የሰሞኑ የጅዳ ቆንስላ
ፅ/ቤት ሃሜትና የዛሬ የኢህአዴግ
ስብሰባ
ንትርክ መንስኤው ከሃገር ቤት ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር በኩል በተላከው
የኢህአዴግ
አዲሱ
አደረጃጀት
ምክኒያት
ነው።
አዲሱ
አደረጃጀት
ደግሞ
ተወስኖ የመጣው ድርጅቱ በቆንስላው
መሪ
እንዲመራ የሚል በመሆኑ ይሄንን ደግሞ በመከከለኛው ምስራቅ በጥንካሬያቸው የሚታወቁት የጅዳ የህወሃት
ኢህአዴግ አመራሮች የተዋጠላቸው አይመስልም።
![]() |
Add caption |
ከቆንስሎቹ ሶስቱም የደቡብ
ሰዎች በመሆናቸው ሌላ ችግር ሆኗል።
ይህ
የቆንስሎቹ
ችግር
ከዚህ
በፊትም
ድርጅቱን
ሊያነጋግሩ
ከውጭ
ጉዳይ
አምባሳደር
ውብሸት
ደምሴ
በመጡ
ግዜም
እንደ
ቅሬታ መነሳቱን ምንጮች ጠቁመዋል። በአሁኑ ሰዓት ቀድመው
የነበሩት የደህዴን መሰረታዊ ድርጅት
አመራሮች
ለቆንስሎቹ
ስልጣናቸውን
ጥለውላቸው
መሄዳቸው
የዛሬ የኢህአዴግ ስብሰባ ዋና አጀንዳ ሆኖ ምሽቱን በብሄር
ጎራ
ለይቶ
ሲያነታርክ ቆይቷል።
የሆነ ው ሆኖ እውነት ኢህአዴግንም ቆንስሎቹ
ሊመሩት ይሆን? ባይዋጥላቸውም የህወሃት
አመራሮች
ዝምታን
መርጠዋል።
የቀድሞው
ጄነራል
ቆንስላ
ዘነበ
ከበደ ከእጃቸው ያፈተለከው የበላይነት የተመለሰ አይመስልም።
ይህ በዚህ እንዳለ ጅዳ ላይ የተጀመረው የብሄር ግጨት
መቀመጫቸውን
ሪያድ
ባደረጉትን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ
ዲፕሎማቶች
እያተራመስ
መሆኑን
ከኤምባሲው
የሚወጡ
መረጃዎች
ይጠቁማሉ
።
በተለይ
ከኦሮሞ
ብሄር
የሚወለዱት አምባሳደር ዶ/ር
መሃመድ
ሃሰን የደቡብ ተወላጅ የሆኑትን
የዲያስፖራውን
ሃላፊ
አቶ
ተመስገን
ኡመር
ከስልጣን
ለማባረር ለውጭ ጉዳይ ሚንስቴር
መ/ቤት
የክስ
ደብዳቤ
አስገብተው
እንደነበር ውስጥ አዋቂ ምንጮች ይገልጻሉ።
አቶ
ተመስገን
ኡመር
በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ
ታማኝ፡አባለነታቸው
ከዲያስፖራው
ሃላፊነታቸው ባሻገር ከአማራ ብሄር
የሚወለዱትን የአምባሳደ መሃመድ ሃሰን አማካሪ እና የንግድ
ዘርፍ
ሃላፊ
የነበሩትን
አቶ ዘላለም ከሃላፊነታቸው
በማንሳት
አቶ
ተመስገን
ኡመር
የአማካሪነት
ቦታውን
ደርበው
እንዲይዙ
መደረጋቸው ፍጥጫውን የበለጠ አካሮታል ። ወትሮም
በመንግስት
ዘንድ
የቀርብ ከትትል የሚደረግባቸው አምባሳደር
ዶ/ር
መሃመድ
ሃሰን በተለያዩ ግዜያት በሚቀርባቸው
ክስ ለጥያቄ ሀገርቤት መጠራታቸው
ይነገራል።
በአጠቃ ላይ ጅዳ እና ሪያድ ውስጥ በዲፕሎማቱ የተጀመረው የብሄር ስልጣን ሹኩቻ ወደ በማህበረሰቡ ወርዶ በጅዳ እና ሪያድ የኮሚኒቲውን ት/ቤት
አስተዳደር ጨምሮ አንዳንድ ማዕከላትን በበላይነት ለመቆጣጠር በብሄር ልማት ማህበራት በኩል የተደራጁ ጽንፈኞች በሚያራግቡት ቅስቀሳ ዲያስፖራውን በስው ሃገር ማብቂያ ወደ ሌለው ደም መፋሰ እንዳይከቱት ያሰጋል። Ethiopian.hagere ጅዳ በዋዲ
No comments:
Post a Comment