በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በዲያስፖራው ዘንድ ተደማጭነት እና ክብር ያላቸው 3 ዲፕሎማቶች ኤንባሲውን ወክለው በታዛቢነት መገኘታቸውን የሚናገሩ ምንጮች ስብሰባው ያለምንም ስጋት እና ሁከት በሰላም እንዲካሄድ ለማስቻል ከፍተኛ አስተዋጾ ማድረጋቸውን አክለው ገልጸዋል። በስብሰው ወቅት የኮሚኒቲው ስራ አመራር የ20 ወራቱን የስራ ሪፖርት በማስደመጥ በአባልቱ መሃከል ከፍተኛ ውይይት መድረጉን የሚናገሩ እማኞች በስራ አመራሩ የቀረበው ሪፖርት በአብዛኛው አባላት ዘንድ ተቃውሞ ገጥሞት እንደነበር ሳይሽሽጉ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የኮሚኒቲው ሊቀምንበር አቶ ቃሲም ያሲን በቀረብው ሪፖርት ዙሪያ ከአድማጮች ለቀረበላቸው ጥያቄ ማብራሪያ በመስጠት በጉባኤው ተሳታፊዎች ዘንድ ሰፊ ውይይት ከመደረጉም በላይ የኮሚኒቲው ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል በኮንተራት ለግለስቦች ቢተላለፍ የበለጠ ውጤታማ መሆን እንደሚችል ከአንድ አድማጭ የተሰነዘረውን ሃሳብ የኤንባሲው ተወካይ ክቡር አቶ ተመስገን ኡመር የኮሚኒቲው ንበረት ለዲያስፖራው ያለውን አጋርነት እና ጠቀሜታ በዝርዝር በማስቀመጥ የኮሚኒቲው ንብረቶች በኤንባሲው ስር እንደመሆናቸው መጠን አካሄዱ ህጋዊ መስረት ሊኖረው ስለማይችል የቀርበውን ሃሳብ ውድቅ በማድረግ ተቀባይነት እንደሌለው አረጋግጠዋል፡፤ የማህበሩ ሁለገብ የመዝናኛ ማዕከል የሆነው ካፍቴሪያ ዘንድሮም 61 ሺህ ሪያል ኪሳራ ማሳየቱን ከቀረበው ሪፖርት መረዳት ተችሏል።በዚህ ጉባኤ ላይ የሃይማኖት አባቶች የህገር ሽማግሌዎች ጨምሮ 1/ ክቡር አቶ አህመድ ጠላህ 2/ ክቡር አቶ ተመስገን ኡመር 3/ ክቡር አቶ መስፍን ድባቡ መገኘታቸውን የሚገልጹ የኮሚኒቲው አባላት ከስጋት እና ጭንቀት ይልቅ የጉባኤውን ምሸት በነጻነት ማሳለፋቸውን አስረድተዋል። ለጉባኤው የቀረበ የተባለው ሪፖርት ግልባጭ በእጃችን እንደገባ ሰሞኑን በዚህ ገጽ በስፋት ለመዳሰስ ይሞከራል።
Ethiopian Hagere ከጅዳ በዋዲ
No comments:
Post a Comment