Monday, August 17, 2015

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ « ልጆቼን ለአደጋ እናቴን በመጨረሻ ዘመኗ ስንቅ አቀባይ ማደረግ አልሻም አለ ! »

የአረቡን ዓለም አስከፊ የስደት ገጽታ በማለዳ ወጉ የሚያስቃኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ የቱንም ያህል ኑሮው የስመረ ቢሆንም አንድም ቀን ነፍሱ በሃሴት ተሞልታ እንደማታውቅ በቀርብ የሚያውቁት ሁሉ ይናገራሉ በተለይ ከቁጥጠር ውጭ በወጣው ስደት ዜጎች ላይ የሚደርሰው ስቃይና በደል መቋጫ እንዲያገኝ ድምጽ አልባ ለሆኑ ግፉሃን ድምጽ በመሆን ጋዜጠኛው እያሰማን ያለው የብዕር ጩኃት  የቱንም ያህል የህዝብን  ቀልብ ስቦ ደረት ቢያስደቃም ድጊቱ  በህወሃት/.... ስረአት ባለስልጣናት ዘንድ ግን አልተወደደለትም።  ጅዳ ቆንስላ /ቤትና ሪያድ ኤንባሲ  ተሰግስገው በዜጎች ንግድ የከበሩ የስረአቱ ፖለቲካ ደላሎች ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ « የዲፕሎማቱን የስራ እንቅስቃሴ አሰናክሏል ህዝብን  በመንግስት ላይ አነሳስቷል » በሚል ተራ ውንጀላ ጣታቸውን ቀስረው  በሀወሃት መራሹ የኢ.... ድህንነት  ጥርስ ውስጥ ገብቶ ጋዜጠኛው በአይነ ቁራኛ መጠበቅ  ከጀመረ  እነሆ  አመታትን አስቆጠሯል።



ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ  ፈጽሞል በተባለው ነገር ተላልፎ እንዲሰጥ ህወሃቶች   ለሳውዲ መንግስት እስካሁን በይፋ ያቀረቡት ጥያቄ ባይኖረም አንደበታቸው በእውሸት  የተገነባ የስረዓቱ ካድሬዎች  ጋዜጠኛው  የስይፍ ሰላባ እንዲሆን ለሳውዲ ሸሪዓ  /ቤት የሃሰት መረጃ ለማቅረብ  ያልበጠሱት ቅጠል ያልፈነቀሉት ድንጋይ  እንደሌለ  ይነገራል። ነብዩ ሲራክ በአንድ ወቅት በሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች ታስሮ ከተፈታ ወዲህ  እስካሁን የጎላ ችግር ባይደርስብትም ለእረፍት ወደ ሃገር ሲያቀና  በቁጥጥር ስር ለማዋል  እቅድ እንዳለ ለጉዳዩ ቅረበት ያላቸው ምስጢራዊ ምንጮች አረጋግጠዋል። በማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ  በሚያጠነጥን  የማለዳ ወግ መረጃ ቅበላው እንደ ጥፋት ተቆጥሮ ክትትል የሚደረግበት ይህ ጋዜጠኛ በወዳጅ ዘመድ ናፍቆት እይተብስለስለ በዜጎች ስቃይና በደል ሰላም ያጣውን አይምሮ ለማሳረፍ   የሚወዳትን ሃገሩንና የተወለደበትን ቀዬ ለመርገጥ አለመታድሉን መረዳት ተችሏል። እያደረገ  ባለው ነገር ሁሉ ደስተኛ መሆኑንና ቅንጣት ያህል ለፈሪዎች ዱላ እንደ ማይበረከክ በዚህ ዙሪያ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ የስጠው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ፤ «ይህ ስጋት በአንዳንድ ወዳጅ ዘመዶቹ እንደተነገረውና ለግዜው ወደ ሃገር ከመሄድ መቆጠቡን ገልጾ በዓረቡ አለም በሚገኙ ዜጎቻን ላይ የሚፈፀመው ቅጥ ያጣ በደል እስኪያበቃ በግሉ እያቀረበ ባለው መርጃ የሚመጣውን ሁሉ በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን  አልሸሸገም ።ጋዜጠኛው  በማስከተል  « ምንም እንኳን የማቀርበው መረጃ ከማህበራዊ ጉዳዮች ያለፈ ባይሆንም በድርጅት አባላትና በተወካዮቻቸው ላይ የምሰነዝረው የሰላ ሂስ ለሁሉም ስጋት መሆኑ ግልጽ ነው፣ ታዲያ ሃገርችን ውስጥ ትክክለኛ ፍትህ የሚሰጥ ቢሆን ብከሰስ እንኳ እንደ ማሸንፋቸው ጥርጥር የለኝም  ዳሩ ግና 4 ዓመት ህጻን የደፈረን /ቤትና የፍትህ ስርአት ተማምኖ ወደ ሀገር መግባት ልጆቼን ለአደጋ እናቴን በመጨረሻ ዘመኗ ስንቅ አቀባይ ማደረጉን ስለማልሻ ከመሄድ መታቀብ ግድ ሆኖብኛል! » በማለት ሃገር ለመግባት  እምነት እንድሌለው ገልጾል። በተያያዘ ዜና  ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ሰሞኑን ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውን ወንድሙን መርዶ አልቅሶ እርሙን ማውጣት በማይችልበት ስደት አለም ከዘመድ አዝማድ ርቆ በሃዘን ላይ ሃዘንን ማስተናገዱን ለማወቅ ተችሏል Ethiopian Hagere Jed Bewad

No comments:

Post a Comment