Sunday, August 30, 2015

እራሱን ጽናት እያለ በሚጠራው ጀሌ ላይ በቀረበው ጽሁፍና ማስተባበያ ለቀረበበት «ዘረፋ» ግልጽ የሆነ ማስረጃ !‏‏

ድምጻችን ይሰማን ለሁለት በመስንጠቅ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመናድ ሀወሃት/.... እንቅልፍ አጥቶ ማደር የጀመረው ዛሬ እንዳልሆነ የታወቃል ።ህወሃት/.... የሃይማኖት ነጻነት ትግሉ በተጀመረ ማግስት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ዘብጥያ በማውረድ ለይስሙላ ያፀደቀውን ህገመንግስታዊ መብት በመተላለፍ የህዝቦችን መብት በጠመንጃ አፈሙዝ ጨፍልቆ ለጸሎት አደባባይ የወጣውን አዛውንት ሴት ወጣት ሳይል ያገኘውን ሁሉ በደም በጨቀዩ ልዩ ኮማንዶዎቹ በጥየት ረሽኗል ከሞት የተረፈውን በቆመጥ ደብድቦ በክሚዎን በማጋዝ ወዳልታወቀ ስፍራ ወስዶ አስሮ በማሰቃየት ላይ ይገኛል። ታዲያ ይህን ሁሉ ግፍና ስቆቃ የተቀበለው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ሰላማዊ ተቃውሞውን የበለጠ በማጠናከር ሳይገድል እየሞተ ለአምባ ገነኖች የአላማ ጽናቱን በተግባር አሳይቷል በማሳየትም ላይ ይገኛል። ይህ የህዘበ ሙስሊሙ አንድነትና ለሃይማኖቱ ነጻነት ያለው ቁርጠኝነት እንቀልፍ የነሳው ሀወሃት መራሹ የኢ.... ስረአት የበግ ልምድ ለብሶ ውሎና አድሩን ህዝበ ሙስሊሙ ጉያ ውስጥ በማድርግ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን ዑለማዎች የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች በኃይል አሊያም በግዜያዊ ጥቅም በማግባባት ለዚህ እርኩስ ሴጣናዊ ተግባሩ ማስፈፀሚያ ግበአት እንዲሆኑ ለማድረግ ሃገር ውስጥና በውጩ አለም እየዞረ  ያልፈነቀለው ድንጋይ ያልቦጠጠው ተራራ የለም። ለአብነት ያህል የፖለቲከኛውን ጁሃር መሃመድ አሳዛኝ ታሪክ ወደ ጎን ትተን በእስቷዝ ሃስን ታጁ ስም አዲስ አበባ ላይ ቀደም ሲል የተበተነውን ከፋፋይ የሆነ ባለ10 ገጽ ጽሁፍ ማስታወስ ከበቂም በላይ በቂ ማስረጃ ነው ።በእስቷዝ ሃስን ታጁ ጽሁፉ ላይ «ሰላማዊ ትግሉን የተቀላቀሉ ወጣቶች አላዋቂ፣ስሜተኛ፣ጃሂል አድርጎ ለማቅረብ ከተደረገው ጥረት ባሻገር የተቃውሞ አካሔድ ሌላ መንገድ ቢፈለግለት በሚል አሳፍሪ አቋም በተለይም የጁሙዓ ተቃውሞዎች መቋረጥ እንዳለባቸውና ኮሚቴዎቻችን ይቅርታ ጥይቀው እንዲወጡ » ህወሃት/.... ህዝበ ሙስሊሙን ተመስሎ በዑለማዎቻችን አንደበት ያሻውን መልዕክት በድፈረት ይስተላለፈበት ! ፈታኝ የትግል ዘመን የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው

ዛሬ ከዚህ አፍራሽ ተዕልኮ ባልተለየ የኢ.... ካድሬዎች አይናቸውን በጨው ታጥበው ሳውዲ አረቢያ ጅዳ ሪያድ ከተማ ውስጥ ብዙሃኑ ተመስለው ሊያሰሙን በሞከሩት ጩኋት በአካባቢው ያሉትን ስመጥር የሃይማኖት አባቶችና እሩቅ ያሉትን የህዝበ ሙስሊሙን ነጻ ሚዲያዎች ቀልብ አሳስተው ለዚህ መስሪ ተግባራቸው ግበአት በማድረግ በህዝበ ሙስሊሙ አንድንተ ላይ አደጋ ከመጋረጥ አልፈው በአቋራጭ የግል ኑሮቸውን ለማደርጀት ሲያደርጉ የነበረው ጥረት በሃገር ሽማግሌና በኃይማኖት አባቶች ውሻ በቀደድው ጅብ እንዳይገባ ሲነገራቸው የነበረውን ምከር አሻፈረን ብለው በህዝበ ሙስሊሙ ትግል ሽፋን ንጹሃን ለማደናገር ሞክረዋል። እንዚህ ወገኖች ጅዳ መካና መዲና ላይ እውነተኛ በሆኑ የትግሉ ባለቤቶች ሲተፉ እኔ ከሞትኩ ስርዶ አይበቀል እንዳለችው እንሰሳ ከፋፋዩን ዶሴያቸውን ሸንክፈው ሪያድ ከተማ ውስጥ በማድብት ጠንካራ ተብሎ በሚነገርለትን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት ለመፈታተን ያለሸረቡት ሴራ እንደሌለ ሰሞኑን በድምጽ ከተገኘ መረጃ ለማወቅ ተችሏል።በጣም የሚያሳዝነው በወቅቱ ለህዝብ  በቀረበው መረጃ የተደናገጡ ከጥቅማቸው ባሻገር የህዝበ ሙስሊሙ የትግል አንድነት ማየት የተሰናቸው እንዚህ ጀሌዎች ብዙሃኑን ተመስለው የሚያሰሙትን ጩህት ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ በማስተጋባት ከአይሌ እህቶቻችን ቦርሳ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ በትግል ሽፋን ስለሚሰበስቡት በመቶሺ የሚቆጠር ገንዘብ አግባብ አለመሆኑ በነዚህ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ቢመከሩም አባታዊ ምክርን ሰምቶ ከመቀበል ይልቅ እንዚህን አባቶች ከመኮነን አልፈው ያልሆነ ስም በመስጠት እየፈጸሙ ያለውን ነወረኛ ተግባር በማድበስበስና ለህዝብ የቀረበውን መረጃ ከህቅ የራቀ አሰመስለው በማናፈስ « ውሻ በበላበት አፉ » እንዲሉ የህዝብ ሚዲያዎችን እስከ መዝለፍ ርቀው የሄዱበት ተግባራቸው ሰሞኑን ሪያድ በሚኖሩ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽምግሌዎች እርቃኑን መቅረት መቻሉ የጀሌዎቹን ማንነት ከመቸውም ግዜ በላይ ግልጽ አድርጎታል ዛሬ እነዚህ ጀሌዎች በፈጸሙት ነገር ሁሉ ተፀጽተው የበደሉትን ሁሉ በአደባባይ ይቀርታ በመጠየቅ ከጥፋታቸው ለመመለስ ቃል መግባታቸውን በደረሰን የድምጽ መረጃ አረጋግጠናል !
ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ

Thursday, August 20, 2015

ሰበር ዜና፡- በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በነፃ እንዲሰናበቱ ተወሰነ

ፌዴራል ዓቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶባቸው በእስር ላይ የቆዩት የቀድሞ የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)፣ የሰማያዊና የአረና ፓርቲ አመራሮችና ሁለት ተከሳሾች በነፃ እንዲሰናበቱ፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሐሴ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ወሰነ፡፡
የአንድነት ፓርቲ የቀድሞ አመራሮች አቶ ሀብታሙ አያሌውና አቶ ዳንኤል ሺበሺ፣ የአረና ፓርቲ አመራር አቶ አብርሃ ደስታ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አቶ የሺዋስ አሰፋና ሌሎች ሁለት ተጠርጣሪዎች በነፃ የተሰናበቱት፣ የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ከጥርጣሬ ባለፈ ተሳትፎአቸውን ማረጋገጥ ባለመቻሉ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አስታውቋል፡፡
በውሳኔው መሠረት አቶ ሀብታሙ የሚጠየቁበት ወይም ሌላ የሚፈለጉበት ጉዳይ ከሌለ በዛሬው ዕለት እንዲፈቱ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ አቶ አብርሃ ደስታ፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺና አቶ የሺዋስ አሰፋ ከዚህ ቀደም ችሎት በመድፈር የተፈረደባቸውን ቅጣት እንዳጠናቀቁ እንዲፈቱ ወስኗል፡፡ ምንጭ ሳተናው ድህረገጽ 

እስራኤል ለስለላ የላከችው ዶልፊን በሃማስ ቁጥጥር ስር ውሏል

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 14 ፣ 2007 ( ኤፍ ቢ ሲ) እስራኤል ከመካከለኛው ምስራቅ ሃገራት ጋር ያላት ግንኙነት የሻከረ እና መተማመን የጎደለው ነው።
በተለይ ደግሞ ከፍልስጤማውያን ጋር ዘወትር አተካሮ በመፍጠር ለበርካታ አመታት በግጭት የታጀበ ግንኙነታቸውን ዛሬም ድረስ ይዘውት ቆይተዋል።
ታዲያ የእስራኤል መንግስትም "ግዛቴንና ህዝቦቼን" ከጥቃት ለመከላከል በሚል ዘወትር የፍልስጤማውያንን እንቅስቃሴ በተለያዩ መንገዶች ይከታተላል።
ከሰሞኑ በጋዛ ሰርጥ በፍስጤማውያን የባህር ሃይል ኮማንዶዎች የተገኘውና በቁጥጥር ስር የዋለው ዶልፊን ግን ግርምትን ፈጥሯል።
ዶልፊኑ በባህር ክልሉ የፎቶ ካሜራ ተገጥሞለት በአካባቢው የእስራኤልን ባላንጣዎች እንቅስቃሴ ሲቀርጽና ሲሰልል ነበር ነው የተባለው።
ዶልፊኑ ባልተለመደ እና ቦታን ለማመልከት በሚመስል ሁኔታ በቦታው ላይ ብቅ ጥልቅ በማለት ያደረገው እንቅስቃሴ የባህር ላይ ቃኝዎችን ትኩረት በመሳቡ በቁጥጥር ስር መዋሉም ነው የተዘገበው።
ሰላዩ ዶልፊን በስፍራው ያለውን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ በተገጠሙለት ካሜራዎች እና የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በመቅዳት ለእስራኤሉ የስለላ ተቋም ሞሳድ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ይሰራ ነበርም ተብሏል።
ዋነኛ ተልዕኮውም በአካባቢው የሚካሄደውን የባህር ሃይል ስልጠና እና ተያያዥ ጉዳዮችን ቀርጾ መላክ እና መልዕክቶችን ማስተላለፍ እንደነበር ነው ከፍልስጤማውያኑ ጋዜጣ ል ቁድስ የተገኘ መረጃ የሚያሳየው።
የፍልስጤሙን ታጣቂ ቡድን ሃማስን ሰሞነኛ እንቅስቃሴ በመቅዳት እስራኤል በቡድኑ አንድ ክንፍ ላይ ልትወስድ ላሰበችው እርምጃ የሚያግዝ መረጃ ማቅረብን ታሳቢ አድርጎ የተካሄደ የስለላ ተግባር ነበር ተብሏል።
ሞሳድ በእንስሳት በሚደረጉ ስለላዎች በተደጋጋሚ ይጠረጠራል፤ ከዚህ ቀደም በግብጽ፣ በኢራን ፣ በቱርክ፣ በሱዳን እና በሌሎችም ሃገራት መሰል ስለላዎችን አካሂዷል በሚል ይታማል።
ድርጅቱ ለእስራኤል ደህንነት ስጋቶችን ለመቀነስ በሚል በእርግቦች፣ በሽኮኮ፣ በሻርኮች እና ሽመላ በሚባሉ የአዕዋፍ ዝርያዎች ሃገራት ላይ በተላያዩ ጊዜያት ስለላውን አካሂዷል።
ምንጭ፤ www.thedailybeast.com

ተተርጉሞ የተጫነው፤ በምናለ ብርሃኑ


(ርዕዮት አለሙ) አክራሪና አሸባሪዉ ኢህአዴግ ወይስ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት?

ልጆች ሆነንእከሌ (እከሊት) አክራሪ ነዉ (ናት) ” ሲባል ይሰጠን የነበረዉ ትርጉም እና አሁን አክራሪነት እየሰጠ ያለዉ ትርጉም ለየቅል ይመስለኛል፡፡ ያኔ አንድ ሰዉ በአክራሪነት ሲጠራ ከብዙሃኑ በተለይ ሁኔታ ሃይማኖቱን ወይም የሚያምንበትን አንዳች ነገር አጥብቆ መያዙን እና በሚያምንበት ነገር ላይ የማይደራደር መሆኑን ከማሳየት አልፎ የአሁኑን አይነት አሉታዊ ትርጉም አይሰጥም ነበር፡፡ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናትና ምርምር ማዕከል የተዘጋጀዉ የአማርኛ መዝገበ ቃላትም ያኔ ቃሉን እረዳበት ከነበረዉ ትርጉም ብዙም የራቀ ፍቺ አያቀርብም፡፡ 1993 . የካቲት ወር የተዘጋጀዉ ይኸዉ መዝገበ ቃላት አክራሪ ለሚለዉ ቃል የሚሰጠዉ ፍቺበሚከተለዉ እምነትና አስተሳሰብ ዉስጥ ፍፁምነት ሊኖር ይገባል ብሎ የሚያምንና የቆየዉን እምነትና አስተሳሰብ ከዘመናዊዉ ሁኔታ ጋር ማስተካከል እና ማጣጣም የማይፈልግ አጥባዊ (ሰዉ)” የሚል ነዉ፡፡ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ግን የቃሉ ፍቺ እየተቀየረ መጥቶ አሁን ያለዉን እጅግ አሉታዊ የሆነ ገፅታ ይዟል፡፡
የህግ ባለሙያዉ ተማም አባቡልጉ የካቲት3 2007. በወጣዉ ኢትዮምህዳር ጋዜጣ ላይአክራሪ ሰዎች እነማን ናቸው?” በሚል ርዕስ ባስነበቡት ፅሁፋቸዉየራሱን ዘር፣ ሃይማኖትና ቡድን ጥቅም ሌሎችን በመጉዳት ጭምር ለማስጠበቅ የሚንቀሳቀስ ወይም ከማስጠበቅ የማይመለስሰዉ እንደሆነ አክራሪ የሚባለዉ ገልፀዋል፡፡
የዚህ ፅሑፍ አላማ አሁን እየተግባባንበት ካለዉ ፍቺ አንፃርየአክራሪነትና የአሸባሪነት ባህሪ የሚንፀባረቀዉ በቅርቡ በተፈረደባቸዉ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ወይስ በከሳሹ መንግስት?” የሚላዉን ጉዳይ መፈተሽ ይሆናል፡፡
የኢህአዴግ የምናብ ቀበሮዎች
ኢህአዴግ እኔን ጨምሮ በርካታ ከሽብር ጋር ሊገናኝ የማይችል ማንነት ያለንን ዜጎች የአሸባሪነት ስም ሰጥቶናል፡፡ ይሄን በአሰብኩ ቁጥር ሁሌም ወደ አእምሮዬ የሚመጣዉ ብዙዎቻችሁ የምታዉቁት የዉሸታሙ እረኛ ታሪክ ነዉ፡፡ እንደምታስታዉሱት ሌሎችን በማታለል የሚዝናናዉ ዉሸታም እረኛ ቀበሮ መጥቶ በጎቹን እየበላበት እንደሆነ አድርጎ የድረሱልኝ ጥሪ በጩኸት በማቅረብ አላፊ መንገደኞችን ይሰበስባል፡፡ መንገደኞቹ ለእርዳታ ሲመጡ ታዲያ ቀበሮዉ በገሀዱ አለም ያለ ሳይሆን የእረኛዉ የምናብ ዉጤት መሆኑን ይረዱና እየተበሳጩ ወደየመንገዳቸዉ ይመለሳሉ፡፡ ኢህአዴግምአክራሪ ደረሰብን አሸባሪ መጣብንእያለ አደንቋሪ ጩኸቱን ለቁጥር በሚያዳግት መልኩ በተደጋጋሚ አሰምቷል፡፡ ጩኸቱን ሰምተዉ ስለሁኔታዉ ለማወቅ የሞከሩትን ሁሉ ግን የጠበቃቸዉ እንደዉሸታሙ እረኛ የምናብ ቀበሮ ሁሉ የዉሸት አክራሪና አሸባሪ ነዉ፡፡የምናብ ቀበሮ የሚበላዉ በግ እንደሌለ ሁሉ የምናብ አክራሪና አሸባሪም የሚያወድመዉ ንብረትም ሆነ የሚያጠፋዉ የሰዉ ህይወት የለም፡፡ እስክንድር ነጋና ሌሎች በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና ጦማሪያን አሸባሪ ሊያሰኝ የሚችል ምን አደረጉ? አንዷለም አራጌ እና ሌሎች የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ምን አጠፉ? ምንም!
የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትም እንደከዚህ ቀደሞቹ ሁሉ የኢህአዴግ የምናብ ቀበሮዎች ናቸዉ፡፡ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ይሁን ሌሎቹ የኮሚቴ አባላት አክራሪም ሆነ አሸባሪ ለመባል የሚያበቃ ያደረጉት ነገር የለም፡፡ ይልቁንም መንግስት በሃይማኖታቸዉ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ እምነቱን ለመበረዝና ለመከለስ የሚያደርገዉን ጥረት እንዲያቆም እጅግ በሰለጠነና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሲጠይቁ የነበሩ በህዝበ ሙስሊሙ የተመረጡ የአላማ ሰዎች ናቸዉ፡፡ ለመረጣቸዉ ህዝብና ለሃይማኖታቸዉ ታማኝ ሆነዉ መገኘታቸዉ ግን ለኢህአዴግ ስላልተስማማዉ እንዲያስራቸዉ ብሎም ለመስማት የሚከብድ አሰቃቂ በደሎችን እንዲፈፅምባቸዉ ምክንያት ሆነ፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በስህተት ያሳየዉ የአንደኛ ተከሳሽ የአቡበከር አህመድ እጆች በካቴና ታስረዉ ሲመረመር የሚያሳየዉ አሳዛኝ ምስል የተመለከተዉን ሁሉ ልብ የሚያደማ ነበር፡፡ በሁኔታዉ ልባቸዉ የተነካ ሙስሊም ወገኖቻችንን
አቡኪ ወንድሜ የእስልምና ብርሃን 
ሁኔታህን አይተን ሁላችን አነባን
ብለዉ እንዲያዜሙ ያስገደደ ነበር፡፡
ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ኮሚቴዎቹ ከታሰሩበት አሰቃቂ ቦታም ሆነዉ ሰላማዊ የሆነዉ ጥያቄ መንግስት በሚወስዳቸዉ ያልተገቡ የአፈና ምላሾች ሳቢያ ሌላ መልክ እንዳይዝ በጎ መልዕክት ከማስተላለፍ ወደኋላ አላሉም፡፡ ኮሚቴዎቹ በዚህ መጠን ከህዝበ ሙስሊሙ አልፈዉ ለሀገር ሰላም ቢጨነቁም ዉሸታሙ እረኛ ግን የተለመዱ የሀሰት ዶክመንተሪዎችን በማቅረብ ስማቸዉን ለማጥፋት ሲታትር ነበር፡፡ ይብስ ብሎ ደግሞ በቅርቡ ከሰባት እስከ ሃያሁለት አመታት የሚደርስ ፍርድ ቀኝ እጁ በሆነዉ ፍርድቤት በኩል አስተላለፈባቸዉ፡፡ ይህ አስገራሚ ፍርድ በሚተላለፍበት ወቅት ግን ኮሚቴዎቹ በጀግንነት ቆመዉ እንባ የሚራጩ ዘመድ ወዳጆቻቸዉን ሲያፅናኑ እንደነበር ችሎቱን የተከታተሉ ሚዲያዎች ዘግበዋል፡፡ አስቀድመዉ በነበሩ ችሎቶች ላይእዚህ የቆምነዉ ፍትህ እናገኛለን በሚል እምነት አይደለም፡፡ ለታሪክ ምስክር ለመሆን እንጂበማለት እንደገለፁት ከካንጋሮ ፍርድቤት የሚጠብቁት ፍትህ ባለመኖሩ የተሰጣቸዉ ፍርድ እንደማያስደነግጣቸዉ ግልፅ ነዉ፡፡ የኮሚቴዎቹ አባባል ኔልሰን ማንዴላ ያልተገባ ስም ተሰጥቷቸዉ ለፍርድ በቀረቡበት ወቅት የተናገሩትንና የግል የህይወት ታሪካቸዉን ባሳተሙበት መፅሐፍ ዉስጥ የሚገኘዉን የሚከተለዉን ሃሳብ ያስታዉሰኛል፡፡
ይህ የፍትህ ስርዐት ጥፋተኛዉ ንፁሑን በህግ ፊት እንዲያቀርበዉ ጉልበት የሚሰጠዉ በመሆኑ ትልቅ ስጋት ዉስጥ ይከተኛል፡፡ የፍትህ ስርዐቱ ልክ ያልሆነዉ ልክ የሆነዉን እንዲከስና ማስቀጣት እንዲችል የሚያደርግ ነዉ……. በመሆኑም ፍትሃዊና ተገቢ ፍርድ አላገኘም፡፡
ያኔ ኔልሰን ማንዴላ አስቀድመዉ እንደተናገሩት የአፓርታይድ መሪዎቹ የሚያሽከረክሩት ፍርድቤት ያልተገባ ፍርድና የወንጀለኛነት ስም ሰጥቷቸዋል፡፡ ዛሬም ኮሚቴዎቹ ኢህአዴግ በሚያሽከረክረዉ ፍርድቤት አማካኝነት ከማንዴላ ጋር ተቀራራቢ የሆነ ፍርድና ተመሳሳይ የሆነ ስያሜ አግኝተዋል፡፡አሸባሪነትዛሬም እንደትላንቱ ሁሉ አምባገነኖች የሚቃወሟቸዉን ንፁሃን የሚመቱበት ዱላ መሆኑን ቀጥሏል፡፡
አክራሪዉ ኢህአዴግ ነዉ!
የኢህአዴግ ባላስልጣናት አክራሪነት ከሱ ሌላ የሆነ ቡድን ወይም ማንነት እንዲኖር የማይፈቅድ እንደሆነናለልማታችን እና ለዲሞክራሲ ግንባታችንዋነኛ ጠር መሆኑን ሁሌም እንደነገሩን ነው፡፡ ከአባባሉ ተነስተን አክራሪ ስንፈልግ ዉለን ብናድር የምናገኘዉ ትልቁ አክራሪ ግን እራሱ ኢህአዴግ ሆኖ ይገኛል፡፡
ከአብዮታዊ ዲሞክራሲ ሌላ ርዕዮተ አለም በሀገራችን እንዳይኖር አይደለም እንዴ የተለየ መስመር የሚከተሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን የሚያፈርሰው? በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጦችና መፅሔቶች የመዘጋታቸዉና ጋዜጠኞቹ የመታሰርና የመሰዳደቸዉ ምክንያትስ እርሱ ከሚቆጣጠራቸዉ ዉጪ የሆኑ ሚዲያዎች እንዳይኖሩ ከመፈለግ የመጣ አይደለምን? የደሃ ሀገራችንን አንጡራ ሃብት እንደ ሃኪንግ ቲም ላሉ የጣልያን ተቋማትን የሚከሰክሰዉ ሁሉን ለመቆጣጠር ባለዉ ክፉ አባዜ ምክንያት መሆኑን መች አጣነዉ? የትምህርትም ሆነ የስራ እድል የኢህአዲግ አባል ካልተሆነ ለማግኘት የጠበበዉ ከኢህአዲግ አክራሪ ባህሪይ የመነጨ መሆኑ ግልፅ ነዉ፡፡ ሌሎች ብዙ የኢህአዲግ አክራሪነት መገለጫዎችን መዘርዘር ይቻላል፡፡ ለማጠቃለል ያህል አንዱን ልጥቀስ
በሜታ ሮቢ ወረዳ አስተዳደር የወራቦ ቀበሌ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑ አስራ አራት ግለሰቦች2007. በተካሄደዉ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ሲደግፉ ነበርበሚል አስገራሚ ምክንያት የተነሳ ማናኛዉንም የህግና የአስተዳደር አገልግሎቾችን ማግኘት እንዳይችሉ በቀበሌ አስተዳደሩ ለሚመለከተዉ ሁሉ ስማቸዉ ተዘርዝሮ ተፅፏል፡፡ ባለፈዉ ረቡዕ ከሰንደቅ ጋዜጣ ጋር ቆይታ ያደረጉት የመድረክ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጥላሁን እንደሻዉ እንዚህን ግለሰቦች ጨምሮ በርካታ የፓርቲዉ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ዘርፈ ብዙ ችግሮች እየደረሱ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የችግሩን ምክንያት ሲያስረዱምእነዚህ ታጋዮቻችን ህዝቡ መድረክን እንዲመርጥ ምን ሲሰሩ እንደነበር ስለሚያዉቅ አሁን እየወሰደ ያላዉ የበቀል እርምጃ ነዉብላዋል፡፡ በዚህ መጠን ከእርሱ ሌላ እንዳይኖር የሚፈልገዉና ኖሮ ሲገኝ ደግሞ ተሸብሮ ህዝቡን የሚያሸብረዉ ኢህአዲግ የማይገባቸዉን ሰዎች አሸባሪ እና አክራሪ ሲል አፉን ያዝ እንኳን አያደርገዉም፡፡ ገዢዉ ፓርቲ ያልተገባ ስም የሰጣቸዉ ሙስሊም እህቶቻችን ቢቸግራቸዉ እንዲህ በማለት ሊያርሙት ሞክረዉ ነበር
የሂጃቡ ነገር ከላይ ከፈጣሪ
የኒቃቡስ ነገር ከላይ ከፈጣሪ
ልባል አይገባም አክራሪ አሸባሪ
የኮሚቴዎቹ እስርና ፍርድ ምን ሊያስከትል ያችላል?
ገዢዉ ፓርቲ ጥያቄዎችም ሆነ ተቃዉሞዎች ሲነሱበት ራሱን ከመመርመር ይልቅ በድፍረት ድምፃቸዉን ያሰሙ አካላትን ማሰርን ይመርጣል፡፡ በዚህም እፎይታን የሚያገኝ ይመስለዋል፡፡የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትም ላይ ያደረገዉ ይህንን ነዉ፡፡ ነገር ግን ይሄ አካሄዱ የተመኘዉን እፎይታ ሊያስገኝለት ይቅርና ለሀገር የሚተርፍ ችግር ሊያመጣ እንደሚችል ጉዳዩን በጥልቀት የተከታተሉ ወገኖች ይገልፃሉ፡፡
ከነዚህ ወገኖችአንዱ የሆነው ጋዜጠኛ ሀይለመስቀል በሸዋምየለህ በቅርቡ ገበያ ላይ በዋለዉናየሀይለማርያም እዳ እና የሙስሊሙ ትግልበሚል ርዕስ ባዘጋጀዉ መፅሐፉ ዉስጥ በርካታ በጉዳዩ ላይ የተሰሩ ጥናቶችን ዋቢ በማድረግ እንደገለፀዉ ኢህአዲግ የሙስሊሙን ጥያቄ ለማፈን እየተጓዘበት ያለዉ መንገድ እጅግ አፍራሽ ዉጤት ይኖረዋል፡፡ ከአፍራሽ ዉጤቶቹ አንዱ ደግሞኢህአዴግ እየተከላከልኩት ነዉ የሚለዉ ፅንፈኝነት መፈጠርሊሆን እንደሚችል መፅሐፉ ያስረዳል፡፡ / አባድር ኢብራሂም ADDIS STANDARD በተሰኘ ወርሃዊ መፅሔት የዚህ ወር እትም The unfair trial of Muslim Leaders ; why it undermines counter terrorism in Ethiopia በሚል ርዕስ ባቀረቡት ፅሁፋቸዉ ዉስጥም ተመሳሳይ ስጋት እናገኛለን፡፡ / አባድር ኮሚቴዎቹ ላይ የተሰጠዉን የጥፋተኝነት ዉሳኔ መነሻ በማድረግ ባዘጋጁት በዚህ ፅሁፋቸዉ የተላለፈዉ ውሳኔ የፍትህን መክሸፍ ከማሳየቱ በላይ እነዚህ የሲቪል ማህበረሰብ መሪዎች ወደፊት ከሚመጣ የሽብር አደጋ የመስዕዋት ጠቦት ሆነዉ ሊያድኑን አለመቻላቸዉ እንዳሳዘናቸዉ ገልፀዋል፡፡ ዶክተሩ ኮሚቴዎቹ ላይ የተላላፈዉ ውሳኔ እንደዉም የሽብር ስጋቱን እንደሚጨምር አምስት መከራከሪያዎችን በማቅረብ ይሞግታሉ፡፡ እኚሁ የህግ ምሁር ከመከራከሪያዎቹ በአንዱ እንዳብራሩትኮሚቴዎቹ በህዝበ ሙስሊሙ ዘንድ እጅግ ተሰሚነት ያላቸዉ መሪዎች እንደመሆናቸዉና በፀረ ሽብር ትግሉ አገላለፅለዘብተኛየሚባሉ ስለሆኑ አክራሪነትን ለመከላከል ግንባር ቀደም አጋር ሊሆኑ የሚችሉ ነበሩ፡፡ ኢህአዲግ እነዚህን ትልቅ አጋር ሊሆኑ የሚችሉ መሪዎችን በመክሰስና በማሰር እዋጋቸዋለሁ የሚለዉን አክራሪ ድርጅቶች የቤት ስራ እንደሰራላቸዉ ዶክተሩ በፅሁፋቸዉ ይገልፃሉ፡፡ ምክንያቱን የሚያብራሩትም እንደነ አቡበከር አይነቶቹ ቅሬታዎችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍረታት የሚታትሩ ሙስሊም መሪዎች ባላቸዉ ተቀባይነት ፅንፈኛ ድርጅቶች ቅቡልነት እንዲያጡ በማድረግና የድርጅቶቹን ትምህርቶች ሊገዳደር በሚችል የሃይማኖቱ ትምህርት በመምታት እስልምናን ሽፋን አድርጎ የሚመጣን የሽበር አደጋ ለመከላከል የነበራቸዉን አቅም በመጥቀስ ነዉ፡፡ ዶክተሩ በሌላኛዉ መከራከሪያቸዉ ደግሞ በሰላማዊ መንገድ ለመወያየት ጥያቄያቸዉን ለማቅረብ በሞከሩ ሙስሊሞች ላይ መንግስት እየፈፀማቸዉ ባሉ በደሎች ሳቢያ አመፅአልባ ትግሉጥያቄ ዉስጥ መግባቱና ሰዎች ወደሌላ አማራጭ ለማየት መገደዳቸዉ እንደማይቀር ያስገነዝባሉ፡፡
ጋዜጠኛ ሀይለመስቀልም ሆነ / አባድር ይሄ ትልቅ ሀገራዊ ችግር የሚያመጣዉ ኪሳራ አሳስቧቸዉ መፍትሄ ፍለጋ ላይ ታች ቢሉም ኢህአዲግ ግን አሁንም ከመጥፎ ድርጊቱ አልታቀበም፡፡ በትላንትናዉ ዕለት እራሱ ኮሚቴዎቹን ለማስፈታት ተንቀሳቅሳችኋል ያላቸዉ ሃያ የዕምነቱ ተከታዮች ላይ ክስ እንደመሰረተ በማህበራዊ ድረገፆች እያነበብን ነዉ፡፡ እስርቤት በነበርኩበት ወቅትም የአዳማ ሙስሊምተማሪዎችን ጨምሮ በተመሳሳይ ክስ በርካታ ሙስሊሞች ይታሰሩ እንደነበር አዉቃለሁ፡፡
ገዢዉ ፓርቲ ስህተቱን በስህተት ለማረም የሚያደርገዉ እንዲህ አይነቱ አሳፋሪ እንቅስቃሴ መገታት ይኖርበታል፡፡ አለበለዚያ በሀሰት ቀበሮ እየተባሉ ፍዳቸዉን የሚያዩ ንፁሃን ወገኖቻችን ጉዳይ አሳስቦን በአንድነት መቆምና ገዢዉን ፓርቲ መታገል ካቃተን ነገ እዉነተኛ ቀበሮዎች ቢመጡ የምንመክትብት ጉልበት አይኖረንም፡፡ ለአሁኑ ግን ለእኔ የታየኝ አደገኛ ቀበሮ ኢህአዴግ ራሱ ነዉ፡፡