Wednesday, March 5, 2014

ትናንት ሌሊት በመርካቶ ወንበር ተራ በሚባለው አካባቢ የእሳት አደጋ ተከሰተ


አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2006 ትናንት ሌሊት 10 ስዓት ከ45  ላይ በአዲስ ከተማ ወረዳ 8 በመርካቶ ልዩ ስሙ ወንበር ተራ በሚባለው አካባቢ ድንገተኛ የእሳት አደጋ ተከሰተ።

የእሳት አደጋው በሰው ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳላደረሰ ነው የተገለፀው።
የአዲስ አበባ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከታተልና መቆጣጠር ባለስልጣን ሰራተኞች እሳቱን በቁጥጥር ስር አውለውታል።
ፖሊስ የአደጋውን መንስኤ እያጠና  ሲሆን፥  የወደመው የንብረት መጠንም  እየተጣራ  ይገኛል
ትናንት  ምሽት በአካባቢው መብራት  ያልነበረ በመሆኑ  በአካባቢው በሚኖሩ  ግለሰቦች የተለኮሰ ሻማ ምናልባትም የአደጋው መንስኤ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል።
በፀጋዬ ወንድወሰን

No comments:

Post a Comment