Monday, August 17, 2015
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ « ልጆቼን ለአደጋ እናቴን በመጨረሻ ዘመኗ ስንቅ አቀባይ ማደረግ አልሻም አለ ! »
የአረቡን ዓለም አስከፊ የስደት ገጽታ በማለዳ ወጉ የሚያስቃኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የቱንም ያህል ኑሮው የስመረ ቢሆንም አንድም ቀን ነፍሱ በሃሴት ተሞልታ እንደማታውቅ በቀርብ የሚያውቁት ሁሉ ይናገራሉ ። በተለይ ከቁጥጠር
ውጭ በወጣው ስደት ፤ ዜጎች ላይ የሚደርሰው ስቃይና በደል መቋጫ እንዲያገኝ ድምጽ አልባ ለሆኑ ግፉሃን ድምጽ በመሆን ጋዜጠኛው እያሰማን ያለው የብዕር ጩኃት የቱንም ያህል
የህዝብን ቀልብ ስቦ
ደረት ቢያስደቃም ፤ ድጊቱ በህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረአት ባለስልጣናት ዘንድ ግን አልተወደደለትም። ጅዳ ቆንስላ
ጽ/ቤትና ሪያድ ኤንባሲ ተሰግስገው በዜጎች
ንግድ የከበሩ የስረአቱ ፖለቲካ ደላሎች ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ « የዲፕሎማቱን የስራ እንቅስቃሴ አሰናክሏል ፡ ህዝብን በመንግስት ላይ
አነሳስቷል » በሚል ተራ ውንጀላ ጣታቸውን ቀስረው በሀወሃት መራሹ
የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ድህንነት ጥርስ ውስጥ
ገብቶ ጋዜጠኛው በአይነ ቁራኛ መጠበቅ ከጀመረ እነሆ አመታትን አስቆጠሯል።

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ፈጽሞል በተባለው ነገር ተላልፎ እንዲሰጥ ህወሃቶች ለሳውዲ መንግስት
እስካሁን በይፋ ያቀረቡት ጥያቄ ባይኖረም አንደበታቸው በእውሸት የተገነባ የስረዓቱ
ካድሬዎች ጋዜጠኛው የስይፍ ሰላባ እንዲሆን ለሳውዲ ሸሪዓ ፍ/ቤት
የሃሰት መረጃ ለማቅረብ ያልበጠሱት ቅጠል
ያልፈነቀሉት ድንጋይ እንደሌለ ይነገራል። ነብዩ ሲራክ በአንድ ወቅት በሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ታስሮ ከተፈታ ወዲህ እስካሁን የጎላ
ችግር ባይደርስብትም ለእረፍት ወደ ሃገር ሲያቀና በቁጥጥር ስር
ለማዋል እቅድ እንዳለ
ለጉዳዩ ቅረበት ያላቸው ምስጢራዊ ምንጮች አረጋግጠዋል። በማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሚያጠነጥን የማለዳ ወግ መረጃ ቅበላው እንደ ጥፋት ተቆጥሮ ክትትል የሚደረግበት ይህ ጋዜጠኛ በወዳጅ ዘመድ ናፍቆት እይተብስለስለ በዜጎች ስቃይና በደል ሰላም ያጣውን አይምሮ ለማሳረፍ ፤ የሚወዳትን ሃገሩንና
የተወለደበትን ቀዬ ለመርገጥ አለመታድሉን መረዳት ተችሏል። እያደረገ ባለው ነገር
ሁሉ ደስተኛ መሆኑንና ቅንጣት ያህል ለፈሪዎች ዱላ እንደ ማይበረከክ በዚህ ዙሪያ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ የስጠው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ፤ «ይህ ስጋት በአንዳንድ ወዳጅ ዘመዶቹ እንደተነገረውና ለግዜው ወደ ሃገር ከመሄድ መቆጠቡን ገልጾ በዓረቡ አለም በሚገኙ ዜጎቻን ላይ የሚፈፀመው ቅጥ ያጣ በደል እስኪያበቃ ፤ በግሉ እያቀረበ ባለው መርጃ የሚመጣውን ሁሉ በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን አልሸሸገም ።ጋዜጠኛው በማስከተል « ምንም እንኳን የማቀርበው መረጃ ከማህበራዊ ጉዳዮች ያለፈ ባይሆንም በድርጅት አባላትና በተወካዮቻቸው ላይ የምሰነዝረው የሰላ ሂስ ለሁሉም ስጋት መሆኑ ግልጽ ነው፣ ታዲያ ሃገርችን ውስጥ ትክክለኛ ፍትህ የሚሰጥ ቢሆን ብከሰስ እንኳ እንደ ማሸንፋቸው ጥርጥር የለኝም ፣ ዳሩ
ግና የ 4 ዓመት ህጻን የደፈረን ፍ/ቤትና የፍትህ ስርአት ተማምኖ ወደ ሀገር መግባት ልጆቼን ለአደጋ እናቴን በመጨረሻ ዘመኗ ስንቅ አቀባይ ማደረጉን ስለማልሻ ከመሄድ መታቀብ ግድ ሆኖብኛል! » በማለት ሃገር ለመግባት እምነት እንድሌለው
ገልጾል። በተያያዘ ዜና ጋዜጠኛ ነብዩ
ሲራክ ሰሞኑን ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውን ወንድሙን መርዶ አልቅሶ እርሙን ማውጣት በማይችልበት ስደት አለም ከዘመድ አዝማድ ርቆ በሃዘን ላይ ሃዘንን ማስተናገዱን ለማወቅ ተችሏል ። Ethiopian Hagere
Jed Bewad
Saturday, August 8, 2015
ሰበር ዜና ሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፀረ ወያኔ /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ተቃውሞ ስትናጥ አደረች !
ሰሞኑን የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ፍ/ቤት በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደውን ኢፍተሃዊ ውስኔ በመቃወም ሪያድ ከተማ ውስጥ ትላንት አርብ ኦገስት 7 2015 ምሸት ኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ተቃውሞውን አሰምቷል ። ቁጥሩ ከፍተኛ እንደሆነ ህዝብ የተገኘበት ይህ ታላቅ
ተቃውሞ የአካባቢውን ድባብ ለውጦት እንደ ነበር ለማወቅ ተችሏል። የተከሰተው ነገር በራሳችን እንደደረሰ ተሰምቶን በሶስት ቀን ውስጥ በተጠራ የተቃውሞ ጥሪ ይህን ያህል ህዝብ አንድነቱን ጥብቆ ለተቃውሞ በነቂስ መውጣቱ የትግሉ አንዱነት ጥንካሬ መገለጫ መሆኑን የገለጹት ሼክ ሲዒድ አህመድ ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ከባድ ፈተና እንደ ተጋረጠበት አውስተው ይህ ፈተና አዲስ ሆኖብን ሳንደናገጥ ትግሉን በበሰለና በስለጠነ መንገድ በማጠናከር እስከ ድል መቀጠል እንደሚገባ በቁጣ የወጣውን ህዝብ ሙስሊም በማረጋጋት በአባታዊ ምክራቸውን ለግሰዋል ።
ሼክ ሰዒድ በማስከተል አቡበከር በአንድ ወቅት በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ወህኒቤት ግፍ እይተፈፀመበት
« ፍ/ቤቱም የኛ ፤ ፖሊሱም የኛ ፤ አቅቤ ህጉም የኛ ፤ መርማሪውም የኛ ስለሆነ የፈለከውን የመከላከያ ምስከር ብታመጣ ብትወጣ ብትወርድ ከፍርድ አታመልጥም እኛ ነን የምንፈርድብህ » ተብሎ በስረአቱ ካድሬዎች በምጸት ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት ተነግሮት የነበረውን በተግባር ማየቱን ሼኩ ለተስብሳቢው በመጥቀስ በመሪዎቻችን ላይ የተፈፀመው ደባ ሊያስደንቀን እንደማይገባ ገልጸው የፍ/ቤቱን ኢፍታሀዊነት ለተሰብሳቢው በተጨባጭ አስረድተዋል። በውቅቱ በቁጣ
ገንፍሎ የወጣውን ህዝብ ለማስተናገድ ተይዞ የነበረው ቦታ በመጨናንቁ የነበረውን የሪያድ የአየር ሙቀት በመቋቋም ከ ምሽቱ 1 ስዓት ጀምሮ እስከ ሊሊቱ 9 ስዓት ድረስ በዘለቀው በዚህ ፀረ ጭቆና
ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች ህዝበ ሙስሊሙን
በገዛ ሃገሩ መቆሚያ መቀመጫ ያሳጣውን የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስረዓት እንዲያጠፋላቸው እያለቀሱ ለፈጣሪያቸው ፀሎት « ዱአ » አድርሰዋል ። የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ፍ/ቤት በህዝበ ሙስሊም ተወካዮች ላይ ያሳለፈው ውሳኔ ሰረዓቱ በመላ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ላይ እየፈጸመ ያለው ሃይማኖታዊ ጭቆና ግፍና በድል አንዱ አካል መሆኑን የገለጹት እንዚህ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከእንግዲህ ትዕግስታቸው መሞጠጡን ጠቅሰው በዚህ አምባ
ገነን ስረዓት ላይ የጀመሩትን ትግል እስከ መጨረሻ አጠናክረው ለመቀጠል በመወሰን የአቋም መግለጫ አውጥተዋል። በሳውዲ አረቢያ ድምጻችን ይሰማ ደጋፊዎች እያካሄዱ ባለው ሃይማኖታዊ ፀረ ጭቆና ትግል የህወሃትን/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ስረዓት የቦንድ ሽያጭና መስል የስረአቱን እንቅስቃሴ በማሽመድመድ የታወቁ ግንባር ቀደምና ጠንካራ መሆናቸው ይነገራል። «ማሳሰቢያ ሊንኩን ተጭነው ያድምጡ ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ
Saturday, April 25, 2015
በሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራውን IS IS ዓለም አቀፍ አሸባሪ ቡደን አወገዙ ።
ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ ሚያዚያ 25 / 2007 ምሸት የክርስትና የእስልምና እምንት ተከታይ የሃይማኖት አባቶች ጨምሮ መላው የሪያድ ነዋሪዎች በተገኙበት የሃዘን መግለጫ ላይ እራሱን እስላማዊ መንግስት ብሎ የሚጠራው አሸባሪ ቡደን በንጹሃን ዜጎቻችን ላይ የፈፀመውን አረመኔያዊ ድርጊት አውግዘዋል ። አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊ ዎች እራሱን አይ ኤስ አይ ኤስ እያለ የሚጠራው አረመኔ ቡደን እንጀራ ፍለጋ ከሃገር በስተሰደዱ ንጹሃን የክርስትና እምናት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ የወሰደው ዘግናኝ እርምጃ ቡዱኑ የለየለት አረመኔና የትኛውንም ሃይማኖት የማይወክል የዘመናችን ጭራቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፤አንድ የእስልምና ሃይማኖት መሪ « ኢማም » በበኩላቸው ሲናገሩ ኢስላም ማለት ሰላም ማለት መሆኑን ገለጸው ሶሪያና ኤራቅን ጨምሮ በስሜን አፍሪካ እንደሚነቀሳቀስ የሚነገርለት ይህ የጨካኞች ቡደን በስሜት የሚነዱ ሃይማኖታዊ መስረተም ሆነ ግንዛቤ የሌላቸው አለም አቀፍ አሸባሪ ቡድኖች
ስብስብ መሆኑን ተናግረዋል። ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን ላይ የተፈፀመው አሰቃቂ ግድያ አለማችንን በኃይማኖት ሽፋን በሽብር በማተራመስ ምድራችንን በንጹሃን ደም ለማጨቅየት ቡድኑ ያለውን አኩይ ፍላጎት የሚያመላክት ለመሆኑ እጀራ ፍለጋ ሲከራተቱ በነበሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመው ሴጣናዊ ተግባር አብነት ነው ብለዋል ። በንጹሃን ደም የጨቀየው አይ ኤስ አይ ኤስ በ 30 ኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው እርምጃ ሃዘናቸው መሪር መሆኑን የገለጹ በስልክ ያነጋገርኳቸው አንድ የስብሰባው ተካፋይ አባወራ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ሊቢያ ላይ የተቀሉት ወገኖቻችን አሞሞት በጭካኔው ወደር የማይገኝለት በዓለም ህዝብ ፊት በአደባባይ የተፈጸመ በመሆኑ በስደት ዓለም በወገኖቻችን ላይ እይደረሰባቸው ካለው ሁሉ ለየት ያለ በመሆኑ ህዘናችንን መሪር ቢያደርገውም በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ቀደም ሲል ህጋዊ በሆነ መንገድ በኮንተራት የመጡ ኢትዮጵያውያን እህቶች አስክሬን ኮሚኒቲው ከማስተናገዱም በላይ በሳውዲ አረቢያ የተለያዩ ግዛቶች ተበትነው የሚገኙ በ አስርሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በአሰሪዎቻቸው ከሚፈጸምባቸው ግፍና በደል እራስቸውን ለመታደግ እግር ወዳመራቸው ሲያቀኑ ህይወታቸውን አጥተው ያለቀባሪና መርዶ ነጋሪ በሳውዲ ሆስፒታሎች ተቆልሎ የሚገኘውን የዜጎቻችንን በድን ቤት የቁጠረው ብለዋል ። እኚህ አባት በማስከተል የሞቱበት ምንክንያት በወል ሳይታወቅና ለቤተሰብ መርዶ ሳይነገር ስረዓተ ቀብራቸው የተፈጸመውን ወገኖቻችንን አሁን ማንሳት በሃዘን ላይ ሃዘን ከማስተናገድ ባሻገር ትርጉም የለውም በሚል ምሬታቸውን በለቅሶ ገልጸዋል።
በሪያድና በጅዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እራሱን አይ ኤስ አይ ኤስ እያለ በሚጠራው አረመኔ ቡድን በታረዱ ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖቻችን የተሰማቸውን ሃዘን ለመግለጽ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን መንግስት ለዜጎች ጥበቃ አለማድረጉን በጽኑ ኮንነዋል። በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲና በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በዜጎቻችን ላይ የደረሰውን አስደጋጭ ዜና ምክንያት በማድረግ የሃዘን መግለጫው ላይ የተሳተፉት ዲፕሎማቶች ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለውን አሰቃቂ ትዕይንት ከማስቆም ይለቅ ነገሩን በማድበስበስ ከሃላፊነት ለማምለጥ የሚጥሩ በመሆናቸው አብዛኛው ህብረተሰብ በነዚህ የመንግስት ሹማምንቶች ላይ ያለው እምነት መሞጠጡ ይነገራል፡፤ አንድ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ከሚታተም ጋዜጣ ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉ በሪያድ የኢትዮጵያ መንግስት ዲፕሎማት ሪያድና ጣይፍ ከተማ ውስጥ ህይወት አጥፍተዋል በሚል ክስ ተመስርቶባቸው አንገታቸው በአደባባይ በስይፍ ስለተቆረጠው ኢትዮጵያውያን የኮንተራት ሰራተኞች ኤንባሲው አንደ ማንኛውም ሰው ዜናውን በሳውዲ ሚድያዎች ከመስማት ባሻገር ምንም አይነት መረጃ እንዳልነበረው መግለጻቸው አይዘነጋም ፡፤ይህን ተከትሎ በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ አንባሳደር ዶ/ር መሃመድ ሃሰን ሃላፊነታቸውን በብቃት አልተወጡ በሚል የስራ ግዜያቸውን ሳይጨርሱ ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ሃገር መመለሳቸው ይታወቃል።
ይህ በዚህ እንዳለ በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤትና በሪያድ ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ሰንደቅ ዓላማዎች ዝቅ ብለው እንዲውለበለቡ ከመደረጉም በላይ ከ 5000 የሚበልጡ የሁለቱም ት/ቤት ኢትዮጵያውያን ታዳጊ ተማሪዎች አይ ኤስ አይ ኤስ ብሎ እራሱን በሚጠራው አሸባሪ ቡደን በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመውን አረምኔያዊ ድርጊት በማውገዝ በዚህ ግፈኛና አረመኔ ቡደን አንገታቸው ለተቀላው ኢትዮጵያውያን የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖች ጸሎት በማድረስ የተሰማቸውን ሃዘን ገልጸዋል።
Ethiopian Hagere Jed Bewadi
Friday, March 20, 2015
እናቶችን የሚያስለቅስ አገዛዝ - የፍርድ ድቤት ዉሎ (ለገሰ ወልደሃና)
የካትት 10/2007 ዓም የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የተጠየቀበት የነዘመነ ምህረት ችሎት፣ በቀጠሮው መሠረት፣ ዛሬ መጋቢት 10/2007 ዓም ተሰይሟ።
ዘመነ ምህረት፣ መለሰ መንገሻና ሌሎች ወደ 25 የሚጠጉ ወጣቶች በማእከላዊ ፓሊሶች ታጅበው 8:ሰአት 20 አካባቢ ፍርድ ቤት ግቢ ገቡ። እንደተለመደው በርቀት እጃቻችንን በማውለብለብ ሰላም አልናቸው። እነሱም ባልታሰረው እጃቸው አፀፋውን መለሱልን።
ዘመነ ምህረት ብዙም አልተጎሳቆለም። መለሰ መንገሻ ግን በጣም ከስቷል። ሰውነቱ ቢጫ ሆኗል። እንደዛም ሆኖ ፈገግታ ግን አልተለያቸው። ችሎት ከመግባታቸው በፊት የተቀመጡበት አግዳሚ ወንበር ላይ ሆነው፣ በምልክት ለመነጋገር ሞክረን ለመግባባት ችለን ነበር። ነገር ግን ፓሊሶች ከኛ ጋር የሚያደርጉት የምልክት መግባባት አይተው፣ ፊታቸውን አዙረው አስቀመጧቸው ። ተስፋ ሳንቆርጥ ሞከርን። አልተሳካም።
የችሎት ሁኔታ እንደሚታወቀው በዝግ የታየ በመሆኑ የነበረውን ሁኔታ ማወቅ አይቻልም። ዘመነና መለሰ መንገሻ ችሎት የገቡት ተለያይተው ነው። ከዚህ መረዳት የሚቻለው የተከሰሱበት መዝገብ ይለያያል ማለት ነው ። ሁለቱም ችሎት ሲገቡ ሌሎች ወጣቶች አብረዋቸው ገብተዋል።
የዛሬው የችሎት ሁኔታ ተጨማሪ የ28 ቀን ጊዜ ቀጠሮ ፓሊስ ጠይቆ ለመጋቢት 08/7007 ዓም ተቀጥሯል።
አንድነት ዘመነ ምህረት፣ የዘመነ ምህረት የበኩር ልጅ፣ በፍርድ ቤት አልተገኘም። የሕጻን አንድነትን ቦታ ተክተው፣ ከሰሜን ጎንደር ተጉዘው የመጡት፣ የቆራጡ ታጋይ ዘመነ ምህረት እናት ነበሩ። እኚህ እናት ታማሚ ናቸው። የወለደ አንጀታቸው አልችል ብሏቸው ህመማቸውን ችለው፣ ከሰሜን ጎንደር፣ ከ700 ኪሎሜትር በላይ ተጉዘው፣ «ልጄ በህይወት መኖሩን ካላየሁ አላምንም» ብለው፣ አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ተገኝተዋል። በጣም ያሳዝናሉ።
የመጡበትን ምክንያት የልጃቸውን በህይወት መኖር አለመኖር ለማረጋገጥ ነበር። በካቴና ታስሮም ቢሆን አይተዋል። በውስጣቸው ምን እንደተሰማቸው ባላውቅም። ጥልቅ የሆነ ሀሳብ ገብቷቸዋል። ለሰው ከመናገር ዝምታን ። ከኚህ የጀግና እናት ጋር ትንሽ ለመጨዋወት ሞክረን ነበር ። እንባቸው እየቀደማቸው ማውራት አልቻልንም። በመጦሪያቸው ጊዜ መንከራተት በጣም ያማል። እስኪ የኝህ እናት ፀሎት ተሳክቶ ዘመነ ተፈቶ ከመንከራተት ያድናቸው ዘንድ እንፀልይላቸው ። (ምንጭ: Millions of voices for freedom)
ድምጻዊ ብረሃኑ ተዘራ ሰሞኑን የለቀቀው ነጠላ ዜማ የስረአቱን ካድሬዎችና ቱባ ባለስልጣናቱን አስበርገገ ።
ኢትዮጵያን ሀገሬ ጅዳ በዋዲ
ከሁለት ሳምንት በፊት « ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ አንድነት ይብጀናል ዛሬ » በሚል ነጠላ ሃገራዊ ዜማው የተደናገጡ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ድህንነት አባላት ክተትል ይደረግበት የነበረው ድምጻዊ ብረሃኑ ተዘራ ሰሞኑንን ወደ አሜሪካ ማቅናቱን ለማወቅ ተችሏል። የህዝብን ፍላጎት በሆነ ነገር በመጨበጥ መግታት እንደ ማይቻል የሚናገረው ድምጽዊ ብርህኑ ተዘራ በተለይ ከኢሳት ድምጽ ጋር ሰሞኑን ባደረገው ቃለ ምልልስ ሲገልጽ « በመንግስት የተከለከለ አንድ ነገር በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው በመጥቀስ ህዝቡ በተቃራኒ ጎራ መቆሙን አውስቷል ይህንንም ተከትሎ ሃገራዊ አንድነትና እውነታን ማንም መገደብ ስለማይቸል « ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ አንድነት ይብጀናል ዛሬ » የሚል ነጠላ ዜማው ወቅታዊና የህዝብን ስሜት የሚገልጽ በመሆኑ በኢትዮጵያውያን ዘንድ በከፍተኛ ደረጃ ተደማጭነትን
ማግኘቱን አክሎ ገልጾል፡ በዚህ ነጠላ ዜማ ውስጥ
« አይደለም አየሩ አይደለም ተራራው ፣
ሲርብ የሚያበላው ሃገር ማለት ሰው ፣
ለሆዱ ያደረ ወዳጁን የረሳ ፣
ነፃነት ምኑ ነው ቢነገር ቢወሳ ፣
» በሚለው የስንኝ ቋጠሮ የተበሳጩ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎችና ቱባ ባለስልጣናት አርቲስቱ በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ተደማጭነት ካለው የኢሳት ድምጽ ጋር ቃለ ምልልስ በማድረጉና ዛሬ አሌክስ አንደር ቨሪጂንያ ውስጥ የህዝብን ትግል መቀላቀሉን በሚያበስረው ዝግጀት በአሁኑ ግዜ ጥላቸውን በማያምኑ የመንግስት ሃይሎች ጥርስ ውስጥ የገባው አርቲስት ወደ ሃገር ሲመለስ ወከባ ሊፈጸምበት እንደሚችል ምስጢራዊ ምንጮች ይገልጻሉ። በአጭር ግዜ ውስጥ የአብዛኛውን ኢትይጵይዊ ትኩረት የሳበው የአርቲስት ብረሃኑ ተዘር ነጠላ ዜማ ኢትዮጵያ በመዲናይቱ አዲስ አበባና በተለያዩ ክፍለ ህገራት ምግቤቶች ቡና ቤቶችና የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ተሽክርካሪዎች ውስጥ ጭመር ሳይቀር በስፋት በመደመጥ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡
«ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ፤
አንድነት ይበጀናል ዛሬ ፤
መቼም አይሻረም ኢትዮጵያዊነቱ፤
መኖር ግን አይሻም ያለነጻነቱ ፤
እኮ ! ማነው ሰጪ ማነውስ ከልካይ፤
ሰው እንዳሻው ቢኖር በሃገሩ ላይ ፤
እያለ የሚያዜማው ድምጽዊ ብርሃኑ ክኢስት ለቀርበለት ጥያቄ አያሌ የሃገር ፍቀር ዘፈኖችን እንደዘፈነ ግልጾ ወገኔ በልስማኝ ሃገሬ የሚለውን ነጠላ ዜማ ከለቀቀ ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ ይህዝብን ተኩረት ማግኘቱ አግርሞትን እንደ ደጫረበት በመናገር ከአቅሙ በላይ የሆኑ ምስጋናዎች ከህዝብ ስለተቸረው በህዝብ ውስጥ ያለውን እውነታ በሙያው ማንጸባረቅ በመቻሉ መደሰቱን ገልጾ ክብርና አድናቆትን ለቸሩት ሀገር ውስጥና በውጭ ሃገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናውን አቅርቧል ። ድምጻው ብረሃኑ ተዘራ ዛሬ በአሜሪካ ቨርጅኒያ ግዛት ውስጥ አዲስ ያወጣውን ነጠላ ዜማ ሲዲ በነጻ እንደ ሚያድል ለመረዳት ተችሏል፡ ይህ በዚህ እንዳለ ከዝግጀቱ በኃላ አርቲስት ብረሃኑ ወደ ህገር ይመለስ አይመለስ እስካሁን በግልጽ የተባለ ነገር ባይኖረም ምናልባት ከመንግስት ጥቃት እራሱን ለመከላከልና በነጻነት ለመኖር አርቲስቱ የሌሎች የህዝብ ትግል አጋሮቹን ፈለግ ሊከተል ይችላል ተብሎ ይታመናል። Ethiopian Hagere Jed bewadi
Monday, February 23, 2015
ሐዋሳ ከተማ በእሣት ስትጋይ አደረች « EBC የቀድሞው ኢ ቲ ቪ በዚህ ዙሪያ ምንም ያለው ነገር የለም »
በሐዋሳ ለጊዜው የጉዳቱ መጠን ያልታወቀ የእሣት ቃጠሎ መድረሱን በአደጋው ያዘኑ ገለጹ፡፡ ከስፍራው እንደተሰማው ለሰኞ አጥቢያ የተነሳው ቃጠሎ ምናልባትም በከተማዋ ታሪክ ከፍተኛው ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡ አደጋው ሲደርስ የእሣት አደጋ “አገልግሎት” በነዋሪዎች ላይ ቅሬታ አስነስቷል፡፡
ለሰኞ አጥቢያ ሌሊት ላይ ነፍሳት ባረፉበት ወቅት የደረሰው የእሣት አደጋ መነሻው በትክክል ባይታወቅም ማምለጥ የሚቻልበት ባለመሆኑ አሟሟቱ የከፋ እንዳደረገው ለማወቅ ተችሏል፡፡ የተለያዩ ወገኖች በምስል ይፋ ያደረጉት ቃጠሎ እንደሚመለክተው የእሣቱ መጠን በቀላሉ የሚቆጣጠሩትና አደጋውን የሚቀንሱበት እንዳልነበረ ያስረዳል፡፡
በሐዋሳ ታሪክ ከፍተኛ ነው የተባለው ይህ ቃጠሎ በህይወት ላይ ያደረሰው አደጋ በትክክለኛው ቁጥሩ ባይገለጽም ከሥፍራው የደረሰን አጭር መልዕክት እንደሚያስረዳው ከሰባት የማያንሱ መሞታቸውን ከ23 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ቃጠሎ ደርሶባቸው የተጎዱ እንዳሉ፤ ሌሊት የተነሳ ቃጠሎ በመሆኑ መረጃ ለመሰብሰብ ቢያስቸግርም ደረሰ የተባለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ቀውስ ከዚህ የበለጠና ምናልባትም ኅሊናን የሚጎዳ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል፡፡
በዚሁ በደረሰን አጭር መልዕክት እሣቱን በቁጥጥር ሥር ለማዋል የከተማዋ የእሣት አደጋ ብርጌድ “እውን ሐዋሳ የእሣት አደጋ ብርጌድ አላት?” የሚያሰኝ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ለመባሉ ምክንያቱ በዝርዝር አልተገለጸም፡፡ ምናልባትም አደጋው ሌሊት ላይ መከሰቱ በሰው ህይወት ላይ የተመዘገበውን አኻዝ ከሚገመተው በላይ ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡
የዝግጅት ክፍላችን በደረሰው የህይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት የተሰማውን ልባዊ ሐዘን በዚህ አጋጣሚ ይገልጻል፡፡
********************************************
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
********************************************
ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)






