Monday, March 31, 2014

የአድባራት አስተዳዳሪዎች ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት መፈረጃቸው ሊቃነ ጳጳሳቱን አስቆጣ

ቅሬታቸውን ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች ገልጸዋል:




የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታይ በኾኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የቤተ ክርስቲያኒቱን እምነትና ሥርዐት እንዲማሩ፣ ዕውቀታቸውንና ገንዘባቸውን በማቀናጀት ሞያዊ ድጋፍ እንዲያበረክቱ በማስተባበር ላይ የሚገኘውን ማኅበረ ቅዱሳንን በአሸባሪነት በመፈረጅ፣ በቅዱስ ሲኖዶስ አማካይነት ጠቅላላ ሀብቱና ንብረቱ የሚታገድበት ውሳኔ እንዲተላለፍ በመንግሥትም በኩል እርምትና ርምጃ እንዲወሰድበት የአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የአድባራት አስተዳዳሪዎች መግለጫ አውጥተውበታል በተባለው ስብሰባ ጉዳይ ሁለት የቅ/ሲኖዶስ አባላት ለከፍተኛ የመንግሥት ሓላፊዎች ቅሬታቸውን ማሰማታቸው ተገለጸ፡፡

የቅ/ሲኖዶሱን ዋና ጸሐፊ ብፁዕ አቡነ ሉቃስንና በአዲስ አበባ ሀ/ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና የጅማ ሀ/ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስን በስም የጠቀሱት የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ምንጮች፣ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን ያቀረቡት ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር ሓላፊዎች እንደኾነ ቢገልጹም የሓላፊዎቹን ስም ከማሳወቅ ተቆጥበዋል።

ቤተ ክርስቲያኒቱ በፀረ ሙስናና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ ከመንግሥት ጋራ የተጠናከረ ሥራ ለመሥራት በቅ/ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ መወሰኗን ሊቃነ ጳጳሳቱ አስታውሰው፣ በዚህም መሠረት ለሙስናና ብክነት የተጋለጡ አሠራሮችን ለማረምና ለማስተካከል ጥረት እያደረገች ቢኾንም ባለሥልጣናቱ ከማን ጋር መሥራት እንዳለባቸው በትክክል አለመለየታቸውንና ግንኙነቱም ሙሰኞችን በአይዟችኹ ባይነት የሚያበረታታ እንደኾነ መናገራቸው ተጠቅሷል፡፡

ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅሬታቸውን በዚህ መልኩ ለባለሥልጣናቱ ለማቅረብ ያስገደዳቸው የአድባራት አስተዳዳሪዎቹ፣ ‹‹ከመንበረ ፓትርያርክ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንንና የሰንበት ት/ቤት ወጣቶችን ለአድማ ያነሣሣል፤ በሀገርና በቤተ ክርስቲያን ላይ ሁከትና ሽብር እንዲፈጠርና ሰላም እንዲደፈርስ ያደርጋል›› ባሉት በማኅበረ ቅዱሳን ላይ የሚወሰደው አስተዳደራዊ ርምጃ በፀረ ሽብር ሕጉ መሠረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁበት መግለጫቸው ነው፡፡

የመንግሥት የተለመደ እገዛ እንዳላቸው በአጽንዖት የጠቀሱት አስተዳዳሪዎቹ በዚሁ መግለጫቸው፣ መንግሥት በፀረ ሽብር ሕጉ ታሳቢነት ገለልተኛ ኦዲተር መድቦ በማኅበሩ ላይ የሀብትና ንብረት ቁጥጥር የማካሔድ ድጋፉ እንዳይለያቸው ያስተላለፉት ጥሪ በሌላቸው ሕጋዊነትና ውክልና የቀረበ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በራስዋ መንገድ ማከናወን በሚገባት ተግባር ላይ አላስፈላጊ ጣልቃ ገብነትን የሚጋብዝና ለውጭ ተጽዕኖ አሳልፎ የሚሰጥ እንደኾነ ተመልክቷል፡፡

በመንበረ ፓትርያርኩ ከተገኙት የመንግሥት ሓላፊዎች ጋራ ባለፈው ሳምንት መጨረሻ እንደተካሔደ በተገለጸው የኹለትዮሽ ውይይት፣ ማኅበረ ቅዱሳንን በመቃወም ሰበብ የወጣው የአስተዳዳሪዎቹ መግለጫ ዋነኛ ዓላማ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ ወስና የምታካሒደውን የአደረጃጀትና የአሠራር ለውጥ ሒደት መጋፋት ነው ተብሏል፡፡ መላውን የሀገረ ስብከቱን አድባራት አገልጋዮች ለመወከል የማይበቁ ጥቂት ግለሰቦችን በመያዝ ይደረጋል የተባለው ይኸው እንቅስቃሴም ‹‹የት እንደሚያደርስ እናየዋለን›› የሚሉ ንግግሮች ጭምር ከሊቃነ ጳጳሳቱ የተሰሙበት እንደነበር ምንጮቹ አስታውቀዋል፤ ጉዳዩም በመጪው ግንቦት በሚካሔደው የቅ/ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዓቢይ መነጋገርያ መኾኑ እንደማይቀር ተጠቁሟል፡፡

ከሀገረ ስብከቱ አድባራት የተውጣጡ ናቸው የተባሉ አስተዳዳሪዎች ያደረጉት ስብሰባ፣ አስተባባሪዎቹ ከፓትርያርኩ ተሰጥቶናል ከሚሉት ፈቃድ በቀር በሀገረ ስብከቱ የፓትርያርኩ ረዳት ሊቀ ጳጳስና በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት ዘንድ በይፋ የታወቀና የተፈቀደ እንዳልነበረ ምንጮቹ ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል፡፡

ማኅበረ ቅዱሳንን በሁከትና ሽብር ለሚከሱ በቂ ሕጋዊነትና ውክልና የላቸውም ለተባሉ አካላት ፓትርያርኩ የሰጡትን የስብሰባ ፈቃድ፣ በቅርቡ ማኀበሩ አገር አቀፍ የአብነት መምህራን የምክክር ጉባኤ እንዳያካሒድ ከተጣለበት እገዳ ጋር ያነፃፀሩ ታዛቢዎች፣ ሁኔታው የፓትርያርኩን ርምጃዎች መርሕ አልባነት የሚያጋልጥ ነው ይላሉ፡፡ ከዚህም ባሻገር መተዳደርያ ደንብ ያለውና ግልጽ ተልእኮ ይዞ የሚንቀሳቀሰው ማኅበር፣ህልውናና አገልግሎት በግልጽ አስተዳደራዊ ጫና ውስጥ መግባቱን እንደሚያመለክት ታዛቢዎቹ ያምናሉ፡፡

ከመዋቅር፣ ከሀብትና ንብረት ቁጥጥር ጋራ በተያያዘ በማኅበሩ ላይ የሚቀርቡት ውንጀላዎች፣ በፀረ አክራሪነት ስም የሚናፈስበትን ፕሮፓጋንዳ በማጠናከር ፖሊቲካዊ ርምጃ እንዲወሰድበት ፍላጎት ያላቸውን አካላት ምኞት በጉልሕ እንደሚያሳይ አስረድተዋል፡፡ ማኅበሩ ሃይማኖቱን የሚጠብቅ፣ ቤተ ክርስቲያኑን የሚከባከብና ሀገሩን የሚወድ ብቁ ዜጋ ለማፍራት ያለውን ዓላማ የሚረዱ ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ምእመናንና የመንግሥት አካላትም የተቃዋሚዎቹን አቋምና መግለጫ በጥንቃቄ እንዲመለከቱትም አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል፣ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖናና ትውፊት ውጭ ነው በተባለ የሌላ እምነት አስተምህሮ የተነሳ በኮሌጁ ደቀ መዛሙርት መካከልና በደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት አባላት ውስጥ ያለው ግንኙነት ውጥረት ውስጥ እንደገባ እየተገለጸ ነው፡፡

ከኮሌጁ ውጭ ከሚገኙና በቅ/ሲኖዶስ ከተወገዙ ግለሰቦችና ቡድኖች ጋር የዓላማና የጥቅም ግንኙነት መሥርተዋል በተባሉ ጥቂት ደቀ መዛሙርት አማካይነት በኮሌጁ ውስጥ ከመንጸባረቅ አልፎ እንደ ሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ ነው የተባለው ይኸው አስተምህሮ፣ አስተዳደራዊ መፍትሔ እንዲበጅለት የደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት ጥር 5 ቀን 2006 ዓ.ም. ለኮሌጁ አስተዳደር ያቀረበው ጥያቄ እስከ አሁን ምላሽ አለማግኘቱ ውጥረቱን የበለጠ እንዳባባሰው ለአዲስ አድማስ የደረሰው መረጃ አመልክቷል፡፡

የአስተምህሮው ውዝግብ አፋጣኝ መፍትሔ አለማግኘቱ ከደቀ መዛሙርቱ አልፎ የምክር ቤት አባላትን ለሁለት እንደከፈለ ተገልጧል፡፡ ኮሌጁንና ደቀ መዛሙርቱን በቅንነትና በትጋት ለማገልገል በደቀ መዛሙርቱ ጠቅላላ ጉባኤ የተመረጠውና ከፍተኛ ሓላፊነት የተጣለበት የደቀ መዛሙርቱ ምክር ቤት፣ ‹‹ከልማቱ ጥፋቱ አመዝኗል›› ያሉት ጸሐፊውና አንድ የአመራር አባሉም ራሳቸውን ማግለላቸው ታውቋል፡፡

‹‹ከቤተ ክርስቲያኒቱ ቀኖናና ትውፊት ውጭ የኾነ የኑፋቄ ትምህርት ሲዘራ ድምፀ ተዓቅቦ ከማድረግ ባሻገር ችግር አለባቸው ከሚባሉት ደቀ መዛሙርት ጎን ተሰልፈው ኮሌጁንም ኾነ ሓላፊነት የሰጠንን ደቀ መዝሙር በቅንነት እንዳናገለግል የአንዳንድ መማክርት አባላት ተግባር አውኮናል›› ያሉት ሁለቱ አባላት፤ በዚህ ሳምንት ለኮሌጁ ዋና ዲን ጽ/ቤት በጻፉት ደብዳቤ፣ ምክር ቤቱ የችግሩ ተባባሪ በመኾኑ ከሓላፊነቱ ታግዶ ጉዳዩ እንዲጣራና እምነታቸውና ሥነ ምግባራቸው በተመሰከረላቸው ደቀ መዛሙርት እንዲተካ ጠይቀዋል፡፡

‹‹የቤተ ክርስቲያንን እንጀራ እየበሉ፣ በጀቷን አውጥታ እያስተማረቻቸው የሌላ እምነት የሚያራምዱ›› ያሏቸውን ወገኖች አጥብቀው እንደሚቃወሙ የገለጹ የደቀ መዛሙርት ተወካዮች በበኩላቸው፣ ኮሌጁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ፣ ቀኖናና ትውፊት ለመጠበቅና ለማስፋፋት የቆመ በመኾኑ አስተዳደሩ፣ በቃል፣ በድምፅና በጽሑፍ የሚቀርቡለትን ማስረጃዎች መርምሮ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጣቸው አሳስበዋል፡፡

Sunday, March 30, 2014

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ምሬታቸውን ለፓርላማ አሰሙ


‹በሕይወቴ ያለምቾት የሠራሁበት ወቅት አሁን ነው›› የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሀብትና ንብረትን ለመጠበቅና ለማስተዳደር ሲባል ‹‹ራሳችንንና ቤተሰቦቻችንን ችግር ውስጥ ከተናል›› በማለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ለፓርላማው ቋሚ ኮሚቴ ምሬታቸውን ገለጹ፡፡
የኦዲት አገልግሎት ኮርፖሬሽን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢና በሥሩ የሚገኙ ተቋማት ላይ ከ1999 እስከ 2002 ዓ.ም. ባለው ሒሳብ ላይ ያካሄደውን ኦዲትና የኦዲት ግኝቶችን አስመልክቶ ማብራርያ እንዲሰጡ፣ ባለፈው ዕለት በፓርላማው የመንግሥት ወጪ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ተጠርተው በተወቀሱበት ወቅት ነው አመራሮቹ ምሬታቸውን የገለጹት፡፡
በዋናው ግቢ ከልዩ ልዩ የተሰብሳቢ ሒሳብ መሰብሰብ የሚገባው 80.7 ሚሊዮን ብር ለረዥም ጊዜ መንከባለሉን፣ የሚሰበሰብ ከሆነም ከማን እንደሚሰበስብ አለመታወቁ፣ በዋናው ግቢ በግዥ ቅድመ ክፍያ ተከፍሎ የመጀመርያው ሳይወራረድና ሳይረጋገጥ ድጋሚ የግዥ ቅድሚያ ክፍያ በተለያዩ አቅራቢዎች ተመዝግቦ መገኘቱና ለረዥም ጊዜ ያልተወራረደ ሒሳብ በድምሩ 29.8 ሚሊዮን ብር መገኘቱ፣ በአንዳንድ ሒሳብ መደቦችና አካውንቶች ጭራሹኑ የባንክ ማስታወቂያ ሒሳብ ያልተሠራላቸው መኖራቸውና የሒሳቡ ትክክለኝነትን ማረጋገጥ አለመቻሉን የኦዲት ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡
ለአብነት ያህል ከተጠቀሱት ውስጥ በዋናው ግቢ በጥሬ ገንዘብ በባንክ ሒሳብ 28 ሚሊዮን ብር መኖሩ የጥሬ ገንዘብ ቆጠራና የባንክ ሒሳብ ባለመዘጋጀቱ ስለትክክለኛነቱ ማረጋገጥ አለመቻሉ፣ እንዲሁም በገንዘብ ያዥ እጅ 10.4 ሚሊዮን ብር በጉድለት መታየቱና ምክንያት ሊቀርብለት አለመቻሉ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ እሸቱ ተሾመና ሌሎች የቋሚ ኮሚቴው አባላት እንዲሁም የዋናው ኦዲተር መሥሪያ ቤት ባለሙያዎችና ዋና ኦዲተሩ አቶ ገመቹ ዱቢሶ የኦዲት ግኝቱን አስመልክቶ የተለያዩ ጥያቄዎችን አቅርበውላቸዋል፡፡
‹‹የአገሪቱን የፋይናንስ ሕግ፣ ደንብ፣ መመርያና አሠራር ለማክበር ችግራችሁ ምንድነው? ዩኒቨርሲቲው ሒሳቡን በወቅቱ ዘግቶ ኦዲት አለማድረጉና ችግሩን በወቅቱ አለማረሙ ምክንያቱ ምንድነው? ተጠያቂነቱን እንዴት ትዘነጋላችሁ›› በማለት ጠይቀዋቸዋል፡፡
በቀረቡት ጥያቄዎች ላይ የማጠቃለያ ምላሽ የሰጡት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ፣ ‹‹በዋናነት መታወቅ ያለበት ችግሩን የማስተካከል ኃላፊነት እንጂ እኛ ተጠያቂ አይደለንም፡፡ ምክንያቱም አሁን ያለው አመራር ከመምጣቱ በፊት የተከሰተ ችግር ነው፤›› በማለት ግንዛቤ እንዲወሰድ ጠይቀዋል፡፡ ‹‹ይህ ማለት ግን ኃላፊነቱ አይመለከተንም ማለት እንዳልሆነ፣ አሁን ያለው አመራር ሚና የተፈጠሩትን ችግሮች ማረም፣ ማስተካከልና በዛላቂነት ለመፍታት ሲስተም መፍጠር ነው፤›› ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ያሉትን ችግሮች ለመፍታት ከተጀመሩ የሲስተም ዝርጋታዎች አንዱ ሕግን በተከተለ መንገድ አሥራ አምስቱን የዩኒቨርሲቲው ግቢዎች የንብረት ቆጠራ ማካሄድና የሀብት ግምታቸውን ማወቅ ነው ብለዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የዩኒቨርሲቲው ንብረቶች የሚመዘገቡት በእርሳስ እንደሆነ፣ የንብረት ክፍል ኃላፊዎች ሲቀየሩና አዲስ ኃላፊ ሲመጣ በላጲስ ጠፍቶ የአዲሱ ኃላፊ ስም እንደሚመዘገብ አስታውቀዋል፡፡
የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርን አስፈቅዶ ዩኒቨርሲቲው ገንዘብ ሲሰበሰብ የነበረው ራሱ በሚያሳትመው የገንዘብ መሰብሰብያ ሰነድ መሆኑን ያስታወሱት ፕሬዚዳንቱ፣ አሁን ግን ገንዘብ ሚኒስቴር በሚያውቀው ሰነድ መሰብሰብ አለበት በመባሉ ወደዚህ ሥርዓት እየተገባ ነው ብለዋል፡፡ ኦዲት መደረግና መሰብሰብ ባልቻሉት ሒሳቦች ላይ ዕርምት ተወስዶ በርካታ ሚሊዮን ብሮች ተሰብስባዋል ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ምክትል ፕሬዚዳንቱ ዶ/ር ጄሎ ዑመር፣ ‹‹ዩኒቨርሲቲው ከ50 ሺሕ በላይ ተማሪዎች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ከ20 ሺሕ በላይ በግቢው ውስጥ ነው የሚኖሩት፡፡ እነሱን በቀን ሦስቴ መመገብ አለብን፡፡ ግቢው ውስጥ ኮሽ ሳይል የመማር ማስተማሩ ሒደት መቀጠል አለበት፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ የፋይናንስም ሆነ የግዥ ሕጉን ማስተናገድ መቻል አለብን፡፡ እነዚህን አጣጥሞ መሄድ ምን ያህል ፈተና እንደሆነ ካልገባን በስተቀር አስቸጋሪ ነው፤›› በማለት ያለውን ሁኔታ ለማሳየት ሞክረዋል፡፡ በተለይ ደግሞ ችግሩ በቀድሞዎቹ አመራሮች ጊዜ የተፈጠረና ሥር የሰደደ በመሆኑ አስቸጋሪ ያደርገዋል ብለዋል፡፡
‹‹እውነት ለመናገር ራሴንም ቤተሰቦቼንም ለችግር አጋልጬ ነው የምሠራው፡፡ ታመኖብን ከገባን አይቀር ብለን እንጂ ምቾት ተሰምቶን አይደለም፤›› ብለዋል፡፡ ‹‹እኔ በሕይወቴ ምቾት ሳይሰማኝ ሥራ የምሠራበት ወቅት ቢኖር ባለፉት ሦስት ዓመታት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን ከተቀላቀልኩ በኋላ ነው፤›› በማለት ምሬታቸውን አሰምተዋል፡፡
የሚቻለውን ያህል ሕግ ለማስከበር እየሠሩ መሆናቸውን የተናገሩት ምክትል ፕሬዚዳንቱ፣ የዩኒቨርሲቲውን መኖሪያ ቤቶች ተረክበው የነበሩ መምህራን ከዩኒቨርሲቲው ቢለቁም መኖሪያ ቤቱን ግን ለቤተሰቦቻቸው ሰጥተው ቤተሰቦቻው አከራይተው እየኖሩ መሆኑ እንደተደረሰበትና ሕገወጥነቱን ለማስቆም ግብግብ ውስጥ መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡
ፕሮጀክቶች ከተጠናቀቁ በኋላ ለዩኒቨርሲቲው መመለስ የሚገባቸው ተሽከርካሪዎች አሁንም በመምህራን ንብረትነት እየተቆጠሩ በመሆናቸው፣ ይህንን ሁኔታ ለመቀየር ንትርክ ላይ መሆናቸውን በማስረዳት ጥረታቸው በፈተና የታጀበ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ምንጭ Aseged Tamene

በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ፅ/ቤት ውስጥ ዲፕሎማቱ በጎጥ ተከፋፍለው ሲጋጩ አመሹ ።


የሰሞኑ የጅዳ ቆንስላ /ቤት  ሃሜትና የዛሬ የኢህአዴግ ስብሰባ ንትርክ  መንስኤው  ከሃገር ቤት  ከውጭ ጉዳይ  ሚንስትር በኩል በተላከው የኢህአዴግ አዲሱ አደረጃጀት ምክኒያት ነው። አዲሱ አደረጃጀት ደግሞ ተወስኖ  የመጣው ድርጅቱ በቆንስላው መሪ እንዲመራ  የሚል በመሆኑ ይሄንን  ደግሞ  በመከከለኛው  ምስራቅ በጥንካሬያቸው  የሚታወቁት የጅዳ የህወሃት ኢህአዴግ አመራሮች የተዋጠላቸው  አይመስልም።
Add caption


ከቆንስሎቹ ሶስቱም የደቡብ ሰዎች  በመሆናቸው  ሌላ ችግር ሆኗል። ይህ የቆንስሎቹ ችግር ከዚህ በፊትም ድርጅቱን ሊያነጋግሩ ከውጭ ጉዳይ አምባሳደር ውብሸት ደምሴ በመጡ ግዜም እንደ ቅሬታ  መነሳቱን ምንጮች ጠቁመዋል።  በአሁኑ ሰዓት ቀድመው የነበሩት  የደህዴን መሰረታዊ ድርጅት አመራሮች ለቆንስሎቹ ስልጣናቸውን ጥለውላቸው መሄዳቸው የዛሬ  የኢህአዴግ ስብሰባ ዋና  አጀንዳ  ሆኖ ምሽቱን በብሄር ጎራ ለይቶ ሲያነታርክ  ቆይቷል።

የሆነ ሆኖ  እውነት ኢህአዴግንም ቆንስሎቹ ሊመሩት  ይሆን? ባይዋጥላቸውም የህወሃት አመራሮች ዝምታን መርጠዋል። የቀድሞው ጄነራል ቆንስላ ዘነበ ከበደ  ከእጃቸው ያፈተለከው    የበላይነት የተመለሰ  አይመስልም።

ይህ  በዚህ እንዳለ  ጅዳ ላይ  የተጀመረው የብሄር ግጨት መቀመጫቸውን ሪያድ  ባደረጉትን የኢ.... ዲፕሎማቶች እያተራመስ መሆኑን ከኤምባሲው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ በተለይ ከኦሮሞ ብሄር የሚወለዱት  አምባሳደር / መሃመድ ሃሰን  የደቡብ ተወላጅ የሆኑትን የዲያስፖራውን ሃላፊ አቶ ተመስገን ኡመር ከስልጣን ለማባረር  ለውጭ ጉዳይ ሚንስቴር /ቤት የክስ ደብዳቤ አስገብተው እንደነበር  ውስጥ አዋቂ  ምንጮች ይገልጻሉ። 

አቶ ተመስገን ኡመር በኢ.... ታማኝ፡አባለነታቸው ከዲያስፖራው  ሃላፊነታቸው ባሻገር ከአማራ ብሄር የሚወለዱትን  የአምባሳደ መሃመድ ሃሰን  አማካሪ እና የንግድ ዘርፍ ሃላፊ የነበሩትን  አቶ ዘላለም ከሃላፊነታቸው በማንሳት አቶ ተመስገን ኡመር የአማካሪነት ቦታውን ደርበው እንዲይዙ  መደረጋቸው ፍጥጫውን የበለጠ አካሮታል ። ወትሮም በመንግስት ዘንድ  የቀርብ  ከትትል የሚደረግባቸው አምባሳደር / መሃመድ ሃሰን  በተለያዩ ግዜያት በሚቀርባቸው ለጥያቄ ሀገርቤት መጠራታቸው ይነገራል። በአጠቃ ላይ ጅዳ እና ሪያድ ውስጥ በዲፕሎማቱ የተጀመረው የብሄር ስልጣን ሹኩቻ ወደ በማህበረሰቡ ወርዶ በጅዳ እና ሪያድ የኮሚኒቲውን ት/ቤት አስተዳደር ጨምሮ አንዳንድ ማዕከላትን በበላይነት ለመቆጣጠር በብሄር ልማት ማህበራት በኩል የተደራጁ ጽንፈኞች በሚያራግቡት ቅስቀሳ ዲያስፖራውን በስው ሃገር ማብቂያ ወደ ሌለው  ደም መፋሰ እንዳይከቱት ያሰጋል። Ethiopian.hagere ጅዳ በዋዲ 

Friday, March 28, 2014

ሰበር ዜና ሪያድ ዲፕሎማቱ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤትን ተቆጣጠሩ ቀደም ሲል ለተመዘበረው 1.7 ሚልዮን ሪያል «ከ6 ሚልዮን ብር በላይ» ወላጆችን ባለዕዳ አደረጉ ::


=======================================================
ከ1500 በላይ በሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚተዳደር የሚታወቀው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት በዲፕሎማቱ ቁጥጠር ስር መዋሉን የሚገልጹ ምንጮች ለዛሬ ማርች 28 2014 በኤምባሲው ደብዳቤ የስብሰባ ጥሪ ተላልፎላቸው የነበሩ ወላጆች ባለመገኝታቸው የስብሰባው አዳራሽ ባዶ ሁኖ መዋሉን አክለው ገልጸዋል፡፤

ንበረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደነበር የሚነገርለትን ት/ቤት ኤምባሲው ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው ጥረት ከግልጥቀም የመነጨ መሆኑንን የሚናገሩ ውስጥ አውቂ ምንጮች ት/ቤቱን ከኮሚኒቲው በመነጠል ከወላጆች በሚመረጥ የቦርድ አስተዳደር ይመራል በሚል ሽፋን ላለፉት 5 አመታት በት/ቤቱ ጥሬ ገዝንዘብ ላይ ግልጽ የሆነ ምዝበራ መፈጸሙን ይናገራሉ። ይህን አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ዲፕሎማቱ ልግል ጥቅማቸው ለማዋል ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልበጠሱት ቀጠል እንደሌለ የሚናገሩ ወገኖች ከዛሬ 7 ወር በፊት ለይስሙላ ህብረተሰቡ በቦርድ አባልነት ለመሳተፍ የሚያስችለውን ማስታወቂያ አውጥተን የሚቀርብ ሰው አጣን ለማለት የመወዳደሪያውን ማመዘኛ ዲግሪ እና ከዛ በላይ ከፍ በማድረግ ማንኛውም ወላጅ በቀላሉ ማቀረብ የማይችላችውን ተጨማሪ ድብዳቤዎች እንዲያቀርብ የሚጠይቅ መስፈርቶችን በማስቀመጥ ወላጆች ት/ቤታቸውን ለማስተዳደር እንዳይችሉ መደረጋቸውን ይገልጻሉ።

ይህ በዚህ እንዳለ ወላጆች ባላቸው አቀም እና የትምህርት ደረጃ አቋቁመው ለዘመናት ያለማንም ድጋፍ እና ረዳት በማስተዳደር ለዚህ ያበቁትን የልጆቻቸውን ዕውቀት መገብያ ማዕከል ኤምባሲው ለመንጠቅ በሪያድ የዲያስፖራው ሃላፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ተመስገን ኡመርን በጓሮ በር አሾልኮ በመስገባት ቀደም ብለው ያዘጋጇቸውን ታማኝ አገልጋይ የቦርድ አባላት ስልጣን ካፀደቁ በሃላ ዛሬ ወላጆችን ለማደናገር በኤምባሲው ማህተም በተደገፈ ደብዳቤ ስብሰባ መጥራታቸው የዲፕሎማቱን አላውቂ ሳሚነት በግልጽ ያሳይል ተብሏል።

ዲፕሎማቱ በኤንባሲ ሽፋን ህገወጥ ተግባር በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ የሚናገሩ ወገኖች 1500 በላይ የሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚቆረቆሩለት የሚነገርለትን ት/ቤት  ቁጥራቸው ከ 50 የማይበልጥ የት/ቤቱ ጉዳይ የማይመለክታቸውን ደጋፊዎቻቸውን ሰብስበው አዳራሽ በማስገባት «አይጥ በበላው ዳዎ እንዲሉ » ምንም የማያውቁትን ወላጆች የ 1.7 ሚሊዮን ሪያል ባለእዳ የሚያደርግ ሪፖርት በዲይስፖራው ሃላፊ አማካኝነት በማቅረብ ዲፕሎማቱ የመረጣቸውን ህገ ወጥ የቦርድ አማራር አባላት ህጋዊ ለማድረግ ከወላጆች ጀርባ ዛሬ የፈጸሙት ደባ በህግ ሊያስጠይቃቸው የሚገባ ብሄራዊ ወንጀል መሆኑን ገልጸዋል። ስብሰባው ላይ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ህሰን መገኘታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። በዚህ ዙሪያ የዲያስፖራውን ሃላፊ አቶ ተመስገን ዑመርን ለማነጋገር የተደረገው ሙከራ አልተሳካም 
Ethiopian Hagere ጅዳ በዋዲ

Thursday, March 27, 2014

ለአማራ ወያኔዎች የመጀመሪያና የመጨረሻ መልእክት


 ነፃነት ዘለቀ (ከአዲስ አበባ)
“መልእክት” ያልኩት አቀራረቤን ቀለል በማድረግ የአንባቢያንን ቀልብ ላለመግፈፍ ነው፡፡ እንጂ መነሻየ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነው፡፡ ማስጠንቀቂያም ይባል መልእክት ዋናው ጉዳይ በግሌ የተሰማኝንና የማምንበትን ለወገኖቼ ድኅነት ስልም የምጽፈው ነገር ለባለአድራሻዎቹ መድረሱ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የሁሉንም ድረገጾች ትብብር በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ እባካችሁን ለሁሉም ካድሬ መልእክቴን አድርሱልኝ፡፡
ሰው ክርስቶስን መሆን እንዳይችል ጠላት መንገድ እየዘጋበት መቸገሩ የሚታወቅ ነው፡፡ መሆን  ቢፈልግ ግን ይችላል፤ የሚከለክለው አንዳችም ነገር የለም፡፡ ክርስቶስ ራሱም ያለው “እንደኔ ሁኑ፤ እኔን ምሰሉ” ነው፡፡ ችግሩ ክርስቶስን ለመሆን ወይም ቢያንስ ለመምሰል የእምነት ጽናትና እውነተኛ ፍቅርን የተላበሰ ስብዕና ማጣት ነው፡፡ ተራራን ሊያዞር የሚችል እምነት፣ የሚጠላንን ብቻም ሳይሆን የሚገድለንንም ጭምር  የሚያፈቅርና ለጨካኞች የሚራራ ልብ፣ የማይወላውል እምነትንና የማያዳላ ፍቅርን የሚገልጥ በጎ ሥራ ካለ ከፈጣሪና ከአንድያ ልጁ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ውህደት መፍጠርና ጓደኛ መሆን የማይቻልበት ምክንያት የለም፡፡ የሚጠይቀው እውነተኛ የልብ መሰበርን ብቻ ነው፡፡
ክርስቶሳዊ ተምሳሌትነትን በተወሰነ ደረጃ በመውሰድ አካሄድን ማረቅና ማስተካከል ይቻላል፡፡ ከወቅቱ አቢይ ሃይማኖታዊ ክንውን እንጀምር፤ ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከፆመ በኋላ በሰይጣን ሦስት ጥያቄዎች ቀርበውለት በአሸናፊነት ተወጥቷል፡፡ የመጀመሪያው ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር፤ “አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንክ እስኪ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ”፡፡ የክርስቶስም መልስ “ ‹ሰው የሚኖረው እግዚአብሔር በሚናገረው ቃል እንጂ በእንጀራ ብቻ አይደለም› ተብሎ ተጽፏል፡፡” አዎ፣ ለአስተዋይ ሰው በእንጀራ ብቻ መኖር እንደማይቻል ግልጽ ነው፡፡ እርግጥ ነው ሰይጣን በሚያስፈልገን ነገር ይመጣብናል፡፡ ሰይጣንና የስለላ ድርጅቶች ተመሳሳይነት አላቸው፤ በምትወደው ነገር ይመጡብህና ወጥመዳቸው ውስጥ ይከቱሃል(cf. blackmailing)፡፡ ክርስቶስንም በዚያ ቀዳዳ የመጣበት አርባ ቀንና አርባ ሌሊትን ካለምንም ምግብ በመክረሙ ተርቦ ነበርና ይሸነፍልኛል ብሎ ነው፡፡ እንዳሰበው ግን አልሆነለትም፡፡ ያ ምናልባት ሥነ መለኮታዊ ጣጣ ስላለው ለምድራዊ ሕይወት ጥሩ አብነት ላይሆን ይችላል፡፡ እናም የአርባ ቀኑን የክርስቶስ ፆም እንርሳውና አብዛኛው የአሁኑ ዘመን ሰው አንድ የምግብ ሰዓት አልፎበት አይደለም ትንሽ ሆዱ ጎደል ካለ እናቱን ከመሸጥ እንደማይመለስ እናስብ፡፡ አሰብን?…
ፈተናዎች በጥቅሉ የሥጋና የነፍስ ተብለው በሁለት ዐቢይ ክፍሎች ሊመደቡ ይችላሉ፡፡ በአማርኛ ፈተናን የሚገልጡ ቃላት ውሱን ናቸው፡፡ በዚህ ረገድ እንግሊዝኛው ሳይሻል አይቀርም፡፡ “test, quiz, exam, examination, temptation, assessment …” የሚባሉ ቃላት አሏቸው፡፡ እነዚህ ቃላት በዐውድ ውስጥ መገኘት ሳያስፈልጋቸው በቁማቸው የሚሰጡት የተወሰነ ምስል አለ፡፡ እኔ አሁን እዚህ ላይ ልጠቅሰው የምፈልገው የፈተና ዓይነት በእንግሊዝኛው አጠራር temptation የሚለውን ነው፡፡ የአባታችን ሆይ ጸሎት ውስጥ “ Our Father who art in heaven … lead us not intotemptation but deliver us from evil.” እንደሚል፡፡
ከመጽሐፍ ቅዱስ ሳንወጣ የክርስቶስን ደቀ መዝሙርና የግምጃ ቤት ኃላፊ የአስቆሮቱ ይሁዳን እናስታውስ፡፡ ከገቢ ገንዘቦች አሥር መቶኛውን ለራሱ እንዲያደርግ ተፈቅዶለት የነበረው ይሁዳ በገንዘብ ፍቅር ክፉኛ የተለከፈ ነበር – ልክ እንደወያኔ፡፡ ይህ በሽታው ተባብሶበት በመጨረሻው ክርስቶስን ራሱን በሠላሣ አላድ ለጠላቶቹ አሳልፎ ሸጦታል፡፡ ገንዘቡን ግን አልተጠቀመበትም፡፡ ያልተጠቀመበትም ምክንያት ክፍያውን እንደተቀበለና ክርስቶስን ያሳድዱት በነበሩ አይሁዳውያን እንዳስያዘው የሰረፀበት ሰይጣን ለጸጸት አጋልጦት በመለየቱ ምክንያት ራሱን ሰቅሎ ስለሞተ ነው፡፡ የይሁዳ ነፍስ አልተማረችም፡፡ ይህን እውነት ከመጽሐፍ ቅዱስ እናገኘዋለን – ሊማር አለመቻሉንም ጭምር፡፡
ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ወደፈተና ይገባል፡፡ ለሆዱና ስለሆዱ በሆዱ የሚፈተን አለ፤ በሆድ መፈተን መጥፎ ፈተና ነው፡፡ ሀገርን የሚያሸጥ የሆድ ፍቅር የተጠናወተው ሰው ደግሞ በሕይወት ዘመኑ በሚኖረው የስብዕና መመሰቃቀል ብቻም ሣይሆን ልጆችን ወልዶ ቢያልፍ በሀፍረት አንገታቸውን ይደፋሉ፤ በሕዝብ ዘንድም መጠቋቆሚያ ይሆናሉ፡፡ታሪኩ የጠቆረና የትውልድ ማፈሪያ ይሆናል – አሁንም እንደወያኔ፡፡
አንድ ሰው ፈተናን ወደቀ የምንለው ነባር እምነቱንና ታማኝነቱን ለሆነ ጥቅም ሲል ክዶ ከትክክለኛው መንገድ ሲወጣ ነው፡፡ በዚህ ረገድ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ታሪክ ስንመለከት ሁለት በፈተና የወደቁ አካላትን እናገኛለን፡፡
ዋናው ተፈታኝና ፈተናውን ከመነሻው የወደቀው ከትግሬው ብሔር የወጣውና ሕወሃት በመባል የሚታወቀው ፀረ-ኢትዮጵያና ፀረ-ሕዝብ ኃይል ነው፡፡ ለዚህ ድርጅት በፈተና መውደቅ መንስኤው ዓላማና ለጥቅም ነው፡፡ የሚታወቅን ነገር መዘርዘር አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡
ሁለተኞቹ ተፈታኞች ሁሉን ነገር እያወቁ ለፍርፋሪ እንጀራና ለማያዙበት የይስሙላ ሥልጣን ሲሉ በሕወሃት ሥር በባርነት አድረው የወጡበትን ሕዝብ ለወያኔ የሸጡ ይሁዳ አማሮች – ብአዴን ተብዬዎቹ – ናቸው፡፡ በሃይማኖታዊ አገላለጽ ሕወሃትን ልምጭ አስይዘውና በሁለንተናዊ ዘመናዊ መረጃ ደግፈው ጃዝ ብለው የላኩት የታላቁ ወንድም (The Big Brother) ባለሟሎችን የሉሲፈር ደቀ መዛሙርት ልንላቸው እንችላለን፡፡ ታሪካዊ ቂም በቀል አርግዘው ኢትዮጵያን ለማጥፋትና በእግረ መንገድም ቤት ያፈራውን ሥልጣንና ሀብት በግል ለመቆጣጠር የተነሡ የትግሬ ወያኔዎችን  በሉሲፈር አጣማጅ በሰይጣን በራሱ ልንመስላቸው እንችላለን፡፡ ለሆዳቸው ያደሩ በተለይም የዕልቂት ዐዋጅ ከታወጀበት የአማራው ሕዝብ እንደተገኙ የሚነገርላቸው ከሃዲዎችን ደግሞ በሰይጣን አገልጋይነት ልንፈርጃቸው እንችላለን፡፡ የሆነው ሆኖ ትግሬም ይሁን አማራ ወይም ሌላ ከእውነተኛው የጤናማ ኅሊና መንገድ ወጥተው ኢትዮጵያን ለማውደም እስከተሰለፉ ድረስ ሁሉም የጥፋት ወኪሎችና የክፉ መንፈስ ምርኮኞች ናቸው፡፡
በኢትዮጵያ ያለው አጥፊ ኃይል ደግሞ የዓለም አቀፉ የጥፋት ኃይል ቅርንጫፍ ነው፡፡ ይህ በከፍተኛ ጥንቃቄና የሸር ጥልፍልፍ ወይም ሤራ (Conspiracy) የሚካሄድ የዓለምን ፖለቲካና ኢኮኖሚ የመቆጣጠር ዕቅድ ጅማሮው ቀደም ቢልም በሁሉም አቅጣጫ በተቀነባበረ ዘመቻ ወደስኬት ጫፍ የደረሱ የመሰሉት ግና አሁን በምንገኝበት የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ነው – የመሠረት ግንባታው ደርዝ መያዝ የጀመረው ግን የዛሬ 300 ዓመታት አካባቢ በ18ኛው መ/ክ/ዘመን መግቢያ አካባቢ እንደሆነ ይነገራል፡፡ የሚያሠማሯቸው ጉዳይ አስፈጻሚ ተላላኪዎች ዘርና ቀለም፣ ፆታና ሃይማኖት ሳይገድባቸው እንደ እስስት ከየሚሄዱበት አካባቢ ሕዝብ ጋር እየተመሳሰሉ ሀገርንና ሕዝብን በቅርበት ይቆጣጠራሉ – ሲያሻቸው መጽሐፍ ቅዱስ ሲያሻቸው ደግሞ ሽጉጥ በመያዝ በመስቀል ከቀላጤ ‘politico-psuedo-religious’ ዘመቻ ዓላማቸውን ከግብ ለማድረስና የባሕርይ አባታቸውን ሊቀ ትጉሃን ዲያብሎስን ለማስደሰት ይጥራሉ፡፡ በመንግሥታት ጀርባ ሥውር መንግሥታትን በማቋቋም ሁሉንም ነገር በዐይነ ቁራኛ ይከታተላሉ – ሊያውም በ“ሁሉን ተመልካች” አንዲት ዐይናቸው! በዓለም አቀፍ ግዙፍ ካምፓኒዎቻቸው አማካይነትም የዓለምን ሀብትና ንብረት ይዘርፋሉ፤ ነዳጅና የተፈጥሮ ማዕድናትን እያሰሱ ለማይጠረቁት ሥውር ቱጃሮቻቸውና የምሥጢራውያን ድርጅቶቻቸው አለቆች ያስረክባሉ – ሁሉ በጃቸው ሁሉ በደጃቸው፤ ጦሩም ስለላውም አስተዳደሩም ምኑም ምናምኑም በነሱው ቁጥጥር ስለሚገኝ የ‹ሪሶርስ›ና የሰው ኃይል ችግር የለባቸውም፡፡ ጦርነቶችን ይፈጥራሉ፤ ሲፈልጉ ያጣላሉ – ሳይፈልጉ ያስታርቃሉ፡፡ መሣሪያዎቻቸውን ለተዋጊ ወገኖች በግልጥና በድብቅ ይሸጣሉ፡፡ ትውልድን ከሃይማኖትና ከባህል አውጥተው መና ለማስቀረት፣ ከሞራልና ሥነ ምግባር ማዕቀፎች ለይተው ባዶ ለማስቀረት እነሆሊውድን ከመሳሰሉ ተቋሞቻቸው ባፎሜታዊ ፊልሞችንና ሙዚቃዎችን በዓለም ይበትናሉ፡፡ ሀሺሺንና መጠጦችን በማምረት በሥውር ያሰራጫሉ፡፡ የሚገርመው እነዚህ ኃይሎች ፀረ-ሀሽሽ መስለው ቢቀርቡም ውሸታቸውን ነው፤ ከአፍጋስታን እስከ ኮሎምቢያና ሜክሲኮ የዐደንዛዥ ዕፅ ምርትና ገበያን የተቆጣጠሩት እነሱው መሆናቸውን የሚገልጡ መረጃዎች የአደባባይ ምሥጢር ከሆኑ ሰንብተዋል፡፡ ወያኔም እንደዚሁ ወጣቱን በጫትና በመጠጥ እያደነዘዘ ሀገር ተረካቢ ትውልድ እንዳይኖር መጣሩን አንርሳ፡፡ በብዙ ነገር መመሳሰላቸውን ልብ እንበል፡፡ ወያኔን የሚገዛ ህግ እንደሌለ ሁሉ እነሱንም የሚገዛ ህግ የለም፡፡ የነሱን ደንቆሮ በሀሰት የዶክትሬት ዲግሪ የምስክር ወረቀት ለዓለም አቀፍ ተልእኮ ቢያሰማሩት ታማኝነቱ እንጂ ትምህርቱ ብዙም ፋይዳ ስለሌለው በአጭበርባሪነት የሚጠይቀው የለም – በወያኔ ቤትም ለባለሥልጣን ያልተበተነ የዲግሪ ዓይነት የለም – ባዶ ጭንቅላት ላይ ጥቁር ቆብና ጥቁር ካባ፡፡ ከነሱ ቁጥጥር የሚወጣን ሀገር መሪ(ዎች) በስለላ ድርጅቶቻቸው ልዩ ኮማንዶና በጨረር አነጣጥሮ ተኳሽ የፓራትሩፐር እስኳድ ያስወግዳሉ – ለሀገሩ የሚቆምን ሀገር ወዳድ ግለሰብም በዚህ መልክ ደመ ከልብ ሆኖ እንዲቀር ያደርጋሉ (ነፍስ ይማር – ኢቅእ(?))፡፡ (ቅን ታዛዦቻቸው ሊያፈነግጡ ወይም ጌታ ሊለውጡ ካሰቡም ይሄው የቅጣት በትር አይቀርላቸውም (ነፍስ ይማር – መዜአ (?))፡፡ … በሚያስወግዷቸው ምትክም የነሱን ፍላጎትና ጥቅም የሚያስከብር መለስ ዜናዊን የመሰለ ፀረ-ሕዝብና ፀረ-ሀገር ወሮበላ በዴሞክራሲ ጭምብላቸው ለላንቲካው ይጎልቱታል – ዋናውን መዘውር በእጅ አዙር የሚይዙት ግን እነሱው ናቸው፡፡ በዓለም ባንክና በአይ ኤም ኤፍ፣ በኔቶና በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አማካይነትም በማይወዱት ሀገር ላይ የኢኮኖሚና ወታደራዊ ማዕቀብ ይጥላሉ፤ እንዳስፈላጊነቱም ጦርነት ያውጃሉ፡፡ ከነሱ ዕይታና ቁጥጥር ውጪ የሚሆን አንዳችም ነገር የለም፡፡ ነፍስና ሥጋህን ብቻ ሳይሆን የምታስበውንም ሁሉ ጭምር በ“Mind Control system”  ሊቆጣጠሩ ይሞክራሉ፡፡ ከፈለጉም በሰው ሠራሽ የመሬት መናወጥና ሱናሚ አንድን ሀገር ሊያደባዩ፣ አለዚያም በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መራጃ ዝናብን ከልክለው በድርቅ ሊመቱ፣ በሌላም በኩል ከመጠን በላይ ዝናብን አዝንበው በጎርፍና በመሬት መንሸራተት ናዳ ሕዝብንና መንግሥታትን ሊያስለቅሱ ይችላሉ፡፡ በአጭሩ የማያደርጉት ነገር የለም፡፡ ደግሞም እውነት ነው፡፡ ወያኔዎችስ? ሥልቱና አፈጻጸሙ ይለያይ እንጂ አንድና አንድ ናቸው፡፡
የወያኔዎች የአንድ ለአምስት የጥርነፋ ሥልት የዚሁ የዓለም አቀፍ ዘመቻ አካል ነው፡፡ በአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ዕዳ ውስጥ የሚዶሉህም በዐይናቸው ሥር አውለው ሊቆጣጠሩህ ነው፡፡ በብድር የተያዘ ሰው ደግሞ ታውቃለህ – ውልፊት ሊል አይችልም፡፡ ሌላ ነገር አምሮህ ብታንጋጥጥ- ማንጋጠጥም አይደለም ለማሰብም ብታስብ ራሱ ያስወነጅልሃል፡፡ ያኔ በአሸባሪነት ባትጠየቅ እንኳን በገንዘብ ዕዳ ያለህን ንብረት ያሸጡሃል ወይም የፍትሃ ብሄር ወንጀልህ ተቀባብቶ ወደ ተሟላ ደረቅ ወንጀል ይዞርብህና ቃሊቲ ልትወርድ ትችላለህ፤ ለማንኛውም እሥር ቤት ውስጥ ነህ – የእሥር ቤቱ ስፋትና ጥበት ላይ የጋራ መግባባት ላይ እስከደረስን ድረስ፡፡ በቤትህ ውስጥ ሳይቀር ከአንተ ዕውቀት ውጪ ተከታታይ ሊመደብብህና መላ እስትንፋስህ ወደ ማዕከላዊ መረጃና ደህንነት መሥሪያ ቤት ሊያመራ ይችላል፤ ስልክህ ሊጠለፍ፣ ኢሜልህ ሊጠለፍ፣ ፌስቡክህ ሊጠለፍ፣ ሚስትህ ልትጠለፍ፣ ልጆችህና ጓደኞችህ ጭምር ሊጠለፉ፣ አስፈላጊ ሆኖ በተገኘ ጊዜ ሁሉ አንተ ራስህም ልትጠለፍና የሰይጣን ጆሮ ይደፈንና ብዙ ሰይጣናዊ ነገሮች ሊደርሱብህ ይችላሉ፡፡ የእነአልማዝ ሠይፉን፣ የእነብርቱካን ሚዴቅሳን፣ የእነደበበ እሸቱን፣ የነስዬ አብርሃን ዝምታ ያዬ አንዳች ነገር ቢጠረጥር ሊፈረድበት አይገባም፡፡ በስማም የተባለበት ሰይጣን ይመስል በአርምሞ የተቀመጡበትን ምክንያት ከነሱ በስተቀር ማንም አያውቅም፡፡ አሣሪህና የስቃይህ ምንጭ ሲደርቅ ጮቤ መርገጡ ዲያብሎሳዊ መሆኑ እርግጥ ቢሆንም ለሰባት ቀን ሀዘን መቀመጡና በፈጣሪ ሥራ ገብቶ በ“ለምን ወሰድክብኝ” እዬዬ ማለቱ ሃይማኖታዊ መደላድል ያለው አይመስለኝም – የቃል መቀነት መጠቀም አስፈላጊ ሆኖ የተገኘውም ይህን ዕንቆቅልሽ በአመስጥሮ ለመጠቆም ነው (አመስጥሮው እዚህ ላይ አበቃ እንጂ)፡፡ ለማንኛውም በዲያብሎስ ግዛት መብቴ ተረገጠ ሰው መሆኔ ተዘነጋ ብሎ መጠየቅ ሞኝነት ነው፡፡ ከሁሉ በባሰ ሁኔታ የጎንህ ፍላጭ ሚስትህ ወይም የአብራክህ ክፋይ ልጅህ ሊሰልሉህ ቢችሉ የዘመኑ የትልቁ ወንድምህ ፋሽን ነውና አይግረምህ፡፡ ወያኔ የትልቁ ዓለም አቀፍ ዘመቻ የምሥራቅ አፍሪካ ዋና መሥሪያ ቤት (Head Quarter) ነው ቢባል ያስኬዳል፡፡ ከጆርጅ ኦርዌል ድንቅ መጽሐፍ (ከ “1984” ውስጥ) እስኪ ቀጣዩን ጥቅስ እንመልከት፡፡

He [Winston Smith] took a twenty-five cent piece out of his pocket. There, too, in tiny clear lettering, the same slogans were inscribed, and on the other face of the coin the head of Big Brother. Even from the coin the eyes pursued you. On coins, on stamps, on the covers of books, on banners, on posters, and on the wrappings of a cigarette packet—everywhere. Always the eyes watching you and the voice enveloping you. Asleep or awake, working or eating, indoors or out of doors, in the bath or in bed—no escape. Nothing was your own except the few cubic centimetres inside your skull.

ተዛማጅ ትርጉም፡- (ዊንስተን ስሚዝ) ሃያ አምስት ሳንቲም ከኪሱ አወጣ፡፡ በዚያች ሣንቲም ላይም በአንደኛው ገጽ በጥቃቅን ፊደላት የተለመደው መፈክር ተጽፏል፤ በሌላኛው ገጽ ላይ ደግሞ የታላቁ ወንድም የራስ ምስል ጉብ ብሏል፡፡ [(መፈክሩ - ‹ ጦርነት ሰላም ነው፤ ነጻነት ባርነት ነው፤ ድንቁርና ጥንካሬ ነው፡፡› የሚል ነው1፡፡)] ከዚህች ትንሽዬ ሣንቲም የምታየው የታላቁ ወንድም ዐይኖች ትክ ብለው ሲያዩህ መግቢያ ያሳጡሃል፡፡ በሣንቲሞች፣ በቴምብሮች፣ በመጽሐፍ ሽፋኖች፣ በዓርማዎች፣ በፖስተሮች፣ በሲጋራ ወረቀቶች፣ የትም ይሁን የትም እነዚህ የታላቁ ወንድም ዐይኖች ያፈጡብሃል፡፡ ምን ጊዜም ዐይኖቹ መግቢያ መውጫህን ይከታተላሉ፤ ድምፆቹም የጆሮ ታምቡርህን ያለ ዕረፍት ይጠልዛሉ፡፡ ተኝተህም ሆነ ሳትተኛ፣ ሥራ ላይም ሆንክ ምግብ ላይ፣ ከቤት ውስጥም ሆንክ ከቤት ውጪ፣ መታጠቢያ ቤትም ውስጥ ሁን በአልጋህ ላይ … የትም ሁን የት ከታላቁ ወንድም ዐይኖችና የዘወትር ክትትል ማምለጫ የለህም፡፡ ጭንቅላትህ ውስጥ ከሚገኘው ነጭ አንጎል ውጪ የኔ ነው የምትለው የግል ንብረት እንዲኖርህ አይፈቀድልህም፡፡ [እርሱንም ቢሆን አንተ አታዝበትም!]

በዲያብሎስ መንፈስ የሚነዳውን የአፍራሽ ኃይል (The Negative Energy) ዓለማቀፋዊ የጥፋት አድማስ በአጭሩ ለማሳየት የሞከርኩት የሀገራችን ጉዳይም ከዚሁ ኃይል ጋር ቀጥተኛ ቁርኝት ያለው በመሆኑ ነው፡፡ ከዘመን ፍርድ ማምለጥ አስቸጋሪ ነውና፡፡ ዓለማችን የሁለት ተፃራሪ ኃይላት መስተጋብራዊ ውጤት ናት፤ እነሱም ገምቢ ወይም አወንታዊ ኃይልና አፍራሽ ወይም አጥፊ ኃይል ናቸው፡፡ ማንም ሰው ከነዚህ ሁለት እርስ በርስ ተጠፋፊ ነባራዊ ሁኔታዎች ውጪ አይደለም፡፡ በምንገኝበት መሬታዊ/ምድራዊ ተጨባጭ ሁኔታ መሠረት አንዱ ካለ ሌላው አይኖሩም፡፡ ገምቢ ካለ አፍራሽ አለ፡፡ በዬቋንቋዎቻችንም ደግ – ክፉ፣ ፍቅር – ጥላቻ፣ ቸር – ንፉግ፣ ሃቀኛ – ዋሾ፣ ወዘተ. የመኖራቸው እውነታ ይህንን ለማጠየቅ ይመስላል፡፡ ችግሩ ምጣኔያቸው ላይ የሚታየው የሚዛን መዛነፍ ነው፡፡ አንዱ ከሌላው ግዘፍ ነስቶ ከታዬ ለምሳሌ የክፋት መንፈስ ከተንሠራፋ ሀገርና ሕዝብ ይጎዳሉ፤ እንደሀገረ ኢትዮጵያ ለአጠቃላይ ውድመት ሊዳረጉም ይችላሉ፡፡ ይህ ዓይነት አስቀያሚ ሁኔታ የሚፈጠረው ኅሊናን በመሸጥ ለሆድና ለጥቅም ማደር ሲከሰት ነው፡፡ ሰዎች ኑሯቸውን ያሸነፉና ያለፈላቸው እየመሰላቸው ብዙ ጣጣ ውስጥ ይገባሉ፤ በዚያም ሳቢያ ከፍለው የማይጨርሱት ዕዳ ውስጥ ይነከራሉ፡፡ የብአዴኖች ወንድምና እህቶቻችን ዕኩይ ተግባርም ከዚህ የሚመደብ ነው – በደቂቃዎች ውስጥ ዕዳሪና ሽንት ለሚሆን የሆድ ቀለብ (እህልና ውኃ)  ሀገርንና ሕዝብን የመሰሉ ዘላለማውያን ኅላዌያት ሲክዱ ማየት የታሪክ አሰቃቂ ፍርድና ምፀት ነው፡፡
ሕወሃት ኢትዮጵያን እያጠፋ ያለው ለዓላማና ለጥቅም ነው፡፡ የሕወሃት ተባባሪዎች የሆኑት ብአዴንና ሌሎቹ ኢትዮጵያን በማጥፋት ላይ ከሚገኘው ሕወሃት ጋር እየተባበሩ ያሉት ወገኖች ግን ለዓላማ ሣይሆን አንድም በድንቁርና ነው፤ አንድም በሆዳምነት ነው፡፡ አማራ አማራን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት ዓላማ ነድፎ ከፀረ-አማራ ኃይሎች ጋር በማበር ሊንቀሳቀስ ይችላል ተብሎ መቼም አይጠበቅም፤ በውነቱ የብአዴኖችን ነገር ስናጤነው የእርግማን ካልሆነ የሌላ አይመስልም፤ ዕንቆቅልሽ ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ አማራ ካልታመመ በስተቀር ዘመዶቹን ለመፍጀት በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ ሳይቀር በመታገያ ዓላማና ግብነት ቀርፆ የሚንቀሳቀስን ሰይጣናዊ ኃይል ሊተባበር አይችልምና ነው፤ በምንም ዓይነት መንገድ፡፡ ተጠየቃዊ አካሄዱም ይህን ታሪካዊ ህፀፅ ሊዳኝበት የሚያስቸለው ክፍተት የለውም – “ዕብደት ነው!” ብሎ የሚያልፈው ካልሆነ በስተቀር፡፡ በመሆኑም ብአዴን ውስጥ የሚገኙ አማሮች በየትኛውም ሚዛን ቢለኩ አንድም የለየላቸው ዕብዶች ወይም የለየላቸው ደናቁርት ማይማን ወይም ደግሞ ፀላኤ ሠናያት የሠፈረባቸው የክፉ መናፍስት ዋሻዎች ቢሆኑ እንጂ ለአማራ የሚቆረቆሩ አማሮች ሊሆኑ አይችሉም – ቃል ቢቸግረኝ እንጂ “ማይም” ማለቴ ራሱ ስህተት ነው፡፡ ማይምነት ከሀገር መሸጥና መለወጥ አይገናኝምና፡፡ ብአዴኖች አማራ አይደሉም ሲባል ደግሞ የደምና የአጥንት ጉዳይ ሳይሆን በፍካሬያዊ ትርጉሙ ነው፡፡ አማራን ከሚያጠፋ፣ ኢትዮጵያን ለመቅበር ጉድጓድ ከማሰ፣ ሀገርን ከሸጠና ከለወጠ ኃይል ጋር ያለ ሀፍረት አብሮ እየሠራ የሚገኝ “ሰው” አማራ ነኝ ቢል እንዴት ማመን እንደሚቻል ብአዴኖችን ራሳቸውን መጠየቅ ነው፡፡ በጣሊያን ጊዜ ከቅኝ ገዢው ባዕድ ወገን ጋር በባንዳነት ያገለግሉ የነበሩ ብዙዎቹ የዛሬዎቹ ገዢዎቻችን ወላጆች በንጽጽር ከብአዴኖች ይሻላሉ፡፡ ምክንያቱም የዚያኔዎቹ ባንዳዎች የካዱት መላዋን ኢትዮጵያን እንጂ የወጡበትን ጎሣና ነገድ አልነበረምና፤ በዚያ ላይ ጣሊያንም ቢሆን የወያኔን ያህል ቀርቶ ካልነኩት የማይነካና በጭካኔው ከወያኔ ፍጹም የማይወዳደር በአንጻራዊ አነጋገር እጅግ ሲበዛ ሰብኣዊ የነበረ ኃይል ነው፡፡ የኒህኞቹ ድርጊት ግን ዘግናኝ ወንጀል ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ወንድምህን፤እህትህን፤ አባትና እናትህን፣ በጥቅሉ በዘመኑ ቋንቋ ዘርህንና ቤተሰብህን እንደዐይጥ ከሚጨፈጭፍ የባንዳ ውላጅ ጋር መተባበር፣ ከዚያም ባለፈ ሰሞኑን እንደምንሰማው የጠላትን አንደበት በመዋስ በእንደራሴነትም ቢሆን የሚያስተዳድሩትን ሕዝብ በአደባባይ መዝለፍ በምንም ዓይነት መለኪያ ጤናማነትን አያሳይም፡፡ (Shall we say proxy badmouthing or insulting?) ይህ ዓይነቱ የብአዴን ድፍረት የኅሊና መታወርንና የአንጎል ጤንነት መቃወስን በግልጥ የሚያመለክት ነው፡፡ የአእምሮ ህክምናም ሳያስፈልገው አይቀርም፡፡…
አሁን ምን ማድረግ ይቻላል? በዚህ መቀጠሉ ያዋጣል ወይ? እስከመቼስ በባለ አንድ ጥርስ ማርሽ ብቻ ማሽከርከር ይቻላል?
ሰዎች ከፈለጉ ለማንኛውም ችግራቸው መፍትሔ መፈለግና ማግኘትም ይችላሉ፡፡ ዋናው ነገር ችግር ውስጥ መገኘትን ማወቅ ነው፡፡ ይህ በራሱ የመፍትሔውን ግማሽ መንገድ እንደመጓዝ ይቆጠራል፡፡ ከዚያም ንስሃ መግባት ነው፡፡ ንስሃ መግባት ሲባል በዚህ ዐውድ መሠረት በሆነ ታሪካዊ አጋጣሚ በተፈጠረ ስህተት ገብተው የሚዋኙበትን የጥፋት ባህር ተረድቶ ከዚያ ለመውጣት ከልብ መጸጸት ማለት ነው፡፡ ጥፋት ሰብኣዊ ነው፡፡ ማንም ሰው ትንሽም ይሁን ትልቅ ስህተት ይሠራል፡፡ ከስህተት ጎዳና ለመውጣትና ተበዳይን ከልብ ይቅርታ ጠይቆ ለመካስ የሚተጋን ሰው ደግሞ ፈጣሪ ይወደዋል፡፡ ሰው ሲባል ከሌሎች እንስሳት የሚለየውና ክፉንና ደግን መለየት የሚያስችለው አንጎል ያለው በመሆኑ ከስህተቱ እየተማረ፣ ደካማ ጎኑን እያስወገደና ጠንካራ ጎኑን ይበልጥ እያሻሻለ ወደበለጠ አእምሯዊና አካላዊ ዕድገት መራመድ ይጠበቅበታል፡፡ ጥፋቱን እንደልማት ቆጥሮ በኩራት የሚጀነን ሰው ከወያኔ የሚመደብ የመከነ አእምሮ ባለቤት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደምናነበው ብዙዎች ቅዱሳንና ሰማዕታት ስህተትን ይሠሩ ነበር፡፡ ከአዳምና ከሔዋን ጀምሮ እነቅዱስ ዳዊት፣ እነሶሎሞን፣ እነጴጥሮስ … ሁሉም ይሳሳቱ ነበር፡፡ ግና በጸጸት ዕንባቸው ስህተታቸውን እያጠቡ ከእግዚአብሔር ምሕረትን እንዳገኙ ቅዱሣት መጻሕፍቱ ያስረዳሉ፡፡ ክርስቶስንና ክርስቶሳውያንን በጦር ያሳድድ የነበረው ኃጢኣተኛው ሳዖል፣ በኋላ ላይ በደገኛው የኢየሱስ መንፈስ ተመርቶ አንገቱን ለሠይፍ እስኪሰጥ ድረስ የክርስቶስ አገልጋይ ሊሆንና በቅዱስ ጳውሎስነቱ ሊታወቅ በቅቷል፡፡ አንድ ነገር እንድገም፡- አንዱ “ወንድሜ ሰባት ጊዜ ስህተትን ቢሠራብኝ ሰባት ጊዜ ሁሉ ይቅር ልለው ይገባኛልን?” ሲል ክርስቶስን ይጠይቀዋል፤ በርሱ ቤት ሰባት ብዙ ቁጥር መሆኑ ነው፡፡ ክርስቶስ ግን በሚገርም ሁኔታ “ሰባት ጊዜ ብቻ አይደለም፤ ሰባት ጊዜ ሰባም ቢሆን ይቅር በለው” ሲል ነው የመለሰለት፡፡ አራት መቶ ዘጠና ጊዜ ቆጥረህ ይቅር በል ለማለት አይደለም – ይቅር ባይነት ገደብ እንደሌለው ነው የዚያ አስተምህሮ ማዕከላዊ አንድምታ፡፡ ይህ ምሳሌ ሁለት መልእክት አለው፡፡ አንዱ ለበዳዮች – ሌላኛው ለተበዳዮች፡፡ በበዳይ ወገን በኩል ያየነው እንደሆነ “ብዙ በድያለሁና ይቅር ስለማልባል በጥፋት ጎዳና እንደተጓዝኩ ዕድሜየኝ ልፍጅ” ከማለት ያድናል፡፡ በተበዳይ ወገን በኩል ሆነን ያየነው እንደሆነ “ዕድሜ ልኩን ሲጫወትብኝ ኖሮ አሁን እንዲህ እንዲህ ያለ ነገር እንዳይደርስበት ስለፈራ ልታረቅህ ይለኛል፤ ደግሞስ ለስንት ጊዜ ያህል ከበደለኝ በኋላ ለምን ብዬ ነው ይቅርታውን የምቀበለው?” ከሚል ሰይጣናዊ ግብዝነት ይታደጋል፡፡ እናስ ምን እናድርግ?
ንስሃ ለመግባት ቅድመ ሁኔታ የለውም፡፡ አንድ ሰው ንስሃ መግባት የሚያስፈልገው ጥፋት በማጥፋቱ ነው እንጂ ባያጠፋማ ለምን? ለይቅርታ ደግሞ የጥፋት ደረጃ ማነስ ወይ መብዛት ለድርድር አይቀርብም፡፡ ዋናው ከልብ መጸጸትና ጥፋትን እርግፍ አድርጎ መተው ነው፡፡
በኢሳት እንደምንከታተለው ከብአዴኖች ምሥጢር እየሾለከ ወደተቃውሞው ጎራ እንደሚገባ ተነግሯል – ከኢሳት አንጻር የመረጃ ምንጭን የማጋለጥ ምሥጢሩ እስካሁን ባይገባኝም (ይህ ዓይነቱ ልበ ሙሉነት የመረጃ ምንጭን በማድረቅ ረገድ አሉታዊ ሚና እንደማይጫወት ባውቅ ደስ ባለኝ)፡፡ ለማንኛውም ይህ መልካም ጅምር ነው፡፡ በራሱ ግን በቂ አይደለም፡፡ በጣም ኢምንት ነው፡፡ ሙሤን ማስታወስ ይገባል፡፡ ሙሤ በፈርዖን መንግሥት ውስጥ ሆኖ ወገኖቹን ከሚጨፈጭፍ ኃይል ጋር – ሳያውቅ ነው – ይሠራ ነበር፡፡ ማንነቱን ከተረዳ በኋላ ግን 40 ሺህ እስራኤላውያንን ይዞ ከምድረ ግብጽ በመውጣት ሕዝቡን ከአስከፊ አገዛዝ ነጻ አውጥቷል፡፡ ብአዴኖችም ይህን ለማድረግ መረጃ ከመስጠት ባለፈ ብዙ ይጠበቅባቸዋል፡፡ በሰፊው የአማራ መሬት የአፓርታይድንና የፋሺዝምን ሥርዓት ሕዝባቸው ላይ መጫናቸውን ትተው ከነፃነት ታጋዮች ጋር በኅቡዕ ኅብረት መፍጠርና የነፃነትን ጊዜ ማፋጠን አለባቸው፡፡ እስካሁን የሠሩት ጥፋት ፊታቸው ላይ እየተደቀነ ሊረብሻቸው አይገባም፡፡ ያን በንስሃ ማጠብ የሚቻለው የሠሩትን ስህተት የሚክስ መልካም ሥራ ሢሰሩ ብቻ ነው፡፡ አንድ ሰው ንስሃ ሲገባ ያጠፋ የነበረውን ጥፋት ዳግመኛ ላለመሥራት ቃል የሚገባበትና የዚያን ተቃራኒ ደግ ሥራ ለመሥራት በዚያውም በደሉን ለማካካስ (atonement) ሌት ተቀን የሚተጋበት ዕድል ያገኛል፡፡ ንስሃ መግባት ሲጀመር ከሙስናና ከደም ማፍሰስ፣ ንጹሓንን በፖለቲካ ሰበብ ከማሰርና ከማንገላታት መቆጠብ ይገባል፡፡ በተመሳሳይ ቅኝት የሚጓዝ ሕይወት መጨረሻው አያምርም፡፡ ብአዴንም ሆነ ሌላው የወያኔ ተባባሪ እሚበላው ያው አንዲት እንጀራ ናት – ከዚያች አታልፍም፡፡ በተረፈ በቅንጦቱ ረገድ ቢጠጣ ዊስኪና ቢራ ነው፡፡ ቢተኛ ሞዝቮልድ አልጋ ላይ ነው፡፡  ይህ ደግሞ ይሰለቻል፤ በወንጀልና በኃጢኣት ወገንን ሸጦ በሚገኝ የደም ገንዘብ ተንፈላስሶ መኖር የሚቻለው ለተወሰነ ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ሰው የሆነ ሰው በደም ደለል ውስጥ መንቦራጨቁ እየተከሰተለት ሲመጣ በሂደት አእምሮውን የሚያስጨንቅ ነገር ይገጥመዋል፡፡ ጭንቀትን ለመሸፈን ከጧት እስከማታ በመጠጥ ብርጭቆ ውስጥ ቢወተፉ ኅሊና ቀስ እያለ መንቃቱ አይቀርምና በሁለትዮሽ የዞረ ድምር – በመጥፎ ሥራና በመጠጥ – መሰቃየት ይከተላል፡፡ ያኔ የሚከሰተውን የኅሊና ጅራፍ ደግሞ የሚቋቋመው የለም፡፡ ስለዚህ ብአዴኖች ከገባችሁበት አረንቋ በአፋጣኝ እንድትወጡ ብታውቁትም ባታውቁትም በኅያው እግዚአብሔር ስም እማጸናችኋለሁ፡፡ ይህን የምላችሁ ለሕዝብ በማዘን ብቻ እንዳይመስላችሁ፡፡ የምትሠሩት መጥፎ ሥራ ከሚያመጣባችሁ የዕልቂት ማዕበል እንድትተርፉ በቅንነት ለእናንተም በማሰብ ጭምር ነው፡፡ ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢገዛ ነፍሱን ግን ማትረፍ ካልተቻለው ምን ይጠቅመዋል? ይላል መጽሐፉ፡፡ የምሕረት በር ሳትዘጋ አሁኑኑ በንስሃ ታጠቡ፡፡ ሕዝባችሁ አምርሮ ጸልዮኣል፤ ጸሎቱም ተሰምቷል፡፡ እግዚአብሔር ይመስገንና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጸሎት በእግዚአብሔር ፊት ክብርንና ሞጎስን አግኝቶ መልስ የሚሰጥበት ጊዜ ተቃርቧል፡፡ ምልክቶቹም ሁሉ እየታዩ ነው፡፡ አንዱን ልንገራችሁ – ያ ወጣት ብላቴና ረዳት አብራሪ – ምንም ነገር ሳይቸግረው – ከነአውሮፕላኑ ለምን ያን የመሰለ ታሪክ የሠራ ይመስላችኋል? አስቡት፤ አስቡበትም፡፡ በዚህ መልክ ጥሪው የሚተላለፍላቸውና የነፃነት ፍልሚያውን የሚቀላቀሉ ወጣቶች በሠልፍ እየተጠባበቁ ናቸው፡፡
አፄ ቴዎድሮስ በጣም ጨካኝ እንደነበሩ ይነገራል፤ ምናልባትም በሁኔታዎች አስገዳጅነት ወደዚያ ደረጃ ተገፍተውም ሊሆን ይችላል፡፡ እርሳቸውም ያን ጠባያቸውን እንደሚያውቁና ሕዝብን ለመቅጣት ከፈጣሪ እንደተላኩ ለሚቀርቧቸው ይናገሩ እንደነበር ተጽፏል፡፡ አንድ ወቅት መነኮሳትን ከያሉበት ይጠሩና በየተራ እያስገቡ “ለመሆኑ እግዚአብሔር አሁን ምን እየሠራ ነው?” ብለው ይጠይቃሉ፡፡ ሁሉም የመሰለውን ይመልሳል፡፡ እርሳቸውን ያስደሰተች መልስ ግን አንድ ኮሣሣና ለነፍሳቸው ያልሳሱ (ሞትን የናቁ ማለቴ ነው) መነኩሴ “እግዚአብሔር በአሁኑ ሰዓት ቁናውን እየሰፋ ነው!” ሲሉ የተናገሩት ነው፡፡ አዎ፣ እሳቸውም አመኑበት፡፡ የሠሩትን ጥፋት ስለሚያውቁ፣ በሠፈሩት ቁና መሠፈርም ደንብ መሆኑን ስለሚረዱ አንገታቸውን ነቅንቀው በአግራሞት ነበር ያን መልስ የተቀበሉትና ባህታዊውን አመስግነው ወደመጡበት በክብር የሸኙት፡፡ ሌሎችን በትዝብት ዐይናቸው መግረፋቸውን ማስታወስ ካስፈለገ ግን ይሄውና አስታወስኩ፡፡
ወያኔንና ግብረ አበሮቹን ለመቅጣት እግዚአብሔር ቁናውን ሠፍቶ ጨርሷል፡፡ ወያኔን ያሣወረው ትዕቢት መቃብር ካልከተተው የማይለቀው ሆኖ እንጂ የወያኔ ጉድጓድ ከተማሰ፣ ልጡም ከተራሰና የመግነዝ በፍታውም ከተዘጋጀ ቆይቷል፡፡ የሚቀረው ሥርዓተ ግንዘቱና ጉዞ ፍትሃቱ ብቻ ነው፡፡ ያም በቅርቡ ይከናወናል፡፡ ለመሆኑ አሁን ሀገሪቷን ማን እያስተዳደራት እንደሆነ በግልፅ የሚያውቅ አለ? እኔ ከፈጣ ውጪ በሰው ደረጃ ኢትዮጵያን የሚያስተዳድር ሰው አላውቅም፡፡ እርግጥ ነው የሆነ የወያኔ ቡድን መኖሩን አልክድም፤  ዋናው ግን በኪነ ጥበቡ እንደምንለው በዚያ ልዩ መለኮታዊ ኪነ ጥበብ ነው ውለን የምንገባው፡፡ ለማንኛውም መላው የኢትዮጵያ ጠላቶች ሂሳባቸውን የሚያወራርዱበትና በኢትዮጵያ ሰማይ ላይ ወያኔ የናኘው ማንኛቸውም የዘረኝነትና የጎሰኝነት አቧራ እንደጉም በንኖ የሚጠፋበት የነፃነት ዘመን ደጅ ላይ ቆሟል፡፡ ይህን ነፃነት ማንም ፈቅዶ አይሰጠንም፤ ማንምም ታግሎ አይነጥቀንም፡፡ የዕንባችን፣ የጸሎታችንና የመገፋታችን ውጤት፣ በወያኔዎች ደባ ለዓመታት የፈሰሰው ደማችን የሚያመጣልን መለኮታዊ ፀጋ እንጂ የሰው ስጦታ አይደለም፡፡ በየከተማው እንደሚያፋድሱት እነአባ መሸ በከንቱን የመሰሉ ሳይሆን በሩቅ ገዳማትና በሥውር ሥፍራዎች ቀን ከሌት ወደፈጣሪ የሚያለቅሱ አባቶችና እናቶች አሉን፡፡ ቢያንስ እነሱን አያሣፍራቸውምና መልሱን በቅርብ እንጠብቃለን፡፡ ኢትዮጵያችን ጥቂቶች በቁንጣን የሚሰቃዩባትና ሚሊዮኖች በጠኔ የሚረፈረፉባት ሀገር ሆና እንደማትቀር ቃል ኪዳን አለ፤ ሀገራችን የቃል ኪዳን ምድር ናት፡፡ እናም አይዞን!!!
ብአዴኖች ግን ወደ ኅሊናችሁ ተመለሱ፡፡ ይህ ጥሪየ ዘርን መሠረት ባያደርግብኝ ደስ ባለኝ፡፡ ነገር ግን ይበልጥ የሚያሣዝኑኝ እነሱ በመሆናቸው ነው ይህን የተለዬ ጥሪ እነሱ ላይ በማተኮር ማስተላለፍ የወደድኩት፡፡ ፈጣሪ መንሹን ሊጨብጥ – ገለባን ከምርቱ ሊለይ የማበራያ ዐውድማውን ለቅልቆ ጨርሷል፡፡ ልብ ያለው ልብ ይበል፤ ከያዘው አሼሼ ገዳሜና አሥረሽ ምቺውም ይመለስ፡፡ የዚህ ዳንኪራና ጮቤ ወጪ የሚሸፈነው ከምሥኪኑ ሕዝብ እየተመዘበረና በሙስና እየተዛቀ መሆኑ የማይካድ ነው፡፡ በዚህ የጥፋት መንገድ እየነጎዳችሁ ያላችሁ ወገኖችም ለቁሣዊ ፍላጎቶቻችሁና ለሰይጣናዊ ሱሶቻችሁ ልጓም አብጁላቸው፡፡ ይህን ስል ወንድም በወንድሙ ላይ የሚፈጽመውን ግፍና በደል ያቁም፣ ወደኅሊናውም ተመልሶ ለሁሉም እኩል በሆነ ህግ ይተዳደር ለማለት እንጂ ሃይማኖታዊ ንስሃ ግቡና ፁሙ ቁረቡ ለማለት ፈልጌ አይደለም፡፡ ለዚያ ዓይነቱ ስብከት ይህ መድረክ ምቹ እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ ሰላም ክረሙልኝ፡፡


“ለውጡ እንደቀረበ ጥርጥር የለኝም” ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር

March 27, 2014

ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ከሁለት ወር በፊት ወደ አሜሪካና የአውሮፓ አገራት ለስራ ጉብኝት ሄደው ነበር፡፡ አሁንም ወደ አሜሪካ ጉዞ ሊያደርጉ እንደሆነ ሰምቻለሁ፡፡ የአሁኑ ጉዞ አላማ ምንድን ነው?
Eng. Yilkal Getnet Semayawi party chairman with Negere Ethiopia newspaper
ኢ/ር ይልቃል ጌትነት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር
ኢንጅነር ይልቃል፡- መጀመሪያ ያደረኩት ጉዞ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች የፓርቲውን አላማና ፕሮግራም፣ የሰራናቸውን እንዲሁም ወደፊት ልንሰራቸው ያሰብናቸውን ስራዎች፤ ሰማያዊ እንደ አዲስ ኃይል ሲመጣ የቆመላቸው ሀሳቦችና እምነቶች ምን እንደሆኑ ለማስተዋወቅ ታስቦ የተደረገ ነበር፡፡ የአሁኑ ግን ከበፊቱ የተለየና ለሰማያዊ ሊቀመንበር በሚል በቀጥታ በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት የተደረገ ግብዣ ነው፡ ፡ የአሁኑ ወጣት የአፍሪካ መሪና ወደፊትም ለአገራቸው መሪ ሊሆኑ የሚችሉ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ጥሩ ስራ የሰሩ፣ በውድድር ከተመረጡ በኋላ በአሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንት በሚደረግ ምርጫ መመዘኛዎቹን ለሚያሟሉ ሰዎች የሚሰጥ እድል ነው፡፡ በመመዘኛዎቹ መሰረት በማሸነፌ የአሜሪካ መንግስት ሙሉውን ወጭ ሸፍኖ ለሶስት ሳምንት በአሜሪካ የመንግስት አወቃቀርና ዴሞክራሲን ጨምሮ በተግባር የሚሰጡ ስልጠናዎችን የማግኘትና፣ የአሜሪካ መንግስት ባለስልጣናትም ባሉበት ከተለያዩ ተቋማት ጋርም ለመገናኘት እድል ይኖረኛል፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ከሌሎች የአፍሪካ አገራት የፖለቲካ መሪዎች ጋር ተወዳድረው ነው ያሸነፉት ማለት ነው?
ኢንጅነር ይልቃል፡- አዎ! ግን ሌሎች ያሸነፉ ተጨማሪ ሰዎች ይኑሩ አይኑሩ አላውቅም፡፡ ይህ የፕሬዝዳንቱም ‹ኢኒሸቲቭ› ይመስለኛል፡፡ ለእኔ ግን የተሰጠኝ አዲስ ትውልድ አመራሮች፣ ወደፊትም በአገራቸው መሪ መሆን የሚችሉ፣ ስትራቴጅካሊ የሚያስቡ፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ላይም ሆነው መልካም ስራ ለሰሩ ሰዎች የሚሰጥ ልዩ የጉብኝት እድል ነው፡፡ በአጠቃላይ ውድድርም ተደርጎ የሚወሰድ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- የአሜሪካ መንግስት ይህንን እድል ሲሰጥ እርስዎ እንደ መሪም ሆነ ሰማያዊ እንደ ፓርቲ ያሸነፋችሁበትን ዋና ዋና መመዘኛዎች ነግረዋችኋል?
ኢንጅነር ይልቃል፡- ሲመርጡኝ ዝርዝር መረጃዎችን ወስደዋል፡ ፡ መሰረታዊ የሚባሉትን ለምሳሌ ያህል የፖለቲካ ቆይታዬ፣ የትምህርት ዝግጅቴን፣ በፖለቲካው ውስጥ የነበረኝን ተሳትፎ የመሳሰሉትን መረጃዎች ለእጩነት በቀረብኩበት ወቅት ከእኔ ወስደዋል፡፡ ከዛ በኋላ ያስመረጠኝን ዝርዝር መስፈርት አላውቅም፡፡ ነገር ግን ወጣት (እስከ 45 አመት ባለው ውስጥ)፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ መልካም ስራ የሰራ፣ ወደፊትም የአገሩ መሪ ሊሆን የሚችል የሚሉት ዋና ዋና መመዘኛዎች እንደሆኑ አውቃለሁ፡ ፡ ይህም በተለይ ከሰማያዊ አንጻር ከሁለት ነገሮች አኳያ እንድናየው ያደርጋል፡፡ አንደኛው በምስራቅ አፍሪካ ያለውን ፖለቲካና እስካሁን ጠቅልሎ የያዘው ኢህአዴግ ነበር፡፡ ሌላ አማራጭ እንደሌለ አድርጎ ነበር የሚያየው፡፡ ሆኖም እንደዚህ አይነት እድል እንደ አሜሪካ ባለ ትልቅ መንግስት የተቃዋሚ መሪ የተለየ ስራ ሰርቷል ተብሎ ሲጋበዝ ሰማያዊ ፓርቲ አዲሱንና ወደ ፖለቲካ ያልመጣውን ትውልድ ወደ ፖለቲካው ለማምጣት በሚያደርገው ጥረት እንደ አንድ ማበረታቻ ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል፡፡ ይህ በሌሎች መስኮች ከምናደርጋቸው የዲፕሎማሲ ስራዎች በተጨማሪ ለሰማያዊ ፓርቲ ከሌሎች ፓርቲዎች በተለየ ይህኛው ግብዣ ሲደረግለት ለሁለተኛ ጊዜ ነው፡፡
ከአሁን በፊት ለሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በአሜሪካ ኤምባሲ ውስጥ የ35 አገራት ኤምባሲዎች የ‹ኢትዮጵያ ፓርትነርስ ግሩፕ› የሚባለው ሲደረግ በአመታዊ ስብሰባቸው ላይ ዋና ተናጋሪ ሆኜ ስለ ኢትዮጵያ ፖለቲካና ስለ ሰማያዊ ፓርቲ ዋና የትግል እንቅስቃሴና የወደፊት አላማችን እንዳስረዳ የተለየ እድል ተሰጥቶኛል፡፡ ይህም ለፓርቲው ሌት ተቀን ለሚሰሩ ወጣቶች፣ እንዲሁም ሁል ጊዜም ቢሆን ወጣቱ ተከታይና ጀሌ እግረኛ ከመሆን አልፎ ራሱ ኃላፊነት የሚወስድ፣ መምራትና የራሱን መሪዎች ማውጣት የሚችል ትውልድ መምጣቱን የሚያሳይ መልካም ጅምር ነው፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- የአሜሪካ መንግስት ከ9/11 እንዲሁም ከ1997 ዓ.ም ምርጫ በኋላ ሶማሊያ ውስጥ ባለው ጥቅም ኢህአዴግ ላይ እስከመጨረሻ ግፊት ማድረግ አልቻለም ነበር፡፡ አሁን ለእርስዎና ለፓርቲዎ ይህን እድል ሲሰጥ ለኢህአዴግ የሚያስተላልፈው መልዕክት ምንድን ነው? የተቃውሞ ጎራውም ቢሆን እስካሁን የሚመራው በ1960ዎቹ ፖለቲከኞች ነው፡፡ አሁን የአሜሪካ መንግስት ይህን እድል ለእርስዎ እንደ መሪና ለሰማያዊ እንደ ወጣት ፓርቲ ሲሰጥ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚኖረው አንድምታ ምንድን ነው?
ኢንጅነር ይልቃል፡- እንግዲህ ይህን ጉዳይ ህዝቡም ሆነ የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ማህበረሰቡ እየተረዳው የመጣ ይመስለኛል፡፡ ባለፈው አርባ አመት በገዥውም ሆነ በተቃዋሚው ያለው በአንድ አይነት እድሜና የግራ ርዕዮት የሚሽከረከር ነበር፡፡ ይህም የኢትዮጵያን ፖለቲካም ሆነ ኢትዮጵያን በሁሉም መመዘኛዎች ወደ ፊት ሊያራምድ አልቻለም፡፡ እንዲያውም ጥላቻ፣ ቂምና ቆርሾ፣ የእስር በእርስ መጠላፍና የዜሮ ድምር ፖለቲካ ሆኖ ቆይቷል፡ ፡ ያ ትውልድ ያላመጣውን ውጤትም ወጣቱ ያመጣዋል የሚል ነው፡ ፡ ኢትዮጵያ የወጣት አገር ነች፡፡ 70 ከመቶ የሚሆነው ከ35 አመት በታች ነው፡፡ ይህ የህብረተሰብ ክፍል በውክልና ደረጃም ሆነ አዲስ አስተሳሰብና ከበድ ያለ ነገር ይፈልጋል፣ ከዓለም ከተለያየ አቅጣጫ መረጃ ያገኛል፣ በአስተዳደጉም አንጻራዊ ነጻነት አለው፣ በአመለካከትም ቢሆን ይህ የህብረተሰብ ክፍል ወደ ፊት እየመጣ ነው፡፡ ከዚህም አንጻር በታክቲክም ሆነ በአመለካከት ይህን የህብረተሰብ ክፍል መደገፍ የሚያዋጣና አይቀሬነቱን የሚያሳይ ይመስለኛል፡፡
ዋናው የኢህአዴግ የፖሊሲ መሰረት ማታለል ነው፡፡ ‹‹እኔ ከሌለሁ ኢትዮጵያ ትበታተናለች፡፡›› በሚል የምስራቅ አፍሪካንም ሆነ የሶማሊያን የሽብር ሁኔታ እንደ ማታለያ እየተጠቀመ፤ እነሱ የስጋት ፖለቲካ ውስጥ መግባታቸውን ስለሚያውቅ እሳት የማጥፋት ስራ ነበር የሚሰራው፡ ፡ ይህ ግን መሰረታዊ መፍትሄ የሚያመጣ ሳይሆን ነገሮችን እያዳፈነ፣ ችግሩን እያባባሰ በመሆኑ እንዲሁም የጠቅላይነት ፖለቲካን ለቀጠናውም ሆነ ለኢትዮጵያ እየጠቀመ አለመሆኑ የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ኃይሎች ተረድተውታል፡፡ አማራጭ የፖለቲካ ኃይልና መሰረታዊ የሆኑ የዴሞክራሲ መመዘኛዎችን ማምጣት፣ መሰረታዊ የሆኑ የዜጎች ልማትና ዴሞክራሲ ማፋጠን፣ በአቻነት የተመሰረተ ግንኙነትን ካልሆነ በስተቀር በጉልበትና በጠብመንጃ የሚደረገው አገዛዝ እንደማያዋጣ የተረዱበት ጊዜ ነው፡፡ አሜሪካኖች አባቶቻቸው የሞቱበት ነገር (the ideals of ower founding fa­thers) የሚሉት የሰውን ልጅ መብትና የሰብአዊ መብት ማክበር ለሁሉም አገራት መድሃኒት መሆኑን ራሳቸው አፍጋኒስታንና ኢራቅ ውስጥ በነበሩበት ወቅት አይተውታል፡፡ በየመን፣ በምስራቅ አፍሪካዋ ሶማሊያም ቢሆን ተመሳሳይ የእሳት ማጥፋት ፖለቲካ ለውጥ እንዳላመጣ ተገንዝበውታል፡፡ በየ ደረጃው በህዝብ ተሳትፎ የሚያድግ ዴሞክራሲና በዜጎችም ይሁን በአገራት መካከል በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ግንኙነት መምጣት ካልቻለ አፋኝነት እንዳልጠቀመ የተረዱበት ጊዜም ይመስለኛል፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- እስካሁን ድረስ ዲያስፖራውም ሆነ አገር ውስጥ ያው የተቃውሞ ኃይል ድምጹን ለማሰማት ሲሞክርም የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ትኩረት አናሳ እንደነበር ይታወቃል፡፡ እናንተ ይህንን አጋጣሚ ስታገኙ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ በስርዓቱ ላይ ትኩረት እንዲሰጥ በአጽንኦት የምታስረዱት ምንድን ነው?
ኢንጅነር ይልቃል፡- አንደኛ ከመንግስት ጋር መስራት በሚሉት መርህ ላይ ኢህአዴግ ስልጣን ስላለው ብቻ በአጭር ጊዜ የጮሌነት ግንኙነት፣ ከዛም በኋላ ለአሸነፈውና የኃይል ሚዛኑ ካደላው ጋር ግንኙነት የማድረግ ዋናው የዘመኑ መገለጫ፣ ስግብግብነትን መሰረት ያደረገ የካፒታሊዝም መርህ ስለሆነ በየትኛውም መንገድ ተሂዶ የአገርን ጥቅም ማስጠበቅ የሚባለው እንደማይጠቅም ማስረዳት እንፈልጋለን፡፡ መንግስት ቢያልፍም በህዝብ ላይ የሚደርሰው በደልና ግፍን እያዩ እንዳላዩ ማለፍ ለዘላቂ የአገራቸው ጥቅም እንደማይበጅ፣ ሁል ጊዜም ቢሆን ግንኙነት መመስረት ካለበት ከአገሪቱና ከአገሪቱ ህዝብ ጋር እንደሆነ፣ ግንኙነቱ ታሪካዊና የህዝብን መሰረታዊ መብቶች ጠብቆ የሚደረግ እንጅ ከአንድ ቡድን ጋር የሚደረግ ግንኙነት ኢትዮጵያን ለመሰለ ታሪክና ክብሩን ለሚወድ ህዝብ ውሎ አድሮ የማይጠቅም መሆኑን፣ በአጠቃላይም የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ፣ መሰረታዊ መብቶችና ሀሳቦች በሚከበርባቸው መልኩ የሚያራምድ አይነት አስተሳሰብን መሰረት ያደረገ ግንኙነት እንዲያደርጉ ነው በዋነኛነት ማሳሰብ የምንፈልገው፡ ፡ ከአንድ ቡድን ጋር የሚደረግ የአጭር ጊዜ ግንኙነት ራሳቸውንም እንደሚጎዳቸው፣ በቀጠናው ይገኛል የሚባለውን መረጋጋትና ሰላምም ሊያመጣ እንደማይችል እንዲረዱት እንፈልጋለን፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ይህን አጋጣሚ በመጠቀም ከዲያስፖራው ጋር በመገናኘት የምትሰሩት ሌላ ድርጅታዊ ስራስ ይኖር ይሆን?
ኢንጅነር ይልቃል፡- አሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ባደረገልኝ ግብዣ ላይ ለሶስት ሳምንት እቆያለሁ፡፡ የትኬትና ተመሳሳይ ጉዳዮችን ከሚሰሩት የአሜሪካ ሰዎች ጋር ስንነጋገር ከዚህ ውጭ አንድ ወር ያህል አሜሪካን አገር እንደምቆይ ገልጨላቸዋለሁ፡፡ በዚህም አጋጣሚ ባለፈው በአየር ንብረትና በድካም ምክንያት ያላዳረስኳቸው ቦታዎች ላይ ስብሰባ የማካሄድ ሀሳብ አለኝ፡፡ ምን አልባትም ወደ ለንደንና ካናዳ ልሄድ የምችልበት አጋጣሚ ይኖራል፡፡ ይህ እንግዲህ ከዚህ ካለው ስራ፣ ከጉዞ ሰነዶችና ከጊዜም ጋር ተደማምሮ በሂደት የምናየው ይሆናል፡፡ በድርጅታዊ ጉዳይ ላይ ለመስራት እቅዱም ሀሳቡም አለን፡፡ እዚያው ያሉት ደጋፊዎቻችንም በጉዳዩ ላይ እየሰሩበት ይገኛሉ፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ወደ ሌላ ርዕሰ-ጉዳይ ልውሰድዎትና፣ ባለፈው እሁድ ሴቶች በተሳተፉበት የታላቁ የጎዳና ላይ ሩጫ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስታችኋል በሚል ከተያዙ በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ ‹‹መረጃን ለማሰባሰብ›› በሚል ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል፡፡ ይህን እንዴት ያዩታል?
ኢንጅነር ይልቃል፡- በዚህ ጉዳይ ከማዘንና ከማፈር ውጭ የምለው ነገር አይኖርም፡፡ ኢህአዴግ በዴሞክራሲ እየማለ፤ ለዜጎች እኩልነት፣ ለጎሳና ሀይማኖት እኩልነት፣ ለሴቶች እኩልነት ጠብመንጃ አንስተን በመዋጋት የልጅነት እድሜያችንን በበርሃ አጥፍተናል እያሉ፤ 23 አመት ቆይተው ግን ሴቶች ለነጻነት በተሰለፉበት ቀን ስለ አገራቸው አንድነትና ስለ መሰረታዊ መብቶች የጠየቁ ሰዎችን እስር ቤት ሲያጉሩ ምን ያህል የማይማርና ወደ ኋላ እየተንደረደረ የሚገኝ፣ የራሱን ሞት እየጠበቀ ያለ መንግስት እንደሆነ ለመረዳት ችያለሁ፡፡ ከዚህ ውጭ ምንም አዲስ ነገር ባላይበትም ትግሉ ውስጥ መግባታችን ምን ያህል ትክክል እንደሆነ ግን አረጋግጦልኛል፡፡ እሱ የማይፈልገው ሀሳብ ከሆነ ለምንም ነገር የማይመለስና ሴት፣ ህጻን፣ ህጋዊም ሆነ አልሆነ ለእሱ ምኑ እንዳልሆነ፣ በስልጣኑ ላይ ለመጣ ወደኋላ የማይመለስ መንግስት መሆኑን ተረድተንበታል፡፡ ይህም ዘላለም ለመጨቆን የተዘጋጀ መንግስት በመሆኑ ወደ ትግል መግባታችን ትክክል መሆኑ እንድንረዳ አድርጎናል፡፡ ይህም ለትግሌ መሰረት ስንቅ ከመሆኑ በተጨማሪ በኢህአዴግ ላይ አዝኛለሁ፣ አፍሬያለሁ፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ባለፉት ሁለት አመታት አረቦቹ አብዮት አካሂደዋል፡፡ ዩክሬን ውስጥ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ለውጥ ነበር፡፡ ለባለፈው አንድ አመት ተኩል ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥም የተቃዋሚዎች እንቅስቃሴ በአንጻራዊነት እየተጠናከረ ነው፡፡ አመጽ እየተለመደ ከመምጣቱ፣ የኑሮ ውድነትና ጭቆናው ከመባባሱ ጋር ተዳምሮ ኢትዮጵያ ውስጥ በቀጣይነት የሚመጣውን ለውጥ እንዴት ነው የሚያዩት?
ኢንጅነር ይልቃል፡- መቼም እኔ የምናገረው ምኞቴንና የምሰራበትን ነገርም ነው፡፡ ከዛ ውጭ ያለውን ነገር ብንወደውም ባንወደውም ራሱ መምጣቱ ስለማይቀር፣ ስለ እሱ መናገር ለእኛ አወንታዊ አስተሳሰብ ስለማይበጅም ሆነ እርግማት ተናጋሪ ስለሚያሰኝ ማድረግ የሚቻለውን በጎ ነገር እያደረግን ብንሄድ የተሻለ ነው የሚሆነው፡፡ እንደ ኢትዮጵያ አይነት በዓለም የመጨረሻ ድሃ ለሆነ፣ ብዙ የጎሳና የእምነት መቃቃር በተፈጠረበት አገር፣ በሩቅም በቅርብም የኢትዮጵያን መረጋጋት የማይወዱ አካላት ባሉት ቀጠና ላይ ሆነን፣ እርስ በራሳችንም በተለያዩ የታሪክ ግጭቶች ውስጥ እያለን እንዲህ አይነቱ ለውጥ ባይኖር ደስ ይለናል፡ ፡ ነገር ግን አልፈለግነውም ማለት አይከሰትም ማለት አይደለም፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ እንዲህ አይነት ጉዳይ እንዳይከሰት የተጠና፣ አስቀድሞ በድርጅቱ የተመራ፣ ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ የሚካሄድ የስልጣን ሽግግር እንዲኖር ሌት ተቀን ይሰራል፡ ፡ ሆኖም ገዥው ፓርቲ በጠቅላይነትና ባታላይነት እቀጥላለሁ ካለ ህዝቡ ውስጥ መሰላቸት በግልጽ ይስተዋላል፣ ችግሮች ከዕለት ዕለት እየተደራረቡ ነው፣ ህዝብ አገሩ ውስጥም ሆነ በአካባቢው የለውጥ ምሳሌዎችን እያየ ነው፣ ችግሩ መሸከም ከሚችለው በላይ ሆኖበታል፡፡
በመሆኑም እነዚህ ለለውጥ መሰረት የሆኑ ነባራዊ ሁኔታዎች እየመጡ ስለመሆኑ የፖለቲካ ተንታኝ መሆን አያስፈልግም፡፡ በዚህ ሁኔታ አገዛዙ ውስጥ ያሉት ሰዎች የሚፈተኑት ከመግዛትና ከመጨቆን አስተሳሰባቸው ወጥተው ወደ እውነታው ቀርበው ለለውጥ ይዘጋጃሉ ወይንስ በተለመደው ግትርነት ይቀጥላሉ? በሚለው ነው፡፡ በሌላ በኩል እኛም ደግሞ አማራጭ ሆነን፣ እነሱን ሳናስደነብር፣ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር እንዲፈጠር መቻቻልና ይቅር ባይነቱ ኖሮን አገራችንን ማዳን የምንችልበት ሆደ ሰፊነትና አስተዋይነት ፖለቲካ በሁለታችንም በኩል ይጠበቃል፡፡ ግን ይህን ታሪካዊ ጉዳይ ከሁለታችን አንዳችን ከሳትነው ሂደት በተፈጥሮ የሚያመጣው ጉዳይ አለ፡፡ ሁሌም ታሪክም፣ ስልጣኔም፣ የሰው ልጅም ይወለዳል፣ ያድጋል፣ ይለወጣል፡፡ ልቡን የደፈነ ሰው ካልሆነ በስተቀር ለውጥ አይቀሬ ስለመሆኑ የሚጠራጠር ያለ አይመስለኝም፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ምን ያህል ንብረት ይወድማል፣ ምን ያህል የሰው ነፍስ ይጠፋል፣ በሂደቱ ምን ያህል የተጠና እና ለአገራችን የሚጠቅም ለውጥስ ይመጣል የሚለው ነው እንጂ የሚያስጨንቀኝ ለውጡ እንደቀረበ ጥርጥር የለኝም፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ይህ ለውጥ ቢከሰት ለውጡን በሚገባው መልኩ ለማስተናገድና ለመምራት ትክሻ ያለው አካልስ አለ ብለው ያስባሉ?
ኢንጅነር ይልቃል፡- እኛ ሰማያዊ ይህን ለውጥ መሸከም የሚችል ትክሻ አለው ብለን ነው የምናምነው፡፡ በእኛ አገር ይህንን አይነት ነገር ደፍረን ስንናገር በሁሉም ወገኖች ዘንድ አይወደድልንም፡ ፡ ለምን እንደማይወደድም ይገባናል፡፡ ባይወዱትም መናገር አለብን፡፡ ከማይወደድበት ምክንያት የመጀመሪያው በጭቆና መንፈሳችን መላሸቁ ነው፡፡ ስለዚህ ‹‹ይቻላል!›› ማለት እንደ ቅዠትና እብደት ይቆጠራል፡፡ ይህም ‹‹ይቻላል›› የሚለውን ከመጥላት፣ ከጭቆናው መብዛት፣ በተደጋጋሚ ከመክሸፍ የመጣ የአቅመ ቢስነት ችግር እንጅ የእኛ ችግር አይደለም፡፡ እነዚህ በጭቆና አስተሳሰብ ስር የወደቁት የእኛን አመለካከት እንዲይዙ ጥረት በማድረግ በተደጋጋሚ ስለ ጉዳዩ እንናገራለን፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ድርጅት ሆነን ስንቋቋም እኛ የተሻለ አማራጭ አለን፣ አገርና ህዝብን ወደተሻለ ደረጃ እናደርሳለን ብለን ነው፡፡ ስለሆነም ስለ ራሳችን ስለ ድርጅታችን በሙሉ ልብ ‹‹እንችላለን!›› ስንል፣ ሌሎች ድርጅቶች ቅር ይላቸዋል፡፡ ይህ ከፖለቲካ እውቀት ማነስ የመጣ ነው፡፡ እኛ እንደ ድርጅት ተቋቁመን ‹‹እንችላለን!›› ካላልንና ህዝብና አገርን ወደ ተሻለ ደረጃ እንደምናደርስ መናገር ካልቻልን ህዝቡ እንዴት ሊከተለን ይችላል? ለምንስ ጊዜያችንን እናጠፋለን?
ሰማያዊ ፓርቲ ባለፈው አንድ አመት ተኩል የፖለቲካ ነገር በቀላሉ የማይመዘን ሆኖ እንጅ መብት መጠየቅን፣ መነቃቃትን፣ ከአይቻልም ባይነት ይቻላል ባይነትን፣ አዲሱ ትውልድ የራሱን እጣ ፈንታ ለመወሰን በድርጅት የመታቀፍንና የመታገልን በአዲስ መልክ ይዞ ብቅ ብሏል፡፡ ይህም ለረዥም ጊዜ በወደቀና በከሸፈ የፖለቲካ አመለካከት ውስጥ በጣም ረዥም ጊዜን የሚጠይቅ ስራ ነው፡ ፡ ይህም በቀላሉ የተገኘ ሳይሆን በርካታ የሰማያዊ ወጣቶች የራሳቸውን የህይወት አማራጭ ትተው በዚህ ጉዳይ ላይ ጥርሳቸውን ነክሰው፣ በግልጽ የፖለቲካ አመለካከት ሌት ተቀን ከአገዛዙ ጋር እየተጋፈጡ፣ እየታሰሩ፣ ዋጋ እየከፈሉ የመጣ ነገር ነው፡፡ በዚህ ሂደታችን ውስጥ ወጣቶች ወደ ፖለቲካው እንዲመጡ ማነቃቃት ችለናል፡ ፡ ከትልልቅ የአደባባይ ምሁራን፣ ከዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰሮች፣ ከውጭም ከአገር ውስጥም ክብርና ይሁንታን አግኝተናል፡፡
ከክርስትናም ሆነ እስልምና ሀይማኖት መሪዎችና አማኞች አካባቢም መከበር ችለናል፡፡ ከዓለም አቀፍ ማህበረሰቡም ቢሆን እንደሚታየው ወጣትና ወደፊት አገራቸውን መምራት የሚችሉ ተብለን መወደስና መሸለም ችለናል፡፡ የዓለም አቀፉም ሆነ የአገር ውስጥ ሚዲያው እንደ አንድ የፖለቲካ ኃይል አይቶናል፡፡ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ለስልጣን መሰረት የሆኑት ነገሮች እነዚህ ናቸው፡፡ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ወጣቶች፣ የአደባባይ ምሁራን፣ ዓለም አቀፍ ማህበረሰቡና ሚዲያው ሰማያዊን እንደ አንድ የፖለቲካ ኃይል ማየት ችሏል፡፡ በእነዚህ ኃይሎች ተቀባይነት ካገኘ አገሪቱን ለመምራት የሚያቅተው ምንም ነገር አይኖርም ማለት ነው፡፡ የራሱ አላማ፣ የራሱ ፕሮግራም አለው፡፡ ይህን ለማስፈጸም የሚችል ቆራጥ አመራር አለው፡፡ በእርግጥ ኢትዮጵያ ትልቅ አገር ብትሆንም ሰማያዊ ለውጥን በአግባቡ ለመረከብና ለመምራት የሚያስችል አቅም እንዳለው መግለጽ እፈልጋለሁ፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ዲያስፖራው የገንዘብም፣ የመረጃና የእውቀትም አቅም እንዳለው ቢታመንም ከ1997 በኋላ ግን ለአገሪቱ ፖለቲካ አሉታዊ ጎን እንደነበረው በስፋት እየተጠቀሰ ነበር፡፡ በአሁኑ ወቅት እናንተ ከዲያስፖራው ተቀባይነት እያገኛችሁ ነውና መልካም ጎኑንና ፖለቲካውን ላይ አለው የሚባለውን አሉታዊ ተጽዕኖ እንዴት ነው የምታስታርቁት?
ኢንጅነር ይልቃል፡- ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ አንድን አካል በቅራኔ መድቦ መታገል የተለመደ ባህል አይደለም፡፡ ለምሳሌ ሰማያዊ ፓርቲ ወጣቱ ላይ ያተኩራል ሲባል፤ በየትኛውም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ግን የሽማግሌዎችን፣ የአደባባይ ምሁራንንና የትልልቅ ሰዎችን ድጋፍ አግኝቷል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የሰማያዊ አመራር አገር ውስጥ ቢሆንም የራሳቸው የፖለቲካ ፋይዳ፣ ካፒታል፣ አንጻራዊ ነጻነት ያላቸው፣ የአገራቸውን ነጻነት በቀናነት የሚመኙ፣ በመረጃው በኩል ቅርብ በመሆናቸው በዲፕሎማሲው መስክ ትልቅ እገዛ ከሚያደርጉት በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ተቀባይነት አለው፡፡ ይህን ጉዳይ ሚዛናዊ በመሆነ መልኩ የመምራት ችግር ካልሆነ በስተቀር በውጭ የሚገኙት ኢትዮጵያውያን አገር ውስጥ ከሚገኙት የተለዩ አይደሉም፡፡ አገር ውስጥ እንዳለው ሁሉ ውጭ ያለውም የአገሩ ሁኔታ ያሳስበዋል፡፡ የአገር ውስጡ የራሱ ሚና ይኖረዋል፡ ፡ በውጭ የሚኖረው ደግሞ የራሱ የሆነ ሚና ይኖረዋል፡፡
እነዚህን ሁለት ጉዳዮች አገር ውስጥ ያለው በተገቢው መንገድ ማስተባበር ይኖርበታል፡፡ አገር ውስጥም ውጭም ያለውን አጣጥሞ የማስኬድ ስራ ነው የምንሰራው፡፡ መሪነት ሲባል እኮ የሰዎችን አቅም ለግብ መጠቀም ነው፡፡ የትኛውም የማህበረሰብ ክፍል፤ አርሶ አደር፣ ነጋዴ፣ ውጭ ያለ፣ አገር ውስጥ የሚገኝ፣ የተማረም ይሁን ያልተማረ፣ ሁሉ ጥቅምና ፍላጎት አጣጥሞ ወደፊት መምራት ነው ዋናው ስራችን፡፡ ዲያስፖራውንም እንደ አፈንጋጭ፣ እንደ አጥፊና ለኢትዮጵያ ችግር ተጠያቂ አድርጎ ማየት በሰማያዊ ፓርቲ የተለመደ አይደለም፡፡
ባለፈው ጉብኝት ባደረኩበት ወቅት የዲያስፖራውን ድክመትና ስህተቶች ያልኳቸውን በአደባባይ ተናግሬያለሁ፡፡ እነሱም ከጊዜ ብዛትና ከመውደቅ መነሳት ብዙ የተማሩት ነገር አንዳለ ተረድቻለሁ፡፡ ይህን ጉዳይ አጣጥሞ የሚመራ አስተዋይ፣ ብልህና ሆደ ሰፊ መሪ ያስፈልጋል፡፡ ይህ እኛ እንደ ድርጅት አዲስ ብንሆንም በፖለቲካው መውደቅ መነሳት ከ1997 ዓ.ም ጀምረን የነበርን ሰዎች በመሆናችን የተፈጠሩትን ነገሮች በቅርበት እናውቃቸዋለን፡፡ ባገኘነው በቂ ልምድም ጉዳዩን በጥበብ መያዝ ችለናል፡፡ ወደፊትም በጥሩ ሁኔታ እንሄዳለን የሚል እምነት አለኝ፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- የዲያስፖራውን ጉዳይ ካነሳን አይቀር፤ ከ1997 በኋላ በነበረው ፖለቲካ ተስፋ ከመቁረጡም ባሻገር በቅንጅት አባል ፓርቲዎች መካከል ተከፋፍሎ እንደነበር ይነገራል፡፡ ባለፈው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ዲያስፖራውን እንዴት አገኙት? አሁንስ ምን አዲስ ነገር ይጠብቃሉ?
ኢንጅነር ይልቃል፡- እኔ ስሄድ የምጠብቀው አነስ ያለ ነገር ነው፡፡ ትግል ውስጥ ስትገባ ያለውን አስቸጋሪ ነገር ቀይሬ ከዚህኛው ወደዚህኛው አሻሽለዋለሁ ነው እንጂ፣ ይህኛው አለኝ ብለህ አትኩራራም፡፡ የዓለም የመጨረሻ ድሃ አገር ነን፡፡ የፖለቲካ ባህላችን አስቸጋሪ ነው፡፡ የእምነት አገር ነው፡፡ የ1966 አብዮት የፈጠረው ችግር አለ፣ 1997 የፈጠረው ችግር አለ፡፡ እንደ ፖለቲከኛ ይህን ችግር እለውጣለሁ የሚል እምነት ይዤ ነው የተነሳሁት፡ ፡ ከላይ የተጠቃቀሱት ችግሮች በአንድም ሆነ በሌላ ምክንያት መኖራቸውን ብገነዘብም አንድ መልካም ነገር መኖሩ ሌሎቹን ችግሮች ያቃልላቸዋል፡፡ ለምሳሌ ያህል የኢሳት መኖር በአገሩ ጉዳይ ተስፋ ቆርጦ የነበረውን የዲያስፖራ ማህበረሰብ መረጃ እንዲኖረውና ተነቃቅቶ እንዲጠብቅ በማድረግ መልካም ስራ አከናውኗል፡፡ በተለይ የሰማያዊ ወጣቶች ‹‹አይቻልም!›› በተባለበት አገር ትንሽም ነገር ሲሰሩ ሲታይና ይህም የማህበረሰባዊ ድህረ- ገጾችን ጨምሮ ለበርካታ ሰዎች መድረሱ አድናቆት አስገኝቶልናል፡፡
እንዲያውም እኛን ከልክ በላይ የማወደስና ነጻ አውጭ አድርጎ የማየት እንጂ በእኛ ላይ ቅሬታ ያለው ሰው የለም፡፡ ለዚህም እድሜያችን እንደመልካም አጋጣሚ ሊታይ የሚችል ነው፡ ፡ እድሜያችን፣ በኢህአፓ፣ በደርግ፣ በመኢሶን የተቋሰለው ትውልድ አለመሆናችን ለፍረጃ ክፍተት አልሰጠም፣ ሰውም እንዲጠላን ምክንያት አልሆነም፡፡ ይህ በእኛ ስራ ሳይሆን በትውልድ ያገኘነው መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ እንዲያውም በሰማያዊ በኩል እንደ ችግር ይቆጠራል ከተባለ ሁሉም ኃይል የራሱ ለማድረግ ስለሚሞክር ሚዛን የማስጠበቅና ማዕከል ላይ ሆኖ የማሰባሰብን ሚና ነው እየተወጣ የሚገኘው፡፡
ከዚህ ውጭ ከርቀት ሆነው ወጣትነታችን ሲያዩ የቆዩና ትውልዱ ጫታም፣ ስደተኛና ይህ ነው የሚባል ቁም ነገር የማይሰራ የሚመስላቸው የነበሩ ሰዎች ስንቀራረብ ትልቅ አድናቆት ችረውናል፡፡ መጀመሪያ ላይ በሆይ ሆይታና በጮኸት የተሰባሰብን ቢመስላቸውም ስለ እኛ ካወቁ በኋላ ‹‹እንዲህ አይነት ወጣትም አለ?›› በሚል ተገርመውብናል፡፡ በመልካም ሁኔታም ነው የተቀበሉን፡፡ እስካሁን ያለው ተስፋ ሰጭ ቢሆንም አሁንም ትልቅ ስራ ይጠይቃል፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ያለፉት የፖለቲካ ውድቀቶች በመፍራት ወጣቱም ሆነ ዲያስፖራው ፓርቲዎችን ለመቅረብ ይፈራል፡፡ ‹‹ምንድን ነው ማረጋገጫችን?›› የሚል ጥያቄም በስፋት ሲነሳ ይስተዋላል፡፡ ለዚህ ጥያቄ እናንተስ መልሳችሁ ምንድን ነው?
ኢንጅነር ይልቃል፡- እኛ የምንሰራው ለአገራችን ብለን እንጂ ማንም እንዲያወድሰንና እንዲያምነን ብለን አይደለም፡፡ የሰራነው ነገር ሲያሳምነው ይከተለናል፤ ያምነናልም፡፡ ባለፈው 10 አመት ውስጥ ፖለቲካው ውስጥ ስለነበርን በመውደቅ በመነሳቱ ላይም አልፈናል፡፡ የራሳችንን ታሪክ ያለን እንጂ ከምንም ዱብ ያልን ፖለቲከኞች አይደለንም፡፡ የሚያከብሩን ሰዎች አሉ፣ በቅርብ የተማርንባቸው ሰዎችም አሉ፣ በተግባር ውጣ ውረድ ውስጥም አልፈናል፡፡ ይህ ለመታመን በቂ ይመስለኛል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ሰማያዊን የመሰረትን ሰዎች ስብሰባ ላይ በአጋጣሚ የተገናኘን ሳይሆን ከእነ ድክመትና ጥንካሬያችን ለረዥም ጊዜ የምንተዋወቅ ሰዎች ነን፡፡ በጎሳ፣ በወንዝ ልጅነት ሳይሆን ነጻ በሆነ የፖለቲካ አስተሳሰብ ተገናኝተን በደንብ የተዋወቅን ሰዎች በመሆናችን በቀላሉ እንዳንፈርስ መልካም እድል ይሰጠናል፡፡
በተጨማሪም ይህ አስተሳሰብ ከመውደቅ የመጣ እንጂ ከእኛ ጥፋት የመጣ አይደለም፡፡ ስጋቱ ቢኖርም እኛ በመታመን እንሰራለን እንጂ አያስጨንቀንም፡፡ ምክንያቱም ችግሩ ከእኔ አሊያም ከአንዱ ጓደኛዬ ድክመት የመነጨ ስላልሆነ ነው፡፡ አገራችን ውስጥ አለመተማመን በመኖሩ፣ ሰዎች ደጋግመው በመውደቃቸው፣ አጠቃላይ ክሽፈት በመብዛቱ የተፈጠረ የወል ስነ ልቦና ነው፡፡ ይህ እንደ አገር የጋራ ችግራችን በመሆኑ ይህን ባህል ለመቀየር እንሰራለን እንጂ አንድ ሰው ለምን አላመነኝም ብዬ አልጨነቅም፡፡ ይህን የወል ስነ ልቦና በድፍረት፣ ከራስ ወዳድነትና ከዝርክርክነት ወጥተን፣ አርዕያና ታማኝ በመሆን፣ የውሳኔ አሰጣጥም ሆነ የገንዘብ አወጣጥን ተጠያቂነት በተሞላበት መንገድ በመፈጸም፣ ከአባላት ጋር የቅርብ ግንኙነት በመመስረት፣ የስልጣን ልዩነትን በማጥፋት ሰው ከአሉባልታ ይልቅ በሳይንስና በምክንያታዊ ነገር እንዲመዘን ማድረግ ይቻላል፡፡
እኛ ልናደርግ የምንችለው ሰውን ተስፋ ያስቆረጡትንና ለመለያየት ምክንያት የነበሩትን ነገሮች መቀነስ ነው፡፡ አለመተማመኑ ግን ደጋግሞ የመክሸፉ ችግር እንጂ የሰማያዊ ልጆች ችግር አይደለም፡፡ የሰማያዊ ልጆች ከአሁን በኋላ ምንም ይምጣ እስካሁን ባደረጉት ነገር ብቻ ሊደነቁ ይገባቸዋል፡፡ ባለፈው አስር አመት ውስጥ የግል ህይወታቸውን መኖር እየቻሉ ለአገርና ለወገን ሲሉ ብዙ ስቃይን የሚቀበሉ ልጆችን ማፍራት ችለናል፡፡ ለነጻነታቸው የሚዘምሩ ወጣት ሴቶችን ማፍራት ችለናል፡፡ የወደቀውንና አይቻልም የሚለውን መንፈስ ማነቃቃት ተችሏል፡፡ የወደፊቱ እንዳለ ሆኖ በእስካሁንም ቢሆን ሊመሰገኑ ይገባቸዋል፡ ፡ አለመተማመኑ በውድቀት የመጣ እንደመሆኑ እሱን መቀየር የሚቻለው በስራ ነው፡፡
ነገረ-ኢትዮጵያ፡- ለነበረን ቆይታ አመሰግናለሁ::
ኢንጅነር ይልቃል፡- እኔም አመሰግናለሁ፡

Sunday, March 23, 2014

ዛሬ ማለዳ በአንበሳ አውቶብስ ላይ በደረሰ አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት አለፈ



ዛሬ ማለዳ 12:55 ላይ ከካራ ቆሬ ወደ መርካቶ ሲጓዝ የነበረ የከተማ አውቶብስ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ድልድይ ውስጥ ገብቶ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።
አደጋው የደረሰው ከካራ ቆሬ ወደ መርካቶ ከ100 በላይ ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው 36 ቁጥር የከተማ አውቶብስ ፥ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለው ረዥም ድልድይ ውስጥ በመግባቱ ነው።
በአደጋው እስካሁን 1 እግረኛን ጨምሮ 4 ወንድ እና 4 ሴት ተሳፋሪዎች ህይዎታቸው ያለፈ ሲሆን 46 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የአውቶብሱ አሽከርካሪና ትኬት ቆራጭ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህይወት መትረፋቸው ታውቋል።
ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በጥቁር አንበሳና ጳውሎስ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኝ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ ከፖሊስና ከእሳት አደጋ ሰራተኞች ጋር በመተባበር የሰው ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ጥረት መደረጉም ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ሲሆን አውቶብሱን ከገባበት ገደል ለማውጣትም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው።
ዘገባውን ከቦታው ያደረሰን ባልደረባችን በቀለ ተመስገን ነው፡፡

Friday, March 21, 2014

የቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ የአገልግሎት ጥራት ማሽቆልቆል አሳሳቢ ሆኗል




ኢሳት ዜና :- የአዲስአበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በታሪኩ አይቶ የማያውቀው የአገልግሎት አሰጣጥ መጨናነቅ እንዳጋጠመውና በዚህም ምክንያት ከዓለም አቀፍ መመዘኛዎች አንጻር የአገልግሎት ጥራቱ ከጊዜ ወደጊዜ እያሽቆለቆለ መምጣቱን አንድ ከድርጅቱ የተገኘ ጥናታዊ ጽሁፍ አመለከተ፡፡
አዲሱ የመንገደኞች ማስተናገጃ ተርሚናል ለሃያ ዓመታት በዓመት 6 ሚሊየን መንገደኞችን በብቃት ሊያስተናግድ ይችላል ተብሎ የተገነባ ቢሆንም በአስረኛ ዓመቱ የመንገደኞች ቁጥር ከ6.5 ሚሊየን በላይ በመድረሱ በኤርፖርቱ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሮአል፡፡
በኤርፖርቱ የሚስተናገዱ አውሮፕላኖች ቁጥርም ባልተጠበቀ ሁኔታ ሲጨምር እንደ ፈረንጆች አቆጣጠር በ2001 በዓመት 9 ሺህ 609 ያህል አውሮፕላኖች ሲስተናገዱ፣ በ2012 ወደ 65 ሺህ 417 አውሮፕላኖች ተስተናግደዋል። የመንገደኞች ቁጥርም በተመሳሳይ ዓመት ከ1.3 ሚሊየን ወደ 6.34 ሚሊየን ከፍ ብለአል።
በአየር ማረፊያው የሚስተናገደው የዕቃ ብዛትም ከ6 እጥፍ ባላይ መጨመሩን መረጃው ጠቁሞ ይህ የመጨናነቅ ችግር ካልተፈታ የኤርፖርቱ አገልግሎት ደረጃው ዝቅ እንደሚልና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው ተመራጭነትና ተቀባይነት እንደሚቀነስ አስጠንቅቋል።
የትራንዚት መንገደኞች ሌላ የተሻለ አገልግሎት ማግኘት ወደሚችሉበት አገር ለመሄድ ስለሚገደዱ በቀጣይ የአገሪቱ አቪየሽን ዕድገት ላይ ቀላል የማይባል ተጽዕኖ ይኖረዋል ሲልም ያስጠነቅቃል።
አውሮፕላን ማረፊያው በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ካላቸው የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መመዘኛዎች አንጻር ሲታይ ጥራቱ ዝቅተኛ የሆነ አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑን መረጃው አመልክቷል፡፡
መረጃው ለዚህ ችግር የአጭርና የረዥም ጊዜ መፍትሔዎችንም ጠቁሟል፡፡ የአጭር ጊዜ እቅዶች ካላቸው ውስጥ አሁን ያለውን የመንገደኞች ተርሚናል በማስፋት ቢያንስ ለቀጣይ አስር ዓመታት እንዲያገለግል ማድረግ እና ዘመናዊ የክብር እንግዶች ሳሎን (VIP SALON) መገንባት የሚሉት ሲገኙበት በረዥም ጊዜ እቅድ ደግሞ አዋጪ በሆነ ቦታ አዲስ ኤርፖርት በመገንባት የቦሌ ኤርፖርትን ለቅርብ ርቀት በረራዎች እንዲሁም ልክብር እንግዶች እና ለሀገር ውስጥ አገልግሎት ማዘጋጀት የሚል የመፍትሔ ሃሳብ አስቀምጧል፡፡