ጋዜጠኛ ሰሎሞን ሙሉ ታፈሰ የነፃው ፕሬስ ካፈራቸው ምርጥና ድንቅ ብእረኞች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይነሳል። የሰሎሞን ልዩ ተሰጥኦ በማንኛውም ጉዳይ ላይ የሚፅፍ መሆኑ ነው። በጭራሽ የማይፈራ ደፋር ጋዜጠኛና ደራሲ ነው። ለእውነት የቆመ፣ ብዙ መስዋእትነት ለአገሩና ለነፃው ፕሬስ የከፈለ ሰው ነው። ዛሬ..ዛሬ ሃብት ጥግ ከደረሱ በርካታ አርቲስቶች ጀርባ ሰሎሞን አለ። ለምሳሌ መጥቀስ ቢያስፈልግ አንዱ ሰራዊት ፍቅሬ ነው።
ሰሎሞን ሕይወት ፊቷን አዙራበት ለአምስት አመት ገደማ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ጀርባ (ጎዳና) ይተኛ ነበር። ራበኝ፣ ጠማኝ፣ ታረዝኩ…ብሎ ማንንም አይጠይቅም። ሶስትና አራት ቀን ምግብ በአፉ ሳይዞር የሚያሳልፍበት ቀናት አሉ። ባለፈው አመት ሰሎሞን ያለበትን ሁኔታ በተመለከተ በዚሁ ማህበራዊ ገፅ መጣጥፍ አቅርቤ ነበር። በለንደን የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሰሎሞንን ሲረዱት ቆይተዋል። ሊመሰገኑ ይገባል። አሁን ግን ሰሎሞን በተደራራቢ ችግርና ስቃይ ውስጥ ወድቋል። የኪንታሮት በሽታ እያሰቃየው፣ በዛ ላይ የሚላስ የሚቀመስ አጥቶ ተቸግሯል። ስቃይና ረሃብ በውስጡ ይዞ የመከራ ቀንና ሌት እየገፋ ነው። ለታፈነው ስቃይ የሚደርስ ወገን ይጥፋ?...ቢያንስ ህክምና የሚያገኝበት?...ጋዜጠኞችና ሌሎች ወገኖች ምን ትላላችሁ?...
( የሰሎሞን ፎቶ, ባለፈው አመት የላከልኝ ደራሲ ፋሲል ተካልኝ ነው..)
No comments:
Post a Comment