ዛሬ ማለዳ 12:55 ላይ ከካራ ቆሬ ወደ መርካቶ ሲጓዝ የነበረ የከተማ አውቶብስ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ድልድይ ውስጥ ገብቶ ስምንት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ።
አደጋው የደረሰው ከካራ ቆሬ ወደ መርካቶ ከ100 በላይ ተሳፋሪዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው 36 ቁጥር የከተማ አውቶብስ ፥ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለው ረዥም ድልድይ ውስጥ በመግባቱ ነው።
በአደጋው እስካሁን 1 እግረኛን ጨምሮ 4 ወንድ እና 4 ሴት ተሳፋሪዎች ህይዎታቸው ያለፈ ሲሆን 46 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የአውቶብሱ አሽከርካሪና ትኬት ቆራጭ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በህይወት መትረፋቸው ታውቋል።
ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በጥቁር አንበሳና ጳውሎስ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የሚገኝ ሲሆን የአካባቢው ማህበረሰብ ከፖሊስና ከእሳት አደጋ ሰራተኞች ጋር በመተባበር የሰው ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ጥረት መደረጉም ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ ሲሆን አውቶብሱን ከገባበት ገደል ለማውጣትም ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው።
ዘገባውን ከቦታው ያደረሰን ባልደረባችን በቀለ ተመስገን ነው፡፡
No comments:
Post a Comment