የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንትና የኦሮሞ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሊቀመንበር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ አረፉ፡፡

ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ሥልጣናቸውን በፈቃዳቸው በቅርቡ የለቀቁት አቶ ዓለማየሁ፣ የካቲት 26 ቀን 2006 ዓ.ም. ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ያረፉት ይታከሙበት በነበረው ታይላንድ ባንኮክ ከተማ መሆኑን የወጣው መግለጫ አመልክቷል፡፡
በ2002 ዓ.ም. የኦሕዴድ ሊቀመንበር፣ በዚያው ዓመት ወርሀ ጳጉሜን ላይ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት አቶ ዓለማየሁ፣ ባጋጠማቸው ሕመም ምክንያት በአገር ውስጥና በውጭ አገር ሕክምና የተከታተሉ ሲሆን፣ ከሁለቱም ሥልጣናቸው በፈቃዳቸው የካቲት 10 ቀን እስከለቀቁ ድረስ ሠርተዋል፡፡
በቀድሞው አጠራር በወለጋ ጠቅላይ ግዛት ቢሎ ቦሼ ወረዳ ከአባታቸው ከአቶ አቶምሳ ሚጃና ከእናታቸው ከወይዘሮ አየለች ብሩ በ1961 ዓ.ም. የተወለዱት አቶ ዓለማየሁ፣
ባለትዳርና የአንድ ወንድና የሁለት ሴቶች ልጆች አባት ነበሩ።
Source ኢትዮጵያ ሪፖርተር
No comments:
Post a Comment