Friday, September 20, 2013

የኢትዮጵያ አየር ሃይል አራት አባላት ከዱ



“ ግንቦት 7 መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል"
የኢትዮጵያ አየር ሃይል አባላት ስርዓቱን ከድተው ግንቦት ሰባትን መቀላቀላቸው ተገለጸ። ሁለት የሻለቃ ማዕረግ ያላቸውና ሁለት ካፒቴን የአየር ሃይል አባልት ግንቦት ሰባትን መቀላቀላቸውን ይፋ ያደረገው ኢሳት በ "ሰበር ዜና" ነው። ማምሻውን ኢሳት ይፋ እንዳደረገው መክዳታቸውን ያረጋገጡት የአየር ሃይል አባላት በቅርቡ በተካሄደው የሶማሌ ጦርነትና በዳርፉር የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ተሰታፊ የነበሩ መሆናቸውን አመልክቷል።

ዜናውን " ሰበር ዜና" በማለት የዘገበው ኢሳት፣ ስርዓቱን የከዱትን የአየር ሃይል አባልት ስም እና እንዴት እንደከዱ አላብራራም። ይሁን እንጂ ኢሳት ዜናውን ከሙሉ ማብራሪያው ጋር እንደሚያቀርብ አስታውቋል። 

http://www.youtube.com/watch?v=y1ugxMwHvrE

No comments:

Post a Comment