እብሪተኛ የመንግስት ታጣቂዎች ለሚቀጥፉት የሰው ህይወት መንግስት ተጠያቂ የሚሆነው መቼ ነው?

ከትናንት በስቲያ በላፍቶ ክፍለ ከተማ አቦ ማዞሪያ አካባቢ በምስሉ የምትመለከቷቸውን የሶስት ልጆች ወላጆች እብሪተኛው ታጣቂ በጥይት በመደብደብ ገድሏቸዋል። ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ውሏል። እሰየው ነው። ግን በቃ?እነዚያን ሶስት ህጻናት ማን ነው የሚያሳድጋቸው? ግለሰቡን አምኖ ክላሽ ያስታጠቀው አካል የማይጠየቀውስ እስከመቼ ነው?
መንግስት የመኪና አሽከርካሪዎች የሶስተኛ ወገን ኢንሹራንስ እንዲገቡ እያስገደደ መሆኑ በመኪኖቹ አደጋ ለሚደርስበት ሰው አንዳች ነገር ነውና ይበረታታል። መንግስት በነካ እጁ የሚያስታጥቃቸው ሰዎች ለሚያደርሱት የመብት ጥሰት ኢንሹራንስ ይግባ!!!
በእኔ እምነት ስለ ተገደሉት ወላጆችና ወላጅ አልባ ስለሆኑት ልጆች መጮህ የሁላችንም ግዴታ ነው።
~~ዳዊት ሰለሞን~~
No comments:
Post a Comment