በአዲስ አበባ በተለምዶ አንበሳ ግቢ ተብሎ በሚጠራው የአንበሶች ማቆያ ማእከል ውስጥ ዛሬ ከጠዋቱ 1:30 ላይ የሞት አደጋ ተከሰተ።
አደጋው የተከሰተው በዛሬው እለት ተረኛ ተንከባካቢ የነበሩት እና አቶ አበራ ሲሳይ የተባሉት የአንበሶቹ መጋቢ ፥ የአንበሶቹን ማዳሪያ እያጸዱ ባሉበት ወቅት ነው ከጥንቃቄ ጉድለት ባልተዘጋው በር የገባው ቀነኒሳ የተባለው አንበሳ ለህልፈተ ህይወት የዳረጋቸው።
የግለሰቡን ህይወት ለማትረፍ በወቅቱ በስራ ላይ የነበሩ የግቢው ሰራተኞች ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካ መቅረቱንም ለማወቅ ተችሏል።
RIP
የሟች አስከሬን ከመንከባከቢያ ስፍራው ወጥቶ ወደ ምኒሊክ ሆስፒታል ተወስዷል።
No comments:
Post a Comment