዉን ሰዉ እልቂት ፍጅት ያስቆማል ያለችዉን አንድ ሺሕ ስድስት መቶ ጦር ባለፈዉ ታሕሳስ አዝምታለች።ተጨማሪ አራት መቶ ወታደሮች ለማዝመት እየተዘጋጀችም ነዉ።የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሐገራት በበኩላቸዉ አምስት ሺሕ ወታደሮች አዝምተዋል።
የፈረንሳዩ ጦር አዛዥ ጄኔራል ፍራንሲስኮ ሶሪያኖ ባለፈዉ ሳምንት እንዳሉት ሰሞኑን በሕዝብ ላይ ለሚፈፀመዉ ጭፍጨፋ ፀረ-ባላካ በሚል ቡድን የተደራጁት የክርስቲያን ሚሊሺያ አብዛኞቹ አባላት ወንጀለኛ እና ወሮበሎች ናቸዉ።ወንጀለኛና ሽፍቶቹ የሚፈፅሙትን ጥቃት ለመከላከል ግን የሐያሊቱ ሐገር ጠንካራ ጦር ቢያንስ እስካሁን የተከረዉ የለም።
አምና መጋቢት የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክን የመሪነት ሥልጣን ይዘዉ የነበሩት የቀድሞዉ የሳሌካ አማፂ ቡድን መሪ ሚሼል ጆቶዲያ እና ጠቅላይ ሚንስትራቸዉ በፈረንሳይ ፍቃድ፥ በቻድ ግፊት ሥልጣን ለቀዉ በምትካቸዉ ሌሎች ከተሾሙ ወር አለፈ። እልቂቱ ግን ባሰ እንጂ አልቆመም። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዘር ማጥፋቱ ጭፍጨፋ እየተዘራ መሆኑን ሲናገር ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል በበኩሉ የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈፀሙን ይዘግባል።
የዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድ ቤት ICC ጠቅላይ አቃቢት ሕግ ፋቶ ቤን ሶዳ በበኩላቸዉ የሳሌካ አማፂያንም፥ የፀረ-ሳሌካ ሚሊሻዎችም በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የፈፀሙትን ወንጀል ለማጣራት ማቀዳቸዉን አስታዉቀዋል።በፈረንሳይ ድጋፍ በቅርቡ ሥልጣን የያዙት የማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ ጊዚያዊ ጠቅላይ ሚንስትር አንድሬ ንዛፓዬከ ግን እኒያኑ የፈረንሳዩ ጀኔራል ወንጀለኛ እና ወሮበላ ያሏቸዉን የክርስቲያን ሚሊሺያ አዛዦች ሰብስበዉ ጥቃቱን እንዲያቆሙ መማፀናቸዉን ዛሬ አስታዉቀዋል።
ሕዝብ ግን ፖላንዳዊዉ የካቶሊክ ቄስ እንዳሉት ከቻለ ይሰደዳል፥ ካልቻለ ግን ዕለት በዕለት እየተጨፈጨፈ ነዉ።የጠቅላይ ሚንስትር ንዛፓዬከ መንግሥት፥ የፈረንሳይ እና የአፍሪቃ ሕብረት ጦር ጭፍጨፋዉን ለማስቆም ሁነኛ እርምጃ እንዲወስዱ ፖለንዳዊዉ ቄስና ብጤዎቻቸዉ የሚያሰሙት ጩኸት ሰሚ አላገኘም።
«ርዕሠ ከተማ ባንጉይ የሚገኙት የመንግሥት ባለሥልጣናት እና የፈረንሳይ ጦር (እልቂቱን) እንዲያስቆሙ በተደጋጋሚ ጠይቄ ነበር።ማንም የተቀበለኝ የለም።አሁን ያለሁት የሴሌካ አማፂያን ከማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ እየለቀቁ በሚሸሹበት በካሜሩን እና በቻድ አዋሳኝ ድንበር ነዉ።እንደ ፀረ-ባላካ ሚሊሻዎች ሁሉ የሴላካ አማፅያንም ሲሸሹ የሚያደርሱት ጥፋት ከባድ ነዉ።»
ሱዳናዊዉ እዉቅ የጦር አበጋዝ ሱልጣን ረቢሕ ዓል ዙቤር ኢብን ፈድል አላሕ የዛሬዋን ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክን ከቻድ ጋር ቀይጠዉ መግዛት ከጀመሩበት ከ1875 (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ጀምሮ የዚያች ሐገር ሕዝብ የራሱን ጉዳይ በራሱ ፍላጎትና ፍቃድ ወስኖ አያዉቅም።
ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ፥ ቻድንና ሌሎች የአካባቢዉ ሐገራትን ከሱልጣን ረቢሕ አል ዙቤር ሐይላት የቀማችዉ ፈረንሳይ በ1960 ለማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ የነፃ ሐገር እዉቅና ብትሰጣትም የዚያች ሐገር ፖለቲካዊ ሒደት አንድም በቀጥታ ከፓሪስ አለያም ለፓሪስ ባደሩት በእንጃሚና፥ በያዉንዴ፥ በኪንሻሳ ገዢዎች ያልተዘወረበት ዘመን የለም።
ማዕከላዊ አፍሪቃ ነፃ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ በተቆጠሩት 53 ዓመታት በመፈንቅለ መንግሥት፥ እራሳቸዉን ወደ ንጉስነት እስከመቀየር በደረሱ የጦር መኮንኖች አገዛዝ፥በርስ በርስና በዉጪ ጣልቃ ገብ ጦር ግጭት ያልታበጠችበት ጊዜ ትንሽ ነዉ።በዚሕ ሁሉ ዘመን የዚያች ሐገር ደሐ ሕዝብ እኩል መጨቆን፥ መረገጥ መሰቃየቱ እንጂ ክርስቲያንና ሙስሊም በሚል ሐይማኖት ለይቶ የተጨፋጨፈበት ዘመን ግን የለም።
ዋና ፀሐፊ ፓን ጊ ሙን «ለበርካታ ትዉልድ ተሳስሮ የኖረ» ያሉት ማሕበረሰብ አንድነትን የበጠሰዉ እልቂት ፍጅትን ለማስቆም ፈረንሳይ እንደ ማሊ ያየር የምድር ጦሯን ማዝመት አልፈለገችም።የራስዋ የፓሪስ፥ የዋሽግተን፥ ለንደን መሪዎች እንደ ሊቢያ ሐያል ፈርጣማ ጦራቸዉን ለማዝመት ምክንያት የላቸዉም።ወደብ አልባ ደሐይቱ ሐገር የሐያሉን ዓለም ትኩረት ለመሳብ እንደ ማሊ ሥልታዊ ጠቀሜታ፥ እንደ ሊቢያ ነዳጅ ዘይት፥ የረጅም ጊዜ የምዕራባዉያን ጠላት ገዢ ሊኖታት ይገባል።የላትም።
የአዉሮጳ ሕብረት እልቂት ፍጅቱ በዓለም መገናኛ ዘዴዎች ወደ ዘር ማጥፋት ወይም የሐይማኖት ተከታዮችን ማፅዳት ከተሸጋገረ በሕዋላ እንኳን ለማዝመት ያቀደዉ ከስድስት መቶ የማይበልጥ ወታደር ነዉ።ሌላዉ ቀርቶ የአፍሪቃ መሪዎች እንኳን የደቡብ ሱዳንን ያክል ሙሉ ትኩረት ሊሰጧት አልፈቀዱም ወይም አልቻሉም።
እንደ ፈረንሳይ ሁሉ እልቂት ፍጅቱን በገሚስ ልብ የሚከታተሉት የአፍሪቃ መሪዎች ያዘመቱት ጦር እስካሁን እልቂቱን ለማስቆም እንደ ፈረንሳይ ጦር ሁሉ የተከረዉ ነገር የለም።እንዲያዉም MISCA በሚል ምሕፃረ-ቃል የሚጠራዉ የአፍሪቃ ሕብረት ጦር አዛዥ ጄኔራል ማርቲን ቱሜንታ ቹሙዋ እንደሚሉት ጦራቸዉ የሚተኩሰዉ በራሱ በጦሩ አባላት ላይ ከተተኮሰበት ብቻ ነዉ።
ጦሩ ሚሊሺያዎቹ ወይም አማፂያኑ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የሚያደርሱትን ጭጨፋ ለማስቆም እርምጃ ካልወሰደ ቦንጊ ድረስ የዘመተበት ዓላማ ምክንያት በርግጥ ግራ አጋቢ ነዉ።ካለፈዉ ታሕሳስ ወዲሕ መረን በለቀቀዉ ጭፍጨፋ ርዕሠ-ከተማ ቦንጊ እና አካባቢዋ ብቻ ከሁለት ሺሕ በላይ ሕዝብ መገደሉ ተዘግቧል።በየመንደሩ በየዕለቱ የሚያልቀዉን ሰዉ በትክክል የቆጠረዉ የለም።ዕልቂቱን ሽሽት የተሰደደ ወይም የተፈናቀለዉን ሕዝብ ከሚረዱት አንዱ ፖለንዳዊዉ ቄስ እንደሚሉት ግድያዉ ባሁን ይዘቱ ከቀጠለ እሳቸዉን ለመሰሉ የዉጪ ሰዎችም ማስጋቱ አይቀርም።ግን ጠመንጃ የታጠቀዉ ጦር የማያደርገዉን ለማድረግ የቆረጡ ይመስላሉ ቄሱ።
«የለም ከዚሕ አንወጣም።ከሕዝቡ ጋር መቆየት እንፈልጋለን።ሕዝቡ ይፈልገናል።በያለንበት በአሸዋ የተሞሉ ጆንያዎችን ደርድረን በምንሰራዉ ምሽግ እንጠለላለን።ጥቃቱ በኛ ላይ በጣም ከከፋ ግን እንወጣ ይሆናል።»
ጄኔራሎቹ ይፎክራሉ።ፖለቲከኞቹ ገና ያቅዳሉ።ዲፕሎማቶቹ ያወራሉ።ሕዝብ ያልቃል።ይሰደዳል።ሐብት ንብረት ይወድማል። ቄሶቹ፥ ርዳታ አቀባዮቹ እልቂት፥ ፍጅት ስደት ስቃዩን ይጋፈጣሉ።ማዕከላዊ አፍሪቃ ሪፐብሊክ።እስከ መቼ ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።
ነጋሽ መሐመድ

Tuesday, February 18, 2014

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ የተከሰተው ውጥረት ወደ ደም መፋሰስ እንዳያመራ አባላቱ ስጋታቸውን ገለጹ !

ከተመሰረተ 20 አመታትን እንዳስቆጠረ የሚነገርለት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ውስጥ የተፈጠረው ቅራኔ መልኩን ለውጦ መቀጠሉን የሚናገሩ ምንጮች በቀደሞው የኮሚኒትው ሊቀመንበር እና በመሃበሩ ስራ አመራር መሃከል በተነሳው አለመግባባት የፌታችን አርብ ፊብርዋሪ 21 / 2014 ምሸት ስራ አመራሩ በጠራው የአባላት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አሰቃቂ ነገር ሊፈጠር እንደሚችል ገልጸዋል ፡፤ 


በቀርቡ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የጠራውን የአባላት ሰብሰባ ተከትሎ የአንባሳደር መሃመድ ሃሰን የቀርብ ዘመድ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ደጋፊዎቻቸውን ወደ አዳራሹ በማስገባት ከማህበሩ ሊቀመንበርነቴ የተነሳሁት ያለአጋባብ ነው በሚል በኮሚኒቲው ሊቀመንበር ላይ ቡጢ መሰንዘራቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰው መለስተኛ ግጨት ስበባው ሳይጀመር መበተኑ ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የአንባሳደር መሃመድ ሃሰን ድጋፍ እንዳላቸው የሚነገርላቸው ሺክ ሙስጠፋ ሁሴን የፊታችን አርብ ፌብርዋሪ 21-2014 የኮሚኒቲው ስራ አመራር በጠራው ጠቅላላ የአባላት ጉባኤ ላይ ሁከት ለመፍጠር በብሄር ላይ የተመሰረተ ቀስቀሳዎችን በማካሄድ ላይ መሆናቸውን የአይን እማኞች ከሪያድ አረጋግጠዋል። 

ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን ፊብርዋሪ 14-2014 ምሸት አያሌ ደጋፊዎቻቸውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ በሚገኘ አንድ ቢሮ ውስጥ በማን አለብኝነት ሰብሰብው ሲመክሩ መታየታቸውን የሚገልጹት ምንጮች ሼኩ ለግብረ አበሮቻቸው አማራ ስልጣናችን ስለነጠቀን ማንነታችንን ለማስከበር እና ስልጣናችንን ለማስመለስ እኛ ኦሮምዎች እጃችንን አጣጥፈን መቀመጥ፡አይገባንም ብለው በመናገር የጥቂት መስል ደጋፊዎቻቸውን በተሳሳተ መንገድ ቀልብ በመሳብ የኮሚኒቲውን አባላት በዘር በሃይማኖት ከፋፍሎ ለማጋጨት አቅማቸው የሚችለውን ሁሉ በማድረግ ላይ መሆናቸውን አጋልጠዋል። የሼክ ሙስጠፋን ድብቅ አጀንዳ ለማስፈጸም ብሄርተኝነትን በስፋት በማራገብ ላይ የተሰማሩት ቅጥረኞች በህገ ወጥ የሃዋላ ንግድ ላይ የተሰማሩ እና ቀደም ሲል በእህቶቻችን ህይወት ዶላር ሲሰብሰቡ የከረሙ የሰራተኛ እና አሰሪ አገናኝ ኤንጀንሲ ባለቤቶች እና ደላላዎቻቸው መሆናቸውን የሚናገሩ ወገኖች ግለሰቦቹ የትኛውንም በሄር አሊያም የሃይማኖት ተቋም እንደማይወክሉ ገለጸው ህብረትሰቡ ከእንደነዚህ አይነት ሴጣናዊ መርህ ካነገቡ መሰሪዎች እራሱን በመከላከል በዘር በሃይማኖት ሳይከፋፈል እንደወትሮው ሁሉ በአንድነት የኮሚኒቲውን ንብረት ነቅቶ መጠበቅ እንደሚገባው መክረዋል። 
የቀድሞው የኮሚኒቲ ለቀመንበር ሼክ ሙስጠፋ ሁሴን በስማቸው በከፈቱት ሁለት ሰራተኛ እና አስሪ አገናኝ እጄንሲ ያስመጦቸው እህቶቻችን በህክምና እጦት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ውስጥ ህይወታቸው ማለፉን የሚያስታውሱ ታዛቢዎች ሼኩ በሳውዲ አረቢያ የደህነት ሃይሎች ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ በኮሚኒቲው መተዳዳሪያ ህገ ደንብ መስረት የሊቀምንበሩን ቦታ የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑት ምክትል ሊቀምንበሩ አቶ ቃሲም ያሲን ተረክበው መሸፈናቸው ሊያስመስግናቸው እንጂ ቡጢ ሊያሰነዘርባቸው እንደማይገባ የሚናገሩ የአካባቢው የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች ሼኩ ከወህኒ ከወጡ በሃላ ጤንነት እደማይሰማቸው በመጥቀስ የኮሚኒቲ ሊቀምንበርነቴን ለምን በአማራ ብሄር ተነጠኩ በሚል ዘረኝነት የተጠቀሱትን ደጋፊዎቻቸውን በመስብሰብ በአባላቱ መሃከል የብሄር እና የሃይማኖት ግጭትን ለመጫር እያሰሙ ያለው ጩሀት አብነት መሆኑንን ይገልጻሉ ። 

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት ማህበር በስሩ ከሁለት ሺህ በላይ ህጻናትን ተቀብሎ የሚያስተናገድ አንድ አለም አቀፍ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ባለቤት እንደነበር የሚገልጹ አንጋፋ የማህበሩ አባላት ት/ቤቱን ከኮሚቲው በመነጠል ኤንባሲው በራሱ ስልጣን ባስቀመጣቸው የቦርድ አባላት ት/ቤቱን እንዳሻው እይዘወረ ላለፉት 4 አመታት ገቢ እና ወጪው ሳይለይ እስካሁንም የጥቂቶች ኪስ ማደለቢያ ሆኖ መቀረቱን ይናገራሉ። ዛሬ በኮሚኒቲው ስራ አመራር እና በሼክ ሙስጠፋ ደጋፊዎች መሃከል የተነሳው የስልጣን ሹክቻ ከጥቅም ጋር የተቆራኘ መሆኑንን የሚናገሩ ወገኖች በአሁኑ ግዜ ብቸኛ የማህበሩ ንብረት የሆነው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል ከት/ቤቱ ባላነሰ ሁኔታ ዘረፋ እየተፈጸመበት መሆኑን ይገልጻሉ፡፤ 

በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ከ 8 መቶ የሚበልጡ አባላት እንዳሉት የሚናገሩ እነዚህ ውስጥ አዋቂ ምንጮች ማህበሩ የፊታችን አርብ ፌብርዋሪ 21 2014 ጠቅላላ ጉባኤ ለማድረግ መወሰኑን በመግለጽ በወቅቱ ግጭቶች እንዳይፈጠሩ ኤንባሲው እና የሚመለከታቸው አካላቶች የዜጎቻችን ህይወት ለመታደግ ጥንቃቄ መውሰድ እደሚገባቸው አክለው ጠቁመዋል። 


Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ 



ማሳሰቢያ ከዚህ በታች የተመለክተው የቪድዮ ሰዕላዊ መግለጫ ቀደም ብሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ውስጥ ጥቂቶች ብዙሃኑን በዘር በሃይማኖት ሲከፋፍሉት የሚያሳይ ነው።